የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፦
በኃይል ማስተላለፊያ ስርዓታችን ላይ በገጠመን ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ ኃይል ተቋርጧል።
በአሁኑ ወቅት ችግሩ የተከሰተው በዚህ ምክንያት ነው ለማለት አስቸጋሪ ቢሆንም ከጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።
የጣና በለስና የፊንጫ ኅይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ከሲስተም ጋር ማገናኘት በመቻሉ የአዲስ አበባን የተወሰኑ አካባቢዎች ኃይል እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል።
በቀጣይም በየደረጃው ሁሉንም የሀገሪቱ ክፍሎች ኃይል እንዲያገኙ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው።
በዚህ አጋጣሚ ለተፈጠረው ችግር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይቅርታ ይጠይቃል።
የካቲት 20/2012 ዓ/ም
#EthiopianElectricPower
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
በዋግኽምራና አካባቢዋ ከትላንት ጀምሮ መብራት ተቋርጧል። በዋግኽምራና አካባቢዋ ከትላንት ግንቦት 21/2013 ዓ.ም ምሳ ሰዓት አካባቢ ጀምሮ የመብራት ሀይል አገልግሎት መቋረጡን ተሰምቷል። መብራት ሀይል አገልግሎት የተቋረጠበት ምክንያት ? የመብራት ኃይል የተቋረጠበት ምክንያት በተመለከተ የ ዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ስለሺ ወርቁና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰቆጣ አገልግሎት…
#Update
ከቀናት በፊት በዋግኽምራና አካባቢው ላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቋረጡን የሚገልፅ መረጃ ተለዋውጠን ነበር።
አካባቢው አሁንም ድረስ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዳላገኘ ተሰምቷል።
በዋግ ኽምራ በሚገኙ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች የተቋረጠው ኤሌክትሪክ አገልግሎት መልሶ ለማገናኘት ጥረት እየተደረገ መሆኑን የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኦፕሬሽንና ጥገና ቢሮ አስታውቋል።
ቢሮው በአካባቢው ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ኤሌክትሪክ የተቋረጠው በ3 የኃይል ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ ስርቆት በመፈፀሙና በመውደቃቸው ነው ብሏል።
ወደስፍራው ለጥገና የተንቀሳቀሰው ቡድን የወደቁትን ምሰሶዎች መልሶ ለመትከል ከእሁድ ጀምሮ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጿል።
ከአንድ ወር በፊት ከአላማጣ እስከ ሰቆጣ በሚገኙት 269 ምሰሶዎች ላይ የፍተሻ ስራ መከናወን መጀመሩን የተገለፀ ሲሆን በስምንት የብረት ምሰሶዎች ላይ የስርቆት ሙከራ መፈፀሙን በማረጋገጥ ምሰሶዎቹ ከመውደቃቸውና ኤሌክትሪክ ከመቋረጡ በፊት መስተካከሉ ተነግሯል።
በአሁኑ የተፈፀመው ስርቆት በመስመሩ ውስጥ በሚገኙትና የፍተሻ ስራ ባልተካሄደባቸው 47 ምሰሶዎች ውስጥ በሶስቱ ነው።
በምሰሶዎቹ መውደቅ ሰቆጣን ጨምሮ አምደወርቅ፣ ዳህና ፣ በአበርገለ፣ በሰሀላ፣በዝቋላና በአካባቢያቸው ኤሌክትሪክ ተቋርጧል።
የዋግ ኽምራ አብዛኛዎቹ አካባቢዎች ኃይል የሚያገኙት ከአላማጣ ባለ 66 ኪሎቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ከሚወጣ መስመር ነው።
#EthiopianElectricPower
@tikvahethiopia

" ወጣቱ ሳይጎዳ በገመድ አስረው በማውረድ በተአምር ህይወቱን ታድገዋል " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የወጣ ወጣት በተአምር ህይወቱ ተርፏል።
በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ የወጣ ወጣት ኃይል እንዲቋረጥ ማድረጉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታውቋል፡፡
በዘርፉ የደቡብ ሁለት ሪጅን እንደገለፀው ወጣቱ ዛሬ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ከወላይታ ሶዶ ወደ ሳውላ በሚሄደው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ወጥቶ " አልወርድም " በማለቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ፦
- ጎፋ ዞን፣
- አሪ ዞን፣
- ባስኬቶ ዞን እና ኦሞ ዞን ሙሉ በሙሉ እንዲሁም ጋሞ ዞን በከፊል ከሦስት ሰዓታት በላይ ኃይል ተቋርጦ ቆይቷል፡፡
በምን ምክንያት የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ እንደወጣ ያልታወቀው ወጣት በአካባቢው ሽማግሌዎችና የመስተዳድር አካላት ቢለመንም ለመውረድ ግን አስቸግሮ እንደነበር መምሪያው ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለሙያዎች ኃይል በማቋረጥ ወጣቱ ሳይጎዳ በገመድ አስረው በማውረድ በተአምር ህይወቱን ታድገዋል፡፡
የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች የሚያስተላልፉት የቮልቴጅ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መምሪያው አሳስቧል፡፡