TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56K photos
1.4K videos
202 files
3.79K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የታማሚ ሁኔታ፦

ቫይረሱ የተገኘበት 26ኛው ግለሰብ የ42 ዓመት የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሲሆን የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ አስቀድሞ መጋቢት 9/2012 ዓ/ም ከአውስትራሊያ አዲስ አበባ እንዲሁም መጋቢት 10/2012 ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ ተጉዟል።

ግለሰቡ የበሽታውን ምልክት በማሳየቱ በላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል። በአሁን ሰዓት ግለሰቡ በድሬዳዋ የለይቶ ህክምና መስጫ ማእከል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል።

#DrLiaTadesse #EPHI
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• ዛሬ በበሽታው የተያዙ ታማሚዎች - 3
• በአሁን ጊዜ በለይቶ ማቆያ ያሉ ታማሚዎች - 25
• ፅኑ ህሙማን - 2
• ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ያገገሙ - 2
• በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ድምር - 29

ማስታወሻ፦ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጡ 2 ታማሚዎች ወደሀገራቸው ተመልሰዋል።

#DrLiaTadesse #EPHI
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ55ቱም ናሙና ውጤት ኔጌቲቭ ነው!

የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ከዚህ ቀደም ወደ አ/አ #EPHI የላካቸው 55 ናሙናዎች ሁሉም ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው በምርመራ መረጋገጡን አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ55ቱም ናሙና ውጤት ኔጌቲቭ ነው! የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ከዚህ ቀደም ወደ አ/አ #EPHI የላካቸው 55 ናሙናዎች ሁሉም ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው በምርመራ መረጋገጡን አሳውቋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በነገራችን ላይ...

በትግራይ ከኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ነፃ መሆናቸው የተረጋገጠው የ55 ናሙናዎች ውጤት የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ከዚህ ቀደም ወደ አዲስ አበባ #EPHI የላካቸውና ምርመራ እንዲደረግባቸው የተደረጉ እንጂ ትላንት በመቐለ በተጀመረው የምርመራ ስራ አይደለም። ይሄን ግልፅ ለማድረግ እንፈልጋለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• ዛሬ በበሽታው የተያዙ ታማሚዎች - 0
• በአሁን ጊዜ በለይቶ ማቆያ ያሉ ታማሚዎች - 24
• ፅኑ ህሙማን - 1
• ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ያገገሙ - 3
• በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ድምር - 29

ማስታወሻ፦ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጡ 2 ታማሚዎች ወደሀገራቸው ተመልሰዋል።

#DrLiaTadesse #EPHI

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• ዛሬ በበሽታው የተያዙ ታማሚዎች - 6
• በአሁን ጊዜ በለይቶ ማቆያ ያሉ ታማሚዎች - 30
• ፅኑ ህሙማን - 2
• ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ያገገሙ - 3
• በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ድምር - 35

ማስታወሻ፦ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጡ 2 ታማሚዎች ወደሀገራቸው ተመልሰዋል።

#DrLiaTadesse #EPHI

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 1843
• ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 59
• ዛሬ በበሽታው የተያዙ ታማሚዎች - 5
• በአሁን ጊዜ በለይቶ ማቆያ ያሉ ታማሚዎች - 37
• ፅኑ ህሙማን - 1
• ህይወታቸው ያለፈ - 0
• ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ያገገሙ - 4
• በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ድምር - 43

ማስታወሻ፦ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጡ 2 ታማሚዎች ወደሀገራቸው ተመልሰዋል።

#EPHI

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሞት መመዝገቡን ኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

አንዲት የ60 ዓመት ታማሚ መጋቢት 19 ፣ 2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማከሚያ ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን በመጋቢት 22፣ 2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡ ይታወሳል፡፡

ይሁንና ከመጋቢት 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል፡፡

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማውን ሀዘን ገልጾ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

#MoH #EPHI #EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EPHI

የኢትዮጵያ መንግስት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወቱ ያለፈ አስከሬን ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ ከልክሏል።

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን እንዳስታወቀው የኮሮና ቫይረስ መስፋፋትን ተከትሎ በውጭ አገራት በቫይረሱ ምክንያት ህይወቱ ያለፈ አስከሬን ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ ታግዷል።

ባለስልጣኑ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከኢትዮጵይ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር ባደረገው ምክክር መሆኑን አስታውቋል።

ባለስልጣኑም ወደ በኢትዮጵያ አየር ክልል የመብረር ፈቃድ ላላቸው በድምሩ 14 አየር መንገዶች ከውጭ አገራት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወቱ ያለፈ ሰው አስከሬን ወደ ኢትዮጵያ ይዘው እንዳይገቡ ማገዱን ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ሉፍታንዛ፣ ተርኪሽ፣ ግብጽ፣ ኳታር ኤርትራ፣ኢምሬት፣ሩዋንዳ፣ኬንያ ጅቡቲ አየር መንገዶችን ጨምሮ በድመሩ 14 አየር መንገዶች አስከሬን ወደ ኢትዮጵያ እንዳያስገቡ ማገዱን ባለስልጣኑ አስታውቋል። እገዳው የኢትዮጵያ አየር መንገድንም እንደሚመለከት ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ምንጭ ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም (ሳሙኤልአባተ)
PHOTO : JAWAR MOHAMMED
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TIGRAY

በትግራይ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል ወደክልሉ በመኪናም ይሁን በአየር የሚገባ መንገደኛ ለ14 ቀናት ለይቶ ማቆያ የመቆየት #ግዴታ አለበት። ይህን ልናሳታውሳችሁ እንወዳለን!

በሌላ በኩል የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሃጎስ ጎደፋይ ከደቂቃዎች በፊት በሰጡን መረጃ መሰረት ዛሬ የተደረገውን 6 የላብራቶሪ ምርመራ ጨምሮ በትግራይ 105 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል (ከዚህ ውስጥ ሀምሳ አምስቱ /55/ #EPHI ተልኮ የተመረመረ ነው) ሁሉም #ነፃ ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia