TIKVAH-ETHIOPIA
1.43M subscribers
55.4K photos
1.39K videos
199 files
3.72K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"...ችግሩ ሲፈጠር የተመለከቱ አካላት ጭምር በሕግ ይጠየቃሉ!" አቶ አገኘሁ

በምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ አስተዳደር ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት እየተደረገ ነው፡፡ ‹‹በችግሩ የተሳተፉ፣ ችግሩ ሲፈጠር የተመለከቱ አካላት ጭምር በሕግ ይጠየቃሉ›› ብለዋል የአማራ ክልል ሠላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገር በውይይቱ መክፈቻ ላይ በሰጡት ሐሳብ፡፡ 

https://telegra.ph/ETH-12-16

(AMMA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ከኢትዮጵያ ሀብት ከሸሸባቸው ሃገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተጀምሯል" - አቶ ዝናቡ ቱኑ (የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር)

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ከአገር የሸሹ ሀብቶችን ለማሰመለስ፤ የሀብት ማሰመለስ ስትራቴጂ ማዘጋጀቱን፣ ሀብቱ የሸሸባቸው አገራትን የመለየት ሥራ መሰራቱንና ከአገራቱም ጋር ውይይት መጀመሩን ገልጿል።

በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዝናቡ ቱኑ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ሀብቱ ከሸሸባቸው አገራት ጋር የተደረገው ውይይት ሁሉም አገራት በሚባልበት ደረጃ ሰምምነት ላይ መደረሱን ጠቅሰው በወንጀል የተገኘ ሀብት የማስመለስ ዳይሬክቶሬት መቋቋሙንም ተናግረዋል።

ከአገራቱ ጋር ባለው ንግግር የተዘረፈው ሀብት በምን መልኩ ይመለሳል? የሚለውን ለመወሰን ያሉ ዓለም አቀፍ ሕግጋትን እያጠኑ እንደሆነና በድርጊቱ ውስጥ የተሳተፉ አካላት በምን አግባብ እንደሚጠየቁ እየተሰራበት እንደሆነም ለቢቢሲ አስረድተዋል።

(ቢቢሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
10 ግለሰቦች በፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለዋል...

በግለሰቦች መካከል የሚነሱ ግጭቶችን የብሔር መልክ በማስያዝ የህብረተሰቡን ደህንነት ለማወክ የሚጥሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስጠነቀቀ፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር መሀመድ ሃመደኒል እንደገለጹት ባፈው ሳምንት በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ አይፓፑ ቀበሌ በግለሰቦች መካከልተከስቶ በነበረ ግጭት የሦስት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

ከድርጊቱ ጋር የተጠረጠሩ 10 ግለሰቦችን ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑንም ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት አካባቢው ወደቀደመ ሠላም መመለሱን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

ይሁንና የግለሰቦችን ግጭት የብሔር መልክ ለማስያዝ አንዳንድ የመንግስት የብዙሀን መገናኛዎችን ጨምሮ በማህበራዊ ሚዲያዎች ዘመቻው መቀጠሉን ኮሚሽነር መሃመድ አመልክተዋል፡፡

በግለሰቦች መካከል በማንኛውም ጊዜ ግጭት ሊከሰት እንደሚችል የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ “ከግጭቱ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት የክልሉ መንግስት አይታገስም፤ ይህን የሚያደርጉ አካላትም ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል” ብለዋል፡፡

በግጭቱ ላይ እየተደረገ ከሚገኘው ምርመራ በተጨማሪ ጉዳዩን የሚያራግቡ አካላትን በህግ ለመጠየቅ የሚያግዙ ምርመራዎች እየተካሄዱ መሆኑንም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቀዋል፡፡

(ኢዜአ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ያሬንጃ ቀበሌ አካባቢ ተኩስ በመክፈት ጉዳት ለማድረስ የሞከረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ውሏል!

በትናንትናው እለት ከአሶሳ ወደ ግልገልበለስ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አገር ቋራጭ አውቶብስ ላይ በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ ያሬንጃ ቀበሌ አካባቢ ተኩስ በመክፈት ጉዳት ለማድረስ የሞከረ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቀዋል፡፡

ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር የዋለው በአውቶቡሱ ተሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አንድ የክልሉ ልዩ ኃይል አባል ባደረገው የተኩስ ለውውጥ በጥይት ተመቶ መሆኑንም ተናግረዋል።

እንደ ክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጻ በአውቶቡስ ውስጥ በነበሩ ተሳፋሪዎች ላይ ምንም የደረሰ ጉዳት የለም፡፡ ሕብረተሰቡም ለጸጥታ አስከባሪ አካላት የሚያደርገውን የተለመደ ትብብር እንዲያጠናክር ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

(ኢዜአ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ስምንት የአፍሪካ ሀገራት የሳተላይት ምስል ግዢ ጥያቄ ለኢትዮጵያ አቀረቡ!

ኢትዮጵያ "የሳተላይት ምስል" ሽያጩን በራሷ መመሪያ መሠረት ከገዢ ሀገራት ጋር ውል በመፈፀም መሸጥ እንደምትጀምር የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንሰቲቲዩት ይፋ አድርጓል። የህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት የሰው ሃብትና ቴክሎጂ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት የሳተላይቷን ቁጥጥርና መረጃ አሰባሰብ ተመልክተዋል።

የቋሚ ኮሚቴው አባላት ለትውልድ የሚተላለፍ አሻራቸውን በማኖራቸው የኢንስቲትዩቱን ሰራተኞች አመስግነዋል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ኢትዮጵያን ከዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ ባለብዙ ተልዕኮ የሳተላይት መረጃ መቀበያ ተከላ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል። የመቀበያ አንቴናው ሀምሳ ሴንቲ ሜትር የምስል ጥራት እና እስከ አምስት የሚደርሱ የሳተላይቶችን መረጃ በአንድ ጊዜ መቀበል የሚያስችል ነው።

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ሰለሞን በላይ ኢትዮጵያ ሳተላይት ባመጠቀች በአራት ቀናት ውስጥ ብቻ ስምንት የአፍሪካ ሀገራት የሳተላይት ምስል ግዢ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ታህሳስ 10 ያመጠቀቻት ሳተላይት የታሰበላትን ቦታ ይዛ ስራዋን በአግባቡ እየሰራች መሆኑ ተገልጿል። ሳተላይቷ በቀን አስራ አራት ጊዜ በተዘጋጀላት ምህዋር እየዞረች መረጃ የምትሰበስብ ሲሆን በቀን አራት ጊዜ ደግሞ የሰበሰበችውን መረጃ የመቀበል ስራ ይሰራል፡፡ በቀጣይ የኮሙኒኬሽን ሳተላይት ግንባታ እንደሚጀመርና በዘርፉ የሚደረገው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተነግሯል፡፡

(MinT)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ ታህሳስ 13/2012 ዓ/ም ነው፤ የመጀመሪያው የዓመቱ የትምህርት አጋማሽ ሊጠናቀቅ ጥቂት ጊዜያት ብቻ ናቸው የሚቀሩት!

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣት ተማሪዎቻችን ያሉበት ሁኔታ ምን ይመስላል የሚለውን ለማጣራት ዛሬ የመረጃ ማሰባሰብ ስራ ሲሰራ ውሏል። አሁንም ችግሮች ያልተቀረፉበት ዩኒቨርሲቲዎች እንዳሉ ለመረዳት ችለናል።

5 ዓመት ሙሉ የለፉ ተማሪዎች ስጋት አድሮባቸው ግቢያቸውን ለቀው ከወጡ፤ ከጓደኞቻቸው ተነጥለው ከትምህርት ገበታቸው ከራቁ በርካታ ሳምንታት አልፈዋል።

አዲስ ገቢ ተማሪዎችም በመጀመሪያ አመት ባዩት ነገር፣ በገጠማቸው ችግር፣ ባደረባቸው ፍራቻ ምክንያት ቤታቸው ከገቡ ቆይተዋል። ዛሬም የማስፈራሪያ መልዕክቶችን የሚሰራጩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዳሉ ታዝበናል። የፌዴራል ፖሊስ ተመድቦ ለውጥ የመጣበት ግቢ እንዳለ ሁሉ ስጋቶች ያልተቀረፈበት ግቢም አለ።

ትላንት፣ ዛሬ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ተማሪዎች የሚማሩበትን ተቋም ጥለው ወደቤተሰቦቻቸው ለመሄድ የወጡም አሉ። በስጋት ምክንያት የሚወዱትን ትምህርት ጥለው የወጡ ተማሪዎች ባሉበት ትምህርት የቀጠሉ ተቋማትም አሉ። አንዳንድ ተቋማት ተማሪዎች እንዲመለሱ ጥሪ ከማቅረብ የዘለለ መሬት ላይ የሚታይ ያለውን ስጋት ሙሉ በሙሉ የሚቀፍ ተማሪን ከተማሪ የማግባባት ስራ እየሰሩ እንዳልሆነ መልእክታቸውን የላኩ ተማሪዎች ገልፀዋል።

መንግስት ችላ ብሎናል፣ ውይይቶች፣ ምክክሮች እየተደረጉ ነው የኛ ችግሮች ግን እየተፈቱ አይደለም ያሉም በርካታ ናቸው። ውድ የሆነው የትምህርት ጊዚያችን እየባከነ ነው መፍትሄ ይሰጥን ሲሉ ተማሪዎች ጠይቀዋል።

More👇
https://telegra.ph/TIKVAH-12-23

@tikvahethiopiaBot
#GRD

በሕዳሴው ግድብ ውሃ አሞላል እና የግድቡ አተገባበር ላይ በካርቱም የተካሄደው የሦስትዮሽ ውሃ ሚንስትሮች ስብሰባ ተጠናቋል፡፡ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ አሁንም ስምምነት አልተደረሰም፡፡ በድርቅ ትርጓሜ እና በድርቅ ጊዜ ግድቡ እንዴት እንደሚያዝ ግን መቀራረብ እንደተፈጠረ የሱዳኑ ውሃ ሚንስትር እንደተናገሩ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ቀጣዩ ስብሰባ በአዲስ አበባ ታህሳስ 30 እና ጥር 1 ይካሄዳል፡፡

(WazemaRadio)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NISS #NIC

ብሔራዊ የመረጃ እና ደህንነት አገልግሎት የስያሜ ለውጥ ሊያደርግ ነው!

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ደመላሽ ገብረሚካኤል፥ ስር ነቀል ተቋማዊ ለውጥ በማድረግ ላይ ያለው አገልግሎቱ የስያሜ እና አሰራር ለውጥ የሚያደርግበት ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። ረቂቅ አዋጁ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ስያሜን ወደ ብሔራዊ መረጃ ማዕከል (ኤን አይ ሲ) እንዲሻሻል ይጠይቃል።

ረቂቅ አዋጁ ከፖለቲካ፣ ብሔር እና ሃይማኖት ጥገኝነት የተላቀቀ ነፃ የመረጃ እና ደህንነት ተቋም የመፍጠር የማሻሻያ ስራ አንዱ አካል መሆኑንም ተናግረዋል። ተቋማዊ ማሻሻያውን ተከትሎ የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት በአስር አመት ወስጥ ሊደርስበት የሚችለውን ደረጃ የሚያመላክት የአስር አመት ስትራቴጂክ እቅድም ተዘጋጅቷል።

(ኤፍ ቢ ሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ፦ - የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቻይና ሻንሲ ግዛት ልኡካን ቡድን ወደ ትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኢንቨስትመንት፣ ትምህርት፣ መአድን ልማት እና የሁለትየሽ ግንኝነት ዙርያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ለማድረግ እየመጣ መሆኑን በግልፅ ደብዳቤ ለክልሉ መንግስት መፃፉ ይታወቃል፡፡ ሆኖም የትግራይ ክልል መንግስት እንግዶቹን ለመቀበል ዝግጅቱን…
ለትግራይ ክልል የተሰጠ ምላሽ...

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ ለሥራ ጉብኝት ወደ ትግራይ ክልል ጉዞ ሊያደርጉ የነበሩ የቻይና የሻንሺ ግዛት ልዑካን አባላት በፌደራል መንግሥት ትዕዛዝ ወደ ክልሉ እንዳይጓዙ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ እገዳ ተደርጎባቸዋል ለሚለው የትግራይ ክልል መንግሥት ቅሬታ ከሱ ዕውቅና ውጪ መሆኑን አስታውቋል።

(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ዶክተር ማርቆስ ተክሌ...

የፌደራል መንግስቱ በውጭ ጉዳይ ሚንስትር በኤዥያና ፓስፊቅ ሀገራት ጉዳዮች መምሪያ እና የቻይና ፔኪንግ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሚስዮን አማካኝነት ከወራት በላይ ከግዛቲቱ ኃላፊዎች ጋር የደብዳቤ ልውውጥና ውይይት አድርጎ ለትግራይ ክልልም በደብዳቤ አሳውቆ በህጋዊ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው።

በቻይና የሻንሺ ግዛት ምክትል ሊቀመንበር የሚመራው ስድስት አባላት ያሉት ይኸው የቻይና የሻንሺ ግዛት ልዑካን ቡድን ከትግራይ ክልላዊ መንግስት ጋር በልማት እና አቅም ግንባታ ዙሪያ ልዩ ልዩ የትብብር የመግባቢያ ሰነዶችንም እንዲፈራረሙ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቅድመ ሁኔታዎችን አመቻችቷል።

ወደ ትግራይ እንዳይጓዙ ለምን ተከለከሉ?

ችግሩ የተከሰተው በ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳይሆን ከሱ እውቅና ውጭ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የጥበቃ አካላት ዘንድ የመረጃ መናበብ ክፍተት የፈጠረው ችግር ይመስላል። ጉዳዩን ከኤርፖት ጥበቃ አካላት እና ከሌሎች ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመነጋገር የምናጣራው ይሆናል።

ችግሩ ከተከሰተ በኃላም የቻይናው የልዑከን ቡድን በትዕግስት እንዲጠብቅ በማድረግ እና ከትግራይ ክልል መስተዳደር ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር በምክትል ፕሬዘዳንት ማዕረግ የትግራይ ክልል የንግድ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር አብርሃም ተከስተ የመግባቢያ ሰነዱን አዲስ አበባ ድረስ መጥተው እንዲፈራረሙ በማድረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ኃላፊነቱን በአግባቡ ተወጥቷል።

(አምባሳደር ዶክተር ማርቆስ ተክሌ)

(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Election2012

ምርጫ ቦርድ ለሚቀጥለው #ምርጫ የሚውሉ የፕላስቲክ ሳጥኖችን ግዢ እያከናወነ እንደሚገኝ የቦርዱ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች አማካሪ ሶልያና ሽመልስ ገለጹ።ሳጥኖቹ ለ48 ሺህ ምርጫ ጣቢያዎች የሚሆኑ የምርጫ ቁሳቁሶች ታሽገው የሚሰራጩባቸው ናቸው።

(Ethiopia Election)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETRSS1

በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ኢትዮጵያ ያመጠቀችው ሳተላይት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚመዘገብ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት ገለፀ፡፡ በአሁኑ ወቅት ሳተላይቷ ምህዋሯን ይዛ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ኢንስትቲዩቱ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ በቀጣዩ ጥቂት ቀናት ውስጥ ደግሞ ሳተላይቷ ወደ ዋናው ስራዋ ትገባለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በሶስት ዓመት ጊዜው ውስጥ የኮሚኒኬሽን ሳተላይት ለማስወንጨፍ መታቀዱም ተነግሯል፡፡

(MinT-EBC)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ትላንትና ዛሬ በተለያዩ ከተሞች በሞጣ ከተማ የተፈፀመውን ድርጊት የሚያወግዙ ሰልፎች ተደርገዋል። ትላንት በሀረር ከተማ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው አደባባይ በመውጣት ድርጊቱን አውግዟል፤ መንግስት ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀርብ ለእምነት ተቋማትም አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግ አሳስበዋል። በአሳሳ እና አርሲ ነጌሌ ተመሳሳይ ሰልፍ ተደርጓል። ዛሬ ደግሞ በጅጅጋ፣ ወራቤ፣ ዶደላ፣ ጪናቀሰን፣ ዱብቲ፣ባሌ ሮቤ ድርጊቱን የሚያወግዙ ሰልፎች ተካሂደዋል። በተደረጉት ሰልፎች ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ሰው አደባባይ ወጥቶ ድርጊቱን አውግዟል።

#Jigjiga
https://telegra.ph/DW-12-24

PHOTO: YeyaseineWodaj
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በህወሀት እና ኤርትራን በሚመራው ፓርቲ (ህግደፍ) መሀል እርቀ-ሰላም ለማውረድ ያሰበ ጉዞ ሰኞ ወደ ኤርትራ ሊደረግ ነው!

በህወሃትና ህግደፍ መሀል አለ የተባለውን ጥርጣሬ እና አለመግባባት ለመቅረፍ ያሰበ ጉዞ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ጠቅላይ ፅ/ቤት፣ የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት እና የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተወካዮችን ያቀፈ ቡድን ወደ አስመራ ሰኞ እንደሚጓዝ ዛሬ ተገልፁዋል። የሚድያ ተወካዮች፣ አርቲስቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አክቲቪስቶች እና ታዋቂ ግለሰቦች ቡድኑን ተቀላቅለው እንደሚጓዙ የፕሮግራሙ አዘጋጆች ዛሬ ተናግረዋል።

(Elias Meseret)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Election2012

"ኢትዮ-ፎረም" የቴሌቪዥን ዝግጅት ምርጫን የተመለከቱ በርካታ ጥያቄዎች ለምርጫ ቦርድ አባል ለዶ/ር ጌታሁን ካሳ አቅርቧል።" 'ምርጫ ይካሄዳል፤ አይካሄድም' የሚል ክርክር ሲደረግ #ምርጫ ቦርድ ለምን ዝም አለ?"ለሚለው ጥያቄ የሰጡትን መልስ ይመልከቱ።

(Ethiopia Election)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Election2012

"ኢትዮጵያ ውስጥ #ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ አለ ወይ?" በሚል የተጠየቁት ዶ/ር ጌታሁን ካሳ "እኛ እስካሁን ድረስ አለ ብለን ነው የምናምነው" ብለዋል። በ"ኮማንድ ፖስት" ስር ስላሉ ቦታዎች ስለሚቀርበው አቤቱታም ምላሽ ሰጥተዋል።

(Ethiopia Election)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Election2012

ኢዴፓ በ2012 እንደሚካሔድ የሚጠበቀው ምርጫ እንዲራዘም ጠየቀ!

ከዓመታት ውዝግብ በኋላ ባለፈው ሳምንት በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና የተሰጠው የእነ አዳነ ታደሰ ኢዴፓ ብሔራዊ ምክር ቤት አሁን ባለው አገራዊ እውነታ ምርጫው መራዘም እንዳለበት አምናለሁ ብሏል፡፡

የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በሰጠው መግለጫ ፅንፈኛ ኃይሎች በተጠናከሩበት፣ በማኅበራዊ ትስስር ገፆችና ሌሎችም መደበኛ መገናኛ ብዙኃን ቅራኔ በብዛት በሚሰራጭበት እንዲሁም፤ የፖለቲካ ሽግግር ባልተደረገበት እውነታ ምርጫው ለኢትዮጵያ ጥቅም ሳይሆን ጉዳት አምጪ ነው ሲል ተደምጧል፡፡

በመሆኑም ምርጫው እስከ ሁለት ዓመት ሊራዘምና አካታች የሽግግር መንግሥት በቅርቡ ሊቋቋም ይገባል ሲል ነው አቋሙን የገለፀው፡፡

በኢትዮጵያ ሲካሄድ የነበረው ባለተስፋ የለውጥ ሂደት የመክሸፍ አደጋ እየገጠመው ነው፤ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትም ከሕዝብ ጥቅም ይልቅ ወደሥልጣን ሽኩቻ እየገቡ ነው ሲልም ኮንኗል፡፡

(AHADU TV)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WNM

የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ዎብን) ዋና ጸሃፊ አንዷለም ታደሠ ትናንት ከእስር እንደተፈታ አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡ አንዷለም የታሰረው ከ5 ቀናት በፊት በወላይታዋ ሶዶ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤተ በእሳት እንዲያያዝ አስድርገኻል በሚል ነበር፡፡ ፓርቲው ውንጀላው የሐሰት ነው ብሏል፡፡

(አዲስ ስታንዳርድ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
FM 89.0 - #DillaUniversity

በዲላ ዩኒቨርሲቲ እና በአልካን ፎር ኮሚዩኒኬሽን ኤንድ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኀ/የተ/የግ/ማኅበር የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ተኮር የኤፍ.ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ዕቃዎች አቀርቦት፣ ተካላ፣ ሙከራና ትግበራን ያካተተ የሰምምነት ውል ተፈራረሙ፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ፣ የአልካን ፎር ኮሚዩኒኬሽን ኤንድ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኀ/የተ/የግ/ማኅበር የሽያጭና የገበያ ጥናት ኃላፊ አቶ ኢዩኤል ሃይለማርያም የስምምነት ውሉን የፈረሙ ሲሆን የድርጅቱ ፕሮጀክት ኃላፊ አቶ አሊ ፋቲ በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡

የማኅበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ አጠቃለይ 13,470465.56 ብር የሚፈጅ ፕሮጀክት ሲሆን በስምምነቱ መሠረት የሬዲዮ ጣቢያ ዕቃዎች አቀርቦት፣ ተካላ፣ ሙከራና ትግበራን ያካተተ አጠቃላይ ሥራው በ120 ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡

(Dilla University)

@tikvahethiopia @tikvaherhiopiaBot
ዶክተር አሚር ጤና ሚኒስቴርን በዚህ ሳምንት በይፋ ይሰናበታሉ፤ ለሌላም ስራ ወደ አሜሪካ ያቀናሉ!

(በጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት)

የስራ መልቀቂያ እንዳስገቡ ከወራት በፊት የተነገረላቸው የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ዛሬ የመልቀቂያቸው ደብዳቤ ተቀባይነት አግኝቶ ከሚኒስትር መ/ቤቱን ላገለገሉበት የምስጋና ሰርተክፌት እንደተዘጋጀ እንደሆነ ተስምቷል።

ጎዴ ለስራ የሚገኙት ዶ/ አሚር ነገ ወይም ከነገ ወዲያ የመልቀቂያ ደብዳቤያቸን ተቀብለው ጤና ሚኒስቴርን ይሰናበታሉ። ዶክተር አሚር አሜሪካ የሚገኝ ለግዜው ስሙ ያልተገለፀ አለም አቀፍ ተቋም ስራ እንዳገኙም ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GRD

በኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ሰሞኑን በሱዳን ካርቱም የተካሄደው የሶስትዮሽ ውይይት ውጤታማ እንደነበር የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ገለፁ።

ሚኒስትሩ ዶክተር ስለሺ በቀለ የኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የውሃ ሚኒስትሮች በካርቱም ያካሄዱት ውይይት ውጤታማ እንደነበር ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድና የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታ አልሲሲ በሩሲያ ሶቺ ከተማ ተገናኝተው ግድቡን በተመለከተ አራት ድርድሮችን ለማካሄድ ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል።

https://telegra.ph/ETH-12-24

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia