TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.82K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NISS #NIC

ብሔራዊ የመረጃ እና ደህንነት አገልግሎት የስያሜ ለውጥ ሊያደርግ ነው!

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ደመላሽ ገብረሚካኤል፥ ስር ነቀል ተቋማዊ ለውጥ በማድረግ ላይ ያለው አገልግሎቱ የስያሜ እና አሰራር ለውጥ የሚያደርግበት ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። ረቂቅ አዋጁ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ስያሜን ወደ ብሔራዊ መረጃ ማዕከል (ኤን አይ ሲ) እንዲሻሻል ይጠይቃል።

ረቂቅ አዋጁ ከፖለቲካ፣ ብሔር እና ሃይማኖት ጥገኝነት የተላቀቀ ነፃ የመረጃ እና ደህንነት ተቋም የመፍጠር የማሻሻያ ስራ አንዱ አካል መሆኑንም ተናግረዋል። ተቋማዊ ማሻሻያውን ተከትሎ የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት በአስር አመት ወስጥ ሊደርስበት የሚችለውን ደረጃ የሚያመላክት የአስር አመት ስትራቴጂክ እቅድም ተዘጋጅቷል።

(ኤፍ ቢ ሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NISS

ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት አለም አቀፍ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ ቡድን በጅቡቲ ወደብ በኩል ወደ ኢትዮጵያ በሽፋን ያስገባው ሁለት ኮንቴነር ህገወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

መነሻውን ከቱርክ ሜርሲን ወደብ ያደረገው ህገወጥ የጦር መሳሪያው፤ በጅቡቲ ወደብ በኩል ወደ ኢትዮጵያ በሽፋን ገብቶ በቁጥጥር ስር የዋለው፤ በወደቡ ለአምስት ወራት ያህል በድብቅ ተቀመጦ፤ በረቀቀ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ከገበ በኋላ መሆኑን አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ግምታቸው ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ የሆኑ 501 እሽግ ካርቶኖች፤ ከ18 ሺህ በላይ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦች ጋር መያዛቸውን የጠቆመው መግለጫው፤ ለሽፋን እንዲያገለግሉ ታስቦ የተዘጋጁና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በውስጣቸው የያዙ 229 እሽግ ካርቶኖችም ጭምር በቁጥጥር ስር ውለዋል።

More
https://telegra.ph/NISS-03-10

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NISS

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ፤ ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና የሌሎች መንግሥታዊ ተቋማት አባል ነን በማለት ኅብረተሰቡን እያጭበረበሩ በሚገኙ ግለሰቦች ላይ ክትትል በማድረግ እርምጃ እየወሰድኩ ነው አለ።

አገልግሎቱ ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዚህ የማጭበርበሪያ ስልት  የሚጠቀሙ አካላት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ነው ያለመከተው።

ሰሞኑን ተደርጓል ባለው ክትትል ፦

- ፈለቀ ዴብሳ ደማ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02፤ 

- አስፋው አዳማ ሙታ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01፤

- ሳምሶን ገነነ መንገሻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5፤

- ተስፋ ሀተው ገምቴሳ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር ሰበታ ክፍለ ከተማ ፤

- ዮሰን በቀለ ትክሳ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር ቡራዩ ክፍለ ከተማ ሐሰተኛ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትን መታወቂያ ይዘው ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጿል።

የሌሎች መንግሥታዊ ተቋማትን ሐሰተኛ መታወቂያ በመጠቀም ለሕገወጥ ድርጊት የሚያውሉ ግለሰቦችም በጸጥታ አካላት ተይዘዋል ብሏል።

ኅብረተሰቡ " የመንግሥታዊ ተቋማት  አባል ነን " በማለት በሐሰተኛ መታወቂያ የማጭበርበር ድርጊት ለመፈጸም ከሚሞክሩ ግለሰቦች ጋር በተያያዘ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙት ፦

👉 በ910 ነፃ የስልክ መስመር እና Info@niss.gov.et በሚለው የኢሜይል አድራሻ ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት

👉 በ816 እና 987 ነፃ የስልክ መስመር ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጥቆማ መስጠት ይችላል ተብሏል።

Credit : EPA

@tikvahethiopia