TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#CBE

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ የአብስራ ከበደ እንዳስታወቁት፣ የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ ብር ከ7መቶ 12 ቢልዮን ብር በላይ የደረሰ ሲሆን ከተመሰረተም 77 ዓመታትን አስቆጥሯል። ባንኩ ሲመሰረት የመነሻ ካፒታሉ አንድ ሚሊዮን የማርያ ትሬዛ የነበረ ሲሆን፣ አሁኑ ላይ ከ7መቶ 12 ቢልዮን ብር በላይ ሃብት ማከማቸት ችሏል።

(የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጎፋ ዞን በኮሌራ አራት ሰዎች ሞቱ!

በጎፋ ዞን በተከሰተው የኮሌራ በሽታ አራት ሰዎች መሞታቸውን የጎፋ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ። በሽታውን ለመቆጣጠር ልዩ ግብረ ኃይል መቋቋሙን ገልጿል። የመምሪያው ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ በቀለ እንደገለጹት ሰዎቹ የሞቱት በዑባ ደብረ- ጸሐይና ዛላ ሁለት ወረዳዎች ነው። ለሰዎቹ በተደረገው የላቦራቶሪ ምርመራ በበሽታው ሕይወታቸው ማለፉን ተረጋግጧል ብለዋል። በበሽታው የተጠቁ 119 ነዋሪዎች በተቋቋሙ ሁለት ጊዜያዊ የክትትልና ድጋፍ  ማዕከላት ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን አቶ ዓለማየሁ አስረድተዋል።

(ኢዜአ)
@tikvahethiopiabot @tikvahethiopia
ይነበብ!

#TIKVAH_ETH የፌስቡክ፣ የትዊተር፣ የኢንስታግራም ገፅ የለውም። በቤተሰባችን ስም የሚለጠፉ መረጃዎች እና መልዕክቶች በሙሉ እኛን የሚወክሉ አይደሉም!

ውድ ቤተሰቦቻችን ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን፣ ከቤተሰባችን አባላት፣ መረጃዎችን #እያሰባሰብን የምናስቀምጠው፦

ሚዛናዊ፣ ሁሉን በእኩል የሚያይ ስለ ነገ የሀገሪቱ ሁኔታ የሚያስብ፤ የሚጨነቅ፣ በምክንያት የሚያምን፣ ቅሬታውን በማስረጃ የሚያሳምን፣ በማህበራዊ ሚዲያ ያልተጨበጡ ወሬዎች የማይደናገር፣ የተረጋጋ፣ ሀገሪቷን ችግር ላይ ከሚጥል ወገንተኛ አካሄድ የነፃ አመለካከት፣ ነባራዊውን የሀገሪቱን ሁኔታ የሚረዳ፣ ቤተሰብ ለመፍጠር በማሰብ ነው።

በተጨማሪም የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆናችሁ ሰራተኞች በስራችሁ ላይ፣ ተማሪዎችም በትምህርታችሁ ላይ አትኩሮታችሁን አድርጋችሁ በቀን በተወሰነ ሰዓት ክፍተት የተፈጠሩ አዳዲስ ጉዳዮችን፣ የቤተሰባችን አባላት ያጋሩትን፣ በሚዲያዎች ሽፋን የተሰጣቸውን ጉዳዮችን እጅግ በአጭሩ ሳትሰለቹ እንድታነቡ ለማድረግ ነው።

እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መረጃ ለማግኘት የምትገሉትን ረጅም ሰዓት፣ እግረ መንገድም የምትመለከቷቸውን የጥላቻ ንግግሮችን ለማስቀረትም ያለመ ነው። በተጨማሪም ከአፀያፊ፣ የሰዎችን ክብር ከሚነኩ አስተያየቶች፣ ለግጭት ከሚያነሳሱ፣ አእምሯቹን ከሚረብሹ መልእክቶች እንድትርቁ ለማድረግ ነው።

ለቲክቫህ ቤተሰቦች መረጃዎች አይደበቁም፤ እንደወረዱም አይቀርቡም፤ እጅግ ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ ከመገናኛ ብዙሃን የምንሰማውን፣ የምናነበውን፣ ከቤተሰባችን አባላትም የሚላኩትን መረጃዎች በጥንቃቄ እናጋራለን።

እጅግ አደገኛ ጊዜ ላይ እንደምንገኝ ሁላችሁም የምታውቁት ነው። ማህበራዊ ሚዲያው ሀገር እያተራመሰ ነው፤ ለዚህም በቂ ማስረጃ ማቅረብ እንችላለን። እኛ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ስለምን እንደዚህ ያለ ነገር ውስጥ፤ ነገ ሊፀፅተን በሚችል ጉዳይ ላይ እንሳተፋለን? በፍፁም አናደርገውም! መረጃዎች ስናጋራ፣ ለፀጥታ እና ደህንነት፣ ለመንግስትም ችግር ሲኖር በገፃችን ጥቆማ ስንሠጥ የምንጠነቀቀውም ያለ ምክንያት አይደለም።

ለምሳሌ፦

ከዚህ ቀደም (ከሁለት ዓመት በፊት) ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሚታወቀው ቀጥታ የቤተሰቡን አባላት መልዕክቶችን እንደዋረደ እያጣራ በማጋራት ነው፤ በተለይ ዩኒቨርሲቲዎች እና ወጣቶች ላይ በማተኮር ያላቸውን ጥያቄዎች፣ ዜጎች በመንግስት ላይ ያላቸው ተቃውሞዎች፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ በዜጎች ላይ የሚደርሱ በደሎች፣ ፍትሃዊ ያልሆኑ ድርጊቶችን፣ በየተቋማት ውሥጥ በሰራተኞች ላይ የሚፈፀሙ በደሎችን ወዘተ...

በዛን ሠዓት እንኳን በድፍረት፣ ያለምንም ፍራቻ፣ ለማንም ሳንወግን ስናቀርብ፣ የናተንም መልዕክቶች ስናጋራ ነበር። ዛሬም አንደ አንድ የሀገሪቱ ዜጋ የትኛውም አካል መንግስት ላይ ቅሬታ ሲኖረው፣ ተበድያለሁ ካለ፣ የትኛውም ወገን ተቃውሞ ሲኖረው በቀጥታ እናቀርባለን። እኛ ከሚቀያየረው ፓርቲ ወይም መንግስት አልያም ሀገር አስተዳዳሪ ጋር ሳይሆን ከህዝቡ ጋር ነን!

ነገር ግን ጊዜ ወዲህ ነገሮች በሙሉ መልካቸውን ቀይረዋል (ለአብነት ዘንድሮ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የተፈጠረውን መመልከት በቂ ነው)፣ እያንዳንዱ ጉዳይ ወደ ብሄር ይቀየራል፣ ወደ ሃይማኖት ይዞራል። ይህ ነው ፈታኙ ሰዓት! አንድ ቦታ በሚሰጥ እና በሚነገር መረጃ ሌላ ቦታ ከፍተኛ እልቂት ሲፈፀም በተደጋጋሚ አይተናል።

በሀሰተኛ መረጃ ሰዎች ሲገደሉ፣ አለመረጋጋት ሲፈጠር፣ ሰዎች ሲፈናቀሉ፣ የእርስ በእርስ ግጭት ሲቀሰቀስ ሰምተናል። ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ በርካታ ጉዳዮች እየተመዘዙ እንደሆነ እየተመለከትን ነው እያንዳንዱን ነገር እንደ ከዚህ ቀደሙ እንደወረደ ይቅረብ ከተባለ ችግር አባባሽ እንጂ ችግር ፈቺ ቤተሰብ ልንሆን አንችልም።

ይህንን ያልተረዱ፤ አንዳንዶች ሆን ብለው፣ ምናልባትም ከሰላም ይልቅ እልቂት የሚፈልጉ፣ ሀገራችን እንድትፈርስ የሚፈልጉ፣ ሰላም ውለን ሰላም ስናድር የሚያማቸው፤ እንቅልፍ የሚነሳቸው ግለሰቦች እያንዳንዱን ብሄር ከየአቅጣጫው እየጠራን ነገሮች እንድናጋጋል ይፈልጋሉ፤ በፍፁም የሌለብንን፣ ወደፊትም የማይኖርብንን የሀይማኖት፣ የብሄር ወገንተኝነት ሊለጥፉብን ይፈልጋሉ እኛ እንዲህ ባለማድረጋችን፣ ለነሱ አጀንዳ ባለመመቸታችን ስድብ ያከናንቡናል፤ የጥላቻ ንግግሮችን ያዘንብቡናል።

እነሱ የሚሉት ካልሆነ ሌላው ጠላታቸው፣ የነሱ መረጃ ካልሆነ ዘረኝነት እና ወገንተኛ እንደሆነ አድርገው ይነግሩናል፤ የቤተባችንን ስም ለማጥፋት ይደክማሉ። ልፉ ሲላቸው 😊 ነገር ግን የቲክቫህ ባለቤቶች የሆኑ አባላት ( 508,500 በላይ ) ሁሉም ወጥቶ አልቆ አንድ ሰው ቢቀር እንኳን ሀገራችንን ወገናችንን አደጋ ላይ ለሚጥል ጉዳይ በፍፁም አንገዛም። ውድ ቤተሰቦቻችን ያለምንም ግፊት እና ማስታወቂያ ከ1 ተነስተን ግማሽ ሚሊዮን መድረሳችንን አትዘንጉት። ብቻችን ብንቀር እንኳን ሀገራችንን ሊያሳጣን፣ ህዝብን ከህዝብ ሊያፋጅብን ይችላል ከምንላቸው ጉዳዮች በሙሉ እንደራቅን እንቀጥላለን።

እኛ ሀገር በማተራመስ ውስጥ እጃችንን አናስገባም! ግጭት በማጋጋል ውስጥ አንሳተፍም! ብሄር ከብሄር፤ ሃይማኖት ከሃይማኖት በሚያጋጭ አፀያፊ ድርጊት እጃችን አይገባም ይህን በማድርጋችን ቅር የሚሰኝ ካለ የቤተሰባችን አባል መሆን አይገባውም። በኃላፊነት ቲክቫህ የኔ ነው ለሚሉ የቤተሰባችን አባላት መረጃዎችን በከፍተኛ ጥንቃቄ እናቀርባለን። በድጋሚ መልስ ብላችሁ ከሁለት ዓመት የነበረውን የሀገሪቱን የፖለቲካ ትኩሳት እና አሁን ያለውን ተመልከቱና ፍርዱን ስጡ!

ከ2 ዓመት በፊት እንደምናደርገው መረጃ እንደደረሰን፣ ከሚዲያዎች እንዳነበብን፣ እንደወረደ አናጋራም፤ ከናተ የተሻለ የሀገሪቱን ፈተና እና ከፊት ያለውን አደጋ የተረዳ አካል ያለ አይመስለንም። በመሆኑም እጅግ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ የቤተሰባችን አባላት #ብቻ ሚዛናዊ፣ ሁሉን አቀፍ፣ እውነተኛ፣ ገለልተኛ መረጃዎች እያሰባሰብን እንድታነቡ እንሰራለን።

እኛ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በየጊዜው የሃይማኖት ካርድ እየተመዘዘ፣ የብሄር ካርድ እየተመዘዘ እልቂት ውስጥ እንድንገባ፤ ሀገራችን ፈርሳ ሀገር አልባ ሊያደርገን በሚችል የማህበራዊ ሚዲያ አጀንዳ በፍፁም ተጠልፈን አንወድቅም!

508,500+☺️የቲክቫህ ቤተሰቦች፣ 508,500+☺️የቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለቤቶች!

Addis Abeba,Ethiopia
Wtsegab@gmail.com
0919743630
@tsegabtikvah
@tsegabwolde
@tikvahethiopia

@tikvahethiopiaBot 👈 የቤተሰባችን ሀሳብ መቀበያ!
ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ🛬አዲስ አበባ ገቡ!

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ። ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋርም የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ እና የፕሬዚዳንቱ አማካሪ የማነ ገብረአብ በጉብኝቱ ተካተዋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ ለሁለት አስርት ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነት ከታደሰ በኋላ በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። በአሁኑ ጉብኝታቸውም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

(ኤፍ ቢሲ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#PMOEthiopia

አዲስ ወግ የውይይት መድረክ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አዘጋጅነት የውይይት ባህልንነና የሐሳብ የበላይነትን ለማዳበር ታልሞ ተቃርኗዊ ዕሳቤዎችን ለማቀራረብ የሐሳብ ብዝኃነትን ለማዳበር እንዲሁም ለነበሩና አዲስ ለተፈጠሩ ችግሮች ፈጠራ የታከለባቸውን መፍትሔዎች ለማበረታታት ታስቦ የሚዘጋጅ መድረክ ነው፡፡ ዛሬም ለሦስተኛ ጊዜ በሂልተን ሆቴል ከተለያዩ ከጋዜጠኞች እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር "የሚዲያው ሚና ሐሳቦችን ለማቀራሀብ" በሚል ርዕስ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ዝግጅቱን አቶ ንጉሱ ጥላሁን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪ ዝግጅቱን ያስጀመሩ ሲሆን ቀጣይ በዶ/ር ሙላቱ አለማየሁ " ሚዲያ በሽግግር ወቅት" በሚል የጥናት ውጤት ያቀረቡ ሲሆን ቀጣይ የውይይት መድረኩን ጋዜጠኛ መለስካቸው አምሀ (ቪ.ኦ.ኤ ) እንዲሁም ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ( AP ) በአወያይነት እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ ተሳታፊዎች ደግሞ የውይይቱ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሶሪያ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም ተመድ ጠየቀ!

ሰሜን ምስራቃዊ ሶሪያ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ አሳሰቡ። በባለፈው ሳምንት የሃገሪቱ መንግሥት በአካባቢው በከፈተው ጥቃት በብዙ አስር ሺዎች የተቆጠረ ህዝብ ከመኖሪያው ተፈናቅሏል።

ዋና ጸኃፊ ጉቴሬዥ የተከፈተው ወታደራዊ ጥቃት ግዙፍነት እና ሲቪሎ ች መኖሪያቸውን እየጣሉ ወደሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የሚሸሹበትንም መስመርም እየደበደቡ ነው የሚሉት ዘገባዎች ዋና ጸኃፊውን እንዳሳሰቡዋቸው ትናንት ቃል አቀባያችው ያወጡት መግለጫ አመልክቷል።

የሶሪያ መንግሥት የርስ በርስ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት እኤአ ከ2011 ወዲህ ሽምቅ ተዋጊዎች ከያዝዋቸው ግዛቶች አሁንም በነሱ እጅ ያለች የመጨረሻዋ የሆነችውን ኢድሊብን ለማስለቀቅ እየሞከረ ነው።

(VOA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA #ERITREA

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኤርትራውን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ሁለቱ መሪዎች ኢትዮጵያና ኤርትራ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚችሉበት ጉዳይ ላይ መክረዋል። የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለአጭር ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማለዳ ላይ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
#OLF

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦ ነ ግ/ በሰሜን ሸዋ ዞን ፍቼ ከተማ ትላንት ቅርንጫፍ ከፈተ። ድርጅቱ በመጪው ምርጫ በሰላማዊና ዴሞከራሲያዊ መንገድ ለመሳተፍ መዘጋጀቱን የግንባሩ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ገልጸዋል። ግንባሩ በከተማውና በዞኑ የሚንቀሳቀስበትን ጽህፈት ቤት የከፈተው አባላቱ፣ ደጋፊዎቹና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት ሥነ ሥርዓት ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለፋሲል ቤተ መንግስት ጥገና የ400 ሚሊዮን ብር ጥናት ተጠናቀቀ!

የአጼ ፋሲል ቤተ መንግስት ህንጻዎችን ለመጠገን የ400 ሚሊዮን ብር የፕሮጀክት ጥናት ተጠናቋል፡፡ የፕሮጀክት ጥናቱ በቀጣዮቹ አምስት አመታት የጥገና ስራውን ደረጃ በደረጃ ለማካሄድ የሚያስችል ነው፡፡

በጥናቱ የአማራ ክልልና የፌደራል የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ከፍተኛ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ ለበጀቱ የፌደራል መንግስትና አለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶችም ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ከክልሉ መንግስት በተመደበ በጀትና ከጎብኝዎች ገቢ በተሰበሰበ 36 ሚሊዮን ብር የቤተ-መንግስቱ ዙሪያ አጥር ጥገና ተጀምሯል፡፡ በ16ኛው ክፍለ ዘመን የታነጸው የአጼ ፋሲል ቤተ መንግስት ህንፃ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1979 በዩኔስኮ በአለም የሰው ሰራሽ ቅርስነት የተመዘገበ መሆኑ ይታወቃል፡፡

(የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
መገናኛ ብዙሃን በግለሰቦችና በቡድኖች ነጻነታቸውን እያጡ መጥተዋል ተባለ!

መገናኛ ብዙሃን ከዚህ ቀደም በመንግስት ይደርስባቸው ከነበረው ነጻነት የማጣት ችግር ባለፈ በአሁኑ ወቅት በግለሰቦችና በቡድኖች አማካኝነት ነጻነታቸውን እያጡ መሆኑ ተገለጸ።

በኢትዮጵያ የህዝብና የግል መገናኛ ብዙሃን በግለሰቦችና በቡድኖች በሚደርስባቸው ጫና የሙያ ነጻነታቸውን እያጡ መሆኑ ተገልጿል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በየወሩ የሚካሄደው የአዲስ ወግ የውይይት መድረክ ‘የሚዲያ ሚና አሳቦችን ለማቀራረብ’ በሚል ርዕስ እየተካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ ላይ የግል መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች፣ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ባለሙያች፣ ታወቂ ግለሰቦች፣ ፖለቲከኞች እና ሌሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጡት ዶክተር ሙላቱ አለማየሁ ‘ሚዲያ በሽግግር ወቅት’ በሚል ርዕስ የመወያያ መነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል።

በዚህም ጊዜ የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ሚና እንደ ነባራዊ ሁኔታ የሚለያይ መሆኑን አንስተዋል። በተለይ የጸር ሽብር አዋጅ መጽደቅ በአገሪቱ የሚዲያ ታሪክ አሉታዊ አስተዋዕጾ እንደነበረው አስታውሰዋል።

በአሁን ጊዜ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ከባለፉት ዓመታት የተሻለ ቢሆንም ከመንግስት ባለፈ ከግልሰቦችና ከቡድኖች በሚደርስ ጫና የሙያ ነጻነት እየቀጨጨ መምጣቱን ዶክተር ሙላቱ ተናግረዋል።

(ኢዜአ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#Election2012 "ኢትዮጵያ ውስጥ #ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ አለ ወይ?" በሚል የተጠየቁት ዶ/ር ጌታሁን ካሳ "እኛ እስካሁን ድረስ አለ ብለን ነው የምናምነው" ብለዋል። በ"ኮማንድ ፖስት" ስር ስላሉ ቦታዎች ስለሚቀርበው አቤቱታም ምላሽ ሰጥተዋል። (Ethiopia Election) @tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Election2012

የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተሞች ምክር ቤቶች እንዲሁም የአካባቢ ምርጫዎች ከጠቅላላ ምርጫ ጋር አብረው እንዲካሄዱ በሐምሌ 2011 በፓርላማ ውሳኔ ተላልፎ ነበር። ዶ/ር ጌታሁን ካሳ (የምርጫ ቦርድ አባል) ግን "ቦርዱ እየተዘጋጀ ያለው ለጠቅላላ #ምርጫ ነው" ብለዋል።

(Ethiopia Election)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ!

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት 5 አፋጣኝ ምላሽ የሚሹ ያላቸውን ጥያቄዎችን ያቀረበ ሲሆን የክልሉ መንግስትም ለጣያቄዎቹ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠይቋል፡፡

1. በሞጣ የደረሰውን ችግር ለማጣራት በፌዴራል እስልምና ም/ቤቱ ለተሰየመው አጣሪ ኮሚቴ ክልሉ አስፈላጊውን እገዛ እንዲደረግ፣

2. ይህን ወንጀል ከመፈጸም በተጨማሪ ከባሕልና ልማዳችን ውጪ በኾነ መንገድ እምነት ተቋማት አቃጥለው ፉከራ እና ጭፈራ ሲያሰሙ የነበሩ ግለሰቦችና አካላትን በአስቸኳይ በመያዝ ተገቢውን ፍርድ አንዲያገኙ እንዲያደርግ፣

3. የንብረትም ሆነ ሌላ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች እና ድርጅቶች ተገቢው ካሳ እንዲሰጣቸውና በክልሉ መንግሥት ይቅርታ እንዲጠየቁ፣

4. የተቃጠሉ መስጂዶችን በአፋጣኝ በማስገንባትየ ዘወተር አገልግሎታቸውን እንዲሰጡ እንዲደረግ፣

5. በአጠቃላይ በክልሉ የሚገኙ ሙስሊሞች ያለባቸውን ችግር የሚያጣራ እና የሚፈታ ኮሚቴ በአጭር ጊዜ ተቋቁሞ ወደ ተግባር እንዲገባ እንዲያደርግ በድጋሚ እናሳስባለን በማለት አምስቱን ጥያቄዎች ምክር ቤቱ አስቀምጧል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በጋምቤላ ክልል የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የተገኙ ሰባት ግለሰቦች ተያዙ!

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎችን ሲያዘዋውሩ ያገኛቸውን ሰባት ተጠርጣሪዎች ባለፉት ሁለት ቀናት በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ቱት ኮር ዛሬ እንደለጹት ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከ12 ህገ-ወጥ የጦር መሳሪዎችና ከ741 ጥይቶች ጋር ነው። “ግለሰቦች የታያዙት ባለፉት ሁለት ቀናት በመንግስትና በግል ተሽከርካሪዎች የጦር መሳሪያዎችንና ጥይቶችን ጭነው ከኢታንግና ላሬ ወረዳዎች ወደ ጋምቤላ ከተማ ለማስገባት ሲሞክሩ ኢታንግ ኬላ ላይ በተደረገ ፍተሻ ነው” ብለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ታህሳስ 13/2012 ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት አካባቢና ትላንት ረፋድ ላይ በተለያዩ ሁለት ተሽከርካሪዎች በመደበቅ በድምሩ 12 ክላሽንኮቭ ጠመንጃና 741 የክላሽና የብሬን ጠመንጃ ጥይትችን ወደ ጋምቤላ ሊያስገቡ ሲሉ መያዛቸውን ተናግረዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎቹ የምርመራ ሒደቱ እንደተጠናቀቀ ክስ እንደሚመሰረትባቸው የጠቆሙት ምክትል ኮሚሽነር ቱት ኮር መሰል የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል የህብረተሰቡ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

(ኢዜአ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
መገናኛ ብዙሃን በግለሰቦችና በቡድኖች ነጻነታቸውን እያጡ መጥተዋል ተባለ! መገናኛ ብዙሃን ከዚህ ቀደም በመንግስት ይደርስባቸው ከነበረው ነጻነት የማጣት ችግር ባለፈ በአሁኑ ወቅት በግለሰቦችና በቡድኖች አማካኝነት ነጻነታቸውን እያጡ መሆኑ ተገለጸ። በኢትዮጵያ የህዝብና የግል መገናኛ ብዙሃን በግለሰቦችና በቡድኖች በሚደርስባቸው ጫና የሙያ ነጻነታቸውን እያጡ መሆኑ ተገልጿል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት…
የሚዲያው ሚና ሃሳቦችን ለማቀራረብ!

#PMOEthiopia እንደ ዶክተር ሙላቱ አለማየሁ ገለጻ የሚዲያው ዘርፍ በሀገራችን ከተጀመረበት 1992 ( እ.ኤ.አ ) ጀምሮ ብዙ ውጣወርረዶችን ማለፉን ይጠቅሳሉ፡፡ አንድ ጊዜ የህዝብን ድምጽ ሌላ ጊዜ ደግሞ የመንግስትን ድምጽ በማሰማት አልፎ አልፎ ገለልተኛ ሆነውም ለመዘገብ ሲሞክሩ ዘመናትን አልፈዋል፡፡

መንግስትም ለዘርፉ እድገት እንዲሁም ለሞያው ክብር ማነቆ የሆኑ ህጎችን ሲቀርጽ አንዳንዴም ከዛ በተቃራኒው ህጎችን ሲያሻሽል ቆይቷል፡፡ የሚዲያዎችን ጉዳይ የመቆጣጠር ኃላፊነት የተሰጠው የኢትዮጵያ የብሮድ ካስት ባለስልጣንም እስካሁን በተሰጠው ስልጣን ለመጠቀም ሲሞክር ቆይቷል፡፡

አሁን ላይ ግን የሚዲያ ነጻነትን ማስከበር በመንግስት ብቻ ሳይሆን እስከ ህዝቡ ዘልቆ የሚገባ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ጋዜጠኛ መብቱ ሳይረገጥ የመዘገብ መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የህብረተሰቡንም ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት መጣስ የለበትም፡፡ ሀገራችንን ወደፊት ሊያሻግሯት ከሚችሉ ጠንካራ ተቋማት መካከል አንዱ ሚዲያ ለመሆኑ ክርክር የለውም ይህንን የምንመራበት መንገድ ግን ሞያዊ ስነ-ምግባሩን በጠበቀ ትክክለኛ፣ ታማኝ፣፡ሚዛናዊ፣ ፍትሐዊ፣ ምሳሌያዊ መርሆዎችን ተጠቅሞ እንዲራመድ ካልስቻልነው ጉዳቱ የዛኑ ያህል የከፋ ይሆናል፡፡

https://telegra.ph/ETH-12-16

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአማራና የትግራይ ክልል ህዝቦችን ግንኙነት...

የአማራ እና የትግራይ ክልል ህዝቦችን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ነገ በአዲስ አበባ ምክክር እንደሚደረግ የሰላም ሚኒስቴር አስታውቋል።

የሰላም ሚኒስቴር ከጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሺፕ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በሚያዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ይገኛሉ ነው የተባለው።

(አውሎ ሚዲያ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፈተናው ቀን ተራዝሟል...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባወጣው የአዲስ ቅጥር ማስተዋቂያ ለተመዘገባችሁ የ2010 እና 2011 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የፈተናው ቀን ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሠው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ገልጿል።

#ሼር በማድረግ መረጃውን ለሌሎች አድርሱ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለብልጽግና ፓርቲ የእውቅና ሰርተፍኬት እንዲሰጠው ውሳኔ አሳለፈ።  

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፓርቲዎች ምዝገባ ጥያቄዎች ዙሪያ የተለያዩ ውሳኔዎችን በዛሬው እለት አሳልፏል። 

ቦርዱ የእውቅና ጥያቄ እና የፓርቲ መለያ ሰንደቅ አላማ የማጸደቅ ጥያቄን ያቀረቡ ፓርቲዎችን ጉዳይ በመመልከት ውሳኔ ማሳለፉንም ነው ዛሬ የገለፀው።

የኢህአዴግ አባል የነበሩ ሶስት ፓርቲዎች እና ሌሎች አምስት ፓርቲዎች በጋራ ራሳቸውን በማክሰም ብልጽግና ፓርቲን መመስረታቸውን በማሳወቅ የእውቅና ሰርተፍኬት እንዲሰጣቸው ህዳር 24 ቀን 2012 ዓ.ም ጥያቄ ማቅረባቸውን ቦርድ አስታውሷል።

https://telegra.ph/ETH-12-25

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሸገር ማስዋብ ፕሮጀክትን ጎበኙ!

የኤርትራዉ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በመሆን አዲስ አበባ ውስጥ በእንጦጦና አካባቢው የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ። የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ መግባታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ፕሬዚዳንቱም በዛሬው ዕለት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በመሆን በእንጦጦ አካባቢ የሚገኘውን የሸገር ማስዋብ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በዚሁ በእንጦጦ አካባቢ የፕሮጀክቱ አካል ሆነው እየተካሔዱ ያሉ የመንገድና ሌሎች የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ከልኡካን ቡድናቸው ጋር በመሆን መጎብኘታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል፡፡ እንዲሁም ፕሬዚዳንት የአንድነት ፓርክን መጎብኘታቸውን የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡

(ኤፍ.ቢ.ሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎቹን እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል!

"ድርጅታችን ብልፅግና ፓርቲ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የእውቅና ሰርተፊኬት በማግኘቱ የድርጅታችን አባላት እና ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን" - ብልፅግና ፓርቲ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia