TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#PMOEthiopia

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከአዲስ አበባ የታክሲ ባለቤቶች፣ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች ጋር የታክሲ ጣቢያውን አጸዱ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በካዛንቺስ የሚገኘውንና የ8 መሥመሮች መነሻ የሆነውን ጣቢያ ያጸዱት ለታክሲ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች አገልግሎት ያላቸውን ክብር ለማሳየት መሆኑን ገልጠዋል።

ምንጭ፡- የጠ/ሚር ፅ/ቤት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአብን ሊቀ መንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በትዊተር ገፃቸው!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ18 ዓመታት በፊት ተቋርጦ የነበረውን የግሪክ አቴንስ በረራ አገልግሎት መጀመሩን አስታወቀ። አየር መንገዱ እንዳስታወቀው፤ የግሪኳ አቴንስ ዳግመኛ ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ መረብ ውስጥ ተቀላቅላለች። አየር መንገዱ ታህሳስ 8 ቀን 2012 ዓ.ም የጀመረው የአቴንስ በረራ በአለም ላይ በሁሉም አህጉራት ያሉትን መዳረሻዎች ወደ 127 ከፍ እንደሚያደርገው ተገልጿል።

(ኢዜአ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አልፈልግም ማለት አልፈልግም ነው!

• "አቁም" ማለት አልፈልግም ነው!
• "መሸሽ" ማለት አልፈልግም ነው!
• "እምቢ" ማለት አልፈልግም ነው!
• "መግፋት/መገፍተር" ማለት አልፈልግም ነው!
• "ዝግጁ አይደለሁም" ማለት አልፈልግም ነው!
• "ተወኝ" ማለት አልፈልግም ነው!
• "ዞር በል" ማለት አልፈልግም ነው!
• "መጮህ" ማለት አልፈልግም ነው!
• "እረፍ" ማለት አልፈልግም ነው!
• "ማልቀስ" ማለት አልፈልግም ነው!

የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያንቺ ንቅናቄ ( Yanchi movement ) ለሶስት ቀን በሚቆየው የሴት ልጅ ጥቃትን በመቃወም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅተዋል፡፡ ዝግጅቱ ትላንት የተጀመረ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የ16 ቀን ንቅናቄ አንድ አካል እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጸውልናል፡፡ በዚህ ንቅናቄ በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ ሌሎች ክበባትም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በሌላ በኩል በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው "መራሂት ክበብ" አትኩሮቱን ሴት ተማሪዎችን በማብቃት ላይ አድርጎ እየሰራ ሲሆን ለሴት ተማሪዎች የፅዳት መጠበቂያ የሚሆን 88 ካርቶን ሞዴስ በመግዛት ለሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሴቶች ህፃናት ወጣቶች እና ኤችአይቪ ኤድስ ዳይሬክትቶሬት አስረክበዋል። የመጀመሪያውን ድጋፋቸውንም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቅርንጫፍ በሆነው በአዋዳ ካምፓስ አድርገዋል።

- በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስም እየሰራችሁት ላለው መልካም ስራና ለሌሎች ወጣቶች ትምህርት የሚሰጥ ተግባር ላይ በመሳተፋችሁ ያለንን አክብሮት እና ምስጋና እናቀርባለን!

#HawassaUniversity

በርቱልን!
@tikvahethiopia @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የጥምቀት ክብረ በዓል በዩኔስኮ መመዝገቡን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ መድረክ በሚሌኒየም አዳራሽ ተካሂዷል። የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የጥምቀት በዓል አከባበርን ከመስቀል በዓል፣ የገዳ ስርዓት እና የፍቼ ጨምበላላ ክብረ በዓላትን ተከትሎ አራተኛው የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ የሚታወስ ነው፡፡

(Mayor Office of AA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SomaliRegionalState

የሶማሌ ክልል በተወካዮች ምክር ቤት ያለው የውክል ቁጥር እንዲስተካከል የክልሉ ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፋ መሐመድ ዑመር ብሔራዊ ምርጫ ቦርድንና የፌዴሬሽን ምክር ቤትን በደብዳቤ ጠይቀዋል። ክልሉ 23 መቀመጫዎች በተወካዮች ምክር ቤት አሉት። ክልሉ በሕገ መንግሥቱ መሠረት 32 መቀመጫዎች ሊኖሩት ቢገባም ዘጠኝ ተቀንሶበት ለረጅም አመታት በ23 የውክልና መቀመጫ መቆየቱን አቶ ሙስጠፋ በደብዳቤያቸው ገልጸዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Congratulations - አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲው ለ 6ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 140 የሕክምና ዶክተሮች ትላንት ታኅሣሥ 11/2012 ዓ/ም በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል፡፡ ከእነዚህም መካከል 37ቱ ሴቶች መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"አንዳንድ አካላት ብሄርን ከብሄርና ሃይማኖትን ከሃይማኖት በማጋጨት ሰላምን ለማወክ የሚያደርጉት ጥረት አይሳካም። እነዚህ ኣካላት የማንንም ብሄርና ሃይማኖት አይወክሉም። የሃይማኖት ብዝሃነት የግጭትና የስጋት ምንጭ ሳይሆን የሰላም ፣ የመቻቻልና የአንድነት መሰረት ነው። በአሁኑ ወቅት የሃይማኖትና የብሄር እኩልነት ወደ ኋላ በማይቀለበስበት ደረጃ ደርሷል፤ ይሄን በመጣስ የሚከናወን አፀያፊ ተግባርን ሁሉም ሊያወግዘው ይገባል።" - ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም (የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AbiyAhemed #LemmaMegersa

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድና የመከላከያ ሚኒስትሩ ለማ መገርሳ መካከል የነበረ አለመግባባት "በበሳል የድርጅታችን ስራ አስፈጻሚ አመራሮችና በቀድሞ የትግል ጓዶች" ተፈቷል ሲል የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ አስታውቋል። ዶ/ር አብይ እና አቶ ለማ በጋራ ለመታገል ተስማምተዋል።

(እሸት በቀለ - ከጀርመን ድምፅ ሬድዮ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AbiyAhemed #LemmaMegersa

አቶ አዲሱ አረጋ ዛሬ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት በአስተዳራዊ ስርዓት በተለይም እንደ ሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታና አዳዲስ ሀሳቦችና የፓርቲ ሪፎርሞች በሚካሄዱበት ወቅት የሀሳብ ልዩነቶች ሊኖሩ ቢችሉም የሀሳብ ልዩነት በራሱ ችግር እንዳልሆነ ገልጸው ትልቁ ጉዳይ ይህን የሀሳብ ልዩነት እንዴት ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንፈታዋለን የሚለው ነው ሲሉ አክለዋል፡፡

አቶ አዲሱ በቅርቡ የፓርቲው አመራር የሆኑት አቶ ለማ መገርሳ ለመገናኛ ብዙሃን በመደመር ፍልስፍና እንዲሁም በፓርቲው ውህደት እንደማይስማሙ የገለጹትን ጠቅሰው ይህንን ጉዳይ በኦሮሞ ባህልና ስርዓት መሰረት የቀድሞ የኦዲፒ የስራ አመራሮች ሌሎችም ኃላፊዎች በተገኙበት የበሰለ ውይይት በማድረግና የነበሩ ልዩነቶችን በማጥበብ ከዚህ በኃላም አንድነትን አጠናክሮ አብሮ ለመስራት ተስማምተናል ብለዋል፡፡

አቶ አዲሱ አክለውም ፓርቲያቸው በዲሞክራሲ ባህል እና በኦሮሞ ባህልና ስርዓት የውስጥ ችግሩን ለመፍታትና ህብረተሰቡ ያለውን ጥያቄ ሁሉ ለመፍታት የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አቶ ለማ መገርሳ ብልፅግናን ደገፉ - ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባትም ተፈታ!

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የመከላከያ ሚኒስትር ለማ መገርሳ መካከል ተከስቶ የነበረው አለመግባባት በተከታታይ በአባ ገዳዎችና የአገር ሽማግሌዎች ጋር በተደረገ ውይይት ከመግባባት ላይ መደረሱ ተነግሯል። አቶ ለማ መገርሳ ያለውን ችግር በሂደት ለመፍታትና ከብልፅግና ፓርቲ ጋርም ለመስራት መስማማታቸውን OBN የቴሌቭዥን ጣብያ ማምሻውን ዘግቧል።

(SBS ሬድዮ አማርኛው አገልግሎት)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የወጪ እና የገቢ ንግድ ተነጣጥለው ኦዲት ሊደረጉ ነው!

የወጪ ንግድና የገቢ ንግድ ተቀላቅለው በመሰራታቸው አስመጪና ላኪዎች ኪሳራቸውን በተለያየ መልክ እያስመዘገቡ ያቀርቡ የነበረውን የውሸት ሪፖርት ለመከላከል ሁለቱም ለየብቻ ኦዲት ሊደረጉ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስትር ዴኤታው አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት፤ ቀድሞ አስመጪ ብቻ የነበሩ በሙሉ ወደ ላኪነት ገብተዋል። እነዚህ የውጪ ነጋዴዎች የውሸት የኪሳራ ሪፖርት እያቀረቡ በመሆኑ፤ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከአሁን በኋላ የወጪ ንግድ ራሱን ችሎ ኦዲት መደረግ ያለበት መሆኑን ለገቢዎች አመልክተዋል።

(EPA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA #SUDAN

የኢትዮጵያ የውሃ ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጄኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ጋር ተወያይተዋል፡፡ ሊቀመንበሩ በሱዳን እና በኢትዮጵያ ግንኙነት መካከል የታየውን የለውጥ ደረጃ አድንቀዋል፡፡

የሱዳን የመስኖ እና የውሃ ሀብት ሚኒስትር ኢንጂነር ያሲር አባስ በተገኙበት ሊቀመንበሩ ትናንት ምሽት በጽህፈት ቤታቸው ከኢትዮጵያ የውሃ ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በዚህ ወቅት ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር በሁሉም መስክ ያላትን ግንኙነት ማጠናከር እንደምትፈልግ መግለፃቸውን የሉዓላዊ ሽግግር ምክር ቤት ሚዲያ አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ልማት ማህበር...

የትግራይ ልማት ማህበር ድህነትን ለመቀነስ እያደረገ ላለው ጥረት የማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አሳሰቡ። የልማት ማህበሩ ከትናንት በስቲያ ባካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን 130 ሚሊዮን ብር አገኘ።

በገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶኑ ላይ የተገኙት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እንዳሉት፣ የልማት ማህበሩ በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ተደራሽነትን ለማስፋት በርካታ ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል።

በተያዘው ዓመትም ከ3 ሺህ በላይ የዳስ ትምህርት ቤቶችን ወደ ሕንጻ ክፍሎች ለመቀየር በማሰብ የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን ማዘጋጀቱን ተናግረዋል። ዶክተር ደብረጽዮን እንዳሉት በአሁኑ ወቅት በክልሉ ካሉ በርካታ ችግሮች መካከል የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ አንዱና መሰረታዊ ጉዳይ ነው። የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ ብቁና አገሩን የሚወድ ትውልድ ለማፍራት ማህበሩ የጀመረውን እንቅስቃሴ እንዲያጠናክርም ጠይቀዋል።

ሥራ ፈጣሪና ችግር ፈቺ ትውልድን ለማፍራት በሚደረገው ጥረት የትግራይ ልማት ማህበርን በገንዘብ፣ በእውቀትና በጉልበት ማጠናከር እንደሚገባም ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ተናግረዋል። በተለይ የማህበሩ አባላትና ደጋፊዎች አቅማቸውን በማሰባሰብና አንድነታቸውን በማጠናከር ለማህበሩ ሲያደርጉት የነበረውን ድጋፍ  አጠናክረው እንዲቀጥሉ አስገንዝበዋል።

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አዲሱ ኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ሳይፀድቅ በመኪኖች ላይ እሰከ 100,000 ብር ጭማሪ እየታየ ነው!

ፓርላማው እስከ 500% የሚደርሰውን ረቂቅ የመኪኖች የኤክሳይዝ ታክስ መመርያ መመልከቱን ተከትሎ በመዲናችን አዲስ አበባ በቲዮታ ኮሮላ እና በቪትዝ መኪኖች ላይ እስከ 100,000 ብር ጭማሪ አየታየ ሲሆን ሌሎች ባገለገሉ መኪኖች ላይም ከ50,000 እሰከ 80,000 ብር ጭማሪ እየታየ ነው።

(Tesfaye Getnet)
PHOTO: Elias Meseret
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች 22 ደርሰዋል!

በምሥራቅ ጎጃም ሞጣ ከተማ ቤተ እምነቶች ላይ ጥቃት አድርሰዋል ተብለው የተጠረጠሩና በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች ቁጥር 22 መድረሱ ተነግሯል። የምርመራ ስራውም እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።

የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ዋና ኢንስፔክተር አያልነህ ተስፋዬ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በጥቃቱ የተጠረጠሩ እስካሁን ድረስ 22 ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ማህበረሰቡ ጥፋተኞችን እየጠቆመ በመሆኑ ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል ተናግረዋል። በፖሊስ የተያዙት ተጠርጣሪዎችም እንደተያዙበት ቅደም ተከተል ወደ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ መደረጉንም ዋና ኢንስፔክትር አያልነህ ጨምረው ገልፀዋል።

የተጠርጣሪዎቹ ቁጥርም ሊጨምር ስለሚችል አዳዲስ ሰዎች በቁጥጥር ስር የሚውሉ ከሆነም ምርመራ በማድረግና ሕጉ በሚያዘው መሰረት ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ይደረጋል ብለዋል። በሞጣ ከተማ ሁኔታዎች መረጋጋታቸውን የተናገሩት ዋና ኢንስፔክተር አያልነህ፤ በከተማዋም ያለው ጥበቃም መጠናከሩን ተናግረዋል።

የክልሉ ፖሊስ ከልዩ ኃይል ጋር በመሆንም የሞጣ ከተማን ወደነበረችበት መረጋጋት ለመመለስ እየተሰራ ነው ያሉት ኢንስፔክተር፤ በተፈጸመው ወንጀል ዙሪያ የምርመራ ሥራውም፣ የማረጋጋት ሥራውም ሆነ ሕዝብ ለሕዝብ የማገናኘት ሥራውን ጎን ለጎን እየተካሄዱ መሆናቸውንም አስረድተዋል። ትምህርት ቤቶች፣ የመንግሥት ቢሮዎች ተከፍተዋል በማለት ምናልባት የተቃጠሉ ሱቆች አካባቢ ያሉት ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ወደ መደበኛው ሕይወቱ ተመልሷል ሲሉ አረጋግጠዋል።

https://telegra.ph/BBC-12-23

(BBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባምባሲ ፖሊስ ማሰልጠኛ...

'በባምባሲ ፖሊስ ማሰልጠኛ' ስልጠናቸውን የተከታታሉ ከ1,000 በላይ ሚኒሻዎች በትላንትናው ዕለት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን  በተገኙበት ተመርቀዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በመንገዶች ምቹ አለመሆን ምክንያት የነዳጅ አቅርቦቱ ላይ ጫና አሳድሯል ተባለ!

በአገር ውስጥ በርካታ አካባቢዎች የተከሰተውን የነዳጅ እጥረት በመንገዶች ምቹ አለመሆን ምክንያት አቅርቦቱ ላይ መስተጓጎል ተፈጥሯል የሚል ግምት እንዳለው የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ገለፀ።

የድርጅቱ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አለማየሁ ፀጋዬ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ እንደተናገሩት ወደ አገር ውስጥ ነዳጅ በዋናነት የሚገባው በሱዳን እና በጅቡቲ በኩል ሲሆን ከጅቡቲ ወደ መሐል አገር የሚወስደው መንገድ በመበላሸቱ እና እንደ ልብ ለማሽከርከር የማይመች በመሆኑ ነዳጅ ጫኝ ተሸከርካሪዎች ለቀናት መንገድ ላይ መቆየት ግድ እንደሚሆንባቸው ገለፀዋል።

አያይዘውም በዚህ የተነሳ በጊዜ መቅረብ ያለበት ነዳጅ ሳይቀርብ በመቅረቱ በከተሞች ላይ የሚታየው ረጃጅም ሰልፎች እንዲከሰት ምክንያት ናቸው ብለዋል።

አለማየሁ ሲናገሩ በሱዳን በኩል የሚገባው ነዳጅ በተገቢው መንገድ እየገባ በመሆኑ የተፈጠረውን ችግር በጥቂትም ቢሆን እያስታገሰው የሚገኝ ቢሆንም በዚሁ ከቀጠለ ግን በቀጣይ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከመጠባበቂያ በማውጣት እና በማከፋፈል ዕጥረቱን ለመቅረፍ እንደሚሰራ ተናግረዋል። ጨምረውም በአገር ውስጥ በቂ መጠባበቂያ የነዳጅ ክምችት መኖሩንም ገልፀዋል።

(አዲስ ማለዳ ጋዜጣ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia