TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.8K photos
1.37K videos
198 files
3.65K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ -ህወሓት ተወካይ አቶ #ጌታቸው_ረዳ በብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ካስተላለፉት የአጋርነት መልዕክት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፦

o ጉባዔው የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ዳር ለማድረስ ትልቅ ሚና አለው ብሎ ህወሓት ያምናል፡፡

o ሀገራችን ካለችበት አጓጊ ተስፋና ስጋት አሸንፋ የምትወጣበትን ውሳኔዎችን ብአዴን እንደሚያሳልፍ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

o ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ብዙ ተጉዘናል፣ አሁንም በተሻለ መልኩ ለመስራት የሚያስችል ቁመና እንደሚፈጠር እንጠብቃለን፡፡

o አንዳንዶቻችን በሂደት ህዝቡን ከመጥቀም ይልቅ ራሳችንን መጥቀም እያሸነፈን ሄዶ የህዝቡን ጥያቄዎች መመለስ ተስኖናል፡፡

o የበደልነውን ህዝብ መካስ ይኖርብናል፡፡
o የአማራ ህዝቦች ክቡር መስዋዕትነት የከፈሉ ኩሩ ህዝቦች ናቸው፡፡

o ከሌሎች ህዝቦች ጋር የሚጋጭ ፍላጎት እንደሌለውም እናምናለን፡፡

o በህዝቦቻችን መካከል #መጠራጠር እንዳንፈጥር መጠንቀቅ ይኖርብናል፡፡

o አልፎ አልፎ በአማራና በትግራይ ህዝቦች መካከል ልዩነት ለመፍጠር የሚደረገው ሙከራ #ሊወገዝ ይገባዋል፡፡

o ቁርኝቱን ይበልጥ ለማጠናከር ህወሓት ከብአዴንና ከአማራ ህዝብ ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ ነው፡፡

o ብአዴን ከ12ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ የክልሉን ህዝብ የተጠቃነት ጥያቄ ጭምር የሚያረጋግጡና ለውጡን የሚያጠናክሩ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ እና ህወሓትም ከብአዴን ጋር በጋር እንደሚሰራ አረጋግጣለሁ፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update መቀለ⬇️

ህወሓት “የፖለቲካ #መስመሩን የመቀየር ዕቅድም ሆነ ምክንያትም የለኝም” ሲል አስታውቋል።

አራተኛ ቀኑን ያስቆጠረው 13ኛው የህወሓት ጠቅላላ ጉባዔ #በመቀለ እየተካሄደ ሲሆን፤ ድርጅቱ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አቶ #ጌታቸው_ረዳ እንደተናገሩት፤ የፖለቲካ መስመር የሚወሰነው በዋናነት የቆመለት የህብረተሰብ ክፍል የደረሰበት የዕድገትና የለውጥ ደረጃ ነው፡፡

ህወሓት ደግሞ ሰፊውን ገበሬና ደሃውን ለሚወግነው ልማታዊ ዴሞክራሲ መስመር የሚያራምድ ነው። ህወሓት የእነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎች የኑሮ ሁኔታ የመለወጥ ዓላማ ይዞ የሚንቀሳቀስ አስተሳሰብ አለው ያሉት አቶ ጌታቸው፤ ይህንንም በሚፈለገው ደረጃ እንደለወጠ ዕምነት ያለው ድርጅት ሲሆን ብቻ ነው የአስተሳሰብ መስመሩን #ሊቀይር የሚችለው ሲሉ አብራርተዋል፡፡

ህወሓት ተራማጅ አስተሳሰብ የሚያራምድ ድርጅት በመሆኑ መሻሻል ያለባቸው ፖሊሲና ስትራተጂዎች ካሉ ግን የህዝቦችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ በሚችል መልኩ ማስተካከያ እያደረገ ይራመዳል ሲሉ ጠቁመዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፕሬሥ ድርጅት
@tikvahethiopia @tsegabwolde
"አቶ በረከትና አቶ ታደሰ በሙስና መጠርጠራቸው #አስደንቆኛል" አቶ ጌታቸው ረዳ
.
.
የቀድሞው ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣን አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳ በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር መዋላቸው እንዳስደነቃቸውና በዚህ ደረጃ ያልጠበቁት መሆኑን አቶ #ጌታቸው_ረዳ ተናገሩ።

ለእስሩ ሌላ ምክንያት ካለ በግልጽ እንዲነገር የጠየቁት አቶ ጌታቸው ከሙስና አንጻር የሚጠየቁ ከሆነ አቶ በረከትና አቶ ታደሰ በመጨረሻው ደረጃ ላይ የሚገኙ ናቸው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

በሁለቱ ግለሰቦች መያዝ ላይ አስተያየታቸውን የተጠየቁት የቀድሞው የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ እስሩ ላይ ጥርጣሬ እንዳለቸውምና ፖለቲካዊ ነው ብለው እንደሚያምኑ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ሁሉንም ዝርዝር ነገሮችን አውቃለሁ ወይም በሁሉም ጉዳይ ላይ ተሳትፌያለሁ እንደማይሉ የተናገሩት አቶ ጌታቸው፣ የአቶ በረከትና የአቶ ታደሰ የመታሰር ዜና ያልጠበቁት እንደሆነ ተናግረዋል።

"እንደፓርቲው ከፍተኛ አመራር እርምጃው አስደንቆኛል። ከሙስና ጋር በተያያዘ ስማቸው የሚነሳ በርካታ ሰዎች አሉ፤ መናገር የምፈልገው በረከትና ታደሰ ግን ከዚህ አንጻር በመጨረሻው ደረጃ ላይ ሊቀመጡ የሚችሉ ናቸው። ነገር ግን ስለማንም በእርግጠኝነት መናገር አልችልም።"

"ከዚህ በፊት በረከት ፀረ-አማራ አመለካከት አለው በሚል ሲከሰስ እንደነበር አውቃለሁ" ያሉት አቶ ጌታቸው "ቢሆንም እስሩ ከአንድ ብሔር ወይም ከሌላ ጋር የተያያዘ ነው አልልም፤ ይህ እስር በአብዛኛው ፖለቲካዊ ነው" ሲሉ አስረድተዋል።

ለእራሳቸው ይሰጉ እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ጌታቸው በግላቸው ምንም ስጋት እንደሌላቸው ነገር ግን በእሳቸው ላይ የተቀነባበረ ክስ ቢቀርብባቸው ብዙም እንደማይደንቃቸው ተናግረዋል።

ጨምረውም ቢሆንም አመራሩ ይህን ያህል ይወርዳል ብለው ስለማያስቡ "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገሮችን ያስተካክላሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል።

በዚህ ወይም በዚያ ተግባር ላይ የተሳተፉ ሰዎች ይኖራሉ ያሉት አቶ ጌታቸው ነገር ግን በረከትንና ታደሰን መክሰስ ግን የማይታመን ነው ሲሉ የተፈጠረባቸውን ስሜት ለቢቢሲ ገልፀዋል።

ተገቢውን ፍትህ ያገኛሉ ብለው እንደሚያስቡ ተጠይቀው ሲመልሱ "ያ ይሆናል ብዬ አላስብም። አንድ ሰው የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚያደርግ ወይም የክልል ወይም የፌደራል መንግሥትን የሚተች በመሆኑ ለእስር የሚዳረግ ከሆነ፤ ተገቢውን ፍትህ ያገኛል ብሎ መጠበቅ በእኔ በኩል የዋህነት ነው። ቢሆንም ተገቢውን ፍትህ ያገኛሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ሰፊ የለውጥ ፍላጎት ህዝቡ ዘንድ መኖሩ በተለይ ወጣቱ ከዴሞክራሲ፣ ከልማት ያሉበትን ጥያቄዎች በተደራጀ መልኩ ማቅረብ መጀመሩ እንደ ትልቅ እድል ነው። አሁንም ቢሆን የጠፉ የባከኑ እድሎች የሚለው የለኝም። ስለዚህ ከለውጥ አንፃር ትልቁ እድል የህዝቡ የለውጥ ፍላጎት ነው። ...ኢህአዴግ ከነችግሩም ቢሆንም ከነ ብዙ ችግሮቹም ቢሆን ያስቀመጣቸው መልካም መሰረቶች አሉ። በተለይ በልማት የህዝባችንን የኑሮ ግንዛቤ ከመሰረቱ የቀየረ ስራ ነው የሰራው ኢህአዴህግ እዚህ ላይ ብዥታ ሊኖረን አይገባም። ሰዎች የማደግ ፍላጎት ተጨማሪ ሀብት የማግኘት ፍላጎት ኢህአዴግ የጀመራቸው እንቅስቃሴዎች የፈጠሩት ነው።" አቶ #ጌታቸው_ረዳ/የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል/

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia