TIKVAH-ETHIOPIA
1.5M subscribers
56.7K photos
1.41K videos
203 files
3.87K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ -ህወሓት ተወካይ አቶ #ጌታቸው_ረዳ በብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ካስተላለፉት የአጋርነት መልዕክት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፦

o ጉባዔው የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ዳር ለማድረስ ትልቅ ሚና አለው ብሎ ህወሓት ያምናል፡፡

o ሀገራችን ካለችበት አጓጊ ተስፋና ስጋት አሸንፋ የምትወጣበትን ውሳኔዎችን ብአዴን እንደሚያሳልፍ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

o ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ብዙ ተጉዘናል፣ አሁንም በተሻለ መልኩ ለመስራት የሚያስችል ቁመና እንደሚፈጠር እንጠብቃለን፡፡

o አንዳንዶቻችን በሂደት ህዝቡን ከመጥቀም ይልቅ ራሳችንን መጥቀም እያሸነፈን ሄዶ የህዝቡን ጥያቄዎች መመለስ ተስኖናል፡፡

o የበደልነውን ህዝብ መካስ ይኖርብናል፡፡
o የአማራ ህዝቦች ክቡር መስዋዕትነት የከፈሉ ኩሩ ህዝቦች ናቸው፡፡

o ከሌሎች ህዝቦች ጋር የሚጋጭ ፍላጎት እንደሌለውም እናምናለን፡፡

o በህዝቦቻችን መካከል #መጠራጠር እንዳንፈጥር መጠንቀቅ ይኖርብናል፡፡

o አልፎ አልፎ በአማራና በትግራይ ህዝቦች መካከል ልዩነት ለመፍጠር የሚደረገው ሙከራ #ሊወገዝ ይገባዋል፡፡

o ቁርኝቱን ይበልጥ ለማጠናከር ህወሓት ከብአዴንና ከአማራ ህዝብ ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ ነው፡፡

o ብአዴን ከ12ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ የክልሉን ህዝብ የተጠቃነት ጥያቄ ጭምር የሚያረጋግጡና ለውጡን የሚያጠናክሩ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ እና ህወሓትም ከብአዴን ጋር በጋር እንደሚሰራ አረጋግጣለሁ፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትግራይ ክልል ምክር ቤት‼️

የትግራይ ክልል ምክር ቤት በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀውን የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ #በመቃወም ውሳኔ አስተላለፈ።

ምክር ቤቱ ውሳኔውን ያስተላለፈው በመቐለ ከተማ እያካሄደ ባለው 5ኛ ዓመት 14 መደበኛ ጉባዔው ነው።

ምክር ቤቱ በውሳኔ ሀሳቡ አዋጁ የፌዴራል መንግስት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ በመግባት የክልላዊ አስተዳደር መብትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስልጣንን እንዲጋፋ የሚያደርግ ነው ብሏል።

በተጨማሪም በክልሎች፣ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች መካከል #መጠራጠር እንዲፈጠር የሚያደርግ እንደሆነም ነው ምክር ቤቱ በውሳኔ ሀሳቡ የገለፀው።

ለዚህም ኮሚሽኑ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በሕገ መንግስት የተሰጣቸውን ስልጣን ተክቶ የወሰንና የማንነት ጉዳዮችን ለመመልከት መቋቋሙ ስሕተት ነው ሲል በውሳኔ ሀሳቡ አስፍሯል። ምክር ቤቱ በመጨረሻም አዋጁን በመቃወም የተዘጋጀውን የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia