TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.7K photos
1.37K videos
198 files
3.64K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከጊምቢቹ⬆️

"ትላንት ረቡዕ ምሽት በጊምቢቹ (ከሆሳዕና 32 ኪሜ) እና አካባቢዎች ባሉ ቦታዎች በጣለው ከፍተኛ ዝናብ እና በረዶ ምክንያት አካባቢው በበረዶ ተሸፍኗል። Dagi ነኝ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲግራት⬆️

"ተዋዶ ያለበት እስላም ክርስቲያኑ
ተዘነጋሽ እንዴ ኢትዮጵያ መሆኑ
አንቺም በሀይማኖትሽ እኔም በሀይማኖቴ
መኖር እንችላለን አይጠበንም ቤቴ። ፀግሽ ከላይ የምትመለከተው ፎቶ ከአዲግራት ነው መስቀልን #ከሙስሊም ወንድሞቻችን ጋር እያከበርን ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁሉም ውስጡ #ስጋና #ደም
ቀለም መልኩ ቢለያይም
ወላጁ #አንድ ነው አባቱ አንድ ነው
ዞሮ ዞሮ #አዳም
.
.
ሰውነት ይከበር!
ሰውነት ይቅደም!
#ETHOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቤንሻንጉል⬇️

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሽ ዞን #አመራሮች ላይ በተፈፀመ ጥቃት፣ አራቱ ህይወታቸው አለፈ።

መስከረም 16፣2011 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አመራሮች ላይ የተፈፀመዉን ጥቃት ተከትሎ በከማሽ ዞን የተፈጠረዉን #ዉጥረት ለማርገብ የፀጥታ ኃይል በስፍራዉ ደርሶ #የማረጋጋት ስራ እየሰራ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ #ሰይፈዲን_ሐሩን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት መስከረም 15፣ 2011 ዓ.ም በአሶሳ ከተማ ላይ ተካሂዶ በነበረዉ የቤኒሻንጉል እና የኦሮሚያ ክልሎች የጋራ የፀጥታ ጥምር ኮሚቴ የዉይይት መድረክ ላይ ተሳትፈዉ መስከረም 16፣ 2011 ዓ.ም ወደ ከማሽ ዞን በመመለስ ላይ የነበሩ የዞኑ አመራሮች ላይ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ኃይሎች ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል፡፡

በጥቃቱም 4 የካማሽ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ህይወታቸዉ አልፏል፡፡ ጥቃቱን የፈፀሙ አካላትን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል መንግስት #የፀጥታ ኃይሎችን በስፍራዉ ማሰማራቱን ኮሚሽነሩ አስታዉቀዋል፡፡

ይሁን እንጂ በከማሽ ዞን አመራሮች ላይ የተፈፀመዉን #ጥቃት ተከትሎ በካማሽ ከተማ ላይ ዉጥረት ነግሷል። የመንግስትና የንግድ ተቋማት ተዘግተዋል፡፡

ዉጥረቱን ለማብረድ የፀጥታ ሃይሎች በስፍራዉ ገብተዉ የማረጋጋት ስራ እየሰሩ መሆናቸዉን ኮሚሽነር ሰይፈዲን ተናግረዋል፡፡

በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች መካከል #ግጭት ለመፍጠር የተለያዩ የጥፋት አጀንዳዎችን ይዘዉ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች እንዳሉ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

እነዚህን ኃይሎች ለመመከት የኦሮሚያና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስታት የጋራ ዕቅድ አዉጥተዉ እየሰሩ መሆናቸዉን ኮሚሽነር ሰይፈዲን ገልጸዋል፡፡

በፀረ ሰላም ሃይሎች ዕኩይ ሴራ በሁለቱ ክልል ህዝቦች መካከል ያለዉ የአንድነትና የትብብር መንፈስ ይበልጥ ያጠነክረዋል እንጂ፣ ሊሸረሽረዉ እንደማይችል ኮሚሽነሩ በመግለጫቸዉ አስታዉቀዋል፡፡

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን በመወከል በ12ኛው የብአዴን ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ንግግር ያሰሙት አቶ አሸብር ረጋሳ ተፈፀመውን ጥቃት በማውገዝ ድርጊቱን የፈፀሙ ኃይሎችን በማጋለጥ ለህግ እንዲቀርቡ የአካባቢው ህዝብ እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በጥቃቱ ህይወታቸዉን ላጡ የከማሽ ዞን አመራሮች የክልሉ መንግስት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማዉ በመግለጫዉ አስታዉቋል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ -ህወሓት ተወካይ አቶ #ጌታቸው_ረዳ በብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ካስተላለፉት የአጋርነት መልዕክት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፦

o ጉባዔው የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ዳር ለማድረስ ትልቅ ሚና አለው ብሎ ህወሓት ያምናል፡፡

o ሀገራችን ካለችበት አጓጊ ተስፋና ስጋት አሸንፋ የምትወጣበትን ውሳኔዎችን ብአዴን እንደሚያሳልፍ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

o ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ብዙ ተጉዘናል፣ አሁንም በተሻለ መልኩ ለመስራት የሚያስችል ቁመና እንደሚፈጠር እንጠብቃለን፡፡

o አንዳንዶቻችን በሂደት ህዝቡን ከመጥቀም ይልቅ ራሳችንን መጥቀም እያሸነፈን ሄዶ የህዝቡን ጥያቄዎች መመለስ ተስኖናል፡፡

o የበደልነውን ህዝብ መካስ ይኖርብናል፡፡
o የአማራ ህዝቦች ክቡር መስዋዕትነት የከፈሉ ኩሩ ህዝቦች ናቸው፡፡

o ከሌሎች ህዝቦች ጋር የሚጋጭ ፍላጎት እንደሌለውም እናምናለን፡፡

o በህዝቦቻችን መካከል #መጠራጠር እንዳንፈጥር መጠንቀቅ ይኖርብናል፡፡

o አልፎ አልፎ በአማራና በትግራይ ህዝቦች መካከል ልዩነት ለመፍጠር የሚደረገው ሙከራ #ሊወገዝ ይገባዋል፡፡

o ቁርኝቱን ይበልጥ ለማጠናከር ህወሓት ከብአዴንና ከአማራ ህዝብ ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ ነው፡፡

o ብአዴን ከ12ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ የክልሉን ህዝብ የተጠቃነት ጥያቄ ጭምር የሚያረጋግጡና ለውጡን የሚያጠናክሩ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ እና ህወሓትም ከብአዴን ጋር በጋር እንደሚሰራ አረጋግጣለሁ፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አርባ ምንጭ⬆️

የኦሮሞ አባ ገዳዎች እና ወጣቶች በአርባ ምንጭ ከተማ ከጋሞ ብሄረሰብ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ምክክር አድርገዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ድሬዳዋ⬇️

የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የፍትኅ ፀጥታና ሕግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ መሐመድ አሕመድ #ያለመከሰስ መብት ተነስቷል።

የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የአቶ መሐመድን ያለመከሰስ መብት ያነሳው በትናንትናው ዕለት ባካሔደው አስቸኳይ ስብሰባ ነው።

በምትካቸው አቶ ኢብራሒም ዩሱፍ መሾማቸውን የጀርመን ድምፅ ራዲዮ ክልሉን ጠቅሶ ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከተው አካል‼️

"ፀግሽ ሰላም ነህ? ጥቆማ ልስጥህ በቤንሻንጉል ጉምዝ መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ነው። ነገሩ በጣም አሳሳቢ ነው ግጭት ለማስነሳት #የሚጣጣሩ አካላት አሉ እና ሰው ፈርቶ ነው ያለው ወደ ሌላ ነገር ሳይሄድ የፀጥታ አካላት አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ለሚመለከተው አካል አድርስልን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀረሪ ክልል⬇️

የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እና ህገ ወጥነትን ለማስቀረት የሚሰራ ኮሚቴ ማቋቋሙን የሐረሪ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ ገልፀዋል፡፡

የሐረሪ ክልል ርዕስ መስተዳር አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ አገራችን በለውጥ ውስጥ እንዳለች ትላንት በሰጡት መግለጫ አስረድተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ለውጡን የማይፈልጉ ጥቅማቸው የተነካ አካላት በእምነትና በጎሳ #ግጭት ለመፍጠር እየጣሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በክልላችንም አልፎ አልፎ ይኸው ሁኔታ እንደሚስተዋል ገልፀዋል ፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ በመቀጠልም #የህግ የበላይነትን ለማስከበር በክልሉ ምክር ቤት የሰላም ኮሚቴ መቋቋሙን ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ የተከማቸውን #ቆሻሻ አስመልክቶም የከተማዋ ነዋሪዎች እስካሁን ላሳዩት #ትእግስት ምስጋና አቅርበው ቆሻሻው በቀጣዮቹ ሁለት
ቀናት ውስጥ ይወገዳል ብለዋል፡፡

በፀጥታው በኩል #ከቄሮ እና #ፋኖ ጋር አብሮ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ባሉበት ቦታ #ሰኞ ምክክር እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከተው አካል‼️

በቤንሻንጎል ጉምዝ ካማሸ ዞን #ያሶ ወረዳ የፀጥታው ሁኔታ እንደሚያሰጋቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል። የፀጥታ ሃይልም ወደአካባቢ እንዲገባ ነዋሪው ጥሪ አቅርቧል። ሰዎች ሊፈጠር ይችላል ካሉት ችግር አንፃር ከቤት መውጣት ሁሉ እንደሚፈኑ ነው የጠቆሙት። የሚመለከተው አካል ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ ይህን መልዕክት አስተላልፈዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሀዋሳ⬇️

የደኢህዴን 10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ #በነገው ዕለት እንደሚጀምር የደኢህዴን ማ/ኮሚቴ ፅ/ቤት ኃላፊው አቶ ሞገስ ባልቻ ገለፁ፡፡ አቶ ሞገስ ባልቻ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫቸው፦

የ10ኛው መደበኛ ጉባኤ ዝግጅት መጠናቀቁን፣ #ሀዋሳና ነዋሪዎቿ በተለመደው እንግዳ ተቀባይነት ባህላቸው እንግዶቻቸውን እየተቀበሉ መሆኑን፣ በጉባኤው በክብር #የሚሰናበቱ አመራሮች እንደሚኖሩ፣ የህገ ደንብ፣ #አርማና #ስያሜ ለውጥን የሚመለከት ውይይት እንደሚካሄድና በጉባኤተኛው እንደሚወሰን እንዲሁም አዳዲስ አመራሮች ወደ ድርጅቱ የመሪነት እርከን እንደሚቀላቀሉ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ የደህዴን ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia