TIKVAH-ETHIOPIA
1.39M subscribers
54.8K photos
1.37K videos
198 files
3.65K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ቤንሻንጉል⬇️

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሽ ዞን #አመራሮች ላይ በተፈፀመ ጥቃት፣ አራቱ ህይወታቸው አለፈ።

መስከረም 16፣2011 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አመራሮች ላይ የተፈፀመዉን ጥቃት ተከትሎ በከማሽ ዞን የተፈጠረዉን #ዉጥረት ለማርገብ የፀጥታ ኃይል በስፍራዉ ደርሶ #የማረጋጋት ስራ እየሰራ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ #ሰይፈዲን_ሐሩን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት መስከረም 15፣ 2011 ዓ.ም በአሶሳ ከተማ ላይ ተካሂዶ በነበረዉ የቤኒሻንጉል እና የኦሮሚያ ክልሎች የጋራ የፀጥታ ጥምር ኮሚቴ የዉይይት መድረክ ላይ ተሳትፈዉ መስከረም 16፣ 2011 ዓ.ም ወደ ከማሽ ዞን በመመለስ ላይ የነበሩ የዞኑ አመራሮች ላይ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ኃይሎች ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል፡፡

በጥቃቱም 4 የካማሽ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ህይወታቸዉ አልፏል፡፡ ጥቃቱን የፈፀሙ አካላትን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል መንግስት #የፀጥታ ኃይሎችን በስፍራዉ ማሰማራቱን ኮሚሽነሩ አስታዉቀዋል፡፡

ይሁን እንጂ በከማሽ ዞን አመራሮች ላይ የተፈፀመዉን #ጥቃት ተከትሎ በካማሽ ከተማ ላይ ዉጥረት ነግሷል። የመንግስትና የንግድ ተቋማት ተዘግተዋል፡፡

ዉጥረቱን ለማብረድ የፀጥታ ሃይሎች በስፍራዉ ገብተዉ የማረጋጋት ስራ እየሰሩ መሆናቸዉን ኮሚሽነር ሰይፈዲን ተናግረዋል፡፡

በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች መካከል #ግጭት ለመፍጠር የተለያዩ የጥፋት አጀንዳዎችን ይዘዉ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች እንዳሉ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

እነዚህን ኃይሎች ለመመከት የኦሮሚያና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስታት የጋራ ዕቅድ አዉጥተዉ እየሰሩ መሆናቸዉን ኮሚሽነር ሰይፈዲን ገልጸዋል፡፡

በፀረ ሰላም ሃይሎች ዕኩይ ሴራ በሁለቱ ክልል ህዝቦች መካከል ያለዉ የአንድነትና የትብብር መንፈስ ይበልጥ ያጠነክረዋል እንጂ፣ ሊሸረሽረዉ እንደማይችል ኮሚሽነሩ በመግለጫቸዉ አስታዉቀዋል፡፡

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን በመወከል በ12ኛው የብአዴን ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ንግግር ያሰሙት አቶ አሸብር ረጋሳ ተፈፀመውን ጥቃት በማውገዝ ድርጊቱን የፈፀሙ ኃይሎችን በማጋለጥ ለህግ እንዲቀርቡ የአካባቢው ህዝብ እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በጥቃቱ ህይወታቸዉን ላጡ የከማሽ ዞን አመራሮች የክልሉ መንግስት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማዉ በመግለጫዉ አስታዉቋል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia