الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.2K subscribers
386 photos
18 videos
8 files
919 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::ትዳር በኢስላም:::☜ #ክፍል_ሀያ_ሶስተ /②③ት 2/ #እናታችን_ሰውዳ     ነብዩ ﷺ ከኸዲጃ ሞት በኃላ ወደ ፈታኝ የህይወት ምእራፍ ተሸጋግረዋል።ነብዩ  ﷺ እናታችን ሰውዳን ረአ ሲያገቡ የሰውዳ እድሜ 55 አመት ነበር።ሚስቶቻቸው አብዛኞቹ ሀምሳዎቹ ውስጥ ከመሆናቸው የተነሳ የነብዩን ﷺ_ ባለቤቶች እድሜ ማወቁ የኢስላም ጠላቶች በነብዩ  ﷺ ላይ የሚቀጥፉት ቅጥፈት በትክክል ለማወቁና ለእነርሱ…
☞::::ትዳርበኢስላም::::☜
    
#ክፍል_ሀያ_አራት/②④ት

#የነብዩ_ﷺ_ከአንድ_በላይ_ሚስት_የማግባታቸው_ጥበብ
የነብዩ  የትዳር ህይወት አጋሮች
6/
#እናታችን_ኡሙ_ሰለማህ

    እነኚህ እናታችንም እንደሌሎቹ
የነብዩ ባለቤቶች ተመሳሳይ ችግር ነበረባቸው። ከባለቤታቸው  #ከአብዱላህ_ኢብኑ_አብድ_አል_አሰድ ጋር ወደ ሀበሻ ከተሰደዱት ሰሀቦች ውስጥ ናቸው። ከሀበሻ ከተመለሱ በኃላ ባለቤታቸው አራት ልጆች ትተው በድር ላይ ሸሂድ ሆኑ። እናታችን ኡም ሰለማህ በዚያን ጊዜ እድሜያቸው ወደ ስልሳ አመት እየተቃረበ ነበር።ነብዩ ይቺን ችግረኛ ሴት የሚረዳቸው መከራቸውን የሚያቃልል ሰው አሰቡ አላገኙም። በመጨረሻም ራሳቸው ሀላፊነቱን ለመውሰድ ማግባትን ወሰኑ።የትዳር ጥያቄ አቀረቡላቸው ። እናታችን ኡም ሰለማህ እንዲህ አሉ፣ "በእድሜዬ የገፋሁ፣የቲሞች ያሉብኛ እና ቀናተኛ ሴት   ስለሆንኩ ለአላህ መልእክተኛ አልሆናቸውም" ብላ ላከች። የአላህ መልእክተኛም መልሰው "አብሽሪ አትጨነቂ የእድሜሽ መግፋት ጉዳዬ አይደለም የቲሞቹንም ተንከባካቢያቸው እኔ ነኝ።ለቅናትሽ ዱአ አደርግልሻለሁ አላህ ያነሳልሻል።" ብለው ላኩባቸው እሺ አሉ ወትሮውንም ያንገራገሩት ለነብዩ በመጨነቅ እንዴት ይህን ሁሉ የቲም ሀላፊነት እጥልባቸዋለሁ በሚል ለነብዩ ካላቸው ታላቅ ክብር ነበር።እኒህ ሴት ነብዩ ከሞቱ በኃላ ከእናታችን አኢሻ ጋር ሆነው አቡ ሁረይራህ ሲሳሳቱ ያርሙ ነበር።

7/
#እናታችን_ዘይነብ_ቢንት_ጀህሽ
       ይቺ እናት
የነብዩ የአጎት ልጅ እና  የታላቁ ሰሀባ የአብደላህ ኢብኑ ጀህሽ እህት ናቸው። ነብዩ  ለዘይድ ኢብኑ ሀሪሳህ ድረዋቸው ነበር።በዘይድ እና ዘይነብ መካከል ከረር ያለ አለመግባባት  ተከሰተ።ዘይድ ረአ ወደ ነብዩ ወጥቶ ጉዳዩን ነገራቸው።ነብዩም ለማረጋጋት ሲሉ ዘይዲን እንዲታገስ መከሩት። ሊሆን አልቻለም።የፀባቸውም መነሻ ዘይድ ለዘይነብ የሚመጥን ሆኖ አለመገኘት ይመስላል። ዘይነብ ረአ ከአረብ ጎሳዎች  ሁሉ ታላቅ የሆነው የቁረይሽ ዘር መሆኗ እና ዘይድ ደግሞ ነብዩ ሰአወ ነፃ አውጥተው እስኪድሩት ጊዜ ድረስ ባሪያ መሆኑ ሳይሆን አይቀርም። ነብዩ ይህን ሲሰሙ ለማስማማት ብዙ ጥረት አደረጉ ነገር ግን አልተሳካም። ፀቡ እያየለ ሂዶ ለመፋታት በቁ።ምን አልባት አንባቢ "ሁለቱ ምርጥ ሰሀቦች ተግባብተው በትዳር ለመቀጠል መስማማት ለምን ተሳናቸው?" የሚል ሀሳብ በአእምሮ ሊመጣ ይችላል።ከክስተቱ በስተኃላ አላህ ለሙስሊሞች አንድ ሊያስተምር የፈለገው ነገር መኖሩ ከዚያ በኃላ የተከሰቱትን ክስተቶች  ማወቅ ለጥያቄው መልስ ያገኛል።

   
#ዘይድ_ኢብን_ሀሪስ ከነብዩ  ﷺጋር የነበራቸው ቁርኝት የጠበቀ መሆን እና ያሳለፉት ጊዜ ረዘም ያለ በመሆኑ በሰዎች ዘንድ የነብዩ ልጅ ተደርገው #ዘይድ_ኢብን_ሙሀመድ እየተባሉ ይጠሩ ነበር።በአረቦች ባህል አንድ ሰው ባእድ የሆነን ሰው አስጠግቶ እያገለገለው ለረጅም ጊዜ ከቆየ እንደልጁ በቁጠር በስሙ ይጠራል።ሁሉ ነገሩ ከስጋ ልጅ ተለይቶ አይታይም ነበር። በዚህም የተነሳ እሱ ያገባትን ሴት አሳዳሪው የነበረው ሰው ማግባትም እርም ነበር።ይህን  መሰል አጉል የጃሂሊያ አስተሳሰብ አላስፈላጊ መሆኑን አላህ በቁርአኑ አውግዞታል። ከዘይድ የተፋቱትን እናታችን #ዘይነብን እንዲያገቡ ነብዩን አዘዛቸው።

☞ ዘይድ ኢብን ሙሀመድ የሚለው አጠራር ትክክል እንዳልሆነ አላህ በቁርአኑ እንዲህ ሲል ውድቅ አድርጎታል።

ادْعُوهُمْ لِآبَائِهِمْ هُوَ أَقْسَطُ عِندَ اللَّهِ ۚ فَإِن لَّمْ تَعْلَمُوا آبَاءَهُمْ فَإِخْوَانُكُمْ فِي الدِّينِ وَمَوَالِيكُمْ ۚ وَلَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌ فِيمَا أَخْطَأْتُم بِهِ وَلَـٰكِن مَّا تَعَمَّدَتْ قُلُوبُكُمْ ۚ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

ለአባቶቻቸው (በማስጠጋት) ጥሯቸው፡፡ እርሱ አላህ ዘንድ ትክክለኛ ነው፡፡ አባቶቻቸውንም ባታውቁ በሃይማኖት ወንድሞቻችሁና ዘመዶቻችሁ ናቸው፡፡ በእርሱ በተሳሳታችሁበት ነገርም በእናንተ ላይ ኀጢአት የለባችሁም፡፡ ግን ልቦቻችሁ ዐውቀው በሠሩት (ኀጢአት  አለባችሁ)፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 5)

   ☞የመሀመድ ልጅ እየተባለ ይጠራ የነበረውን ሰሀቢይ የፈታትን
ሚስት አግባ በማለት አላህ (سبحانه وتعالى) እንዲህ ሲል አዟቸዋል፣

وَإِذْ تَقُولُ لِلَّذِي أَنْعَمَ اللَّهُ عَلَيْهِ وَأَنْعَمْتَ عَلَيْهِ أَمْسِكْ عَلَيْكَ زَوْجَكَ وَاتَّقِ اللَّهَ وَتُخْفِي فِي نَفْسِكَ مَا اللَّهُ مُبْدِيهِ وَتَخْشَى النَّاسَ وَاللَّهُ أَحَقُّ أَن تَخْشَاهُ ۖ فَلَمَّا قَضَىٰ زَيْدٌ مِّنْهَا وَطَرًا زَوَّجْنَاكَهَا لِكَيْ لَا يَكُونَ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ حَرَجٌ فِي أَزْوَاجِ أَدْعِيَائِهِمْ إِذَا قَضَوْا مِنْهُنَّ وَطَرًا ۚ وَكَانَ أَمْرُ اللَّهِ مَفْعُولًا
ለእዚያም አላህ በእርሱ ላይ ለለገሰለትና (አንተም ነጻ በማውጣት) በእርሱ ላይ ለለገስክለት ሰው (ለዘይድ) አላህ ገላጩ የሆነን ነገር በነፍስህ ውስጥ የምትደብቅና አላህ ልትፈራው ይልቅ የተገባው ሲሆን ሰዎችን የምትፈራ ሆነህ «ሚስትህን ባንተ ዘንድ ያዝ፤ (ከመፍታት) አላህንም ፍራ» በምትል ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ዘይድም ከእርሷ ጉዳይን በፈጸመ ጊዜ በምእምናኖች ላይ ልጅ አድርገው ባስጠጉዋቸው (ሰዎች) ሚስቶች ከእነርሱ ጉዳይን በፈጸሙ ጊዜ (በማግባት) ችግር እንዳይኖርባቸው እርሷን አጋባንህ፡፡ የአላህም ትእዛዝ ተፈጻሚ ነው፡፡
(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 37)
ነብዩ 
የሰው ምላስ ፈርተው ሀቁን ከማሰረተማር ወደ ኃላ እንደማይሉ አላህ በተደጋጋሚ በቁርአኑ ውስጥ መስክሮላቸዋል። በዚህ ጉዳይ የሰዎች ቀልብ ይሰበራል በማለት ወፈ ኃላ ለማለት ሲሞክሩ አላህ በግልፅ ትዛዝ አስተላለፈባቸው።እሳቸው ማንንም ሳይፈሩ የኢስላምን ድንጋጌ ማስተማር ነበረባቸው። ምክንያቱም ከሳቸው በኃላ ሌላ ነብይ መጥቶ ሊያስተካክል አይችልም።እርሳቸው የመጨረሻ ነብይ ናቸውና።ከዚህ ጋር በተያያዘ ነበር አላህም የመጨረሻ ነብይ እንደሆኑ በቁርአኑ በግልፅ ያወጀው።ይህንንም በተመለከተ አላህ እንዲህ ይላል፤
مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِّن رِّجَالِكُمْ وَلَـٰكِن رَّسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا
ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም፡፡ ግን የአላህ መልክተኛና የነቢዮች መደምደሚያ ነው፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡።(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 40)
    እውነታው እና በቁርአን የተመሰከረለት
የነብዩ እና የእናታችን ዘይነብ ቢንት ጀህሽ ጋብቻ ያሳለፍነውን ይመስል ነበር።ነገር ግን አንዳንድ ሙናፊቆች የሚያወሩት ያልተጨበጠ እና ከሀቅ የራቀ ቅጥፈት በስፋት ሲናፈስ ይስተዋላል። መፅሀፏ አጭር ከመሆኗ አንፃር  ለእያንዳንዱ ውሸት አጥጋቢ መልስ እንዳልፅፍ ይረዝማል የሚል ፍራቻ አደረብኝ በጥቅሉ የሚያወሩት ወሬ እዚህ ግባ የማይባል እና ውሃ ቀጠነ የማይቋረጥ መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ
@Tidar_Be_Islam👈👈
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::ትዳርበኢስላም::::☜      #ክፍል_ሀያ_አራት/②④ት #የነብዩ_ﷺ_ከአንድ_በላይ_ሚስት_የማግባታቸው_ጥበብ የነብዩ  ﷺ የትዳር ህይወት አጋሮች 6/ #እናታችን_ኡሙ_ሰለማህ     እነኚህ እናታችንም እንደሌሎቹ የነብዩ ﷺ ባለቤቶች ተመሳሳይ ችግር ነበረባቸው። ከባለቤታቸው  #ከአብዱላህ_ኢብኑ_አብድ_አል_አሰድ ጋር ወደ ሀበሻ ከተሰደዱት ሰሀቦች ውስጥ ናቸው። ከሀበሻ ከተመለሱ በኃላ ባለቤታቸው አራት…
☞::::ትዳርበኢስላም::::☜
    
#ክፍል_ሀያ_አምስት/②⑤ት

#የነብዩ_ﷺ_ከአንድ_በላይ_ሚስት_የማግባታቸው_ጥበብ
የነብዩ  የትዳር ህይወት አጋሮች።

8/
#እናታችን_ጁወይሪያህ_ቢንትሀሪስ

      ጁወይሪያህ  የሙረይሲእ ቀን በበኒል ሙስጠሊቅ ጦርነት የተገደለው እና የኢስላም ታላቅ ጠላት የነበረው የማ ቲዕ ኢብን ሶፍዋን ባለቤት ነበሩ። አባታቸው ሀሪስ ኢብኑ አዶራር የበኒል ሙስጠሊቅ ህዝቦች አለቃቸው ሲሆን ሙስሊሞች ላይ ከፍተኛ ስቃይ እና መከራ እንዲደርስ ትእዛዝ ያስተላልፍ ነበር።
የበኒል ሙስጠሊቅ ህዝቦች ሙስሊሞች ላይ ከፍተኛ ስቃይ እና መከራ ሲፈፅሙ የነበሩ ጎሳዎች ነበሩ።ጁወይሪያህ ባላቸው ማቲእን ኢብን ዶፍዋን በጦርነቱ ከተገደለ በኃላ ከበርካታ ሴቶች ጋር ተማርከው በሙስሊሞች እጅ ወደቁ። ጦርነቱ ተጠናቆ ነብዩ 
የተማረከውን የምርኮ ገንዘብ(ገኒማህ) በፈረስ ለተዋጉ ሁለት እጅ በእግር ለተዋጉ አንድ እጅ እያደረጉ በእጣ ሲያከፋፍሉ ጁወይሪያህ ለሳቢት ኢብኑ ቀይስ ረአ ድርሻ ሆኑ ገንዘብ ከፍለው ከሳቢት ኢብን ቀይስ ነፃ ለመውጣት ተስማሙ፣አምጪ የተባሉት ገንዘብ ስላልሞላቸው ወደ ነብዩ ሰአወ ቀርበው "የአላህ መልእክተኛ ሆይ ፣እኔ የበኒል ሙስጠሊቅ ህዝቦች አለቃ ልጅ ነኝ ።ዛሬ እንደምታዩኝ በዚህ ችግር ውስጥ ገብቻለሁ፣እናም ለሳቢት ገንዘብ ከፍዬ ነፃ እንዲያወጣኝ ተስማምተን ነበር፣የምከፍለው ገንዘብ ይስጡኝ" ብለው ሲጠይቋቸው  "ከዚህም  የተሻለ ላደርግልሽ እችላለሁ" አሏቸው። "እሱ ምንድነው?" አሉ ጁወይሪያህ "ገንዘቡን ከፍየልሽ ከፈለግሽ ከእኔ ጋር ትኖሪያለሽ ከፈለግሽ ወደ አባትሽ ትመለሻለሽ" አሏቸው። ጁወይሪያም "የአላህ መልእክተኛ ሆይ እርሰዎን አግኝቼ እንዴት ቤተሰብ ያምረኛል? እርሰዎን መርጫለሁ"አሉ። ነብዩ     ጁወይሪያን ካገቡ በኃላ ቁጥሩ እጅግ በርካታ የሆነ የበኒሙስጠሊቅ ህዝብ እስልምናን ተቀበለ።እስልምናን ያልተቀበሉትም ቢሆኑ በሙስሊሞች በየመንገዱ  ላይ የሚደርስባቸውን ስቃይ ትተው በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ ፈቀዱላቸው።

9/
#እናታችን_ኡሙ_ሀቢባ

      እናታችን ኡሙ ሀቢባ  እስልምናን ከመቀበሉ በፊት ከአቡ ጀህል በመቀጠል ነብዩን እና ሙስሊሞችን እጅግ ሲበዛ ያሰቃይ የነበረው የአቡ ሱፍያን ልጅ ናቸው።ኡሙ ሀቢባ በጊዜው ኢስላምን ተቀብለው መካ ውስጥ ስቃዩ ሲበረታ ባቸው ከባላቸው ጋር በመሆን ወደ ሀበሻ ከተሰደዱት ሰሀቦች ውስጥ አንዷ ነበሩ። ሀበሻ ከደረሱ በኃላ ባላቸውን በድንገት በሞት አጡ።በዚህም የተነሳ ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት እና መከራ በላያቸው ላይ አጠላባቸው።ወደመካ አይመለሱ የሚጠብቃቸው ኩፍር ነው ይህን የማይቀበሉ ከሆነ የሚጠብቃቸው እስራት እና ግርፋት መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። አባታቸው እንኳን የገዛ ልጁን መካ ውስጥ ለምን ኢስልምና ይኖራል ብሎ በቁጭት ሙስሊሞችን የሚያሰቃይ ሰው ነው።ይህ ጭንቀታቸው እና ችግራቸው ወደ አላህ መልእክተኛ ዘንድ ደረሰ። በሁኔታው ነብዩ አዘኑ በወቅቱ አባታቸው ሀይለኛ የኢስላም ጠላት መሆን ያልበገራቸው ይቺ ለኢስላም ብለው ውቅያኖሱን አቋርጠው የተሰደዱት እንስት የሚረዱበት እና የተሰበረውን ልባቸውን የሚጠግኑበት ነገር እሷን ወደርሳቸው አስጠግተው በቅርበት መንከባከብ ነበር። ይህም ሀሳባቸው በተባረከው የሀበሻ ንጉስ ድጋፍ ተሳካ።
የነብዩ     ወኪል ሆኖ ኡሙ ሀቢባን ኒካህ አስሮ በክብር ወደ መዲና እንዲልክላቸው ወደ ሀበሻው ንጉስ መልእክተኛ ላኩ። ንጉሱም በታዘዘው መሰረት 400 ዲናር ጥሎሽ በመጣል እና በጣም የሚያስደስት ስጦታ በመጨመር ኒካሁን አስሮ ለነብዩ     ላከላቸው።ኡሙ ሀቢባ የነብዩን መልእክት በሰሙ ጊዜ ሀዘናቸው እና ትካዜያቸው ጠፍቶ በጣም ተደሰቱ። በሰላም ከነብዩ ዘንድ መዲና ደረሱ። ከነብዩ ጋር የደስታ ህይወትን መኖርም ጀመሩ። ለአላህ ብሎ የተሰደደ ሰው ሁሉንም ነገር የተሻለ ያደርግለታል።

    ☞ ነብዩ  
  ሀቢባን ካገቡ በኃላ የአቡ ሱፍያን ተንኮል እና ጫና በሙስሊሞች ላይ እየቀነሰ መጣ።ከዛ በኃላ አቡ ሱፍያን ሙስሊሞችን ለመውጋት ወደ መዲና ተንቀሳቅሶ አያውቅም።የተጀመረውን የሰላም ድርድር ለማደስ ወደ መዲና የመጣውም ልጁ የአላህን መልእክተኛ በማግባታቸው ምክንያት ነበር። ወደ መዲና በመጣበት ሰአት ልጁን ለመጠየቅ ወደ ቤታቸው  ሲያቀና ከልጁ ያገኘው መልስ እንዲህ የሚል ነበር፣ #የሰው_ልጅ_የትልቅነት_የመገለጫ_ኢስልምናን_ሲቀበል_ብቻ_ነው_እናም_እስልምናን_ተቀበል
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ አቡ ሱፍያን ቀልቡ እየተለሳለሰ ይመጣ ጀመር።በስተመጨረሻም  ኢስልምናን ሊቀበል ችሏል።

#የመጨረሻዉ_ክፍል_ይቀጥላል

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::ትዳርበኢስላም::::☜      #ክፍል_ሀያ_አምስት/②⑤ት #የነብዩ_ﷺ_ከአንድ_በላይ_ሚስት_የማግባታቸው_ጥበብ የነብዩ  ﷺ የትዳር ህይወት አጋሮች። 8/#እናታችን_ጁወይሪያህ_ቢንትሀሪስ       ጁወይሪያህ  የሙረይሲእ ቀን በበኒል ሙስጠሊቅ ጦርነት የተገደለው እና የኢስላም ታላቅ ጠላት የነበረው የማ ቲዕ ኢብን ሶፍዋን ባለቤት ነበሩ። አባታቸው ሀሪስ ኢብኑ አዶራር የበኒል ሙስጠሊቅ ህዝቦች አለቃቸው…
☞::::ትዳርበኢስላም::::☜
    
#ክፍል_ሀያ_ስድት/②⑥ት_የመጨረሻዉ_ክፍል

#የነብዩ_ﷺ_ከአንድ_በላይ_ሚስት_የማግባታቸው_ጥበብ
የነብዩ  የትዳር ህይወት አጋሮች

10/
#እናታችን_ሶፍያ_رضي الله عنها

     የአላህ መልእክተኛ ሶፍያን
የማግባታቸው ምክንያት የኢስላም ጠላቶች እንደሚቀጥፉት የተለያየ ቅጥፈት ሳይሆን እውነታው እንደሚከተለው ነው።በኸይበር ዘመቻ ወቅት ለጦርነት ከተሳተፉት አይሁዶች ውስጥ አዲስ ተጋብተው በጫጉላ ቤት የነበሩት ሶፊያ ከእነባለቤታቸው ይገኙበታል። በሙስሊሞች እና በአይሁዶች መካከል በተካሄደው ጦርነት የሶፍያ ባለቤት ይገደላል፣ሶፍያም በሙስሊሞች ይማረካሉ። በዚህ መካከል ጦርነቱ ከተጠናቀቀ በኃላ ዲህየት አል ከልቢ የሚባል ሶሀቢይ ወደ ነብዩﷺ  መጥቶ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ ከተማረኩ እንስቶች መካከል አንድ ባሪያ ይስጡኝ" ብሎ ይጠይቃቸዋል፣ነብዩም "የመረጥካትን እንስት ባሪያ ውሰድ" የሚል ምላሽ ይሰጡታል፣ወደ ተማረኩት እንስቶች ዘንድ በመሄድ ሶፍያን ሲመርጥ ሶሀቦች ያዩታል።የሶፍያን በአይሁዶች ዘንድ ያላቸውን ታላቅ ደረጃ የሚያውቁት ወደ ነብዩ ሰአወ ዘንድ መጥተው "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሶፍያ እና የሶፍያ ቤተሰቦች በአይሁዶች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ንጉሶች ናቸው። እናም ሶፍያ የምትገባው ለእርሰዎ ነው!! ከእርሰዎ ውጭ ለሌላ የምትሰጥ ከሆነ ቅሬታ ሊመጣ ይችላል። ህዝቦቿም የሚያመጡት ሀሳብ አይታወቅም።"
የሚል ሀሳብ ሰጧቸው ነብዩም በሀሳቡ ተስማሙ። አስጠሯቸው እና ለሶፍያ እንዲህ አሏቸው፣ "ሁለት አማራጮችን አቀርብልሻለሁ፣የፈለግሽውን መምረጥ ትችያለሽ ይኸውም እስልምናን የማትፈልጊ ከሆነ ነፃ አውጥቼሽ ወደ ቤተሰቦችሽ  መቀላቀል ትችያለሽ፣እስልምናን የምትቀበይ ከሆነ ህይወትሽ ከእኔ ጋር ይሆናል(ኒካህ አደርግልሻለሁ)" በማለት ምርጫ ሰጧት ።እሷ ግን የመለሰችላቸው እጅግ አስገራሚ መልስ ነበር።እንዲህም አለቻቸው "የአላህ መልእክተኛ ሆይ እንዴት ክህደትን እና እስልምናን ባማራጭነት ያቀርቡልኛል።እኔ እኮ እስልምናን የተቀበልኩት ወደ ርሰዎ ከመምጣቴ በፊት ነው።ሞቴም ህይወቴም ኢስላም ነው።እኔ ለአይሁድ ቤተሰቦቼ ጉዳይ የለኝም" ብለው መለሱላቸው።

     ☞ ነብዩም
በተናገሩት መሰረት ኒካህ አሰሩላቸው።በዚህ ኒካህ ምክንያት በርካታ የአይሁድ ታላላቅ ሰዎች ጭምር እስልምናን ተቀበሉ።ያልሰለሙትም ቢሆኑ ነብዩን እና ሰሀቦችን አዛ ማድጋቸውን በእጅጉ ቀነሱ። ይህ ጋብቻ ለኢስላም ትልቅ አስተዋፅኦ ነበረው።

11/
#እናታችን_መይሙናህ( رضي الله عنها)

      እናታችን መይሙናህ ከነብዩ
በፊት 2 ባል አግብተው የፈቱ ሲሆን የአንድ የአረቦች ንጉስ የነበረ ሰው ሚስት እህት ናቸው። ይህ ሰው ያስተዳድራቸው የነበሩ ሰዎች እጅግ በጣም ሀይለኛ አስቸጋሪ የሚባሉ ጎሳዎች ነበሩ። የዲን አስተማሪ እንፈልጋለን በማለት ከነብዩ ሰአወ የተላኩላቸውን #ሰባ_ሰሀቦች ገለዋል። በዚህ የተነሳ ከነብዩ ሰአወ ጋር ከፍተኛ የሆነ ጠላትነት ነበራቸው።
ሙስሊሞችን በአገኙት አጋጣሚ ለማጥቃት ወደኃላ አይሉም ነበርበአረቦች የተለመደው እና ኢስላምም ያልተቃወመው አንድ ቆንጆ ልምድ አላቸው።ይኸውም ሁለት የተለያዩ ጎሳዎች ከፍተኛ የሆነ ጥላትነት በመካከላቸው ሲፈጠር በአማችነት ትስስር ውስጥ ይገቡ እና ወደ ወዳጅነት ይቀይሩታልይህን ጠላትነት ለማርገብ ሲባል የአላህ መልእክተኛ እናታችን መይሙናን አገቡ።ነብዩ ﷺእንዳሰቡትም የእነዚህ ሰዎች ተንኮል ለመቀነስ እና ወደ ኢስላም የሚያደርጉትን ጥሪ ከመስተጓጎል ተቆጥበዋል።

☞ ነብዩ  ባለቤቶቻቸውን ያገቡበት መንገድ በአጠቃላይ ሲታይ በቀጥታ የጌታቸውን ትዛዝ ከመፈፀም ጋር የተያያዘ ነበር።እኛ ሙስሊሞች ሴቶችም ሆናችሁ ወንዶች ለጠላ ት ወሬ ጆሮ ሳንሰጥ የነብዩን ሱና ለመከተል ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል። አንዳንድ ሙስሊም ወንድሞችን ሳይ በጣም አዝናለሁ። መስፈርቱን ሳያሟሉ እና ነገሮችን ሚስጥር ሳያወጡ የየዋህ እህቶቻችንን ህይወት አበላሽተው ወረታቸው ካለቀ በኃላ ወደ መጀመሪያዋ ሚስታቸው ይጠቃለላሉ።ይህ ታላቅ ክህደት ነው።ሴት እህቶቻችን ይህን በማየት ሁለተኛ ሲነሳ ልባቸው ላይ ጥላቻ እስከ ማሳደር ደርሷል።በእርግጥም ይህ ተራ ወንበዴ በሰራው ተነስቶ በአጠቃላይ ሁለተኛ የሚለውን መጥላት ወይም ሁለተኛ መሆን ውርደት ነው ብሎ ማሰብ ከአቂዳ ጋር የሚጋጭ አስተሳሰብ ነው። የሴቶች ሁሉ አይነቶች ተብለው የተመሰከረላቸውን እነ እናታችን ኢሻን እንደ የበታች መቁጠር ነው

❗️የነቢያች የትዳር ሕይዎት ይሄንን ይመስላል ከዚህ ፁሁፍ ብዙ ነገር እና እዉቀት እደገኛችሁ ተስፋ አለኝ።

እስኪህ ከመጀመሪያዉ እስከመጨረሻዉ ያነበባችሁ አስተያየት ፀፉልኝ بارك الله فيكم

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam