الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.4K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
925 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::ትዳርበኢስላም::::☜      #ክፍል_ሀያ_አምስት/②⑤ት #የነብዩ_ﷺ_ከአንድ_በላይ_ሚስት_የማግባታቸው_ጥበብ የነብዩ  ﷺ የትዳር ህይወት አጋሮች። 8/#እናታችን_ጁወይሪያህ_ቢንትሀሪስ       ጁወይሪያህ  የሙረይሲእ ቀን በበኒል ሙስጠሊቅ ጦርነት የተገደለው እና የኢስላም ታላቅ ጠላት የነበረው የማ ቲዕ ኢብን ሶፍዋን ባለቤት ነበሩ። አባታቸው ሀሪስ ኢብኑ አዶራር የበኒል ሙስጠሊቅ ህዝቦች አለቃቸው…
☞::::ትዳርበኢስላም::::☜
    
#ክፍል_ሀያ_ስድት/②⑥ት_የመጨረሻዉ_ክፍል

#የነብዩ_ﷺ_ከአንድ_በላይ_ሚስት_የማግባታቸው_ጥበብ
የነብዩ  ﷺ የትዳር ህይወት አጋሮች

10/
#እናታችን_ሶፍያ_رضي الله عنها

     የአላህ መልእክተኛ ሶፍያን የማግባታቸው ምክንያት የኢስላም ጠላቶች እንደሚቀጥፉት የተለያየ ቅጥፈት ሳይሆን እውነታው እንደሚከተለው ነው።በኸይበር ዘመቻ ወቅት ለጦርነት ከተሳተፉት አይሁዶች ውስጥ አዲስ ተጋብተው በጫጉላ ቤት የነበሩት ሶፊያ ከእነባለቤታቸው ይገኙበታል። በሙስሊሞች እና በአይሁዶች መካከል በተካሄደው ጦርነት የሶፍያ ባለቤት ይገደላል፣ሶፍያም በሙስሊሞች ይማረካሉ። በዚህ መካከል ጦርነቱ ከተጠናቀቀ በኃላ ዲህየት አል ከልቢ የሚባል ሶሀቢይ ወደ ነብዩﷺ  መጥቶ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ ከተማረኩ እንስቶች መካከል አንድ ባሪያ ይስጡኝ" ብሎ ይጠይቃቸዋል፣ነብዩም ﷺ "የመረጥካትን እንስት ባሪያ ውሰድ" የሚል ምላሽ ይሰጡታል፣ወደ ተማረኩት እንስቶች ዘንድ በመሄድ ሶፍያን ሲመርጥ ሶሀቦች ያዩታል።የሶፍያን በአይሁዶች ዘንድ ያላቸውን ታላቅ ደረጃ የሚያውቁት ወደ ነብዩ ሰአወ ዘንድ መጥተው "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሶፍያ እና የሶፍያ ቤተሰቦች በአይሁዶች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው ንጉሶች ናቸው። እናም ሶፍያ የምትገባው ለእርሰዎ ነው!! ከእርሰዎ ውጭ ለሌላ የምትሰጥ ከሆነ ቅሬታ ሊመጣ ይችላል። ህዝቦቿም የሚያመጡት ሀሳብ አይታወቅም።"
የሚል ሀሳብ ሰጧቸው ነብዩም በሀሳቡ ተስማሙ። አስጠሯቸው እና ለሶፍያ እንዲህ አሏቸው፣ "ሁለት አማራጮችን አቀርብልሻለሁ፣የፈለግሽውን መምረጥ ትችያለሽ ይኸውም እስልምናን የማትፈልጊ ከሆነ ነፃ አውጥቼሽ ወደ ቤተሰቦችሽ  መቀላቀል ትችያለሽ፣እስልምናን የምትቀበይ ከሆነ ህይወትሽ ከእኔ ጋር ይሆናል(ኒካህ አደርግልሻለሁ)" በማለት ምርጫ ሰጧት ።እሷ ግን የመለሰችላቸው እጅግ አስገራሚ መልስ ነበር።እንዲህም አለቻቸው "የአላህ መልእክተኛ ሆይ እንዴት ክህደትን እና እስልምናን ባማራጭነት ያቀርቡልኛል።እኔ እኮ እስልምናን የተቀበልኩት ወደ ርሰዎ ከመምጣቴ በፊት ነው።ሞቴም ህይወቴም ኢስላም ነው።እኔ ለአይሁድ ቤተሰቦቼ ጉዳይ የለኝም" ብለው መለሱላቸው።

     ☞ ነብዩም ﷺ በተናገሩት መሰረት ኒካህ አሰሩላቸው።በዚህ ኒካህ ምክንያት በርካታ የአይሁድ ታላላቅ ሰዎች ጭምር እስልምናን ተቀበሉ።ያልሰለሙትም ቢሆኑ ነብዩን እና ሰሀቦችን አዛ ማድጋቸውን በእጅጉ ቀነሱ። ይህ ጋብቻ ለኢስላም ትልቅ አስተዋፅኦ ነበረው።

11/
#እናታችን_መይሙናህ( رضي الله عنها)

     
እናታችን መይሙናህ ከነብዩ ﷺ በፊት 2 ባል አግብተው የፈቱ ሲሆን የአንድ የአረቦች ንጉስ የነበረ ሰው ሚስት እህት ናቸው። ይህ ሰው ያስተዳድራቸው የነበሩ ሰዎች እጅግ በጣም ሀይለኛ አስቸጋሪ የሚባሉ ጎሳዎች ነበሩ። የዲን አስተማሪ እንፈልጋለን በማለት ከነብዩ ሰአወ የተላኩላቸውን #ሰባ_ሰሀቦች ገለዋል። በዚህ የተነሳ ከነብዩ ሰአወ ጋር ከፍተኛ የሆነ ጠላትነት ነበራቸው።
ሙስሊሞችን በአገኙት አጋጣሚ ለማጥቃት ወደኃላ አይሉም ነበርበአረቦች የተለመደው እና ኢስላምም ያልተቃወመው አንድ ቆንጆ ልምድ አላቸው።ይኸውም ሁለት የተለያዩ ጎሳዎች ከፍተኛ የሆነ ጥላትነት በመካከላቸው ሲፈጠር በአማችነት ትስስር ውስጥ ይገቡ እና ወደ ወዳጅነት ይቀይሩታልይህን ጠላትነት ለማርገብ ሲባል የአላህ መልእክተኛ
እናታችን መይሙናን አገቡ።ነብዩ ﷺእንዳሰቡትም የእነዚህ ሰዎች ተንኮል ለመቀነስ እና ወደ ኢስላም የሚያደርጉትን ጥሪ ከመስተጓጎል ተቆጥበዋል።

☞ ነብዩ  ባለቤቶቻቸውን ያገቡበት መንገድ በአጠቃላይ ሲታይ በቀጥታ የጌታቸውን ትዛዝ ከመፈፀም ጋር የተያያዘ ነበር።እኛ ሙስሊሞች ሴቶችም ሆናችሁ ወንዶች ለጠላ ት ወሬ ጆሮ ሳንሰጥ የነብዩን ሱና ለመከተል ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል። አንዳንድ ሙስሊም ወንድሞችን ሳይ በጣም አዝናለሁ። መስፈርቱን ሳያሟሉ እና ነገሮችን ሚስጥር ሳያወጡ የየዋህ እህቶቻችንን ህይወት አበላሽተው ወረታቸው ካለቀ በኃላ ወደ መጀመሪያዋ ሚስታቸው ይጠቃለላሉ።ይህ ታላቅ ክህደት ነው።ሴት እህቶቻችን ይህን በማየት ሁለተኛ ሲነሳ ልባቸው ላይ ጥላቻ እስከ ማሳደር ደርሷል።በእርግጥም ይህ ተራ ወንበዴ በሰራው ተነስቶ በአጠቃላይ ሁለተኛ የሚለውን መጥላት ወይም ሁለተኛ መሆን ውርደት ነው ብሎ ማሰብ ከአቂዳ ጋር የሚጋጭ አስተሳሰብ ነው። የሴቶች ሁሉ አይነቶች ተብለው የተመሰከረላቸውን እነ
እናታችን ኢሻን እንደ የበታች መቁጠር ነው

❗️የነቢያች የትዳር ሕይዎት ይሄንን ይመስላል ከዚህ ፁሁፍ ብዙ ነገር እና እዉቀት እደገኛችሁ ተስፋ አለኝ።

እስኪህ ከመጀመሪያዉ እስከመጨረሻዉ ያነበባችሁ አስተያየት ፀፉልኝ بارك الله فيكم

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam