الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.4K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
925 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::ትዳርበኢስላም::::☜      #ክፍል_ሀያ_አራት/②④ት #የነብዩ_ﷺ_ከአንድ_በላይ_ሚስት_የማግባታቸው_ጥበብ የነብዩ  ﷺ የትዳር ህይወት አጋሮች 6/ #እናታችን_ኡሙ_ሰለማህ     እነኚህ እናታችንም እንደሌሎቹ የነብዩ ﷺ ባለቤቶች ተመሳሳይ ችግር ነበረባቸው። ከባለቤታቸው  #ከአብዱላህ_ኢብኑ_አብድ_አል_አሰድ ጋር ወደ ሀበሻ ከተሰደዱት ሰሀቦች ውስጥ ናቸው። ከሀበሻ ከተመለሱ በኃላ ባለቤታቸው አራት…
☞::::ትዳርበኢስላም::::☜
    
#ክፍል_ሀያ_አምስት/②⑤ት

#የነብዩ_ﷺ_ከአንድ_በላይ_ሚስት_የማግባታቸው_ጥበብ
የነብዩ  ﷺ የትዳር ህይወት አጋሮች።

8/
#እናታችን_ጁወይሪያህ_ቢንትሀሪስ

     
ጁወይሪያህ  የሙረይሲእ ቀን በበኒል ሙስጠሊቅ ጦርነት የተገደለው እና የኢስላም ታላቅ ጠላት የነበረው የማ ቲዕ ኢብን ሶፍዋን ባለቤት ነበሩ። አባታቸው ሀሪስ ኢብኑ አዶራር የበኒል ሙስጠሊቅ ህዝቦች አለቃቸው ሲሆን ሙስሊሞች ላይ ከፍተኛ ስቃይ እና መከራ እንዲደርስ ትእዛዝ ያስተላልፍ ነበር።
የበኒል ሙስጠሊቅ ህዝቦች ሙስሊሞች ላይ ከፍተኛ ስቃይ እና መከራ ሲፈፅሙ የነበሩ ጎሳዎች ነበሩ።
ጁወይሪያህ ባላቸው ማቲእን ኢብን ዶፍዋን በጦርነቱ ከተገደለ በኃላ ከበርካታ ሴቶች ጋር ተማርከው በሙስሊሞች እጅ ወደቁ። ጦርነቱ ተጠናቆ ነብዩ  ﷺ የተማረከውን የምርኮ ገንዘብ(ገኒማህ) በፈረስ ለተዋጉ ሁለት እጅ በእግር ለተዋጉ አንድ እጅ እያደረጉ በእጣ ሲያከፋፍሉ ጁወይሪያህ ለሳቢት ኢብኑ ቀይስ ረአ ድርሻ ሆኑ ገንዘብ ከፍለው ከሳቢት ኢብን ቀይስ ነፃ ለመውጣት ተስማሙ፣አምጪ የተባሉት ገንዘብ ስላልሞላቸው ወደ ነብዩ ሰአወ ቀርበው "የአላህ መልእክተኛ ሆይ ፣እኔ የበኒል ሙስጠሊቅ ህዝቦች አለቃ ልጅ ነኝ ።ዛሬ እንደምታዩኝ በዚህ ችግር ውስጥ ገብቻለሁ፣እናም ለሳቢት ገንዘብ ከፍዬ ነፃ እንዲያወጣኝ ተስማምተን ነበር፣የምከፍለው ገንዘብ ይስጡኝ" ብለው ሲጠይቋቸው  "ከዚህም  የተሻለ ላደርግልሽ እችላለሁ" አሏቸው። "እሱ ምንድነው?" አሉ ጁወይሪያህ "ገንዘቡን ከፍየልሽ ከፈለግሽ ከእኔ ጋር ትኖሪያለሽ ከፈለግሽ ወደ አባትሽ ትመለሻለሽ" አሏቸው። ጁወይሪያም "የአላህ መልእክተኛ ሆይ እርሰዎን አግኝቼ እንዴት ቤተሰብ ያምረኛል? እርሰዎን መርጫለሁ"አሉ። ነብዩ   ﷺ  ጁወይሪያን ካገቡ በኃላ ቁጥሩ እጅግ በርካታ የሆነ የበኒሙስጠሊቅ ህዝብ እስልምናን ተቀበለ።እስልምናን ያልተቀበሉትም ቢሆኑ በሙስሊሞች በየመንገዱ  ላይ የሚደርስባቸውን ስቃይ ትተው በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ ፈቀዱላቸው።

9/
#እናታችን_ኡሙ_ሀቢባ

     
እናታችን ኡሙ ሀቢባ  እስልምናን ከመቀበሉ በፊት ከአቡ ጀህል በመቀጠል ነብዩን እና ሙስሊሞችን እጅግ ሲበዛ ያሰቃይ የነበረው የአቡ ሱፍያን ልጅ ናቸው።ኡሙ ሀቢባ በጊዜው ኢስላምን ተቀብለው መካ ውስጥ ስቃዩ ሲበረታ ባቸው ከባላቸው ጋር በመሆን ወደ ሀበሻ ከተሰደዱት ሰሀቦች ውስጥ አንዷ ነበሩ። ሀበሻ ከደረሱ በኃላ ባላቸውን በድንገት በሞት አጡ።በዚህም የተነሳ ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት እና መከራ በላያቸው ላይ አጠላባቸው።ወደመካ አይመለሱ የሚጠብቃቸው ኩፍር ነው ይህን የማይቀበሉ ከሆነ የሚጠብቃቸው እስራት እና ግርፋት መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። አባታቸው እንኳን የገዛ ልጁን መካ ውስጥ ለምን ኢስልምና ይኖራል ብሎ በቁጭት ሙስሊሞችን የሚያሰቃይ ሰው ነው።ይህ ጭንቀታቸው እና ችግራቸው ወደ አላህ መልእክተኛ ዘንድ ደረሰ። በሁኔታው ነብዩ አዘኑ በወቅቱ አባታቸው ሀይለኛ የኢስላም ጠላት መሆን ያልበገራቸው ይቺ ለኢስላም ብለው ውቅያኖሱን አቋርጠው የተሰደዱት እንስት የሚረዱበት እና የተሰበረውን ልባቸውን የሚጠግኑበት ነገር እሷን ወደርሳቸው አስጠግተው በቅርበት መንከባከብ ነበር። ይህም ሀሳባቸው በተባረከው የሀበሻ ንጉስ ድጋፍ ተሳካ። የነብዩ   ﷺ  ወኪል ሆኖ ኡሙ ሀቢባን ኒካህ አስሮ በክብር ወደ መዲና እንዲልክላቸው ወደ ሀበሻው ንጉስ መልእክተኛ ላኩ። ንጉሱም በታዘዘው መሰረት 400 ዲናር ጥሎሽ በመጣል እና በጣም የሚያስደስት ስጦታ በመጨመር ኒካሁን አስሮ ለነብዩ   ﷺ  ላከላቸው።ኡሙ ሀቢባ የነብዩን መልእክት በሰሙ ጊዜ ሀዘናቸው እና ትካዜያቸው ጠፍቶ በጣም ተደሰቱ። በሰላም ከነብዩ ዘንድ መዲና ደረሱ። ከነብዩ ጋር የደስታ ህይወትን መኖርም ጀመሩ። ለአላህ ብሎ የተሰደደ ሰው ሁሉንም ነገር የተሻለ ያደርግለታል።

    ☞ ነብዩ   ﷺ  ሀቢባን ካገቡ በኃላ የአቡ ሱፍያን ተንኮል እና ጫና በሙስሊሞች ላይ እየቀነሰ መጣ።ከዛ በኃላ አቡ ሱፍያን ሙስሊሞችን ለመውጋት ወደ መዲና ተንቀሳቅሶ አያውቅም።የተጀመረውን የሰላም ድርድር ለማደስ ወደ መዲና የመጣውም ልጁ የአላህን መልእክተኛ በማግባታቸው ምክንያት ነበር። ወደ መዲና በመጣበት ሰአት ልጁን ለመጠየቅ ወደ ቤታቸው  ሲያቀና ከልጁ ያገኘው መልስ እንዲህ የሚል ነበር፣
#የሰው_ልጅ_የትልቅነት_የመገለጫ_ኢስልምናን_ሲቀበል_ብቻ_ነው_እናም_እስልምናን_ተቀበል
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ አቡ ሱፍያን ቀልቡ እየተለሳለሰ ይመጣ ጀመር።በስተመጨረሻም  ኢስልምናን ሊቀበል ችሏል።

#የመጨረሻዉ_ክፍል_ይቀጥላል

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam