الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.5K subscribers
359 photos
17 videos
7 files
913 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
#የተከበርከው__ወንድሜ__ሆይ! ☜

ትዳር ከማሰብህ በፊት!
ስለ ትዳር ትርጉም በደንብ እወቅ!
በትዳር ውስጥ ብዙ ነገሮች አሉ!
እናም! የሚገጥምህን ነገሮች ሁሉ አምነህ ለመቀበል + መስዓላውን + ሀላፊነትን ለመወጣት……… +… ………አስበህ መወሰን!

ከዛም!
ለትዳር የምትሆንህን ሴት ስትመርጥ ድኗን እንጂ! መልኳን አይሁን!
ምክንያቱም! በአላህ ፈቃድ በድኗ ውስጥ ሁሉንም ነገር ታገኛለህና!

ደግሞ!
አይን ቀላዋጭ ነውና ብዙ ያምረዋል!
ስለዚህ! ልብህ #ያረፈባትን ሴት ምረጥ + አግባ!

ከአገባህ ቡኋላም!
#ለውዷ ሚስትህ እዘንላት + የወደፊት የልጆችህ እናት ለምትሆነው!

በተለይ! የተከበረከው ባለ ትዳር ወንድሜ ሆይ!
ለውዷ ባለቤትህ ምን አይነት ባል መሆን እንዳለብህ ላስታውስህ ነው!
እናም!
#ምክሬን በወቀሳ እንዳታስብብኝ!

እንዲሁም! አሁን የምጠቅሳቸውን ክፍተቶች በትዳርህ ላይ ካጋጠሙህ ራስህን ፈትሸህ!
#ለማስተካከል ሌት ተቀን ደፋ ቀና ማለት አለብህ!

ከዚህ ነገር አላህ ከጠበቀህ አላህን እያመሰገንክ ለትዳርህ መፅናትና መጨነቅ አለብህ! ምክናያቱም #ትዳር ነውና!

አንተ ጋር ያለችው ሚስትህ ብትሆንም አማና መሆኗን ልታውቅ ይገባል!
እነሆ ይሄንን አማና በጥንቃቄ ልትይዝ አላህን ልትፈራ ይገባሀል!
አባቷ ልጅቱን ላንተ ሲሰጡህ ሀቋን ትጠብቃለህ + ገመናዋን ትሸፍናለህ + ጥሩ ሰው ትሆንላታለህ… ………………ብለው ነው!
የሚጠቅማትን ነገር ልታገርግላት + የሚጎዳትን ነገር በሷ ላይ ከማድረግ ልትታቀብ ይገበሃል!!

#ሚስትህ ያአንተን ሀቅ እንድታውቅ እንደምትጓጓው ሁሉ የጌታዋንም ሀቅ ልታሳውቃት + በኸይር ልትረዳት + አደጋ እንዳይደርሰባት ልትጠብቃት ይገባል!

ነብዩ መሀመድ (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል :- ሁላቹሁም ጠባቂዎች ናችሁ + ሁላቹሁም ከምትጠብቁት ነገር ተጠያቂዎች ናችሁ!

#ቤተሰቦቿ ጋር ሆና!
ስታገኝ የነበረውን ነገር አንተ ልትነፍጋት አይገባም!
በቻልከው አቅም ልታደርግላት ይገባል!
#ስትታመም ልታሳክማት + ሲከፋት አይዞሽ ልትላት + ስትደሰት አብረሀት ልትደሰት +………………+………… የሚያስፈልጉ ነገሮችን ልታቀርብላት + ልታደርግላት ወደ ቤትህ አስገብተሀታል እኮ!
አንተን ብላ ሁሉን ጥላ መጥታለችና እባክህ ተንከባከባት!!

#ተመልከት ! አንድ አላህን የማይፈራ ወንድ በጠዋት ከቤት ይወጣና ቁርስ + ምሳ + ራት + የሚበላው ከልጆቹ እናት ከሆነችው #ከሚስቱ ተነጥሎ ነው!

ቢያንስ እንኳ! ከነዚህ የምግብ ሰርዓቶች #በአንዱ ላይ ተገኝቶ ከልጆቹ እናት ጋር ሰብሰብ ብሎ አይመገብም! ይህ! በደል (ዙልም) አይደለምን???

#ሚስቱ ከዛ በፊት ከቤተሰቦቿ ጋር መብላት ለምዳ በአንዴ ብቻሽን ተመገቢ ብትባል ሊከብዳት ይችላል!!

ስለዚህ! ወንድሜ! አላህን ፈርተህ + ለትዳርህ ለሚስትህ ክብር + ቦታ ሰጥተህ!
#አቅሙ ካለህ ቤተሰቦቿ ጋር ትኖረው ከነበረው ኑሮ! የተሻለ ልታኖራት ይገባል!
ከሌለህ ግን! ማድረግ የምትችለውን በመልካም ንግግርን ልታናግራት + ጥሩ መልስን ልትመልስላት + ጥሩ ፍቅር ልትሰጣት + ልታዝንላት + ልትንከባከባት + ልታስደስታት………………… ይገባል!!

#ከሚስትህ ጋር ስትኖር! በመልካም መኗኗርን ለመኖር ታገል + ጣር!
#በመልካም መኗኗር የሚባለው አባባል ካልገባህ! የወደፊት የትዳርህ ዕድሜ አጭር + ዘላቂነት እንዳይኖረው እንዳይሆን ያስፈራልና ጠንቀቅ በል!!!

#ከባለቤትህ ጋር በአላህ ፈቃድ በመልካም ለመኗኗር ይረዳህ ዘንድ ልጠቁምህ:–
ዕዘንላት + ተንከባከባት + ውደዳት + አክብራት(ክብሯን ጠብቅላት) + ከልብህ መራራትን ራራላት + በተለያዩ አጋጣሚዎች ውዴታህን +ፍቅርህን ግለፅላት!
አንተ ይሄን አድርግ! አላህ ነገሩን ሁሉ ያገራልሀል!
አላህ ሁሉን አዋቂ + ባሪያውን የሚደግፍ ጌታ ነውና!!

#ሚስትህ ላንተ ሚስት በመሆኗ ብቻ እንደ #ባርያ/ህ ልታያት + ልታፈጋት + ልትጨቁናት + ልትረግጣት + ልትበድላት (ልትዞልማት)አይገባህም!
ሌላው ቢቀር ሙስሊም #እህትህ መሆኗንም አትዘንጋ!

#የሚያስፈልጋትን ሁሉ ነገር አሟልተህላት! ነገር ግን! በምላስህ #አዛ የምታደርጋት ከሆነ!
የአንተ ሁሉን ማድረግ እርሷ ዘንድ #ዜሮ + ጥቅም አልባ ሊሆን ይችላል!!!

#በል እንዳውም! አላህ ካዘነላቸው ውጭ!
አንዳንድ ወንድሞች #ከቤት አውጥቼ እንዳልወረውርሽ + ከነ ልጆችሽ ወደ ቤተሰቦችሽ እንዳልሸኝሽ + አንች የምናምን ልጂ… ………………………… እረ ስንቱን ይዘረዝራሉ! ብር አይደለም! ምላሳቸውን ነው!!

#ጥሩ ያልሆኑ + በጆሮ ለመስማት የሚሰቀጥጡ ንግግሮችን ሲናገሩ ይደመጣል!

#ሴትን ልጅ እንዲህ እየተናገረ + ሞራሏን እየጎዳው + ልቧን ባሻው ወቅት እየሰበረ +… ……………+……………#የፈለገውን ብያርግላት! እንዴት ይመለሳል?አትጠራጠር አድራጎትህ የአንድኛው እንኳ ምንም ላይመስላት ይችላል!!!

#አስብ + ተረዳ………!

#ሴት__ልጅ! ከምንም በላይ የምትፈልገው ሰላምን + ደስታን + ፍቅርን ……………ነው!
ምንም የሌለው ወንድ!
ነገር ግን! ሀቋን የሚጠብቅ + የሚንከባከባት + የሚያዝንላት + የሚራራላት… ………………ከሆነ!
ከእሱ ጋር በደስታ መኖርን ትመርጣለች!!

ከዚህ ተቃራኒ(አክስ) ደግሞ ለሀገር + ለወገን + ለዘመድ የሚበቃ ሀብት ኖሮት!
ግና ሞራሏን የሚጎዳው + መጥፎና አፀያፊ ቃል የሚናገር + ሀቋን የማይጠብቅ / የማያውቅ + የማይራራላት + …………………ከሆነ!
በሀብት ተኮፍሶ………የሰው ልጂ #ሰው መሆኗን እረስቶ/ ዘንግቶ!
እንደ #ዕቃ የሚቆጥራት ከሆነ!
ከዚህ አይነት ሰው ጋር በጭራሽ አትኖርም!!!
ምንም አይነት አንገት የሚያስደፋ ችግር ቢገጥማት ማለት ነው!!

#ወንድሜ ሆይ! በትዳርህ ግልፅነት ይኑርህ!
አንተ ከሚስትህ ሊሟሉልህ የምተፈልገውን ነገሮች እንዳለ ሁሉ!
አንተም ለእርሷ አሟልተህ መገኘት ይኖርብሀል!
ለምሳሌ :- ከሷ መጥፎ ሽታ እንዳይሸትህ እንደምትፈልገው ሁሉ!
አንተም በአንተ ላይ ያሉ መጥፎ ሽታ ሁሉ ልታስወግድ ግድ ይልሀል!
እርሷ ፈገግ እንድትልልህ እንደምትፈልገው ሁሉ! አንተም ፈገግ ልትል ግድ ይልሀል!
የሚያስፈልጉህን ነገሮች እንድታሟላልህ እንደምትፈልገው ሁሉ
አንም የእርሷን ፍላጎት ማሟላት ይኖርብሀል!!!

#ወንድሜ ሆይ! ባለቤትህ ( ሚስትህ ) በውጭ + በስራህ ቦታ የሚገጥምህን ውጣ ውረድ ላታውቅ ትችላለችና ትዕግስት አድርግ!

በመታገስህ ከአላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) በትልቅ ምንዳ ላይ ተስፋ አለህና!
የትዳር አጋርህ ላይ አንድ የምትጠላው ባህሪ ቢኖራት ሌሎች ብዙ የሚወደዱ ባህሪዎች አሏትና ታገስ!
#ሁሌም ጥቃቅን የሆነና ደካማ ጎኗን አታስብ! ይልቁንም ብዙ መልካም ስነ ምግባር አላትና ሁሌም ቢሆን መልካም ጎኗን ማስታወስ ይጠበቅብሀል!

#የሰው__ልጅ! አላህ ሲፈጥረው በባህሪው ምስጋናን ይወዳልና!
በተለይ! ለሚስትህ ምስጋና አቅርብላት!
በአላህ ፈቃድ ደካማ ጓኗን ለማስተካከል ከፈለክ! ጥሩ ጎኗን እያወደስክ ስታመሰግናት + ግልፅ ስትሆን + ስትወያይ ደካማ ጎኗን ለማስታካከል ሁሌም ትጥራለችና ሁሌም ቢሆን ሳይጋነን የአንተ አድናቆትህ አይለያት!
ባለቤትህ (ሚስትህ) ለአንተ ንግስትህ ነች!
ባለቤትህን ከማንም ጋር አታወዳድራት!!!

ወላሁ ተዓላ አዕለም#ሼር

💌:::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::👇💌

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8riR2kM4HsIJg
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞ትዳር_በኢስላ☜   #ክፍል_ስድስት/⑥ ☞ከአንድ በላይ ሚስት በቀደምት ህዝቦች ዘንድ   #በቀደምት_ቻይናውያን_ዘንድ የቻይና ወንዶች በቀድሞ ዘመን የመጀመሪያ ሚስታቸውን ካገቡ በኃላ በርካታ ልጅ አገረዶችን በመግዛት እንደፈለጉ ይጠቀሙባቸው ነበር። #በኃላየ ተገቡት ወይም የተገዙት ሴቶች ለመጀመሪያዋሚስት ታዛዥ የመሆን ግዴታ አለባቸው ከሌሎች ሚስቶቹ የሚወለዱት ልጆች ለመጀመሪያዋ ሚስት እንደልጅ ታስበው…
☞:::::ትዳር በኢስላም:::::☜

 
#ክፍል_ሰባት_⑦ት

     
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_በኢስላም

   ባለፈው እንዳሳለፍነው በጃሂሊያ ዘመን (ኢስላም ከመታደሱ በፊት) በአለም ላይ ያሉ ሀገራት ለሴት ልጅ ያላቸው ክብር እና ግምት በእጅጉ የወረደ በመሆኑ ያለምንም የቁጥር ገደብ ብዙ ሴቶች በአንድ ባል ስር እንዲተዳደሩ ይገደዳሉ።በዚህ ድርጊት ምክንያት በሴቶች ላይ የሚደርስባቸው ግፍና በደል ወንዶችን ምንም የሚያስጨንቃቸው አልነበረም።

    የሰው ልጅ አይነታ የሆኑት
#የአላህ_መልእክተኛ_ሰአወ ኢስላምን ለማደስ ከመጡ በኃላ በጃሂልያ ይተገበር የነበረው ፈር የለቀቀው በሴቶች ላይ ይደረግ የነበረው #ግፍና_መከራ ገፈው ጣሉት።ከአንድ በላይ ሚስትን በተመለከተ እስልምና ቁጥርን ብቻ መገደብ ሳይሆን በሚስቶችም መካከል ፍትሀዊነትም ጭምር ትኩረት ሰጥቶ አስተካክሏል

#በፍትህ_ማስተዳደር_ያልቻለ_አንድ_ትብቃው_እሷንም_ማስተዳደር_ያልቻለ_ማስተዳደር_እስኪችል_ድረስ እንዲፆም_እና_እንዲታገስ በማድረግ ከእንግዲህ ሴት ልጅን እንደፈለጉ ማድረግና መጨቆን እንዳከተመለት ለሴት ልጅ ኢስላም ሙሉ የሆነ ዋስትና እንደሰጣት ታወጀ።አዋጁም ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ ተስተጋባ።

    ከዚህም በተጨማሪ
ሴት ልጅ ውጭ ወጥታ ከወንድ ጋር እንዳትጋፋ የወንዶች ዘለፋ እንዳያገኛት ሂጃቧን ጠብቃ ቤቷ እንፍትሆን በማድረግ እሷን የመንከባከብ ግዴታውን በወንዶች ላይ አደረገ።እየቻለ ቢያስቸግራት ፀቡ ከማንም ጋር ሳይሆን ከአላህ ጋር እንደሆነ ነብዩ ሰአወ አስጠነቀቁ። በኢስላም ውስጥ #ሴት_ መሆን_መታደል ነው።እንዲሉ በአጠቃላይ እስላም ለሴቶች ምሽግ ነው።ነገር ግን የኢስላም ጠላቶች ኢስላም ከአንድ በላይ በመፍቀዱ የሴቶችን መብት ይጋፋል። የሚል የእብድ ወሬ ሲያናፍሱ ይደመጣሉ።ኢስላም ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ማስገደድ ሳይሆን በአለፉ እምነቶችና ባህሎች ፈር ለቆ የነበረውን ከአንድ በላይ ሴቶችን ማግበስበስ በገደብ እና በፍትህ እንዲሆን ህግ ማሰረቀመጥ እንደሆነ በዝርዝር አሳልፈናል..

እስከ አራት የተፈቀደ ለመሆኑ ማስረጃ

               
#ቁርአናዊ_ማስረጃ
   አላህ ሱብሀነ ወተአላ እንዲህ ብሏል፣

وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا

በየቲሞችም (ማግባት) አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ (ዝሙትንና ከተወሰነላችሁ በላይ ማግባትንም ፍሩ)፡፡ ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡ (ሱረቱ አል-ኒሳእ - 3)

    ☞ይህ የቁርአን አንቀፅ፣ በኢስላም ውስጥ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የሚፈቀድ መሆኑን ግልፅ ማስረጃ ነው።ነገር ግን በሴቶች መካከል በፍትህ ማስተዳደርን ቅድመ መስፈርት አድርጎ ደንግጓል።
#ፍትህ ዋና ቅድመ መስፈርት ለመሆኑ የቁርአን አንቀፁ የወረደበት ሰበብ ማወቅ መልክቱ ግልፅ ያደርገዋል..

    እናታችን አኢሻ ረአ እንዲህ ይላሉ፣ "አንድ ሰው በውስጡ የሚያሳድጋት ብዙ ንብረት ያላት የቲም
ሴት ልጅ ነበረችው፣ ንብረቷን ፈልጎ ጥሎሹን በትክክል ሳይሰጣት አገባት።ከዚያ ይቺ የቁርአን አንቀፅ ወረደች.።

   ☞  በሌላ ዘገባ ዑርወት ኢብኑ ዙበይር ወደ እናታችን አኢሻ ዘንድ መጣና ስለ
"وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ"
ጠየቃቸው እሳቸውም እንዲህ ብለውታል፣ "የወንድሜ ልጅ ሆይ;አንድ ወንድ ሃላፊ ሆኖ የሚያሳድጋት የቲም
ሴት ልጅ ገንዘቧ እንዲሁም መልኳ አስቀንቶት መህሯን በትክክል ሳይሰጣት እንዳያገባት ማለት ነው፣ ይህ ነው የተከለከለው። እሷን ማግባት የሚፈልግ ከሆነ መህሯን ለሌሎቹ እንደሚሰጠው አድርጎ በፍትህ መህሯን ለሌሎች ሚስቶች የሚገባውን ሰጥቶ ያግባት።ነገር ግን ፍትህ ማጓደልን ከፈራ እሷን ትቶ ሌሎችን የሚያስደስቱትን እስከ አራት ማግባት ይችላል ማለት ነው።" ቡኻሪ ዘግበውታል።.

#ይቀጥላል_ኢንሻአላህ_ሼር_ያድርጉ👇👇👇

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::ትዳር በኢስላም::::☜   ክፍል ዘጠኝ/⑨ኝ    #ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ     አላህ ለወንድ ልጅ ከአንድ በላይ እስከ አራት ሚስት ማግባት እንዲችል ሲፈቅድለት የሰው ልጅ ሊደርስበት የማይችል ሚስጥራዊ ሂክማ አለው።     በኢስላም ውስጥ አብዛሀኞቹ  በቁጥር የተገደቡ ኢባዳዎች የቁጥራቸውን ሚስጥር ጥራትና ልቅና የተገባው ጌታችን አላህ ሱወ ብቻ ነው የሚያውቀው።የዙህር ሶላት ለምን…
☞::::::ትዳር በኢስላም:::::::::☜

  ክፍል አስር/⑩

  
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ

3/
#የሴቶች_ቁጥር_በእጅጉ_መጨመር_እና
     
#በአንፃሩ_የወንዶች_ቁጥር_መቀነስ

  በአለም ላይ በተደረገው ጥናት እና ቆጠራ በየክፍለ ዘመኑ ያሉ ወንዶች በቁጥር እጅግ አናሳ ሲሆን የሴቶች ቁጥር በእጅጉ የጨመረ ነው።ይህም የሚሆንበት የተለያዩ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ የተወሰኑትን ለናሙና ያክል እንጥቀስ፣

ሀ/. በአለም ላይ የወንዶች ሞት በተለያዩ ምክንያቶች መጨመር የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ (medical school of harvard) በ2016 ይፋ ባደረገው ጥናት ከሴቶች ይልቅ ወንዶች በውል ተለይተው ለማይታወቁ የተለያዩ የካንሰር በሽታዎች የመጋለጥ እድላቸው የሰፋ ነው።ይህም የሚሆንበት ምክንያት የሴቶች x ክሮሞዞም ካንሰርን የመቋቋም እድሉ ከፍተኛ ነው ይላል ጥናቱ።ከዚህም በተጨማሪ ሰውን በከፍተኛ ገዳይ ከሆኑት የልብና የጭንቅላት በሽታ ከሴቶች ይልቅ ወንዶች በይበልጥ የተጋለጡ ናቸው ይላል ።

ለ/. ወንዶች በተለያዩ ሱሶች እና አደንዛዥ እፆች የመለከፍ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑ ነው። በዚህምየተነሳ የጉበት፣የሳንባ እና የመሳሰሉት ካንሰሮች ተጠቂ መሆናቸው የመሞት እድላቸው እንዲጨምር አድርጎታል።

ሐ/ . ከወንዶች ውልደት የሴቶች ውልደት የበዛ መሆኑ ሌላው ምክንያት ነው። የሴቶችን እና የወንድ ቁጥር የሚወስነው እንዲሁም
ሴት ወይም ወንድ ይወለድ ብሎ የሚያዘው አምላካችን አላህ ብቻ ነው።ይህ በእንዲህ እንዳለ እንደመንስኤ ነው የሚሉት "x" ክሮሞዞም ከያዘው በፍጥነት ዝግ ያለ መሆን እና ማህፀን ውስጥ የመቆየት እድሜው ከፍተኛ መሆን የሴቷን የዘር ፍሬ የማግኘት እድሉ ከፍተኛ ነው።በዚህም ምክንያት ሴቶች በውልደት ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ ይላሉ።
…… አንዳንድ ይህ ሚስጥር የገባቸው የኢስላም ጠላቶች ሃቁን ሽምጥጥ አድርገው በውልደትም ሆነ በቁጥር ወንዶች ይበልጣሉ። በማለት በኢንተርኔት አሰራጭተዋል መፅሀፍም ፅፈዋል። እያወቁ የዋሹት እንጅ ትክክለኛ መረጃ እንዳልሆነ
#ሊሰመርበት ይገባል።

    ………እውነታው እንደዚህ ከሆነ እያንዳንዱ ወንድ ማግባት የሚችለው አንድ
ሴት ብቻ ተብሎ ቢደነገግ ይህ ትክክለኛ ፍትህ ነው??? አንቺ ሙስሊሟ እህቴ ሆይ ሳታገቢ የቀረሽ አንቺ ብትሆኝ ደስ ይልሻል??ይቺን አለም ያለቤተሰብ ያለባል ያለ ልጅ መኖር ያስደስትሻል?? ሙስሊሟ እህቴ ራስሽ ላይ አድርገሽ ፍርድ ስጭ።ወላሂ በጣም ልብ የሚያደማው አንዳንድ ጋጠ ወጥ ሴቶች የሌላ ሰው ህጋዊ  ባልን በድብቅ ለአራት ለአምስት ቀምተው ውስጥ ለውስጥ ባል አድርገው ይዘው በህጋዊ መንገድ ሁለተኛ ሆና ለገባችው ሙስሊም ተቆርቋሪ መስለው በኢስላም ላይ የሰላ ትችትን ሲሰነዝሩ ከማመም በላይ ያማል።

☞ ሙስሊም እህቴ ሆይ ካፊሮች አላህ በሚጠላው መንገድ አንድን ወንድ ብዙ ሆነው ሲጋሩት እያየሽ አንቺ በክብር ሁለተኛ ሚስት መሆንሽን እንደነውር የሚቆጥሩት በኢስላም ላይ ጦርነት እንጂ ለአንቺ ክብር ተቆርቁረው አይምሰልሽ።
#የአንቺን_ባል_ቢያገኙ_ለአስርም_ለሀያም_ቢሆን_የሚቀራመቱት_መሆኑን_ማን_በነገረሽ?????

የሆነው ይሁን ብለሽ የማያስተማምን ወንድ ለብቻ ከማግባት ከሁለነገሩ ለሚታመነው ወንድ አራተኛ ህጋዊ ሚስት ሆነሽ ብትገቢ እመክርሻለሁ። (ኡስታዝ ግን በአሁኑ ሰአት አይደለም አራተኛ ለመሆን ለሁለተኛስ ቢሆን እውነት የሚስቱን ሀቅ በትክክል የሚወጣ ወንድ አለ?????? )

4/
#ወንድ_ልጅ_እድሜ_ልኩን_
#የመውለድ_አቅም_መኖር

   አንድ ወንድ ልጅ ግንኙነት ማድረግ እስካላቆመ ድረስ የማስረገዝ አቅምን አላህ ሰጥቶታል። በተቃራኒ
ሴት ልጅ መውለድ የምትችለው በተወሰነ የእድሜ ክልል ውስጥ ብቻ ነው። ስለሆነም አንድ ወንድ ሚስቱ ማርገዝ በማትችልበት የእድሜ ክልል ውስጥ ከገባች በኃላ ተጨማሪ ልጆች የመውለድ ፍላጎት እና የማሳደግ አቅም ካለው የሚፈለገውም ዘርን ማብዛት ስለሆነ የመጀመሪያ ሚስቱን ሳይፈታ ተጨማሪ ሚስት አግብቶ ተጨማሪ ልጆችን ለመውለድ እንዲችል ከአንድ በላይ የመፈቀዱ ሸሪአዊ ጥበብ ነው።ዘርን ማብዛት በእስልምና የሚበረታታ ተግባር ነው።ለዚህም ነብዩ ሰአወ እንዲህ ብለዋል፣

{النكاح من سنتي،فمن لم يعمل بسنتي فليس مني،وتزوجوا فإني مكاثر بكم الآمم} (رواه ابن ماجه)

"ሚስት ማግባት ፈለጌ(ሱናዬ) ነው፣ በሱናዬ ያልሰራ ከእኔ አይደለም፣ተጋቡ፣የትንሳኤ ቀን ከሌሎች ነብያት በቁጥራችሁ እፎካከርባቹሀለሁ" ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል።

5
#ሴት_ልጅ_በተደጋጋሚ_በወር_አበባና_በወሊድ_ደም_ላይ_መቆየቷና_የባል_ስጋዊ_እርካታ_መፈለግ

     ወንድም ሆነ
ሴት የሚያገቡበት ዋነኛ አላማ እራሳቸውን ሀራም ላይ እንዳይጥሉ እና ለጥፋት እንዳይዳረጉ ሲባል መሆኑን ለሁሉም ግልፅ ነው። ይህ አላማ በየትኛው መንገድ እንከን እንድገጥመው አይፈለግም።

#ሴት_ልጅ_በወር_አበባ_እና_በወሊድ_ደም_ላይ_እያለች_ከባሏ_ጋር_የግብረ_ስጋ_ግንኙነት_መፈፀም_አይፈቀድላትም።  በወር አበባ ሰአት ግንኙነት መፈፀም ከታላቅ ወንጀል ውስጥ የሚቆጠር ነው።በተጨማሪም በዚህ ሰአት የግብረ ስጋ ግንኙነት ለሴቷም ጤንነት ጥሩ አይደለም። በዚህ ጊዜ መላ ሰውነቷ ስለሚላላ እና ማህፀኗ ስለሚደማ ከፍተኛ የጤና ቀውስ ሊያጋጣት ይችላል። ባል ሚስቱ የወሊድ እና የወር አበባ ደሟን እስከምትጨርስ የመታገስ ልምድ ከሌለውና ስሜቱ የሚያስቸግረው ከሆነ በወር አበባ እና በወሊድ ደም ምክንያት #ወደ_ዝሙት_እንዳያመራና ችግር ላይ እንዳይወድቅ እንዲሁም ሚስቱን በወር አበባ ሰአቷ ተገናኝቶ ከባድ ወንጀል ውስጥ እንዳይዘፈቁ ሲባል አቅም ካለው ከአንድ በላይ በማግባት ከጥፋት ለመታደግ ሲባል የተፈቀደ አማራጭ ነው።. ይቀጥላል#ሼረ_ያድርጉ👇

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
#ሴት_ልጅን_ሸሪዐዊ_ዕውቀት_ማስተማር_ሕብረተሰብን_ማስተማር_ነው!

ሴቶች ...☜
– እናቶች
– እሕቶች
– ሚስቶች
– ልጆች ናቸው ።

ሴት ስትማር እራሷን ቀይራ ልጇንም በኢስላማዊ ተርቢያ ኮትኩታ ታሳድጋለች።

☞ያኔ መጪው ትውልድም ከመሠረቱ ያብባል ። ሕፃናት አፋቸውን በ “ላኢላሃ ኢለላህ” በ “አላሁ አክበር” ከሊማ ይፈታሉ ።
☞ለማንነታቸው ተምሳሌት ማንንም ሳይሆን ታላቁና ተወዳጁ የአላህ ነቢይ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን እና ሶሓቦችን ያደርጋሉ።  ገና በልጅነት አዕምሮዋቸው ግባቸውን በጀነቱል ፊርደውስ ይቀርፃሉ ።

በኢስላም ውስጥ ለኢስላም ኖረው ለኢስላም መሞትን ይመኛሉ ።

☞ያኛው ተናፋቂ የነሶሓቢው ኢብኑ ዑመር ፣ ኢብኑ መስዑድ (ሪድዋኑላሂ ዐለይሂም) ፣ የነ ኢማሙ ሻፊዒይ ፣ የነኢማሙ አሕመድ ፣ የነኢማም ቡኻሪ ፣የነኢብኑ ሐጀር ፣ የነኢብኑ ተይሚያህ  የነኢማም ዐብዱልወሃብ፣ የነኢብኑ ባዝ ፣ የነአልባኒ ተተኪ ትውልድ ይፈጠራል ።

በሽርክና ቢድዐ የተጨማለቀው ጨለማ ዘመን በዕውቀት ላይ በተመረኮዘው ተተኪ ትውልድ በተውሒድና በሱና ብርሐን ይታደሳል

በጭፍን ተከታይነት ፣ በዘር ወገንተኝነት ፣ በጅሕልና ፅልመት ፣ በአውሬነት ባሕሪ የተላበሰ ክፉ ዘመን የነገው እናቶች በገበዩት ሸሪዐዊ ዕውቀት እራሳቸውን ልጆቻቸውንም ኮትኩተው በኢስላማዊ አደብ በማሳደግ ትውልድን ሊቀይሩ ከምንም በላይ አስፈላጊና ይበልጥ የተገባ ነው ።
☞ስለዚህ ውዷ እሕቴ ይህን ሃላፊነትሽን ለመወጣት ዛሬውኑ ሸሪዐዊ ዕውቀትን መፈለግ ይኖርብሻል የሚለው ትልቁ ልባዊ ምክሬ ነው ።
#ሼር_በማድረግም_አስተላልፉት

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam