الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.6K subscribers
359 photos
16 videos
7 files
912 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
💌::::::::እውነተኛ ፍቅር::::::::::💌

▶️ክፍል 9⃣

#የመጨረሻው ክፍል-----🍃

#ወረቃ ከከድጃ ቤት ወጥቶ ያመራው ወደ ወንድሙ ኩወይልድ ቤት ነበር፡፡ እንደገመተውም ሰክሮ አገኘው፡፡ በእጁ የመጠጥ ብርጭቆ ጨብጧል ወረቃም አጠገቡ ቁጭ አለ፡፡ ኩወይልድ ከመጠጡ ሊጎነጭ ሲል ወረቃ ከለከለውና ከእጁ ተቀበለው፡፡ ከዚያም ወረቃ
" #በኒ ሀሺሞች አንተን ሊገሉህ እየተመካከሩብህ ነው፡፡ በተለይ ሀምዛ ከነቤቱ አቃጥየው አሻራውን አጠፋለሁ እያለ ይዝትብሀል" አለው፡፡ ኩወይልድ "በምን ወንጀል ነው ይህንን ክፉ ስራ የሚፈፀምብኝ ? "ሲል ጠየቀው፡፡ ወረቃም "የወንድማቸው ልጅ #መሀመድን ስትሳደብ ሰሙህ፡፡ በርግጥ እንደ መሀመድ ያለ ጨዋ ሰው አይሰደብም ፤ ከድጃ ወደ ሻም ስትልከው በጉዞ ያጋጠመውንና የታየውን ተዓምር መይሰራ ሲናገር ሰምተህ የለ? " አለው፡፡ ኩወይልድም "በርግጥ #መሀመዱልአሚን ለኔ የተከበረና ጨዋ ሰው ነው ግን ከድጃን ለጋብቻ ጠየቁለት እኔ ደግሞ እንቢ አልኩኝ" ሲለው "እኛ ቤተሰብህ በዚህ ጉዳይ ሳንመካከር ብቻህን ለምን መልስ ሰጠህ" አለው ወረቃ፡፡
#ኩወይልድም "በሁለት መንገድ ፈርቼ ነው ጋብቻውን ያልተቀበልኩት አንደኛው ከፀሀይ መውጫ እስከ መግቢያ የናኘው ዝናዬ እንዳይበላሸ ሁለተኛው መሀመድ የከድጃ ተቀጣሪ፤ እናትና አባት የሌለው የቲም በመሆኑ ነው" አለው፡፡ #ወረቃም "ቁረይሾች ዘንድ የተወደደውን የመሀመዱልአሚንን የዘር ግንድ ለመቀላቀል የማይፈልግ ማንም የለም፡፡ አንተ ከድጃን ብትከለክላቸውም እርሷ ራሷን #ለመሀመድ #አጭታለች፡፡ አንተ ግን ለጀግናውና ለአንበሳው ሀምዛ ፤ ለስመገናናው አባስ ለተወዳጁ አቡጣሊብ ጠላት ሆንክ " አለው፡፡
ኩወይልድ አሰብ አደረገ፡፡ ወንድሙ ወረቃ የነገረው እውነት ከሆነ የርሱ ከድጃን መከልከል ዋጋቢስ ነው፡፡ ከዚያም ለወረቃ እንዲህ አለው " #ወንድሜ ሆይ እነሱ ጋር ሄደህ ኩወይልድተስማምቷል ብትላቸው የመሀመድ አጎቶች እንዳይሳለቁብኝ ፈራሁ፡፡"
#ወረቃም "ኩወይልድ ሆይ ለዚህ ሀሳብ አይግባህ በኒሀሽሞች እንዳይቀየሙህ ይቅርታ እንዲያደርጉልህ ለማድረግ ቃል እገባልሀለው " አለው፡፡
በዚህ ጊዜ ኩወይልድ ደስ አለው፡፡ ለወረቃም የመሀመድ ቤተሰቦች ዘንድ ሄዶ እንዲያስምናቸውና ይቅርታ እንዲያደርጉለት ከዚያም ውክልና ወስዶ ከድጃን ኒካህ እንዲያደርጉላት ነገረው፡፡ ወረቃም እንደተባለው አደረገ፡፡ #የሙሀመድ (ሰዐወ) ቤተሰቦች ተስማሙ፡፡ ወደ ከድጃ አጎት አምር ኢብኑ አሰድ ጋር በመሄድ የማጫውን ጥሎሽ አሟልተው ኒካህ ተደርጎ እንዳበቃ እርድ ተከናውኖ ስጋው ለድሆች ተከፋፈለ፡፡ የአካባቢውን ሰዎች በሙሉ ጋበዙ፡፡ ከተጋበዙት ሰዎች መሀል መሀመድን (ሰዐወ) በህፃንነታቸው ያጠባቻቸው ሀሊመቱ አስሰዕዲያ ነበረች፡፡ #የተከበረችው ከድጃም ለመሀመድ (ሰዐወ) ያላትን የላቀ ፍቅር ለመግለፅ ለመሀመድ የጡት እናት ለሀሊማ 40 በጎችን በስጦታ አበረከተች እንዲሁም ባሪያዋ የነበረው ዘይድ ኢብኑ ሀሪስን ሰጠቻቸው፡፡
#በመጨረሻው #የደስ ደስ ቀን የመካ ሹማምንቶችንና ታላላቅ ሰዎች የከድጃ ቤተሰቦች ያዘጋጁትን ድግስ ተመግበው እንዳበቁ ወረቃ ኢብኑ ነውፈል እንዲህ አለ
" #እንግዶቼ #ሆይ በዚህች በመካ ዙሪያ ያላችሁም ይሁን ከሌላ አካባቢ ተጋብዛችሁ የመጣችሁ ሁላችሁም እወቁት በዛሬው ዕለት በዚች ሰዐት ልጃችንን ከድጃ ቢንት ኩወይልድን ለመሀመድ ኢብኑ አብደላህ ድረነዋል ፣ ሰጥተነዋል፡፡ ደስ ይበላችሁ ደስ ብሎናል" አላቸው፡፡
#ከዚህ በኋላ ነበር በአለማችን ከኢስላም ጥሪ በፊት ድንቅና አስገራሚ ጋብቻ በታላቁ ነበይ (ሰዐወ) እና በከድጃ (ረዐ) መካከል የተከናወነው፡፡ ከገንዘብና ከሹመት በላይ መልካም ስነምግባርና ጥሩ ፀባይን አስበልጣና አፍቅራ ኸድጃ (ረዐ) ነቢያችንን አገባች፡፡

እዉነተኛ ፍቅር ማለት ይህ ነዉ ቃናtv ላይ እና በህንድ ፊልም አይደለም፡፡ ይህ ፍቅር በኸድጃ በፊት የነበረ ነዉ ሞዴላችን መሆን ያለበት ነብዩ ሙሀመድ መሆን አለባቸዉ።

❥ሀያት ቢንት ከድር ❥

ለአስተያየት 👉@HalalTedar_bot

🍃🍃🍃🍃ተፈፀመ🍃🍃🍃🍃

ፁሁፉን አስመልክቶ አስተያየት ከለ👇

@Hayatbintkedir👈👈

💌::::::::ቴሌግራማችን::::::::::::💌

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8riR2kM4HsIJg
#የተከበርከው__ወንድሜ__ሆይ! ☜

ትዳር ከማሰብህ በፊት!
ስለ ትዳር ትርጉም በደንብ እወቅ!
በትዳር ውስጥ ብዙ ነገሮች አሉ!
እናም! የሚገጥምህን ነገሮች ሁሉ አምነህ ለመቀበል + መስዓላውን + ሀላፊነትን ለመወጣት……… +… ………አስበህ መወሰን!

ከዛም!
ለትዳር የምትሆንህን ሴት ስትመርጥ ድኗን እንጂ! መልኳን አይሁን!
ምክንያቱም! በአላህ ፈቃድ በድኗ ውስጥ ሁሉንም ነገር ታገኛለህና!

ደግሞ!
አይን ቀላዋጭ ነውና ብዙ ያምረዋል!
ስለዚህ! ልብህ #ያረፈባትን ሴት ምረጥ + አግባ!

ከአገባህ ቡኋላም!
#ለውዷ ሚስትህ እዘንላት + የወደፊት የልጆችህ እናት ለምትሆነው!

በተለይ! የተከበረከው ባለ ትዳር ወንድሜ ሆይ!
ለውዷ ባለቤትህ ምን አይነት ባል መሆን እንዳለብህ ላስታውስህ ነው!
እናም!
#ምክሬን በወቀሳ እንዳታስብብኝ!

እንዲሁም! አሁን የምጠቅሳቸውን ክፍተቶች በትዳርህ ላይ ካጋጠሙህ ራስህን ፈትሸህ!
#ለማስተካከል ሌት ተቀን ደፋ ቀና ማለት አለብህ!

ከዚህ ነገር አላህ ከጠበቀህ አላህን እያመሰገንክ ለትዳርህ መፅናትና መጨነቅ አለብህ! ምክናያቱም #ትዳር ነውና!

አንተ ጋር ያለችው ሚስትህ ብትሆንም አማና መሆኗን ልታውቅ ይገባል!
እነሆ ይሄንን አማና በጥንቃቄ ልትይዝ አላህን ልትፈራ ይገባሀል!
አባቷ ልጅቱን ላንተ ሲሰጡህ ሀቋን ትጠብቃለህ + ገመናዋን ትሸፍናለህ + ጥሩ ሰው ትሆንላታለህ… ………………ብለው ነው!
የሚጠቅማትን ነገር ልታገርግላት + የሚጎዳትን ነገር በሷ ላይ ከማድረግ ልትታቀብ ይገበሃል!!

#ሚስትህ ያአንተን ሀቅ እንድታውቅ እንደምትጓጓው ሁሉ የጌታዋንም ሀቅ ልታሳውቃት + በኸይር ልትረዳት + አደጋ እንዳይደርሰባት ልትጠብቃት ይገባል!

ነብዩ መሀመድ (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል :- ሁላቹሁም ጠባቂዎች ናችሁ + ሁላቹሁም ከምትጠብቁት ነገር ተጠያቂዎች ናችሁ!

#ቤተሰቦቿ ጋር ሆና!
ስታገኝ የነበረውን ነገር አንተ ልትነፍጋት አይገባም!
በቻልከው አቅም ልታደርግላት ይገባል!
#ስትታመም ልታሳክማት + ሲከፋት አይዞሽ ልትላት + ስትደሰት አብረሀት ልትደሰት +………………+………… የሚያስፈልጉ ነገሮችን ልታቀርብላት + ልታደርግላት ወደ ቤትህ አስገብተሀታል እኮ!
አንተን ብላ ሁሉን ጥላ መጥታለችና እባክህ ተንከባከባት!!

#ተመልከት ! አንድ አላህን የማይፈራ ወንድ በጠዋት ከቤት ይወጣና ቁርስ + ምሳ + ራት + የሚበላው ከልጆቹ እናት ከሆነችው #ከሚስቱ ተነጥሎ ነው!

ቢያንስ እንኳ! ከነዚህ የምግብ ሰርዓቶች #በአንዱ ላይ ተገኝቶ ከልጆቹ እናት ጋር ሰብሰብ ብሎ አይመገብም! ይህ! በደል (ዙልም) አይደለምን???

#ሚስቱ ከዛ በፊት ከቤተሰቦቿ ጋር መብላት ለምዳ በአንዴ ብቻሽን ተመገቢ ብትባል ሊከብዳት ይችላል!!

ስለዚህ! ወንድሜ! አላህን ፈርተህ + ለትዳርህ ለሚስትህ ክብር + ቦታ ሰጥተህ!
#አቅሙ ካለህ ቤተሰቦቿ ጋር ትኖረው ከነበረው ኑሮ! የተሻለ ልታኖራት ይገባል!
ከሌለህ ግን! ማድረግ የምትችለውን በመልካም ንግግርን ልታናግራት + ጥሩ መልስን ልትመልስላት + ጥሩ ፍቅር ልትሰጣት + ልታዝንላት + ልትንከባከባት + ልታስደስታት………………… ይገባል!!

#ከሚስትህ ጋር ስትኖር! በመልካም መኗኗርን ለመኖር ታገል + ጣር!
#በመልካም መኗኗር የሚባለው አባባል ካልገባህ! የወደፊት የትዳርህ ዕድሜ አጭር + ዘላቂነት እንዳይኖረው እንዳይሆን ያስፈራልና ጠንቀቅ በል!!!

#ከባለቤትህ ጋር በአላህ ፈቃድ በመልካም ለመኗኗር ይረዳህ ዘንድ ልጠቁምህ:–
ዕዘንላት + ተንከባከባት + ውደዳት + አክብራት(ክብሯን ጠብቅላት) + ከልብህ መራራትን ራራላት + በተለያዩ አጋጣሚዎች ውዴታህን +ፍቅርህን ግለፅላት!
አንተ ይሄን አድርግ! አላህ ነገሩን ሁሉ ያገራልሀል!
አላህ ሁሉን አዋቂ + ባሪያውን የሚደግፍ ጌታ ነውና!!

#ሚስትህ ላንተ ሚስት በመሆኗ ብቻ እንደ #ባርያ/ህ ልታያት + ልታፈጋት + ልትጨቁናት + ልትረግጣት + ልትበድላት (ልትዞልማት)አይገባህም!
ሌላው ቢቀር ሙስሊም #እህትህ መሆኗንም አትዘንጋ!

#የሚያስፈልጋትን ሁሉ ነገር አሟልተህላት! ነገር ግን! በምላስህ #አዛ የምታደርጋት ከሆነ!
የአንተ ሁሉን ማድረግ እርሷ ዘንድ #ዜሮ + ጥቅም አልባ ሊሆን ይችላል!!!

#በል እንዳውም! አላህ ካዘነላቸው ውጭ!
አንዳንድ ወንድሞች #ከቤት አውጥቼ እንዳልወረውርሽ + ከነ ልጆችሽ ወደ ቤተሰቦችሽ እንዳልሸኝሽ + አንች የምናምን ልጂ… ………………………… እረ ስንቱን ይዘረዝራሉ! ብር አይደለም! ምላሳቸውን ነው!!

#ጥሩ ያልሆኑ + በጆሮ ለመስማት የሚሰቀጥጡ ንግግሮችን ሲናገሩ ይደመጣል!

#ሴትን ልጅ እንዲህ እየተናገረ + ሞራሏን እየጎዳው + ልቧን ባሻው ወቅት እየሰበረ +… ……………+……………#የፈለገውን ብያርግላት! እንዴት ይመለሳል?አትጠራጠር አድራጎትህ የአንድኛው እንኳ ምንም ላይመስላት ይችላል!!!

#አስብ + ተረዳ………!

#ሴት__ልጅ! ከምንም በላይ የምትፈልገው ሰላምን + ደስታን + ፍቅርን ……………ነው!
ምንም የሌለው ወንድ!
ነገር ግን! ሀቋን የሚጠብቅ + የሚንከባከባት + የሚያዝንላት + የሚራራላት… ………………ከሆነ!
ከእሱ ጋር በደስታ መኖርን ትመርጣለች!!

ከዚህ ተቃራኒ(አክስ) ደግሞ ለሀገር + ለወገን + ለዘመድ የሚበቃ ሀብት ኖሮት!
ግና ሞራሏን የሚጎዳው + መጥፎና አፀያፊ ቃል የሚናገር + ሀቋን የማይጠብቅ / የማያውቅ + የማይራራላት + …………………ከሆነ!
በሀብት ተኮፍሶ………የሰው ልጂ #ሰው መሆኗን እረስቶ/ ዘንግቶ!
እንደ #ዕቃ የሚቆጥራት ከሆነ!
ከዚህ አይነት ሰው ጋር በጭራሽ አትኖርም!!!
ምንም አይነት አንገት የሚያስደፋ ችግር ቢገጥማት ማለት ነው!!

#ወንድሜ ሆይ! በትዳርህ ግልፅነት ይኑርህ!
አንተ ከሚስትህ ሊሟሉልህ የምተፈልገውን ነገሮች እንዳለ ሁሉ!
አንተም ለእርሷ አሟልተህ መገኘት ይኖርብሀል!
ለምሳሌ :- ከሷ መጥፎ ሽታ እንዳይሸትህ እንደምትፈልገው ሁሉ!
አንተም በአንተ ላይ ያሉ መጥፎ ሽታ ሁሉ ልታስወግድ ግድ ይልሀል!
እርሷ ፈገግ እንድትልልህ እንደምትፈልገው ሁሉ! አንተም ፈገግ ልትል ግድ ይልሀል!
የሚያስፈልጉህን ነገሮች እንድታሟላልህ እንደምትፈልገው ሁሉ
አንም የእርሷን ፍላጎት ማሟላት ይኖርብሀል!!!

#ወንድሜ ሆይ! ባለቤትህ ( ሚስትህ ) በውጭ + በስራህ ቦታ የሚገጥምህን ውጣ ውረድ ላታውቅ ትችላለችና ትዕግስት አድርግ!

በመታገስህ ከአላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) በትልቅ ምንዳ ላይ ተስፋ አለህና!
የትዳር አጋርህ ላይ አንድ የምትጠላው ባህሪ ቢኖራት ሌሎች ብዙ የሚወደዱ ባህሪዎች አሏትና ታገስ!
#ሁሌም ጥቃቅን የሆነና ደካማ ጎኗን አታስብ! ይልቁንም ብዙ መልካም ስነ ምግባር አላትና ሁሌም ቢሆን መልካም ጎኗን ማስታወስ ይጠበቅብሀል!

#የሰው__ልጅ! አላህ ሲፈጥረው በባህሪው ምስጋናን ይወዳልና!
በተለይ! ለሚስትህ ምስጋና አቅርብላት!
በአላህ ፈቃድ ደካማ ጓኗን ለማስተካከል ከፈለክ! ጥሩ ጎኗን እያወደስክ ስታመሰግናት + ግልፅ ስትሆን + ስትወያይ ደካማ ጎኗን ለማስታካከል ሁሌም ትጥራለችና ሁሌም ቢሆን ሳይጋነን የአንተ አድናቆትህ አይለያት!
ባለቤትህ (ሚስትህ) ለአንተ ንግስትህ ነች!
ባለቤትህን ከማንም ጋር አታወዳድራት!!!

ወላሁ ተዓላ አዕለም#ሼር

💌:::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::👇💌

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8riR2kM4HsIJg
🚫::::::::::::ወንድሜ:::::::::::🚫

#ወንድሜ ስማኝማ ልንገርህ የኔ የምትላት ሴት/ሚስት ማግኘት የምትፈልግ ከሆነ ከዛችም ከዛችም መተዋወቅና ስልክ መለዋወጥ አቁም፡፡

እናም ለራስህ ጊዜ ስጠው.......
የምታገኛቸው ሴቶች ሁሉ ሚስት አይሆኑህም ምክንያቱም አንተም ለምታገኛቸው ሴቶች ሁሉ ባል መሆን አትችልማ!!

#ፍቅር ለገበያ አይቀርብም ላንተ ያላትን መቸም ከግርግር መሀል ማግኘት አትችልም፡፡ ምክንያቱም "10 ያባረረ አንድ አይዝምእና።

በቃ ዳር ሆነህ ጠብቃት ከግርግር ምን አለህ ለአንተ ያላት ብትዘገይ እንጅ ፈፅሞ አትቀርም ና ግን ልብ ማለት ያለብህ መልካም ሚስት አላህ ሲያድል እንጅ በትግል አትገኝም፡፡

እንዲህ ስልህ ደግሞ የምታያቸውን ሁሉ ለማግኘት አትሞክር እንጅ ሁሉንም ላለማየት አይንህን ጨፍን እያልኩ እንዳልሆነ ተረዳኝ !! #ሸሪዐ በፈቀደው ሰበብ አድርስ ላመንክባት ና የኔ ናት ብለህ ላሰብካት እስከ መጨረሻ ታገልላት፡፡

📌ከሁሉም በላይ ግን መልካም ሚስት ስትፈልግ መልካም ባል ሆነህ ተገኝ ፎርሙላው ይህ ነው እና ።

💌::::::::::::ቴሌግራማችን::::::::::::💌

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
🚫::::::ለዉዱ ወንድሜ መልክት:::::🚫

ሱብሃን አላህ 📌☞የሴት ፈተና ኢስላምክን እንዲህ ሊያስጥልክ ይችላልና ተጠንቀቅ❗️
ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ ﻣﻦ ﺍﻋﻈﻢ ﺍﻷﺳﺒﺎﺏ ﺍﻟﺘﻲ ﺗﻨﻘﺺ ﺍﻳﻤﺎﻥ ﺍﻟﺮﺟﻞ
በሚስር(ግብፅ) ከተማ ውስጥ መስጂድን በአዛን
በሰላት አጥብቆ የሚይዝ አንድ
ሰው (ሙዓዚን) ነበር። በርሱም ላይ ጥሩ
መታዘዝ እና የኢባዳህ ብርሃኖች
ይታዩበት ነበር፡፡
ከእለታት አንድ ቀን አዛን ሊያደርግ ወደ መናራህ ወጣ፡ ታዲያ አዛን ላይ ሆኖ
ከመስጂዱ ስር ወዳሉ ነስራኒዮች ቤት አይኑን ሲልክ ድንገት ከአንዱ ቤት ውስጥ
አንዲትን እንስት ይመለከታል ከመቅፅበት
በውበቷ ተመርኮ ፈተና ላይ ይወድቃል ፡
በፍጥነትም እርሷ ወዳለችበት ቤት ይሄድና ዘው ብሎ ይገባል ልጅቱም ምን ፈልጎ እንደመጣ ትጠይቀዋለች

🚫☞እርሱም፡- እንዲህ ሲል መለሰላት አንቺን ነው የምፈልገው

📌☞እርሷም ፡- ለምንድን ነው እኔን የፈለከኝ?"ብላ ጠየቀችው

🚫☞እርሱም፡- ልቤ ባንቺ ተፈትኗል የልቤን
መሰባሰቢያ ይዘሺዋል አላት

📌☞እርሷም፡- ያለምንም ጥርጥር መቼም እሺ ልልህ አልችም አለቸው

🚫☞እርሱም፡- እንግዲያውስ አገባሻለሁ" አላት

📌☞እርሷም ፡- አንተ ሙስሊም ነህ እኔ ነስራኒይያህ (ክርስቲያን) ነኝ አባቴ ደግሞ እንዲህ ሆነህ አንተን አይድረኝም አለችው"

🚫☞እርሱም፡- "ግዴለም እኔ ላንቺ ስል ነሳራ (ክርስቲያን) እሆናለሁ አላት፡

📌☞እርሷም ፡-እንደዛ ያደረግክ እነደሆን
(ክርስቲያን ከሆንክ) እኔም ፍቃደኛ ነኝ
(አገባሀለሁ)

ከዚያም ይሄ ሰው እርሷን ለማግባት ሲል ነሳራ (ክርስቲያን) ሆነና ከነርሱ ጋር ቤት
ተቀመጠ ታዲያ በዚያኑ እርሷን ጠይቆ ባገባበት የሰርጉ ዕለት ቤቱ ውስጥ ወዳለ ከፍ ወዳለ ቆጥ ሲወጣ ወደቆ
ወዲያኑ # ህይወቱ_አለፈች ፡:
እርሷንም ሳያገኝ እስልምናውን አጥቶ በኩፍር ላይ ሞተ ።
(አል፡ዳኡ ወ’ደዋአ ሊኢብኑ አል፡ቀይም ገፅ 167)
ሰዓይድ ኢብኑ ሙሰየብ(አላህ ይዘንለትና) እንዲህ
ይል ነበር፡ <<አላህ ሱብሀነ
ወተዓላ አንድንም ነብይ አላከም፡ሸይጣን በሴት ፈተና ሲያጠፋቸው ከነርሱ ላይ
ተስፋ ባይቆርጥ እንጂ>>
(መውሱዓቱ ኢብኑ አቢ ዱንያ ቅጽ 4 ገፅ 540)
አል-ሀሰን ኢብኑ ሳሊህ(አላህ ይዘንለትና) እንዲህ
ሲል ይናገራል፡ <<ሸይጣን
ለሴት ልጅ እንዲህ ሲል ሰምቻለሁ፡አንቺ የኔ ግማሽ ጎኔ ነሽ፡እኔ በአንቺ የምወረውርብሽ ቀስቴ ነሽ ደግሞም ባንቺ ከወረወርኩ አልስተም፡እንቺ
የሚስጥሬ ቦታ ነሽ፡አንቺ የኔ የጉዳዬ መልክተኛ ነሽ>>
(መውሱዓቱ ኢቡኑ አቢ ዱንያ ቅፅ 4 ገፅ 539)
ለወንድ ልጅ ከባዱ ፈተና
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል
ለወንዶች ከሴቶች ይበልጥ ጎጂ ፈተና በኋላዬ አልተውኩም
(ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል

#ወንድሜ_ከእንድህ_አይነት_ፊቲና_አላህ_ይጠብቅህ
ከወደዳቹት #ሼር_አድርጉ_ሸር_የለበትም_እና

💍::::::::::::::ቴሌግራማችን::::::::::::::💍

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
🚫::::::ለዉዱ ወንድሜ መልክት:::::🚫

ሱብሃን አላህ 📌☞የሴት ፈተና ኢስላምክን እንዲህ ሊያስጥልክ ይችላልና ተጠንቀቅ❗️
ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ ﻣﻦ ﺍﻋﻈﻢ ﺍﻷﺳﺒﺎﺏ ﺍﻟﺘﻲ ﺗﻨﻘﺺ ﺍﻳﻤﺎﻥ ﺍﻟﺮﺟﻞ
በሚስር(ግብፅ) ከተማ ውስጥ መስጂድን በአዛን
በሰላት አጥብቆ የሚይዝ አንድ
ሰው (ሙዓዚን) ነበር። በርሱም ላይ ጥሩ
መታዘዝ እና የኢባዳህ ብርሃኖች
ይታዩበት ነበር፡፡
ከእለታት አንድ ቀን አዛን ሊያደርግ ወደ መናራህ ወጣ፡ ታዲያ አዛን ላይ ሆኖ
ከመስጂዱ ስር ወዳሉ ነስራኒዮች ቤት አይኑን ሲልክ ድንገት ከአንዱ ቤት ውስጥ
አንዲትን እንስት ይመለከታል ከመቅፅበት
በውበቷ ተመርኮ ፈተና ላይ ይወድቃል ፡
በፍጥነትም እርሷ ወዳለችበት ቤት ይሄድና ዘው ብሎ ይገባል ልጅቱም ምን ፈልጎ እንደመጣ ትጠይቀዋለች

🚫☞እርሱም፡- እንዲህ ሲል መለሰላት አንቺን ነው የምፈልገው

📌☞እርሷም ፡- ለምንድን ነው እኔን የፈለከኝ?"ብላ ጠየቀችው

🚫☞እርሱም፡- ልቤ ባንቺ ተፈትኗል የልቤን
መሰባሰቢያ ይዘሺዋል አላት

📌☞እርሷም፡- ያለምንም ጥርጥር መቼም እሺ ልልህ አልችም አለቸው

🚫☞እርሱም፡- እንግዲያውስ አገባሻለሁ" አላት

📌☞እርሷም ፡- አንተ ሙስሊም ነህ እኔ ነስራኒይያህ (ክርስቲያን) ነኝ አባቴ ደግሞ እንዲህ ሆነህ አንተን አይድረኝም አለችው"

🚫☞እርሱም፡- "ግዴለም እኔ ላንቺ ስል ነሳራ (ክርስቲያን) እሆናለሁ አላት፡

📌☞እርሷም ፡-እንደዛ ያደረግክ እነደሆን
(ክርስቲያን ከሆንክ) እኔም ፍቃደኛ ነኝ
(አገባሀለሁ)

ከዚያም ይሄ ሰው እርሷን ለማግባት ሲል ነሳራ (ክርስቲያን) ሆነና ከነርሱ ጋር ቤት
ተቀመጠ ታዲያ በዚያኑ እርሷን ጠይቆ ባገባበት የሰርጉ ዕለት ቤቱ ውስጥ ወዳለ ከፍ ወዳለ ቆጥ ሲወጣ ወደቆ
ወዲያኑ # ህይወቱ_አለፈች ፡:
እርሷንም ሳያገኝ እስልምናውን አጥቶ በኩፍር ላይ ሞተ ።
(አል፡ዳኡ ወ’ደዋአ ሊኢብኑ አል፡ቀይም ገፅ 167)
ሰዓይድ ኢብኑ ሙሰየብ(አላህ ይዘንለትና) እንዲህ
ይል ነበር፡ <<አላህ ሱብሀነ
ወተዓላ አንድንም ነብይ አላከም፡ሸይጣን በሴት ፈተና ሲያጠፋቸው ከነርሱ ላይ
ተስፋ ባይቆርጥ እንጂ>>
(መውሱዓቱ ኢብኑ አቢ ዱንያ ቅጽ 4 ገፅ 540)
አል-ሀሰን ኢብኑ ሳሊህ(አላህ ይዘንለትና) እንዲህ
ሲል ይናገራል፡ <<ሸይጣን
ለሴት ልጅ እንዲህ ሲል ሰምቻለሁ፡አንቺ የኔ ግማሽ ጎኔ ነሽ፡እኔ በአንቺ የምወረውርብሽ ቀስቴ ነሽ ደግሞም ባንቺ ከወረወርኩ አልስተም፡እንቺ
የሚስጥሬ ቦታ ነሽ፡አንቺ የኔ የጉዳዬ መልክተኛ ነሽ>>
(መውሱዓቱ ኢቡኑ አቢ ዱንያ ቅፅ 4 ገፅ 539)
ለወንድ ልጅ ከባዱ ፈተና
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል
ለወንዶች ከሴቶች ይበልጥ ጎጂ ፈተና በኋላዬ አልተውኩም
(ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል

#ወንድሜ_ከእንድህ_አይነት_ፊቲና_አላህ_ይጠብቅህ
ከወደዳቹት #ሼር_አድርጉ_ሸር_የለበትም_እና

💍::::::::::::::ቴሌግራማችን::::::::::::::💍

https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
በዉስጥ መስመር ከደረሰኝ ግጥም

#አትዘን #ወንድሜ

ችግር ቢደራረብ ቢበዛ መከራ
መሞከር አለብህ ለመሆን ጠንካራ።

ጊዜያዊ ነውና የዚች አለም ህይወት
አይክፋህ ወንድሜ ቀለል አርገህ እያት።

ህይወት ስታስከፋህ አኸይራን አስታወስ
ስቃይ የለምና ከአኸይራ የሚብስ

አከይራህ እድያምር ዛሬ ላይ ጠንክር
እጅ አትስጥ በጭራሽ ለምንም ነገር።
የፈለገ ይምጣ የፈለገ ይሂድ
በአላህ ተመካና ወደፊት ተራመድ።

የሚሆነው ሁሉ ዛሬ በምድር
የተፃፈኮነው በአላህ ቀደር።

®

💍:::::::ቴሌግራማችን:::::::💍

t.me/Tidar_Be_Islam
t.me/Tidar_Be_Islam
☞::::::ወንድሜ::::::☜

#ወንድሜ_ምርጫህ_ይሁን_በመንሀ_ሰለፊያ_ላይ_ያለችዋን_እህት

በአሏህ ሰም አጅግ በጣም ሩኁሩህ በጣም አዛኝ በሆነዉ

ሰለፊ የምትባለው ሴት በሱመያ ስም የምትነግደዋ ሴት ሳትሆን በመንሀጅ ሰለፊያ ላይ ያለችዋን ሴትን ያገባ ምንኛ ተድሎል በሂጃባ የደመቀች እንቁ ናት ፣ ሃያዋ እጅግ ውብ ነው የህልውናዋ ሚስጥር ነው። ተቅዋ እሳ ዘንድ የህይወቷ ስንቅ ነው። እርዳታ ሆነ እገዛ ወደ ፈጣሪዎ ብቻ ነው የምትማፀነው።

ከሰው የተብቃቃችና ወደ አላህ የምትከጅል ልዩ ፍጡር ናት ሁሌም ኢስላምና ሙስሊሞችን በመካደም ላይ የፀናች ናት ልፍቷ ሙስሊሙን ኡማ መሰረት በማድረግ በተውሂድ እና ሱና ላይ አንድ ለማድረግ  በቁርዓን እና በሀድስ አጥብቃ የታጠቅች ናት የሰለፊያ እንስት ፈፅሞ  ቅጥፈት አታውቅም  እንደ ባለጌዎች ባግኘችበት ቦታ አትገንም ሰውንም   አትሰድብም  ጥረቶ  ኢልም መማር ብቻ ሳይሆን ባወቀችው መተግበር ላያት ሰው ዚክርና ተቅዋን ላይ እንጂ  ፊልም ወይም ነሽዳ  ሆነ ቅጥፈት የተምላባቸው ነገሮች ላይ አፍጣ አትውልም ሁሌም   የምትፈራው አላህን ብቻ ነው ለሂጃባና ለዲና ሁሌም ትሞታለች እሳ የምታፈራው ልጅ ለተውሂድ እና ለሱና የሚታገል እንጅ ለአህሉል ቢድዓ ጥብቅና የሚቆም አይደለም እሳ የምታፈራልህ ልጅ በኢልም  የጠነከረ እንጅ በነሽዳ ክራር የሚለፈልፍ አይደለም እሳ የምታፈራልህ ልጅ ልፋቱ ለመንሀጅ ሰለፊያ  ጥበቃና ከለላ እንጂ ለቢዳዓ አንጃዎች ከሱና ላፈነገጡ ቡድተኝነት

የሚቆም አይደለም ።
#ሰለፊያ_ሴትን ያገባ ለባላ ፍፁም ታማኝ በዲን ላይ አደራ የምትል ናት ሁሌም ለባላ በሃላል ስራ የምታበረታታ   ከሃራም ተግባር የምታስጠነቅቅ ሁሌም ለባሎ እጅግ ፍቅር በተሞላበት አይን ትመለከተዋለች፣ ሲረሳ ታስታውሰዋለች፣ ሲዘናጋ ታነቃዋለች  ሁሌም በኢባዳ ላይ አደራ ትለዋለች ለአካባቢዋ ሞዴል የክብር ካባ የለበሰች የልዩና ውብ ስነ ምግባር ባለቤት ነች ሁሌም እጆቿ ለምስኪን እና ለደካሞች የተዘረጋ ለእንግዳ ታላቅ ከብርና ልዩ እንክብካቤ ታደርጋለች ፈፅሞ በደስታዋ ሆነ በችግራ ወቅት የቲሞችን አትረሳ ወላጆቻን በጀነት ለማሸለም ሁሌም በመልካም ስራ ላይ ትለፋለች ጎረቤቷን በእጅጉ ታከብራለች ያላትን አካፍላ ትበላለች  የረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰላም ሱና በሰለፎች ግንዛቤ  የተከተለችዋ ሰለፍያ ሷሊሂን የሆነች እንስት ሁሌም በላጭ ነች::

አላህ ወደ መልካሙ ነገር ይምራን አሚን

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
#የኔ_ውድ_አትበለኝ!!!

የኔ ውድ አትበለኝ #ከኒካህ በፊት
ወንድም ያመራናል የፈሳድ መንገድ
ብሎም ያሳጣናል የረሡሉን ሱና
መዘዙ ብዙ ነው ያደርገናል መና

ከኒካህ በፊት ያሉት ጣፋጭ ቃሎች
እነርሱ አይሆኑም የኢማን መስፈርቶች

#ወንድሜ_ልንገርህ_አንዴ___ስማኝማ

ስሜት ተከትለው ብለው ከበር ቻቻ
ከሞቱ በኋላ የለም ማረኝ ጌታ
እኮ ከወደድከኝ የት አለ ተግባሩ?
የሰው ልጅ አቋሙ በተግባር ማማሩ

ይቺንም ያቺንም ልታይ ቁንጅናቸው
መቼም አታውቀውም ስትገፍ ሒጃባቸው

አንተም ተጠምደሀል በምዕራብ ወጥመድ
ተከትለህ ላትሄድ በረሡል መንገድ

ደግሞም ላያገባኝ ግራ ሲያጋባኝ
የሴት ልጅ ክብሬ ከቶ ሊያሳጣኝ

ከኒካህ በፊት ጣፋጭ ንግግሮች
አዎ ያሳያሉ የኢማን ጉድለቶች
ደግሞም ያመራሉ የሸይጧን መንገዶች

ለምን አስፈለገን መከተል ስሜት
ምንም ነገር ሳናውቅ አውቃለሁ ማለት
በገዛ እጃቾን ጀሀነም መግዛት
ምኑ ላይ ነው ክፋት አሏህን መፍራት?????
የልጅቷ አኽሏቅ ከተረዳሀት እውነት ከወደድካት
ኒካህ እሰርላት ጣፋች ንግግሮች የዛኔ አሰማት
ከኒካህ በፊት ሒጃብ አትግፈፋት
አኺራ ልትዘነጋ ሰበብ አትሁናት

ሴት ልጅ ሞኝ ናት ቶሎ ታምናለች
ለወንድ ልጅ ፍቅር እጅ ትሰጣለች
እኔ ጋስ ከሆንኩኝ አትሁን ክብሪት
ይልቁን እንጣር ውሀ ለመሆን
በጋራ እናጥፋው የሸይጧን እሳት


ፋይዳው ምኑ ላይ ነው ሶሏት መስገዳችን
ቁርዐን መቅራታችን ሀዲስ መስማታችን
ዕምነት መግለፃችን
ከቶ ካልታወቀን ስንበደል ነፍሳችን???
@almutehabin