الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.6K subscribers
359 photos
16 videos
7 files
912 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
💌::::::::እውነተኛ ፍቅር::::::::::💌

▶️ክፍል 9⃣

#የመጨረሻው ክፍል-----🍃

#ወረቃ ከከድጃ ቤት ወጥቶ ያመራው ወደ ወንድሙ ኩወይልድ ቤት ነበር፡፡ እንደገመተውም ሰክሮ አገኘው፡፡ በእጁ የመጠጥ ብርጭቆ ጨብጧል ወረቃም አጠገቡ ቁጭ አለ፡፡ ኩወይልድ ከመጠጡ ሊጎነጭ ሲል ወረቃ ከለከለውና ከእጁ ተቀበለው፡፡ ከዚያም ወረቃ
" #በኒ ሀሺሞች አንተን ሊገሉህ እየተመካከሩብህ ነው፡፡ በተለይ ሀምዛ ከነቤቱ አቃጥየው አሻራውን አጠፋለሁ እያለ ይዝትብሀል" አለው፡፡ ኩወይልድ "በምን ወንጀል ነው ይህንን ክፉ ስራ የሚፈፀምብኝ ? "ሲል ጠየቀው፡፡ ወረቃም "የወንድማቸው ልጅ #መሀመድን ስትሳደብ ሰሙህ፡፡ በርግጥ እንደ መሀመድ ያለ ጨዋ ሰው አይሰደብም ፤ ከድጃ ወደ ሻም ስትልከው በጉዞ ያጋጠመውንና የታየውን ተዓምር መይሰራ ሲናገር ሰምተህ የለ? " አለው፡፡ ኩወይልድም "በርግጥ #መሀመዱልአሚን ለኔ የተከበረና ጨዋ ሰው ነው ግን ከድጃን ለጋብቻ ጠየቁለት እኔ ደግሞ እንቢ አልኩኝ" ሲለው "እኛ ቤተሰብህ በዚህ ጉዳይ ሳንመካከር ብቻህን ለምን መልስ ሰጠህ" አለው ወረቃ፡፡
#ኩወይልድም "በሁለት መንገድ ፈርቼ ነው ጋብቻውን ያልተቀበልኩት አንደኛው ከፀሀይ መውጫ እስከ መግቢያ የናኘው ዝናዬ እንዳይበላሸ ሁለተኛው መሀመድ የከድጃ ተቀጣሪ፤ እናትና አባት የሌለው የቲም በመሆኑ ነው" አለው፡፡ #ወረቃም "ቁረይሾች ዘንድ የተወደደውን የመሀመዱልአሚንን የዘር ግንድ ለመቀላቀል የማይፈልግ ማንም የለም፡፡ አንተ ከድጃን ብትከለክላቸውም እርሷ ራሷን #ለመሀመድ #አጭታለች፡፡ አንተ ግን ለጀግናውና ለአንበሳው ሀምዛ ፤ ለስመገናናው አባስ ለተወዳጁ አቡጣሊብ ጠላት ሆንክ " አለው፡፡
ኩወይልድ አሰብ አደረገ፡፡ ወንድሙ ወረቃ የነገረው እውነት ከሆነ የርሱ ከድጃን መከልከል ዋጋቢስ ነው፡፡ ከዚያም ለወረቃ እንዲህ አለው " #ወንድሜ ሆይ እነሱ ጋር ሄደህ ኩወይልድተስማምቷል ብትላቸው የመሀመድ አጎቶች እንዳይሳለቁብኝ ፈራሁ፡፡"
#ወረቃም "ኩወይልድ ሆይ ለዚህ ሀሳብ አይግባህ በኒሀሽሞች እንዳይቀየሙህ ይቅርታ እንዲያደርጉልህ ለማድረግ ቃል እገባልሀለው " አለው፡፡
በዚህ ጊዜ ኩወይልድ ደስ አለው፡፡ ለወረቃም የመሀመድ ቤተሰቦች ዘንድ ሄዶ እንዲያስምናቸውና ይቅርታ እንዲያደርጉለት ከዚያም ውክልና ወስዶ ከድጃን ኒካህ እንዲያደርጉላት ነገረው፡፡ ወረቃም እንደተባለው አደረገ፡፡ #የሙሀመድ (ሰዐወ) ቤተሰቦች ተስማሙ፡፡ ወደ ከድጃ አጎት አምር ኢብኑ አሰድ ጋር በመሄድ የማጫውን ጥሎሽ አሟልተው ኒካህ ተደርጎ እንዳበቃ እርድ ተከናውኖ ስጋው ለድሆች ተከፋፈለ፡፡ የአካባቢውን ሰዎች በሙሉ ጋበዙ፡፡ ከተጋበዙት ሰዎች መሀል መሀመድን (ሰዐወ) በህፃንነታቸው ያጠባቻቸው ሀሊመቱ አስሰዕዲያ ነበረች፡፡ #የተከበረችው ከድጃም ለመሀመድ (ሰዐወ) ያላትን የላቀ ፍቅር ለመግለፅ ለመሀመድ የጡት እናት ለሀሊማ 40 በጎችን በስጦታ አበረከተች እንዲሁም ባሪያዋ የነበረው ዘይድ ኢብኑ ሀሪስን ሰጠቻቸው፡፡
#በመጨረሻው #የደስ ደስ ቀን የመካ ሹማምንቶችንና ታላላቅ ሰዎች የከድጃ ቤተሰቦች ያዘጋጁትን ድግስ ተመግበው እንዳበቁ ወረቃ ኢብኑ ነውፈል እንዲህ አለ
" #እንግዶቼ #ሆይ በዚህች በመካ ዙሪያ ያላችሁም ይሁን ከሌላ አካባቢ ተጋብዛችሁ የመጣችሁ ሁላችሁም እወቁት በዛሬው ዕለት በዚች ሰዐት ልጃችንን ከድጃ ቢንት ኩወይልድን ለመሀመድ ኢብኑ አብደላህ ድረነዋል ፣ ሰጥተነዋል፡፡ ደስ ይበላችሁ ደስ ብሎናል" አላቸው፡፡
#ከዚህ በኋላ ነበር በአለማችን ከኢስላም ጥሪ በፊት ድንቅና አስገራሚ ጋብቻ በታላቁ ነበይ (ሰዐወ) እና በከድጃ (ረዐ) መካከል የተከናወነው፡፡ ከገንዘብና ከሹመት በላይ መልካም ስነምግባርና ጥሩ ፀባይን አስበልጣና አፍቅራ ኸድጃ (ረዐ) ነቢያችንን አገባች፡፡

እዉነተኛ ፍቅር ማለት ይህ ነዉ ቃናtv ላይ እና በህንድ ፊልም አይደለም፡፡ ይህ ፍቅር በኸድጃ በፊት የነበረ ነዉ ሞዴላችን መሆን ያለበት ነብዩ ሙሀመድ መሆን አለባቸዉ።

❥ሀያት ቢንት ከድር ❥

ለአስተያየት 👉@HalalTedar_bot

🍃🍃🍃🍃ተፈፀመ🍃🍃🍃🍃

ፁሁፉን አስመልክቶ አስተያየት ከለ👇

@Hayatbintkedir👈👈

💌::::::::ቴሌግራማችን::::::::::::💌

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8riR2kM4HsIJg