الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.4K subscribers
391 photos
19 videos
8 files
925 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::ትዳር በኢስላም::::☜   ክፍል ዘጠኝ/⑨ኝ    #ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ     አላህ ለወንድ ልጅ ከአንድ በላይ እስከ አራት ሚስት ማግባት እንዲችል ሲፈቅድለት የሰው ልጅ ሊደርስበት የማይችል ሚስጥራዊ ሂክማ አለው።     በኢስላም ውስጥ አብዛሀኞቹ  በቁጥር የተገደቡ ኢባዳዎች የቁጥራቸውን ሚስጥር ጥራትና ልቅና የተገባው ጌታችን አላህ ሱወ ብቻ ነው የሚያውቀው።የዙህር ሶላት ለምን…
☞::::::ትዳር በኢስላም:::::::::☜

  ክፍል አስር/⑩

  
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ

3/
#የሴቶች_ቁጥር_በእጅጉ_መጨመር_እና
     
#በአንፃሩ_የወንዶች_ቁጥር_መቀነስ

  በአለም ላይ በተደረገው ጥናት እና ቆጠራ በየክፍለ ዘመኑ ያሉ ወንዶች በቁጥር እጅግ አናሳ ሲሆን የሴቶች ቁጥር በእጅጉ የጨመረ ነው።ይህም የሚሆንበት የተለያዩ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ የተወሰኑትን ለናሙና ያክል እንጥቀስ፣

ሀ/. በአለም ላይ የወንዶች ሞት በተለያዩ ምክንያቶች መጨመር የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ (medical school of harvard) በ2016 ይፋ ባደረገው ጥናት ከሴቶች ይልቅ ወንዶች በውል ተለይተው ለማይታወቁ የተለያዩ የካንሰር በሽታዎች የመጋለጥ እድላቸው የሰፋ ነው።ይህም የሚሆንበት ምክንያት የሴቶች x ክሮሞዞም ካንሰርን የመቋቋም እድሉ ከፍተኛ ነው ይላል ጥናቱ።ከዚህም በተጨማሪ ሰውን በከፍተኛ ገዳይ ከሆኑት የልብና የጭንቅላት በሽታ ከሴቶች ይልቅ ወንዶች በይበልጥ የተጋለጡ ናቸው ይላል ።

ለ/. ወንዶች በተለያዩ ሱሶች እና አደንዛዥ እፆች የመለከፍ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑ ነው። በዚህምየተነሳ የጉበት፣የሳንባ እና የመሳሰሉት ካንሰሮች ተጠቂ መሆናቸው የመሞት እድላቸው እንዲጨምር አድርጎታል።

ሐ/ . ከወንዶች ውልደት የሴቶች ውልደት የበዛ መሆኑ ሌላው ምክንያት ነው። የሴቶችን እና የወንድ ቁጥር የሚወስነው እንዲሁም ሴት ወይም ወንድ ይወለድ ብሎ የሚያዘው አምላካችን አላህ ብቻ ነው።ይህ በእንዲህ እንዳለ እንደመንስኤ ነው የሚሉት "x" ክሮሞዞም ከያዘው በፍጥነት ዝግ ያለ መሆን እና ማህፀን ውስጥ የመቆየት እድሜው ከፍተኛ መሆን የሴቷን የዘር ፍሬ የማግኘት እድሉ ከፍተኛ ነው።በዚህም ምክንያት ሴቶች በውልደት ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ ይላሉ።
…… አንዳንድ ይህ ሚስጥር የገባቸው የኢስላም ጠላቶች ሃቁን ሽምጥጥ አድርገው በውልደትም ሆነ በቁጥር ወንዶች ይበልጣሉ። በማለት በኢንተርኔት አሰራጭተዋል መፅሀፍም ፅፈዋል። እያወቁ የዋሹት እንጅ ትክክለኛ መረጃ እንዳልሆነ
#ሊሰመርበት ይገባል።

    ………እውነታው እንደዚህ ከሆነ እያንዳንዱ ወንድ ማግባት የሚችለው አንድ ሴት ብቻ ተብሎ ቢደነገግ ይህ ትክክለኛ ፍትህ ነው??? አንቺ ሙስሊሟ እህቴ ሆይ ሳታገቢ የቀረሽ አንቺ ብትሆኝ ደስ ይልሻል??ይቺን አለም ያለቤተሰብ ያለባል ያለ ልጅ መኖር ያስደስትሻል?? ሙስሊሟ እህቴ ራስሽ ላይ አድርገሽ ፍርድ ስጭ።ወላሂ በጣም ልብ የሚያደማው አንዳንድ ጋጠ ወጥ ሴቶች የሌላ ሰው ህጋዊ  ባልን በድብቅ ለአራት ለአምስት ቀምተው ውስጥ ለውስጥ ባል አድርገው ይዘው በህጋዊ መንገድ ሁለተኛ ሆና ለገባችው ሙስሊም ተቆርቋሪ መስለው በኢስላም ላይ የሰላ ትችትን ሲሰነዝሩ ከማመም በላይ ያማል።

☞ ሙስሊም እህቴ ሆይ ካፊሮች አላህ በሚጠላው መንገድ አንድን ወንድ ብዙ ሆነው ሲጋሩት እያየሽ አንቺ በክብር ሁለተኛ ሚስት መሆንሽን እንደነውር የሚቆጥሩት በኢስላም ላይ ጦርነት እንጂ ለአንቺ ክብር ተቆርቁረው አይምሰልሽ።
#የአንቺን_ባል_ቢያገኙ_ለአስርም_ለሀያም_ቢሆን_የሚቀራመቱት_መሆኑን_ማን_በነገረሽ?????

የሆነው ይሁን ብለሽ የማያስተማምን ወንድ ለብቻ ከማግባት ከሁለነገሩ ለሚታመነው ወንድ አራተኛ ህጋዊ ሚስት ሆነሽ ብትገቢ እመክርሻለሁ። (ኡስታዝ ግን በአሁኑ ሰአት አይደለም አራተኛ ለመሆን ለሁለተኛስ ቢሆን እውነት የሚስቱን ሀቅ በትክክል የሚወጣ ወንድ አለ?????? )

4/
#ወንድ_ልጅ_እድሜ_ልኩን_
#የመውለድ_አቅም_መኖር

   አንድ ወንድ ልጅ ግንኙነት ማድረግ እስካላቆመ ድረስ የማስረገዝ አቅምን አላህ ሰጥቶታል። በተቃራኒ ሴት ልጅ መውለድ የምትችለው በተወሰነ የእድሜ ክልል ውስጥ ብቻ ነው። ስለሆነም አንድ ወንድ ሚስቱ ማርገዝ በማትችልበት የእድሜ ክልል ውስጥ ከገባች በኃላ ተጨማሪ ልጆች የመውለድ ፍላጎት እና የማሳደግ አቅም ካለው የሚፈለገውም ዘርን ማብዛት ስለሆነ የመጀመሪያ ሚስቱን ሳይፈታ ተጨማሪ ሚስት አግብቶ ተጨማሪ ልጆችን ለመውለድ እንዲችል ከአንድ በላይ የመፈቀዱ ሸሪአዊ ጥበብ ነው።ዘርን ማብዛት በእስልምና የሚበረታታ ተግባር ነው።ለዚህም ነብዩ ሰአወ እንዲህ ብለዋል፣

{النكاح من سنتي،فمن لم يعمل بسنتي فليس مني،وتزوجوا فإني مكاثر بكم الآمم} (رواه ابن ماجه)

"ሚስት ማግባት ፈለጌ(ሱናዬ) ነው፣ በሱናዬ ያልሰራ ከእኔ አይደለም፣ተጋቡ፣የትንሳኤ ቀን ከሌሎች ነብያት በቁጥራችሁ እፎካከርባቹሀለሁ" ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል።

5
#ሴት_ልጅ_በተደጋጋሚ_በወር_አበባና_በወሊድ_ደም_ላይ_መቆየቷና_የባል_ስጋዊ_እርካታ_መፈለግ

     ወንድም ሆነ ሴት የሚያገቡበት ዋነኛ አላማ እራሳቸውን ሀራም ላይ እንዳይጥሉ እና ለጥፋት እንዳይዳረጉ ሲባል መሆኑን ለሁሉም ግልፅ ነው። ይህ አላማ በየትኛው መንገድ እንከን እንድገጥመው አይፈለግም።

#ሴት_ልጅ_በወር_አበባ_እና_በወሊድ_ደም_ላይ_እያለች_ከባሏ_ጋር_የግብረ_ስጋ_ግንኙነት_መፈፀም_አይፈቀድላትም።  በወር አበባ ሰአት ግንኙነት መፈፀም ከታላቅ ወንጀል ውስጥ የሚቆጠር ነው።በተጨማሪም በዚህ ሰአት የግብረ ስጋ ግንኙነት ለሴቷም ጤንነት ጥሩ አይደለም። በዚህ ጊዜ መላ ሰውነቷ ስለሚላላ እና ማህፀኗ ስለሚደማ ከፍተኛ የጤና ቀውስ ሊያጋጣት ይችላል። ባል ሚስቱ የወሊድ እና የወር አበባ ደሟን እስከምትጨርስ የመታገስ ልምድ ከሌለውና ስሜቱ የሚያስቸግረው ከሆነ በወር አበባ እና በወሊድ ደም ምክንያት #ወደ_ዝሙት_እንዳያመራና ችግር ላይ እንዳይወድቅ እንዲሁም ሚስቱን በወር አበባ ሰአቷ ተገናኝቶ ከባድ ወንጀል ውስጥ እንዳይዘፈቁ ሲባል አቅም ካለው ከአንድ በላይ በማግባት ከጥፋት ለመታደግ ሲባል የተፈቀደ አማራጭ ነው።. ይቀጥላል#ሼረ_ያድርጉ👇

            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam