الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.2K subscribers
393 photos
19 videos
8 files
926 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
#የተከበርከው__ወንድሜ__ሆይ! ☜

ትዳር ከማሰብህ በፊት!
ስለ ትዳር ትርጉም በደንብ እወቅ!
በትዳር ውስጥ ብዙ ነገሮች አሉ!
እናም! የሚገጥምህን ነገሮች ሁሉ አምነህ ለመቀበል + መስዓላውን + ሀላፊነትን ለመወጣት……… +… ………አስበህ መወሰን!

ከዛም!
ለትዳር የምትሆንህን ሴት ስትመርጥ ድኗን እንጂ! መልኳን አይሁን!
ምክንያቱም! በአላህ ፈቃድ በድኗ ውስጥ ሁሉንም ነገር ታገኛለህና!

ደግሞ!
አይን ቀላዋጭ ነውና ብዙ ያምረዋል!
ስለዚህ! ልብህ #ያረፈባትን ሴት ምረጥ + አግባ!

ከአገባህ ቡኋላም!
#ለውዷ ሚስትህ እዘንላት + የወደፊት የልጆችህ እናት ለምትሆነው!

በተለይ! የተከበረከው ባለ ትዳር ወንድሜ ሆይ!
ለውዷ ባለቤትህ ምን አይነት ባል መሆን እንዳለብህ ላስታውስህ ነው!
እናም!
#ምክሬን በወቀሳ እንዳታስብብኝ!

እንዲሁም! አሁን የምጠቅሳቸውን ክፍተቶች በትዳርህ ላይ ካጋጠሙህ ራስህን ፈትሸህ!
#ለማስተካከል ሌት ተቀን ደፋ ቀና ማለት አለብህ!

ከዚህ ነገር አላህ ከጠበቀህ አላህን እያመሰገንክ ለትዳርህ መፅናትና መጨነቅ አለብህ! ምክናያቱም #ትዳር ነውና!

አንተ ጋር ያለችው ሚስትህ ብትሆንም አማና መሆኗን ልታውቅ ይገባል!
እነሆ ይሄንን አማና በጥንቃቄ ልትይዝ አላህን ልትፈራ ይገባሀል!
አባቷ ልጅቱን ላንተ ሲሰጡህ ሀቋን ትጠብቃለህ + ገመናዋን ትሸፍናለህ + ጥሩ ሰው ትሆንላታለህ… ………………ብለው ነው!
የሚጠቅማትን ነገር ልታገርግላት + የሚጎዳትን ነገር በሷ ላይ ከማድረግ ልትታቀብ ይገበሃል!!

#ሚስትህ ያአንተን ሀቅ እንድታውቅ እንደምትጓጓው ሁሉ የጌታዋንም ሀቅ ልታሳውቃት + በኸይር ልትረዳት + አደጋ እንዳይደርሰባት ልትጠብቃት ይገባል!

ነብዩ መሀመድ (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ ብለዋል :- ሁላቹሁም ጠባቂዎች ናችሁ + ሁላቹሁም ከምትጠብቁት ነገር ተጠያቂዎች ናችሁ!

#ቤተሰቦቿ ጋር ሆና!
ስታገኝ የነበረውን ነገር አንተ ልትነፍጋት አይገባም!
በቻልከው አቅም ልታደርግላት ይገባል!
#ስትታመም ልታሳክማት + ሲከፋት አይዞሽ ልትላት + ስትደሰት አብረሀት ልትደሰት +………………+………… የሚያስፈልጉ ነገሮችን ልታቀርብላት + ልታደርግላት ወደ ቤትህ አስገብተሀታል እኮ!
አንተን ብላ ሁሉን ጥላ መጥታለችና እባክህ ተንከባከባት!!

#ተመልከት ! አንድ አላህን የማይፈራ ወንድ በጠዋት ከቤት ይወጣና ቁርስ + ምሳ + ራት + የሚበላው ከልጆቹ እናት ከሆነችው #ከሚስቱ ተነጥሎ ነው!

ቢያንስ እንኳ! ከነዚህ የምግብ ሰርዓቶች #በአንዱ ላይ ተገኝቶ ከልጆቹ እናት ጋር ሰብሰብ ብሎ አይመገብም! ይህ! በደል (ዙልም) አይደለምን???

#ሚስቱ ከዛ በፊት ከቤተሰቦቿ ጋር መብላት ለምዳ በአንዴ ብቻሽን ተመገቢ ብትባል ሊከብዳት ይችላል!!

ስለዚህ! ወንድሜ! አላህን ፈርተህ + ለትዳርህ ለሚስትህ ክብር + ቦታ ሰጥተህ!
#አቅሙ ካለህ ቤተሰቦቿ ጋር ትኖረው ከነበረው ኑሮ! የተሻለ ልታኖራት ይገባል!
ከሌለህ ግን! ማድረግ የምትችለውን በመልካም ንግግርን ልታናግራት + ጥሩ መልስን ልትመልስላት + ጥሩ ፍቅር ልትሰጣት + ልታዝንላት + ልትንከባከባት + ልታስደስታት………………… ይገባል!!

#ከሚስትህ ጋር ስትኖር! በመልካም መኗኗርን ለመኖር ታገል + ጣር!
#በመልካም መኗኗር የሚባለው አባባል ካልገባህ! የወደፊት የትዳርህ ዕድሜ አጭር + ዘላቂነት እንዳይኖረው እንዳይሆን ያስፈራልና ጠንቀቅ በል!!!

#ከባለቤትህ ጋር በአላህ ፈቃድ በመልካም ለመኗኗር ይረዳህ ዘንድ ልጠቁምህ:–
ዕዘንላት + ተንከባከባት + ውደዳት + አክብራት(ክብሯን ጠብቅላት) + ከልብህ መራራትን ራራላት + በተለያዩ አጋጣሚዎች ውዴታህን +ፍቅርህን ግለፅላት!
አንተ ይሄን አድርግ! አላህ ነገሩን ሁሉ ያገራልሀል!
አላህ ሁሉን አዋቂ + ባሪያውን የሚደግፍ ጌታ ነውና!!

#ሚስትህ ላንተ ሚስት በመሆኗ ብቻ እንደ #ባርያ/ህ ልታያት + ልታፈጋት + ልትጨቁናት + ልትረግጣት + ልትበድላት (ልትዞልማት)አይገባህም!
ሌላው ቢቀር ሙስሊም #እህትህ መሆኗንም አትዘንጋ!

#የሚያስፈልጋትን ሁሉ ነገር አሟልተህላት! ነገር ግን! በምላስህ #አዛ የምታደርጋት ከሆነ!
የአንተ ሁሉን ማድረግ እርሷ ዘንድ #ዜሮ + ጥቅም አልባ ሊሆን ይችላል!!!

#በል እንዳውም! አላህ ካዘነላቸው ውጭ!
አንዳንድ ወንድሞች #ከቤት አውጥቼ እንዳልወረውርሽ + ከነ ልጆችሽ ወደ ቤተሰቦችሽ እንዳልሸኝሽ + አንች የምናምን ልጂ… ………………………… እረ ስንቱን ይዘረዝራሉ! ብር አይደለም! ምላሳቸውን ነው!!

#ጥሩ ያልሆኑ + በጆሮ ለመስማት የሚሰቀጥጡ ንግግሮችን ሲናገሩ ይደመጣል!

#ሴትን ልጅ እንዲህ እየተናገረ + ሞራሏን እየጎዳው + ልቧን ባሻው ወቅት እየሰበረ +… ……………+……………#የፈለገውን ብያርግላት! እንዴት ይመለሳል?አትጠራጠር አድራጎትህ የአንድኛው እንኳ ምንም ላይመስላት ይችላል!!!

#አስብ + ተረዳ………!

#ሴት__ልጅ! ከምንም በላይ የምትፈልገው ሰላምን + ደስታን + ፍቅርን ……………ነው!
ምንም የሌለው ወንድ!
ነገር ግን! ሀቋን የሚጠብቅ + የሚንከባከባት + የሚያዝንላት + የሚራራላት… ………………ከሆነ!
ከእሱ ጋር በደስታ መኖርን ትመርጣለች!!

ከዚህ ተቃራኒ(አክስ) ደግሞ ለሀገር + ለወገን + ለዘመድ የሚበቃ ሀብት ኖሮት!
ግና ሞራሏን የሚጎዳው + መጥፎና አፀያፊ ቃል የሚናገር + ሀቋን የማይጠብቅ / የማያውቅ + የማይራራላት + …………………ከሆነ!
በሀብት ተኮፍሶ………የሰው ልጂ #ሰው መሆኗን እረስቶ/ ዘንግቶ!
እንደ #ዕቃ የሚቆጥራት ከሆነ!
ከዚህ አይነት ሰው ጋር በጭራሽ አትኖርም!!!
ምንም አይነት አንገት የሚያስደፋ ችግር ቢገጥማት ማለት ነው!!

#ወንድሜ ሆይ! በትዳርህ ግልፅነት ይኑርህ!
አንተ ከሚስትህ ሊሟሉልህ የምተፈልገውን ነገሮች እንዳለ ሁሉ!
አንተም ለእርሷ አሟልተህ መገኘት ይኖርብሀል!
ለምሳሌ :- ከሷ መጥፎ ሽታ እንዳይሸትህ እንደምትፈልገው ሁሉ!
አንተም በአንተ ላይ ያሉ መጥፎ ሽታ ሁሉ ልታስወግድ ግድ ይልሀል!
እርሷ ፈገግ እንድትልልህ እንደምትፈልገው ሁሉ! አንተም ፈገግ ልትል ግድ ይልሀል!
የሚያስፈልጉህን ነገሮች እንድታሟላልህ እንደምትፈልገው ሁሉ
አንም የእርሷን ፍላጎት ማሟላት ይኖርብሀል!!!

#ወንድሜ ሆይ! ባለቤትህ ( ሚስትህ ) በውጭ + በስራህ ቦታ የሚገጥምህን ውጣ ውረድ ላታውቅ ትችላለችና ትዕግስት አድርግ!

በመታገስህ ከአላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) በትልቅ ምንዳ ላይ ተስፋ አለህና!
የትዳር አጋርህ ላይ አንድ የምትጠላው ባህሪ ቢኖራት ሌሎች ብዙ የሚወደዱ ባህሪዎች አሏትና ታገስ!
#ሁሌም ጥቃቅን የሆነና ደካማ ጎኗን አታስብ! ይልቁንም ብዙ መልካም ስነ ምግባር አላትና ሁሌም ቢሆን መልካም ጎኗን ማስታወስ ይጠበቅብሀል!

#የሰው__ልጅ! አላህ ሲፈጥረው በባህሪው ምስጋናን ይወዳልና!
በተለይ! ለሚስትህ ምስጋና አቅርብላት!
በአላህ ፈቃድ ደካማ ጓኗን ለማስተካከል ከፈለክ! ጥሩ ጎኗን እያወደስክ ስታመሰግናት + ግልፅ ስትሆን + ስትወያይ ደካማ ጎኗን ለማስታካከል ሁሌም ትጥራለችና ሁሌም ቢሆን ሳይጋነን የአንተ አድናቆትህ አይለያት!
ባለቤትህ (ሚስትህ) ለአንተ ንግስትህ ነች!
ባለቤትህን ከማንም ጋር አታወዳድራት!!!

ወላሁ ተዓላ አዕለም#ሼር

💌:::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::👇💌

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8riR2kM4HsIJg
💍::::::::ባል እና ሚስት:::::::::💍

#ኢምራን ቢኒ ሀሰን ሚስት እጅግ በጣም ቆንጆ ናት እሱ ግን መልክ ጥፍ ነው ።

አንድ ቀን ኢምራን ለሚስቱ ሁለታችንም የጀነት ነን አላት እንዴት ባክህ አለችው ።

#ሚስቱ ምን መሰለሽ ባለቤት እኔ አላህ ሱብህነላ ወተአላ አንቺን የመሰለች ቆንጆ ሰጥቶኝ አመሰገንኩት ።

አንቺ ደግሞ እኔን ያህል መልክ ጥፍ ሰው ጋር እየኖርሽ ትግስት አደረገሽ ታዲያ አመስጋኝና ታጋሽ የጀነት አይደሉም አላት ሱብህነላህ ታጋሽና አመስጋኝ ያድርገን
…… #አሚን🤲🤲#ሼር መድረጉን አይርሱ

💍:::::::::::::ቴሌግራማችን:::::::::::::::💍

https://t.me/joinchat/AAAAAEOFD8pkvHISwAMj2w
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞::::::ትዳር በኢስላም:::::::::☜   ክፍል አስር/⑩    #ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ 3/#የሴቶች_ቁጥር_በእጅጉ_መጨመር_እና       #በአንፃሩ_የወንዶች_ቁጥር_መቀነስ   በአለም ላይ በተደረገው ጥናት እና ቆጠራ በየክፍለ ዘመኑ ያሉ ወንዶች በቁጥር እጅግ አናሳ ሲሆን የሴቶች ቁጥር በእጅጉ የጨመረ ነው።ይህም የሚሆንበት የተለያዩ ምክንያቶች ይጠቀሳሉ የተወሰኑትን ለናሙና ያክል…
☞:::ትዳር በኢስላም :::☜

 
#ክፍል
...ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ
6#አንዳንድ_ወንዶች_በተፈጥሯቸው_የፆታዊ_
ፍላጎት_ጅማዕ_አቅም_ከፍተኛ_መሆን ይህ ከፍተኛ ሸህዋ ያለው ወንድ አንዲት ሴት ብቻ ትብቃህ ቢባል ከሁለት ነገሮች አንዱ  መከሰቱ አይቀሬ ነው።በአንድ በኩል ሴቷን ከአቅም በላይ ለሆነ ጉዳት ሊያጋልጣት ሲቺል ብሎም የእድሜ ልክ ታማሚም አድርጎ ሊጥላት ይችላል።በሌላ በኩል ይህ ሰው ይቺ አንድ ሚስት የማትበቃው ከሆነ እና ሁለተኛ ሚስት ማግባት ያልተፈደቀ ከሆነ አማራጩ አንድና አንድ ነው።እሱም ዲኑና ዱኒያውን የሚያበላሽበትን ፣የሚስቱን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥልበትን አስከፊና አጥፊ የሆነውን
#ዝሙትንና_በሀራም_ መንገድ_ስሜቱን_ማርካት ምርጫው ያደርጋል። አላህ ይጠብቀን የምንሰማውና የምንታዘበውም ነገር ይህንን ያረጋገጠ ነው።ከሚስቱ ውጭ በሀራም መንገድ ሲባልግ እጅ ከፍንጅ የተያዘ ወይም ለሰራተኝነት የያዛት ሴት ላይ ሀራም የሚፈፅም ወይም በሹክሹክታ የሚታማ ሰዎች ዘንድ ቁጥብ መስሎ የሚቀርብ ማንነቱን አዋቂው አላህ ብቻ ነው።በተለይማ ሚስቱ አቅመ ደካማ ወይም ረጅም የወር አበባ የምታይ ወይም ራስ በራስ የምትወልድ ከሆነች እና ለረጅም ጊዜ በወሊድ ደም ላይ የምትቆይ ከሆነች ይህ ሰው ስሜቱ ተቋቁሞ ማለፍ ለእርሱ ከባድ ፈተና ነው። አንዳንድ ጊዜ ካላገቡት ወንዶች የበለጠ በሸህዋ የሚሰቃይ ሊሆን ይችላል።እንደነዚህ አይነቶችን ችግሮች ለመፍታት ሲባል ሁሉን አዋቂ የሆነው አላህ ለሰው ልጆች በዝሙት መንገድ ራሳቸውን አደጋ ላይ እንዳይጥሉ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን ፈቀደ።
#ሙስሊሟ_እህቴ_ሆይ„ አጋጣሚውን ተጠቅሜ ትንሽ ምክር ልለግስሽ ወደድኩ፣ የባልሽን ሁኔታ እና ማንነት መገንዘብ ብዙ ይከብድሻል ብዬ አላስብም ባልሽ በአንቺ #በቂ_እርካታ አላገኘም ብለሽ የምታስቢ ከሆነ ጉዳዩ በደንብ ሊያሳስብሽ ይገባል።ከዚህ ቀጥሎ የሚመጣው ነገር ሊያስፈራሽ ይገባል። በመጀመሪያ ባልሽን ለማርካትና ለማስደሰት ባልሽ የሚፈልጋትን ሴት ለመሆን ሞክሪ። ይህን አልፎ በቂ እርካታ የማያገኝ ከሆነ በአንቺ አነሳሽነት ከባልሽ ጋረወ በግልፅ ለመወያየት ሞክሪ ፣የሚፈልገውን ተረጂው ፣ስሜቱን እንዲደብቅሽ አታድርጊ፣የማትረጂው ከሆነ ባልሽ ከአንቺ እየራቀ ሌሎችን ማየት ይጀምራል። #በዝሙት አስቀያሚ መድረክ ታድሞ የዱኒያውንም የአኼራውንም ህይወቱን ከማበላሸቱ በፊት እንዲሁም ማንነታቸው ከማይታወቁ ሴቶች ጋር ተጨማልቆ የአንቺም የቤትሽም ህልውና አደጋ ላይ ከመውደቁ በፊት ልትነቂ ይገባል።
☞ባልሽን ስሜቱን ተረድተሽ ሁለተኛ የሚያስፈልገው ከሆነ ከአንቺ ጋር ተስማሚ፣ለአንቺም ለባልሽም አሳቢ ለዲኗ ተቆርቋሪ የሆነችውን ሴት እንዲያገባ ምከሪው ብቸኛው መፍትሄ
#የአንቺ_ቅንነት ነው። አንዳንድ ባሎች ሚስቶቻቸውን በግልፅ በስሜት እንደማያረኳቸውና ተጨማሪ ሚስተረ ማግባት እንደሚፈልጉ ሲያወያየረዋቸው በአብዛኞቹ ሚስቶች ላይ ቀናነት አይታይባቸውም።እንደውም #ሁለተኛ_የምታገባ_ከሆነ_እኔን_ፍታኝ የሚል ለመስማት የማያስደስት ንግግር ሲናገሩ ይደመጣሉ።ለእንዲህ አይነቱ ችግር መፋታት መፍትሄ ያመጣል የሚል አስተሳሰብ የለኝም፣ይቺ እህት በዚህ ምክንያት ከዚህኛው ባሏ ብትፋታ ቀጥላ ከምታገባው ባሏ ጋር ለመስማማቷ ምን ዋስትና አላት??ፍቺ ቀላል ነገር አይደለም ምን አልባት ቤተሰብ ተመስርቶ ከሆነ ያን ቤተሰብ አፍርሶ ችግር ላይ መጣል እጅግ ከባድ ሊሆን ይችላል።የሚያሳዝነው አንዳንድ ሙስሊም ተብዬ ሴቶች ከካፊር ሴቶች የወረሱት ነገር ባሎቻቸው በሀላል መንገድ ሁለተኛ ከሚያገባባቸው ከፈለጋት ሴተኛ አዳሪ ጋር እንደፈለገ ቢሆን ደስታውን አይችሉትም።ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!! ይህ በአላህ ዲን አማኝ ከሆነች ሙስሊም ሴተወ አይጠበቅም፣ይህ ለዲን ተቆርቋሪ ከሆነች ሴት ሊሰማ አይገባም። ይህ የሱሀብይ ሴቶችን ፈለግ ከምትከተል ሴት የሚጠበቅ አይደለም።
7#የመጀመሪያዋ_ሚስት_መውለድ_አለመቻልባል የመውለድ ችሎታ እያለው
ሚስቱ በተለያየ ምክንያት አለመውለዷ ቢረጋገጥና ባል ልጅ የመውለድ ፍላጎት ቢኖረው በእነዚህ ሁለቱ ባልና ሚስቶች መካከል ሊከሰት የሚችለው ነገር 2 አማራጭ ብቻ ነው።
ሀ/ ልጅ ወልዶ የሰውየው ዘሩ ወደኃላ ቅሪት እንዲኖረው የማትወልደውን ሚስቱን ፈቶ ሌላ ሚስት ማግባት
ለ/ የመጀመሪያዋን ሚስት ሳይፈታ ሌላ ሁለተኛ ሚስት አግብቶ ልጅ መውለድ፣ከእነዚህ ሁለት አማራጮች ሊወጣ አይችልም።ነገር ግን የመጀመሪያውን ተግባራዊ ቢያደርጉት በአመዛኙ የተፈታችው ሴት ባል የማግኘት እድሏ የጠበበ ነው።ምክንያቱም የተፈታች እና መውለድ የማትችል ሴት የሚፈልግ ወንድን ፈልጎ ማግኘት በጣም ከባድ ነው እና በዚህም ምክንያት ይቺ ሴት ፈታኝ የህይወት ውጣ ውረድ ሊገጥማት ይችላል።
ማገናዘብ የሚችሉት አብዛኛዎቹ ሴቶች ያለጥርጥር ሁለተኛውን አማራጭ ይከተላሉ። ምክንያቱም ከሞቀ ቤቷ፣የምትከበርበት ቀዬዋ እና ከሚያስብላትና ከሚንከባከባት ባሏ ትታ ወጥታ ያለተንከባካቢ ሜዳ ላይ መውደቅን አትፈልግም።ለእነዚህ መሰል ጥቅሞች ሲባል ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ተደነገገ።
☞ ሙስሊሟ እህቴ ሆይ፣የአላህ ተውፊቅ ሳይሆን ቀርቶ አንቺ ልጅ ለመውለድ ካልታደልሽ መውለድ የሚችለው ባልሽን አይዞህ ብለሽ ከጎኑ በመቆም ነገሮችን አመቻችተሽ በዲኗ ጠንካራ በአኽላቋ ምስጉን፣ልጆችን በተርቢያ ልታሳድግ የምትችል ሚስት እንዲያገባ እገዛ አድርጊለት፣ ይህ ታላቅ ተግባር ነው፣በዚህ ስራሽ ከሰው ጥሩ ነገር አትጠብቂ
#አላህ ግን አጅርሽን እጥፍ ድርብ አድርጎ እንደሚከፍልሽ አትጠራጠሪ።
8#ሚስቱ_ለረጅም_ጊዜ_የሚቆይ_ህመም_ታማሚ_የሆነችበት_ወን   የአላህ ውሳኔ ሆኖ
ሚስቱ ለረጅም ጊዜ የአልጋ ቁራኛ የሆነችበት ሰው ያለው አማራጭ ከሶስት አንዱ ሊሆን ይችላል።
#አንደኛ_አማራጭ፣ በእድሜ ልኩ እንደሷው ታማሚ ሆኖ ስሜቱን አፍኖ ይዞ ልጅም እንኳን ባይወልድ መካን ሆኖ ዱኒያ በቃኝ ብሎ መኖር ሊሆን ይችላል።ነገር ግን ይህ በአብዛኛው ሰው ካለመኖሩ በተጨማሪ ኢስላም እንደዚህ ያለ ጭፍን ሰው አምላኪነትን ይቃወማል።አንድ ሰው ስለታመመ የሌላው ሰው ህይወት አላህ በማይወደው መንገድ ማበላሸት የተወገዘ ነው። ምክንያቱም የሰው ልጅ ወደዚች ምድር የመጣበት ዋነኛ አላማ አላህ በብቸኝነት መገዛት ነው ፣ህይወቱም ሞቱም እርዱም ስግደቱም ለአላህ ስለሆነ።
#ሁለተኛው_አማራጭሚስቱ የረጅም ጊዜ ታማሚ ከሆነች እና ስሜቱን መቆጣጠር አቅቶት ዝሙት ዎች የመውደቅ አደጋ ከተጋረጠበት የታመመች ሚስቱን ፈቶ ሌላ ሚስት አግብቶ የግሉን ህይወት መምራት ሊሆን ይችላል። ይህን ተግባር አንዳንድ ሰዎች ሊቀበሉት ይችላሉ።ነገር ግን ሌላ አማራጭ የሚኖር ከሆነ አብራው  የኖረችው ሚስቱን አሁን ስለታመመች አሁን መፍታቱ ታላቅ ግፍ ነው።ህ
#ሶስተኛው_አማራጭ፣ የታመመች ሚስቱ በቤቷ እያለች ሌላ ሚስት ፈልጎ በማግባት ሁለቱን በክብር ማስተዳደር ሊሆን ይችላል።ይህ አማራጭ ወደር የሌለው አማራጭ ነው ምክንያቱም ባልም ሚስትንም እኩል ፍትህ ይሰጣል።ባልም ሚስትህ ስለታመመች አብረህ  ተጎሳቆል ብሎ አያስገድድም።ሚስትንም ስለታመመሽና ባልሽን መንከባከብ ስላልቻልሽ ቤቱን ለቀሽ ውጭ ብሎ አያስገድዳትም።
☞ከአንድ በላይ በሸሪዓችን ባይፈቀድ ኖሮ ከላይ ያሳለፍናቸው  አንደኛው ወይም ሁለተኛው አማራጭ ተግባራዊ መሆኑ የሚያጠራጥር አልነበረም።ከአንድ በላይ ባይፈቀድ ኖሮ የዚች ታማሚ ሴት እጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም ነገር ግን
#ሀያሉ
ጌታችን ጥበበኛ ስለሆነ ለወንዶች ከአንድ በላይ ሚስት ማግባትን ፈቀደላቸው።
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::ትዳር በኢስላም :::☜   #ክፍል ⑪ ...ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ 6#አንዳንድ_ወንዶች_በተፈጥሯቸው_የፆታዊ_ ፍላጎት_ጅማዕ_አቅም_ከፍተኛ_መሆን ይህ ከፍተኛ ሸህዋ ያለው ወንድ አንዲት ሴት ብቻ ትብቃህ ቢባል ከሁለት ነገሮች አንዱ  መከሰቱ አይቀሬ ነው።በአንድ በኩል ሴቷን ከአቅም በላይ ለሆነ ጉዳት ሊያጋልጣት ሲቺል ብሎም የእድሜ ልክ ታማሚም አድርጎ ሊጥላት ይችላል።በሌላ በኩል ይህ…
☞::::::ትዳር_በኢስላም::::☜

 
#ክፍል_አስራ_ሁለት

  
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ

9)
#ብዙ_ልጅ_የመውለድ_ፍላጎት

   አንድ ሰው ብዙ ልጅ የመውለድና ዝርያውን የማብዛት አቅምና አላማ ካለው እና የመጀመሪያ
ሚስቱ ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ልጆችን ወልዳ ያቆመች ከሆነ ሌላ ሴት አግብቶ ተጨማሪ ልጆችን ለማግኝት በማሰብ ሁለተኛ ሚስት ማግባት አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው። ምክንያቱም ነብዩ ሰአወ በዚህ ተግባር ላይ እንዲህ ሲሉ አበረታተዋል፣

"ወላድ እና ተወዳጅ የሆኑትን አግቡ የቂያም ቀን ከሌሎች ነብያቶች ጋር በብዛታችሁ እወዳደርባችሁ አለሁ።በሌላ ዘገባ ተጋቡም ተባዙም፣እኔ ሌሎችን ህዝቦች እፎካከርባቹሀለሁና።"

10 )
#ሌላ_ሀገር_ለረጅም_ጊዜ_እየቆየ
#የሚመለስና_የመጀመሪያ_ሚስቱ_አብሮ_ለመውሰድ_የማይችል_ሰው

   ይህ ሰው በሄደበት አገር ላይ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ከሆነ ሰው ነውና
#ፆታዊ_ፍላጎት ሊያስፈልገው ይችላል።በዚህ ሰአት አማራጭ በሸሪአዊ መንገድ ተስማሚ ሆነችውን ሴት መርጦ ማግባት ወይም ሀላል ባልሆነ መንገድ በዝሙት ስሜቱን ማርካት። የትኛው እንደሚሻል ማንም የሚጠፋው አይመስለኝም። #ዚናና የሀላል ኒካህ እንዴት ሊወዳደር ይችላል? በፍፁም ይህን በተመለከተ #ዚዋጅ_አልሚስያር የሚለውን ንዑስ ርእስ ማንበብ ጠቃሚ ነው።

11/
#በተለያዩ_ምክንያቶች_የመጀመሪያ_
#ሚስቱ_ጋር_ፍቅር_ከጠፋ

   ምክንያቱ በሚታወቅም ሆነ ባልታወቀ ሚስቱን የሚጠላ ከሆነ ምን አልባትም መልኳ ወይም ፀባይዋ የማይመቸው ከሆነ እና በዚህም ምክንያት ለፆታዊ ፍላጎት የማታነሳሳ እና የእሱን ስሜት የማታረካ ብሎም ሃራም ላይ ልወደቅ እችላለሁ ብሎ የሚሰጋ ከሆነ ቤት ያለችውን ሚስት ሳይፈታ ሌላ ሚስት ማግባት የሚችልበት ሁኔታ ነው።ቤት ያለችው
ሚስቱ ለተለያዩ ለእሷም ሆነ ለእርሱ ጥቅም ሲባል በኒካሁ ሊያቆያት ከፈለገ እና እሷም መፈታትን ካልፈለገች ሁለተኛ ሚስት መፈቀዱ ሸሪዓዊ ጥበቡ ነው።

12)
#ባል_በሌላቸው_ሴቶች_ላይ_የሚከሰትን
    
#ችግር_ለመታደግ_ሲባል

   በኢስላም ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት መፈቀዱ በርካታ ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ አስችሏል። ከእነዚህም ውስጥ;

ሀ/ ባሏ ለሞተባት እና በርካታ የቲሞችን ለያዘች ሴት፣ ይቺ ሴት የእሷን ልጆች ወዶ ለመጀመሪያ ሚስትነት  የሚያገባት ወንድ እጅግ በጣም አናሳ
ነው።ስለሆነም አንድ ሰው እሷን በሁለተኛ ሚስትነት ሲያገባት ሁለት ታላላቅ መልካም ስራዎችን በአንድ ጊዜ እየሰራ ነው።አንዱ ይቺ የቲም የታቀፈች እና ፈቃጅ የሌላትን ሴት በማግባት መጠለያና ምሽግ ሆኖ ያገለገላት ሲሆን በዝያዘውም የፆታዊ ፍላጎቷን በማሟላት ከሀራም እንድትርቅ ያደርጋል።ሁለተኛው የታቀፈቻቸውን የቲሞች አባታቸውን በመተካት የአባትነት ሃላፊነት ወስዶ ይንከባከባቸዋል። በዚህም ትልቅን ምንዳ ከአላህ ይለግሰዋል።
የቲም  የተንከባከበ ሰው ጀነት ውስጥ የነብዩን ሰአወ ጉርብትና እንደሚያገኝ ነብዩ ሰአወ እንዲህ ብለዋል፣

"ጀነት ውስጥ እኔ እና የቲምን የሚንከባከብ ሰው እንደዚህ ነን(ተጎራባች ነን)" በአመልካች እና በመካከለኛ ጣቶቻቸው በማመልከት በሁለቱ መካከል ለያይተው አሳዩ(ልዩነታችን የዚህን ያህል ነው እንደማለት ነው)።

ለ/ ብዙም ውበት የሌላት ሴት ወንዶች ለመጀመሪያ ሚስትነት የማይመርጧት ወይም አካል ገየዳተኛ ሆና የመጀመሪያ ሚስት ለመሆን የማትችል እና የመሳሰሉ ችግሮች ያለባቸው ሴቶች፣ ይቺን ሴት ይህ አይነት ችግር ስላለባቸው የትዳርን ህይወት ሊነፈጉ አይገባም።በዚህም የተነሳ የመጀመሪያ ሚስት መሆን ቢያቅታቸው ሁለተኛ ሚስት ሆነው የትዳርን ህይወት ማግኘት አለባቸው ሲል ኢስላም ደነገገው።
ሐ/ የአንድ ሰው ወንድሙ ወይም የቅርብ ዘመዱ ሚስትና ልጆቹን ጥሎበት ቢሞት ልጆቹን አባታቸውን ተክቶ ለመንከባከብና የወንድሙ ሚስት ያለባል የቲም ይዛ ጉዳት ላይ እንዳትወድቅ ሲባል በሁለተኛ ሚስትነት መያዝ በአመዛኙ ለሟች ልጆች እና ሚስት ትልቅ እረፍት እና ደስታን ይሰጣል።ለዚህም ሲል አላህ በጥበቡ ፈቀደው።እነዚህ እና መሰል በሴቶች ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት ሁለተኛ ሚስት መፈቀድ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው።
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_መስፈርቶች

ይቀጥላል
            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam