الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
22.2K subscribers
393 photos
19 videos
8 files
926 links
﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾

ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን

ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir
Download Telegram
الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
☞:::ትዳር በኢስላም :::☜   #ክፍል ⑪ ...ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ 6#አንዳንድ_ወንዶች_በተፈጥሯቸው_የፆታዊ_ ፍላጎት_ጅማዕ_አቅም_ከፍተኛ_መሆን ይህ ከፍተኛ ሸህዋ ያለው ወንድ አንዲት ሴት ብቻ ትብቃህ ቢባል ከሁለት ነገሮች አንዱ  መከሰቱ አይቀሬ ነው።በአንድ በኩል ሴቷን ከአቅም በላይ ለሆነ ጉዳት ሊያጋልጣት ሲቺል ብሎም የእድሜ ልክ ታማሚም አድርጎ ሊጥላት ይችላል።በሌላ በኩል ይህ…
☞::::::ትዳር_በኢስላም::::☜

 
#ክፍል_አስራ_ሁለት

  
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_የመፈቀዱ_ጥበብ

9)
#ብዙ_ልጅ_የመውለድ_ፍላጎት

   አንድ ሰው ብዙ ልጅ የመውለድና ዝርያውን የማብዛት አቅምና አላማ ካለው እና የመጀመሪያ ሚስቱ ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ልጆችን ወልዳ ያቆመች ከሆነ ሌላ ሴት አግብቶ ተጨማሪ ልጆችን ለማግኝት በማሰብ ሁለተኛ ሚስት ማግባት አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው። ምክንያቱም ነብዩ ሰአወ በዚህ ተግባር ላይ እንዲህ ሲሉ አበረታተዋል፣

"ወላድ እና ተወዳጅ የሆኑትን አግቡ የቂያም ቀን ከሌሎች ነብያቶች ጋር በብዛታችሁ እወዳደርባችሁ አለሁ።በሌላ ዘገባ ተጋቡም ተባዙም፣እኔ ሌሎችን ህዝቦች እፎካከርባቹሀለሁና።"

10 )
#ሌላ_ሀገር_ለረጅም_ጊዜ_እየቆየ
#የሚመለስና_የመጀመሪያ_ሚስቱ_አብሮ_ለመውሰድ_የማይችል_ሰው

   ይህ ሰው በሄደበት አገር ላይ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ከሆነ ሰው ነውና
#ፆታዊ_ፍላጎት ሊያስፈልገው ይችላል።በዚህ ሰአት አማራጭ በሸሪአዊ መንገድ ተስማሚ ሆነችውን ሴት መርጦ ማግባት ወይም ሀላል ባልሆነ መንገድ በዝሙት ስሜቱን ማርካት። የትኛው እንደሚሻል ማንም የሚጠፋው አይመስለኝም። #ዚናና የሀላል ኒካህ እንዴት ሊወዳደር ይችላል? በፍፁም ይህን በተመለከተ #ዚዋጅ_አልሚስያር የሚለውን ንዑስ ርእስ ማንበብ ጠቃሚ ነው።

11/
#በተለያዩ_ምክንያቶች_የመጀመሪያ_
#ሚስቱ_ጋር_ፍቅር_ከጠፋ

   ምክንያቱ በሚታወቅም ሆነ ባልታወቀ ሚስቱን የሚጠላ ከሆነ ምን አልባትም መልኳ ወይም ፀባይዋ የማይመቸው ከሆነ እና በዚህም ምክንያት ለፆታዊ ፍላጎት የማታነሳሳ እና የእሱን ስሜት የማታረካ ብሎም ሃራም ላይ ልወደቅ እችላለሁ ብሎ የሚሰጋ ከሆነ ቤት ያለችውን ሚስት ሳይፈታ ሌላ ሚስት ማግባት የሚችልበት ሁኔታ ነው።ቤት ያለችው ሚስቱ ለተለያዩ ለእሷም ሆነ ለእርሱ ጥቅም
ሲባል በኒካሁ ሊያቆያት ከፈለገ እና እሷም መፈታትን ካልፈለገች ሁለተኛ ሚስት መፈቀዱ ሸሪዓዊ ጥበቡ ነው።

12)
#ባል_በሌላቸው_ሴቶች_ላይ_የሚከሰትን
    
#ችግር_ለመታደግ_ሲባል

   በኢስላም ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት መፈቀዱ በርካታ ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ አስችሏል። ከእነዚህም ውስጥ;

ሀ/ ባሏ ለሞተባት እና በርካታ የቲሞችን ለያዘች ሴት፣ ይቺ ሴት የእሷን ልጆች ወዶ ለመጀመሪያ ሚስትነት  የሚያገባት ወንድ እጅግ በጣም አናሳ
ነው።ስለሆነም አንድ ሰው እሷን በሁለተኛ ሚስትነት ሲያገባት ሁለት ታላላቅ መልካም ስራዎችን በአንድ ጊዜ እየሰራ ነው።አንዱ ይቺ የቲም የታቀፈች እና ፈቃጅ የሌላትን ሴት በማግባት መጠለያና ምሽግ ሆኖ ያገለገላት ሲሆን በዝያዘውም የፆታዊ ፍላጎቷን በማሟላት ከሀራም እንድትርቅ ያደርጋል።ሁለተኛው የታቀፈቻቸውን የቲሞች አባታቸውን በመተካት የአባትነት ሃላፊነት ወስዶ ይንከባከባቸዋል። በዚህም ትልቅን ምንዳ ከአላህ ይለግሰዋል።
የቲም  የተንከባከበ ሰው ጀነት ውስጥ የነብዩን ሰአወ ጉርብትና እንደሚያገኝ ነብዩ ሰአወ እንዲህ ብለዋል፣

"ጀነት ውስጥ እኔ እና የቲምን የሚንከባከብ ሰው እንደዚህ ነን(ተጎራባች ነን)" በአመልካች እና በመካከለኛ ጣቶቻቸው በማመልከት በሁለቱ መካከል ለያይተው አሳዩ(ልዩነታችን የዚህን ያህል ነው እንደማለት ነው)።

ለ/ ብዙም ውበት የሌላት ሴት ወንዶች ለመጀመሪያ ሚስትነት የማይመርጧት ወይም አካል ገየዳተኛ ሆና የመጀመሪያ ሚስት ለመሆን የማትችል እና የመሳሰሉ ችግሮች ያለባቸው ሴቶች፣ ይቺን ሴት ይህ አይነት
ችግር ስላለባቸው የትዳርን ህይወት ሊነፈጉ አይገባም።በዚህም የተነሳ የመጀመሪያ ሚስት መሆን ቢያቅታቸው ሁለተኛ ሚስት ሆነው የትዳርን ህይወት ማግኘት አለባቸው ሲል ኢስላም ደነገገው።
ሐ/ የአንድ ሰው ወንድሙ ወይም የቅርብ ዘመዱ ሚስትና ልጆቹን ጥሎበት ቢሞት ልጆቹን አባታቸውን ተክቶ ለመንከባከብና የወንድሙ ሚስት ያለባል የቲም ይዛ ጉዳት ላይ እንዳትወድቅ
ሲባል በሁለተኛ ሚስትነት መያዝ በአመዛኙ ለሟች ልጆች እና ሚስት ትልቅ እረፍት እና ደስታን ይሰጣል።ለዚህም ሲል አላህ በጥበቡ ፈቀደው።እነዚህ እና መሰል በሴቶች ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት ሁለተኛ ሚስት መፈቀድ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው።
#ከአንድ_በላይ_ሚስት_መስፈርቶች

ይቀጥላል
            ቴሌግራማችን

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam