ቴዎ ፍሎስ theophilus
220 subscribers
144 photos
7 files
6 links
" ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን::
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:5)
በዚህ ቻናል የተለያዩ ትምህርቶችና፡ ስብከቶች እንዲሁም ፡ስነ መለኮታዊ ይዘት ያላቸዉ አስተምሮቶች ይቀርበታል። በተጨማሪም ቅዱሳን በinbox ለሚጠይቁት ጥያቄ መልስን የሚያገኙበት መንፈሳዊ ቻናል ነዉ።


መንፈሳዊ ጥያቄን ለመጠየቅ inbox @tsedeM
Download Telegram
አንዲት አህት አብሯት ለሚሰራ ለስራ ባልደረባዋ ወንጌል ዘወትር ያለመታከት ትመክርለታለች: ባገኘችዉም ቁጥር በጣም ስልችት እስከሚለዉ ድረስ ትሰብከዋለች: አንድ ቀን በጣም ምርር😡 አለዉና አንድ ጥያቄ ጠየቃት እንዲህም ሲል: አንቺ ግን መንግስተ ሰማይ ትገቢያለሽ? አላት እርሷም እንደምትገባ በሙሉ እርግጠኝነት መለሰችለት። እርሱም እንዲህ አላት አንቺ የምትገቢ ከሆነማ እኔ መግባት አልፈልግም አላት።😊
ወንጌልን በጥበብ በቅርባችን ላሉ ልንመሰክር ይገባል

የወንጌል ሰባኪነትን ስራህ አድርግ ትምህርት ክፍል 2 በቅርብ ቀን ይዤላችሁ እመጣለሁ ጠብቁኝ።
#ፀደቀ ነኝ
ቴዎ ፍሎስ theophilus
Photo
ከዚህ በፊት መንፈሳዊ መፅሃፍትን ነበር የምጠቁማችሁ ዛሬ ካየዋቸዉ መንፈሳዊ ፊልሞች መካከል እነዚህ ድንቅ ፊልሞች ልጠቁማችሁ ብዬ ነዉ

#ፀደቀ ነኝ
#የመፅሐፍ #ግብዣዬ

በሀገራችን ብዙ ፀሐፍቶች የተለያዩ መፅሐፍ ይፅፋሉ፣ ነገር ግን ትክክለኛ የመፅሐፍ ይዘትና አካሄዱን ተከትለዉ የሚፅፉ ፀሐፊዎች ጥቂቶች ናቸዉ። ምክንያቱም መፅሐፍ እንዴት ይፃፍል? የሚለዉን የሚጠቁሙ መፅሐፍ በሀገራችን በጣም ጥቂት ስለሆኑ። እኔ ያገኘሁት ይህ ሆህያተ ጥበብ የተሰኘዉን #የዶ/ር #ተስፍዬ #ሮበሌ መፅሐፍ ነዉ። በጣም ጥቂት ናቸዉ ያልኩት የማዉቀዉ ይህን ብቻ ቢሆንም ምናልባት ሌላ ሊኖር ይችላል ብዬ ነዉ። ያገኛችሁት ካለ ብትጠቁሙኝ ደስ ይለኛል። ጥቂት መፅሐፍቶችን ከመዉጣታቸዉ በፊት ለመገምገም አድሉን አግንቼ ነበር፣ አብዛኛዉን ትኩረት የማደርገዉ ከሀሳብ ፍሰትና ከቃላት አጠቃቀም አንፃር ነዉ። ይህን መፅሐፍ ካነበብኩ በኃላ መፅሐፍ በተለያየ አይነት መንገድ መገምገም እንዳለበት ተረዳሁ። እጅግ በጣም የጠቀመኝ መፅሐፍ ነዉ። በተለይም መፅሐፍ የመፃፍ ሀሳብ ያላችሁ ወይም የጀመራችሁ ካላችሁ ይህንን #ሆህያተ #ጥበብ የተሰኘዉን የዶ/ር ተስፍዬ ሮበሌን መፅሐፍ ብታነቡ በብዙ ትጠቀማላችሁ።

#ፀደቀ #መንፈሰ
የነገረ መለኮት መፅሐፍ ማንበብ ለምትፈልጉ ይህንን መፅሐፍ ካለበት አፈላልጋችሁና አሳዳችሁ ገዝታችሁ አንብቡት። በቀላሉ በመፅሐፍ መደብር አታገኙትም ምክንያቱም ቆየት ያለና ተፈላጊ መፅሐፍ ስለሆነ። እኔም ይህን መፅሐፍ ያገኘሁት በብዙ ድካም ነዉ።
ለአንድ መፅሐፍ መደብር ባለቤት ይህን መፅሐፍ እንዲያመጣልኝ ከአደራ ጋር አዝዤዉ ነበር። በተደጋጋሚም መጣ እንዴ? ብዬ ለመጠየቅ ወደ እዛ መፅሐፍ መደብር እሄድ ነበር። በመጨረሻ የመጣ ቀን ያልከኝ መፅሐፍ መጥቷል ሲለኝ እንደ ቶማስ ካልነካዉ አላምን ብዬ ነበር። እጄ ከገባ በኃላ ነዉ ያመንኩት።😊

ምን ለማለት ነዉ ይህንን መፅሐፍ ካገኛችሁት በፍፁም እንዳታልፉት

#ፀደቀ ነኝ
እግዚአብሔር ሆይ አንተ የማትጠረጠር መታመኛ ፥ የማታሰጋ እረፍት ፥የማትሰጋ ፅኑ ፥ የማትዝል ብርቱ ፥ የማይጨልምብህ ብርሃን፥ የማይጎድልህ ባለፀጋ ፥የማትቀደም ፊተኛ ፥የማትነፃፀር ብቸኛ ፥የማትታረም ትክክል .................... ነህ

#ፀደቀ ነኝ የእርሱ ጥገኛ
ራዕይ ምዕ12 1:17 የተጠቀሰችዉ ሴት ማናት? ይህ የበርካታ ቅዱሳን ጥያቄ ነዉ። ነገ የዚህን ምላሽ ይዤላችሁ እቀርባለሁ ጠብቁኝ።
" ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች።"
(የዮሐንስ ራእይ 12:1)

ይህቺን ሴት በተመለከተ አራት ምልከታዎች አሉ።
1 ከሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቅድስት ማርያም ናት።
2 ከክርስቲያን ሳይንስ ሜሪ ቤከር ናት።
3 ከ replacement theology ቤተክርስቲያን ናት።
4 እስራኤል ናት።
የትኛዉ ምልከታ ትክክል እንደሆነ ቃሉን በትኩረትና በጥልቀት በማጥናት ምላሽን እንሰጣለን። እስከዛዉ እናንተም በማጥናት ቆዩኝ።

#ፀደቀ ነኝ
የበርጠሜዎስ ጩኸት በሚል ርዕስ ድንቅ የሆነ ትምህርት ነገ እንጀምራለን

#ፀደቀ ነኝ
ስብከትህን በቻልከዉ አቅም አብዛኛዉን ሰዉ እንዲገባዉ አድርገህ ስበክ በሰበከዉ ስብከት አብዛኛዉን ሰዉ ግራ ከገባዉ ወይም ከነጭራሹ ካልገባዉ በመጀመሪያ አንተ በደንብ እንደገባህ አረጋግጥ

ስብከት በሚል ርዕስ የጀመርነዉን ትምህርት ክፍል 23 በቅርብ ቀን ይዤላችሁ እቀርባለሁ
#ፀደቀ ነኝ
እምነትን መጠበቅ ክፍል 2 ዛሬ ማታ 2:00 ይለቀቃል
በብዙ የምትጠቀሙበት ትምህርት ነዉ ጠብቁኝ

#ፀደቀ #ነኝ
ዛሬ ማታ 2:00 #እምነትን #መጠበቅ ክፍል 4 ይለቀቃል በብዙ የምትጠቀሙበት ትምህርት ነዉ
#ፀደቀ ነኝ