ቴዎፍሎስ theophilus
215 subscribers
147 photos
7 files
7 links
" ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን::
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:5)
በዚህ ቻናል የተለያዩ ትምህርቶችና፡ ስብከቶች እንዲሁም ፡ስነ መለኮታዊ ይዘት ያላቸዉ አስተምሮቶች ይቀርበታል። በተጨማሪም ቅዱሳን በinbox ለሚጠይቁት ጥያቄ መልስን የሚያገኙበት መንፈሳዊ ቻናል ነዉ።


መንፈሳዊ ጥያቄን ለመጠየቅ inbox @tsedeM
Download Telegram
በመስቀል በዓል ከተሰቀለው ይልቅ የተሰቀለበት እንጨትና፣ያንን የተሰቀለበትን እንጨት አፈላልጋ አገኘች የተባለችዉ፣ ንግስት እሌኒ ቦታ አላቸዉ ደግሞም ዋና መልእክት ናቸዉ።የተሰቀለዉ የተረሳበት የመስቀል በዓል፣በበዓሉ የተሰቀለዉ ማዕከል ስላልሆነ መስቀልን እያከበሩ የተሰቀለዉን ያሳዝኑታል።

#ከፀደቀ #መንፈሰ
ጌታ ኢየሱስ እናንተ ደካሞች ሸክም ሁሉ የከበደባችሁ ሸክማችሁን አራግፍችሁ ወደ እኔ ኑ፣ ቢለን ኖሮ ምን ይዉጠን ነበር? ማን ወደ እርሱ ይሄድ ነበር? የትስ እናራግፍ ነበር? ሸክማችንን አራግፈን መምጣት እንደማንችል ስለሚያዉቅ ከነሸክማችሁ ኑ፣ብሎ ሸክማችንን አራግፎልን እረፍትን ሰጠን። ቀሊል የሆነዉን ደግሞ የእርሱን ቀንበር በፍቃዳችን ተሸከምን። ቤተክርስቲያን በምድር የክርስቶስ ወኪል ነች። ሰዎች፣ከነድማቸዉ፥ከነሀጢአታቸዉ፥
እንዲመጡ መጋበዝ፣ከመጡ በኃላ ደግሞ እጆቿን ዘርግታ መቀበል መቻል አለባት።የቤተክርስቲያን ሀላፊት ከነሸክሙ የመጣን ሰዉ ሸክሙን እንዲያራግፍ አድርጋዉ ቀሊል የሆነዉን የክርስቶስን ቀንበር በፍቃዱ እንዲሸከም ማድረግ ማስቻል ነዉ። ሀጢአተኛዉ ፥ደካማዉ፣ ወደ ቤተክርስቲያን መጥቶ በሃጢሃቱ ፀንቶ የሚኖርና ሸክሙ ተስማምቶት የሚቀጥል ከሆነ ያቺ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ ቤተክርስቲያን መሆኗን እጠራጠራለሁ።
#ከፀደቀ #መንፈሰ
#ሚኒሊክ #አስፍዉ
" በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 5:17)
ሰሞኑን መንገድ ላይ፣አግኝታችሁኝ፣ ምናልባት ሰላም ሳልላችሁ ካለፍኩ፣ ኤርፎን አድርጌ #በአስቴር #አበበ ድንቅ #ዝማሬ ተመስጬ ሊሆን ስለሚችል እንዳትቀየሙኝ በቅድሚያ ላሳስባችሁ እወዳለሁ😊

ማን ነበር 2017 ዓመት የበረከት ዓመታችን ነዉ ያለዉ።እዉነት ነዉ ይኸዉ 12 ስንጠብቅ ከጠበቅነዉ በላይ 26 ሆኖ ድንቅ የሆነ በረከትን ገና በመስከረሙ ተቀበልን።

ድንቅ የሆነ የዝማሬ አልበም ነዉ ተባረኩበት
የእምነት ጥንካሬዉ በሚታመንበት ይወስናል። በእግዚአብሔር ላይ ባለኝ እምነት እርግጠኛ ሆኜ ስናገር የእኔ እምነት ጠንካራ ሆኖ ሳይሆን ያመንኩት አምላክ እርሱ ፍፁም ታማኝ ስለሆነ ነዉ።

#ከፀደቀ #መንፈሰ
የያዝነዉ #ወንጌል በእዉነት እንደሚለዉጥ ከማለት ባለፈ #real ከገባን፣ሰዎች በየትኛዉም አይነት ሸክም ዉስጥ ሆነዉ ቢመጡ ስለሚለዉጣቸዉ #ወንጌል እናስተምራቸዋለን እንጂ በእነርሱ ላይ ፣ለመፍረድ አንጣደፍም።
በምናየዉ ነገር ብቻ አይተን የምናገል ከሆነ ይህ ከወንጌል አቅም በላይ ነዉ እያለን ነዉ። የምናገለግለዉ #ጌታችን ኢየሱስ ዛሬም ደካሞችን በምድር ላይ በወከላት በቤተክርስቲያን በኩል ጥሪ ፣ያቀርባል ጥሪዉ ደግሞ እናንተ #ደካሞች ሸክም #ሁሉ የከበደበባችሁ ወደ እኔ #ኑ የሚል ነዉ። የእርሱ ሎሌዎች ከሆንን የጌታችንን መልእክት ሳንቀንስ እናስተጋባ፡ ምክንያቱም የሚጠራዉ በእኛ ተማምኖ ሳይሆን እራሱን ታምኖ ስለሆነ።
#ከፀደቀ መንፈሰ
" ስለ እናንተ እንደ ተሰጠኝ እንደ እግዚአብሔር መጋቢነት፥ የእግዚአብሔርን ቃል ፈጽሜ እንድሰብክ እኔ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ሆንሁ።"
(ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:25)
ማርቲን ሉተር የተሃድሶን እንቅስቃሴን በሚጀምርበት ወቅት፣አንድ ሰዉ እንዲህ አለዉ ዓለም ሁሉ እኮ እያወገዘህ እኮ ነዉ ሲለዉ፣ ማርቲን ሉተር እንዲህ አለ እኔ ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር ሆኜ ዓለምን አዉግዣታለዉ አለ።
Happy Reformation Day!

#Grace Alone

#Faith Alone

#Christ Alone

#Gloy of God Alone


#scripture Alone
ማርቲን ሉተር ማነዉ?
ክፍል 1
ማስተካከያ 1805 ሳይሆን በ1505 ነዉ
ማርቲን ሉተር ማነዉ ክፍል 2 ከፀደቀ
19 01 2013
ማርቲን ሉተር ማነዉ? ክፍል 3
ይህ በተገለጠልኝ ጊዜ በፍፁም ዳግም እንደተወለድኩ ተሰማኝ የገነት በሮች ወለል ብለዉ ተከፍተዉ እኔ ገባዉ በዚየን ወቅት ስለ ብሉይና አዲስ ኪዳን መፅሐፍ የነበረኝ ግንዛቤ አቅጣጫ ተለወጠ (ማርቲን ሉተር)
28 01 2013
ማርቲን ሉተር ማነዉ የመጨረሻዉ ክፍል 4
ቀን 04 02 2013
ከፀደቀ
ያለ እምነት ከማጋፍት በእምነት መዳሰስ ይሻላል

#ከፀደቀ መንፈሰ
የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሰረቷ የነበረዉ መፅሐፍ ቅዱሳዊ በሆነ አስተምህሮና አስተሳሰብ ነበር፣ ከጊዜ ሂደት በኃላ ግን ከመፅሐፍ ቅዱስ ሀሳብ በጣም እየራቁ በመጡ ቁጥር ፣መፅሐፍ ቅዱስን የሚያስተምረዉን ሉተር ይሄ መፅሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም ብለዉ አወገዙት። ተወዳጆች ከቃሉ በራቅን ቁጥር መፅሐፍ ቅዱስን ብቻ የሚያስተምርን ሰዉ፣ሀሰተኛ ነዉ ማለታችን አይቀርምና በጊዜ #ከቃሉ ጋር እንቆራኝ።

#ከፀደቀ መንፈሰ
በፅድቅህ ልክ ብታርቀን ምን ያህል ከፊትህ እንርቅ ነበር? አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ በምህረትህ ብዛት ስላቀረብከን እናመሰግናለን።