ቴዎ ፍሎስ theophilus
220 subscribers
144 photos
7 files
6 links
" ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን::
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:5)
በዚህ ቻናል የተለያዩ ትምህርቶችና፡ ስብከቶች እንዲሁም ፡ስነ መለኮታዊ ይዘት ያላቸዉ አስተምሮቶች ይቀርበታል። በተጨማሪም ቅዱሳን በinbox ለሚጠይቁት ጥያቄ መልስን የሚያገኙበት መንፈሳዊ ቻናል ነዉ።


መንፈሳዊ ጥያቄን ለመጠየቅ inbox @tsedeM
Download Telegram
ሊያስታብይ የሚችል አንድም ነገር ሳይኖርህ ትሁት ነኝ ብትለኝ ትሁት ስለመሆንክ እርግጠኛ አይደለሁም። ምክንያቱም የአንዳንድ ሰዉ ትህትና እስኪያገኝ ድረስ ስለሆነ። ካገኘ በኃላ ትዕቢተኞች ራሱ እንዴት ያለ ትዕቢተኛ ነዉ የሚሉት ትዕቢተኛ የሆነ ሰዉ አለ ቀድሞ ትሁት የነበረ። ሊያስታብይ የሚችሉ ነገሮች አሉ ለምሳሌ ገንዘብ፥እዉቀት፥ዝና..እነዚህ ሁሉም ባይኖሩህ እንኳን አንዱ ነገር ኖሮህ ባለህና በያዝከዉ ነገር ትሁት ስትሆን ነዉ እዉነተኛ ትህትና።
#ከፀደቀ #መንፈሰ
እንዳንድ ሰዎች አንዳንድ ቦታ ምናልባት ላያስፈልጉን ይችላሉ እግዚአብሔር ግን ሁል ጊዜ ያስፈልገናል ብንበረታ መበርቻ አቅማችን ብንወድቅ መነሻ ድጋፍችን ነዉና።

#ከፀደቀ #መንፈሰ
ርዕስ #እምነትን #መጠበቅ ክፍል 4

#ንግግርህ #ይገልጥሃል
እምነትህ በንግግርህ ይንፀባረቅ

#ከፀደቀ #መንፈሰ
ርዕስ #sexual #purity ክፍል 3

የ pornography #ሱስ የሚፈጥረዉ #ችግርና #መፍትሄው

#ከፀደቀ #መንፈሰ
ቀን 21/03/2016
እንደ አይሁድ ባህል ከዋነኛዉ ቀጥሎ መናኛ ማቅረብ የተለመደ ነዉ። ጌታ ኢየሱስ ሆይ ካንተ  መናኛ መጠበቅ ግን አንተን አለማወቅ ነዉ።

#ከፀደቀ #መንፈሰ
ስለወደደን ወደድነዉ እንጂ መዉደዳችንን አይቶ አይደለም የወደደን አስቀድሞ ነዉ እርሱ የወደደን
#ከፀደቀ #መንፈሰ
ርዕስ #በእግዚአብሔር #ፊት #ጻዲቅ ክፍል 1

የእግዚአብሔር ፅድቅ ክርስቶስ አጸደቀን

#ከፀደቀ #መንፈሰ
ቀን 24_06_2016
ርዕስ #በእግዚአብሔር #ፊት #ጻዲቅ ክፍል 2

የእኛ ፅድቅ በእግዚአብሔር ፊት
#ለመፅደቅ #ፅድቅን #ያዋጣ #የለም
#ከፀደቀ #መንፈሰ
ቀን 28_06_2016
በስራዬ ነዉ መፅደቅ የምፈልገዉ የሚሉ ሰዎች እግዚአብሔር የሚፈልገዉን የፅድቅ ልክ ቢያዉቁ ያለ ማንገራገር የእግዚአብሔር ፅድቅ የሆነዉን ክርስቶስን ይቀበሉ ነበር።
#ከፀደቀ #መንፈሰ
አራት መነኩሴዎች ከሚኖሩበት ሀገር ወደ ሌላ ሀገር ለመሄድ ጉዞን ይጀምራሉ፣ አርፍደዉ ስለተነሱ የፈለጉበት ቦታ በጊዜ ስላልደረሱ፣ እዛዉ በደረሱበት ቦታ አረፍ ብለዉ ለመሄድ ይወስናሉ፡ ሰዓቱም ስለመሸ ምሽቱንም ባሉበት ቦታ ድንኳን ይዘዉ ስለነበር ድንኳናቸዉ ዘረጉ። ከመተኛታቸዉ በፊት ለመፀለይ ይስማማሉ ከመፀለያችን በፊት አንድ ህግ እናዉጣ አለ አንደኛው መነኩሴ ይህም ህግ ሁላችንም የምንፀልየዉ በዉስጣችን ነዉ ምን አይነት ነገር ቢፈጠር ማዉራት አይፈቀድም አለ፣ የቀሩት ሁሉም በወጣዉ ህግ ተስማምተዉ በዉስጣቸዉ ድምፅ ሳያሰሙ መፀለይ ይጀምራሉ። በጣም ስለጨለመ በድንኳናቸዉ ዉስጥ ሻማ ለኩሰዉ ነበር የሚፀልዮት። ትንሽ እንደቆዮም ከዉጪ በመጣ ንፍስ እየበራ የነበረዉ ሻማ ያጠፍዋዉ።
አንደኛዉ መነኩሴ ከመካከላቸዉ ወይኔ ሻማዉ እኮ ጠፍ አለ፣ ሁለኛዉ መነኩሴ ቀበል አድርጎ በፀጥታ ነዉ መፀለይ ያለብን አለ፣ሶስተኛዉ ደግሞ እባካችሁ ዝም እንበል ያወጣነዉን ህግ እየጣሳችሁ እኮ ነዉ አለ፣ አራተኛዉ መነኩሴ በመጀመሪያ ፈገግ ብሎ እኔ ብቻ ነኝ ያላወራሁት አለ።
ይህንን ታሪክ ያነሳሁት አንድ መልእክት ለማስተላለፍ ነዉ።
በዚህን ጊዜ የአገልጋዮችን ስህተት ወደ social media ይዞ መጥቶ መተቸት የተለመደ ነዉ፣ በአስተምህሮ ወይም በልምምድ ስህተት ዉስጥ ያለን ሰዉ እንድንቃመዉ መፅሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ያስተምረናል 👉ፊል 3:2 ማቴ 16፡12 ገላ 5:5_11_12 1ዮሐ 2:22...... መፅሐፍ ቅዱስ ስህተትን እንድንቃወም ብቻ ሳይሆን የሚያስተምረን ስህተትን ስንቃወም አስቀድመን ማወቅ ስላለብን ነገር እንደ መመሪያ ያስተምረናል። ነገሩ ስህተት መሆኑን ብቻ ማወቅ ሳይሆን ያንን ስህተት የምናቀናበትን መንገድ አስቀድመን ማወቅ መቻል አለብን። ምክንያቱም በአሁን ሰዓት ስህተት የሆነን ነገር ለመቃወም በተሳሳተ መንገድ እየተቃወሙ ያሉ እየበዙ ስለመጡ። በቤተክርስቲያን ዉስጥ በአስተምህሮም ሆነ በልምምድ በስህተት መንገድ ያሉ አገልጋዮች ከመፅሐፍ ቅዱስ መምሪያ ዉጪ ስለሆኑ ነዉ። ከመመሪያው ዉጪ ሆነዉ የተሳሳቱትን የምንመልሳቸዉ በመመሪያዉ ነዉ። ስለዚህ የሳቱትን ለመመለስ የመፅሐፍ ቅዱስ መመሪያን ልንከተል ይገባል። ለእኛ ሲባል የሚሻር የመፅሐፍ ቅዱስ መመሪያም ሆነ ህግ የለም። ለምሳሌ መፅሐፍ ቅዱስ " ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር" ይላል(1ኛ ጴጥ4:11) ይህ ለሁሉም ሰዉ የሚሰራ መመሪያ ነዉ። የተሳሳተን ሰዉ በመሳደብ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል በመናገር ነዉ ልናቀናዉ የምንችለዉ። እኛ ስንሳደብ የእኛ ስድብ ልክ ስለማይሆን።" ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን።" ይላል መፅሐፍ ቅዱስ።እግዚአብሔር የአንደበታችንን ቃል ብቻ ሳይሆን የልባችንን motive (ምክንያት) የሚያይ አምላክ ነዉ የተሳሳተን ሰዉ ስንቃወም እርሱን ለመመለስና ገንዘብ ለማድረግ እንዲሁም በእዛ ስህተት መንገድ የሚሄዱትን ምዕመናንን ለማቅናት እንጂ የተሳሳቱትን ፈፅሞ ለመስበርና ለማጥፍት መሆን የለበትም " እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። የወደቁ አይነሡምን? የሳተስ አይመለስምን? "( ኤር 8:4) ይላል የሳቱት ቢመለሱ እኛ ለእነርሱ የሚመለስ ልብ እንዳለን እናረጋግጥ። ተሳስታችኋል የተባሉ ከስህተታቸዉ የተመለሱ እዉነተኛዉን አስተምህሮ የሚያስተምራቸዉ አጥተዉ ግራ በመጋባት ዉስጥ ያሉ በርካታ ሰዎች አሉ።😔 ስህተትን መናገር ብቻ ሳይሆን ከስህተቱ ለተመለሰ ሰዉ በፍቅር የሚያቅፍ እጅ ሊኖረን ይገባል።ለዚህ ደግሞ እዉነትን በፍቅር ልንይዘዉ ይገባል " ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን"(ኤፌ4:15) ስህተቱን ለመናገር እንደረበታነዉ ሁሉ እዉነተኛዉን አስተምህሮ ለማስተማር መትጋት አለብን። " እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው። "(ዮሐ8:32) በስህተት የተያዘን ሰዉ ነፃ የምናወጣዉ በእዉነት ነዉ። 1+1 ሶስት አይደለም ፥4ትም አይደለም፥10ም አይደለም እያልክ ያልሆነዉን ከምትነግረኝ የሆነዉን 2 ብትነግረኝ ያልሆነዉን እኔ በቀላሉ እለያለሁ። አማኞች ስህተት የሆነዉ ነገር እንዲለዩ እዉነተኛዉን የእግዚአብሔርን ቃል እናስተምራቸዉ።
ይህ ከላይ የገለፅኩላችሁ ስህተትን ስንቃወም መፅሐፍ ቅዱስ ከሚሰጠን መመሪያዎች በጥቂቱ ናቸዉ።
መጀመሪያ ወዳነሳሁላችሁ ታሪክ ልመላሳችሁ፣ አራቱም መነኩሴዎች ያወጡትን ህግ ሽረዋል። አራቱም የሻሩት ልክ በሚመስል ምክንያት ነዉ፣ አንደኛዉ የሻማ መጥፍቱን እንዲያዉቁ ተናገረ ፥ሁለተኛው ደግሞ የወጣዉን ህግ ለተናገረዉ ሰዉ ለማስታወስ ተናገረ፥ሶስተኛዉ ደግሞ ሁለቱም ፀጥ እንዲሉ እንዳይናገሩ ተናገራቸዉ፥አራተኛዉ በስተመጨረሻ እኔ ብቻ አልተናገርኩም ብሎ አለመናገሩን ተናገረና ህጉን አፈረሰ።

ተወዳጆች የእግዚአብሔር ቃል የሁላችንም መመሪያ ነዉ። አንድ አገልጋይ ከተሳሳተ ልንመልሰዉ የሚገባ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንጂ አሳማኝ በሚመስል ምክንያት ግን ስህተት በሆነ መንገድ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ህግ በመሻር መሆን የለበትም።
ጌታ ኢየሱስ ታልፎ በሚሰጥበት ምሽት
ይሁዳ ጭፍሮችንና ከካህናት አለቆች ከፈሪሳውያንም ከሎሌዎችን ጋር በችቦና በፋና በጋሻ ጦር ሆኖ ወደ ኢየሱስ መጣ
ኢየሱስም የሚመጣበትን ሁሉ አውቆ ወጣና ማንን ትፈልጋላችሁ አላቸው። የናዝሬቱን ኢየሱስን ብለው መለሱለት። ኢየሱስ። እኔ ነኝ አላቸው። አሳልፎ የሰጠውም ይሁዳ ደግሞ ከእነርሱ ጋር ቆሞ ነበር።እንግዲህ። እኔ ነኝ ባላቸው ጊዜ ወደ ኋላ አፈግፍገው በምድር ወደቁ።ደግሞም። ማንን ትፈልጋላችሁ? ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም። የናዝሬቱን ኢየሱስን አሉት።
ኢየሱስ መልሶ። እኔ ነኝ አልኋችሁ፤ እንግዲህ እኔን ትፈልጉ እንደ ሆናችሁ እነዚህ ይሂዱ ተዉአቸው አለ፤ይህም። ከእነዚህ ከሰጠኸኝ አንዱን ስንኳ አላጠፋሁም ያለው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። ስምዖን ጴጥሮስም ሰይፍ ስለ ነበረው መዘዘው፥ የሊቀ ካህናቱንም ባርያ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቈረጠ፤ የባርያውም ስም ማልኮስ ነበረ።ኢየሱስም ጴጥሮስን። ሰይፍህን ወደ ሰገባው ክተተው፤ አብ የሰጠኝን ጽዋ አልጠጣትምን? አለው።
(ዮሐ 18_1_11) ጴጥሮስ የማልኮስን ጆሮ ለመቁረጥ በቂ ምክንያት ነዉ ያለዉ። ግን ልክ አልለበረም። ኢየሱስ ጎበዝ ብሎ አላበረታታዉም ወዲያዉኑ ሰይፍህን ወደ ሰገባዉ ክተት ነዉ ያለዉ። ተወዳጆች ከእኛ ልክ ካልሆነ አሳማኝ ከሚመስል ምክንያት ይልቅ የእግዚአብሔር ቃል መመሪያ ሁሌም ልክ ነዉ።
ክፍል 2 ይቀጥላል ..

#ከፀደቀ #መንፈሰ