#ትምህርተ_ንስሐ (በአቡነ ሺኖዳ)
#ክፍል_2
#የንስሐ_አፈፃፀም_3_ደረጃዎች
#ሀ የንስሀ የመጀመሪያ ደረጃ ኃጢአትን መተው ብቻ ሳይሆን ንስሐ ለመግባት ማሰብ ወይም መፈለግ ነው። ይህ ኃጢአትን ከመተው የሚቀድም ነው ። ሰዎች ንስሐ ለመግባት ባልፈለጉና ባላሰቡ መጠን በኃጢአት እየተደሰቱ ኃጢአትን እየሰሩ ይኖራሉ። በእነርሱ አመለካከትም የያዙት የኃጢአት ኑሮአቸው መልካም ስለሚመስላቸው አይለወጡም ። ስለዚህ ንስሐ ለመግባት ማሰብና መፈለግ የንስሐ የመጀመሪያ ደረጃ ነው ።
#ለ ሁለተኛው ደረጃ ፦ በንስሐ ሂደት ሁለተኛው ደረጃ ኃጢአትን መተው ነው ። ኃጢአትን መተው ሲባልም ኃጢአትን ከኅሊናና ከልቡና ጨርሶ በፍፁም ማጥፋት ነው ። ይህም ኃጢአትን ከማሰብ መለየት ማለት ነው ። ፀፀቱ ወይም ንስሐው ልቡናው ከኃጢአት እስኪነፃ ድረስ መሆን አለበት ። ከዚህ አንፃር ኃጢአትን መተው የንስሐ ሁለተኛው ደረጃ ነው።
#ሐ ሶስተኛው ደረጃ ፦ የንስሐ የመጨረሻ ደረጃ ኃጢአትን መጥላት ነው ። ይህም ኃጢአትን በፍፁም ልብ መጥላት ፣ አለማሰብና ባሕርይን ለኃጢአት አለማስገዛት ማለት ነው ። ይህ ደግሞ የፍፁምነት ደረጃ ነው ። ሰው ኃጢአትን ከልቡ ከአስወገደና ፍፁም ካላሰባት ከፍጹምነት ደረጃ ደርሷልና ንፁህ ነው ይባላል። ሰው በመንፈሳዊ ሕይወቱ ውስጥ ከፍተኛውንና ዋነኛውን ኃጢአት ለመተው የሚችለው በክርስትና ሕይወቱ የዕለት ተዕለት ብስለት የሚገለጡለትን ረቂቃን ኃጢአቶች በመተው ነው።
ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት
👉 ኢዮአታም
ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret

#ክፍል_3
#የንስሐ_መሰናክሎች (እንቅፋቶች)
ሰይጣን ከሚዋጋቸው የድኀነት መንገዶች ውስጥ ንስሐን የሚያክል የለም። ምክንያቱም ንስሐ ጠላት ዲያቢሎስ የክርስቲያኖች ሕይወት ለማጥፋት የገነባውን የኃጢአት ሕንፃ ሁሉ በእግዚአብሔር ቸርነት እንዳልነበር በማድረግ ስለሚያፈርስበት ነው ። ከዚህ የተነሳ የሰው ልጅ ንስሐ እንዳይገባ ፣ ቢገባም ቶሎ እንዳይሆን የተቻለውን ከማድረግ ፈጽሞ አያርፍም ። ከሚጠቀማቸው መሰናክሎች መካከል የሚከተሉት ይገኛሉ ።
#ሀ እንቅፋት መፍጠር ፦ እነዚህ ድንገተኛ ፈተናዎች ወይም አጋጣሚዎች ሊሆኑ ይችላሉ ። እነዚህ አጋጣሚዎች ወይም ፈተናዎች ተነሳሒው በድፍረት ወደ ንስሐ እንዳይመጣና ከኃጢአቱ እንዳይመለስ ተፅእኖ የሚያሳድሩ ናቸው ።
#ለ ኃጢአተኛው ራሱን ከእርሱ የቀለጠ ኃጢአት ሠሩ ከሚላቸው ጋር በማነፃፀር የተሻለ እንደሆነ እንዲገምትና ንስሐም እንደማያስፈልገው ራሱን ማሳመን ፤ #ቅድስና ግን ከኃጢአተኛ ሕይወት ሕይወት ጋር ሊነፃፀር አይገባም ። ኖኀ በብዙ ኃጢአተኞች መካከል ቅዱስ እንደነበር ዮሴፍ፣ ሎጥና ሙሴም በኃጢአተኞች መካከል ቅዱሳን እንደነበሩ እኛም መቀደስ አለብን እንጂ እራሳችንን ማነፃፀር የለብንም ።
#ሐ ከሥጋ ድካም የተነሳ በአካባቢ ተፅእኖ መመራት ፦ ተነሳሒው ሰው በዓለም የማይታለል ጽኑ አቋም እንዲኖረው ያስፈልጋል ። ቅዱስ ጳውሎስ "ይህን ዓለም አትምሰሉ " እንዳለ ። (ሮሜ 12÷2) #ዓሣ ትንሽ ሲሆን ማዕበል በሚያናውጠው ባሕር ውስጥ ይዋኛል ። ክርስቲያንም እንዲህ ሊሆን ይገባዋል ። ደካማ ስጋን ቢለብስም ፈተናውን ተቋቁሞ ለንስሐ መብቃትና በመንፈሳዊ ሕይወት መኖር ይገባዋል ።
#መ መዘግየት ፦ ዲያቢሎስ ንስሐ እንዳንገባ የሚዋጋን በቀጥታ አይደለም ። ነገር ግን የተለያዩ ስውር ፈተናዎችን እየደቀነ እንዳንገባ ያዘገየናል። #መዘግየት ከሚያስከትለው አደጋ አንዱ ለንስሐ የተዘጋጀውን ልቡና መለወጥና ለንስሐ ያለውን ዕድል ማጥፋት ነው ።
#ሠ ተስፋ መቁረጥ ፦ ይህ ንስሐ የማይቻልና ሊደረግ የማይሞከር እንደሆነ አድርጎ ማሰብ ነው። ሰይጣን በኃጢአት ከመውደቃችን በፊት የእግዚአብሔርን ቸርነትና ይቅርታ በማሰብ እንድንሰራ ያደርገናል ፤ ከሰራነው ቡሃላ ደሞ የእግዚአብሔርን ፍርድና ጨካኝ እንደሆነ ያሳስበናል ። ንስሐ እንዳንገባም ተስፋ ያስቆርጠናል ።
💚 @zekidanemeheret 💚
💛 @zekidanemeheret 💛
❤️ @zekidanemeheret ❤️

#ትምህርተ_ንስሐ (በአቡነ ሺኖዳ )
#ክፍል_3
#ለንስሐ_የሚያበረታቱ_ሁኔታዎች
#1 ማንነትህን ካወቅህ ከኀጢአት በላይ ነህ ። ሰው እግዚአብሔር ምን ያህል እንዳከበረው ያወቀ እንደሆነ ራሱን በኃጢአት አያዋርድም ።ሰው ማነው ? አንተ አንቺ ማነህ ?
#ሀ አንተ እግዚአብሔር የሕይወት እስትንፋስ ሰጥቶ የፈጠረህ ፍጥረት ነህ ። አንተ አፈር ብቻ አይደለህም ። ከ4ቱ ባህርያተ ስጋ ከ3ቱ ባህርያተ ነፍስ የተፈጠርክ ሕያው ሰው ነህ ። ሕያው በመሆንህም ለጊዜው በምድር የምትኖር ብትሆንም በክብር ወደ አምላክህ በመሄድ ሰማያዊ ሕይወትን ለመኖር የተፈጠርክ መሆንህን አስብ ። ስለዚህም በመንፈስ ኑር ። ከዓለም ከስጋዊ ስራም ተለይ ።
#ለ አንተ በመልኩና በምሳሌው የተፈጠርክ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ። በእግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠርክ ከሆንክ እንዴት ኃጢአትን ትሰራለህ ? በኃጢአት ወድቀህስ እንዴት የእግዚአብሔር ምሳሌ ልትባል ትችላለህ ? ስለዚህ ነገር ቅዱስ አትናቴዎስ "ሰው በበደለ ጊዜ የእግዚአብሔር ምሳሌ መሆኑ ይቀራል ። ቅድስናውን ያጣልና " በማለት ተናግሯል። ጌታችንም ሰው የሆነው ወደነበርንበት የቅድስና ሕይወት ሊመልሰን ነው ።የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ያወቀ ሰው ኃጢአት አይሰራም ፤ ኃጢአትን ባለመስራትም አባቱን የሚመስል ይሆናልና ። አባቱን የማይመስል ልጅም ልጅ አይደለም። ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጅነትህን ከኀጢአት በመለየት ልታረጋግጥ ይገባሀል። በዚህም አባትህን ትመስላለህና ። "የአብርሃም ልጆች ብትሆኑ የአብርሃምን ሥራ ባደረጋችሁ ነበር " እንደ ተባለ። የእግዚአብሔር ልጆች የኖሩትን የተቀደሰ ሕይወት ካልኖርን የእግዚአብሔር ልጆች አይደለንም ። በመሆኑም በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ ልንል አንችልም ። "... ፃድቅ እንደሆነ ካወቃችሁ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከእርሱ እንደተወለደ ዕወቁ " (1ኛ ዮሐ 2÷29)
#ሐ አንተ የእግዚአብሔር ማደሪያ የመንፈስቅዱስ ቤተ መቅደስ ነህ ። "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ " (ምሳ 20÷26) ይህ አባባል የሰው ልብ የእግዚአብሔር ማደሪያ መሆኑን ያመለክታል። ቅዱስ ጳውሎስም " የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ እንደሆናችሁ ፡ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን ? ማንም የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እሱን ያፈርሰዋል የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ቅዱስ ነውና #ያውም-እናንተ ናችሁ። "(1ቆሮ 3÷16) ። #ዲያቢሎስ_በኃጢአት ሊፈትንህ ወደ አንተ በመጣ ጊዜ
✞ እኔ ለአንተ አይደለሁምና ከእኔ ወግድ በለው
✞ እኔ የእግዚአብሔር መቅደስና የመንፈስቅዱስ ማደሪያ ነኝ በለው
✞ እኔ የሥላሴ ባሪያ ነኝ በለው
✞ እኔ በእኔ ያድር ዘንድና ወደ ልቡናዬ ይገባ ዘንድ እግዚአብሔር ልቤን የሚያንኳኳ ነኝ በለው
✞ እኔ አብና ወልድ ማደሪያቸው ሊያደርጉኝ ወደ እኔ የሚመጡ ሰው ነኝ በለው

#ክፍል_4
#ኃጢአት_ምንድነው ?
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን መልእክቱ " ኃጢአት ስታድግ ሞትን ትወልዳለች " ካለ ቡሃላ በሮሜ መልእክቱ ደግሞ "የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነው " ብሏል። (ያዕ 1÷15 ሮሜ 6÷23) ። ስለዚህ ኃጢአት የኀሊናም የመንፈስም ሞት ነው ። ከዚህ በመነሳት ነው የጠፋው ልጅ ወደ አባቱ ቤት በተመለሰ ጊዜ አባቱ "... ደስም ይበለን፤ ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኗል ፡ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም " በማለት የተናገረው ። (ሉቃ 15÷24) #ኃጢአት በዓለም መታለል እና መጥፋት ነው ። በሉቃስ ወንጌል ላይ ተመዝግቦ የምናገኘው የጠፋው ልጅ ፣ የጠፋችው በግና ድሪም ኀጢአት በዓለም ተታሎ መጥፋት መሆኑን ያሳዩናል ። #ኀጢአተኛ ሰው በማወቅም ሆነ ሳያውቅ በኀጢአት መንገድ ላይ እየተጓዘ በመሆኑ ከእግዚአብሔር የጠፋ ነው ። ሌላው #ኃጢአት ከእግዚአብሔር መለየት ነው ፦ ኃጢአት ከእግዚአብሔር መለየት መሆኑን ሲያመለክት ቅዱስ ጳውሎስ " ብርሃን ከጨለማ ፤ ክርስቶስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው ? "ብሎአል (2ቆሮ 6÷14)
#ኃጢአት እግዚአብሔርን ማጣት ነው ። በኃጢአት የሚኖር ሰው ራሱንና ልቡናውን ከእግዚአብሔር በመለየቱ እግዚአብሔርን ያጣል ። ስለሆነም ኃጢአት ከሁሉ በፊት የእግዚአብሔርን ፍቅር ማጣት ነው ። ጌታችንም "የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል " (ዮሐ 14÷23) ከማለቱም በላይ "ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም " (1ዮሐ 2÷15) በማለት ዮሐንስ ይሄንን ያጠናክርልናል ። እግዚአብሔርን የሚወድ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ወደ ሚያቀርበው ያዘነብላል። በተጨማሪም #ኃጢአት ለእግዚአብሔር አለመታዘዝ ፣ በእርሱ ላይ ማመፅ እርሱንም መፃረር ጭምር ነው ። የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እንደ ቀላል ነገር መቁጠርና ሁሉን ማየት በሚችል በእግዚአብሔር ፊት ትዕዛዛቱን መተላለፍና ፈሪሃ እግዚአብሔርን ማጣት ነው ።
#ኃጢአት መንፈስ ቅዱስን መቃወም ነው ! ፦ በውስጣችን ያለው የእግዚአብሔር መንፈስ ለእግዚአብሔር ልጆች እንደሚገባ በቅድስና እንድንኖርና የጽድቅን ሥራም እንድንሰራ ይፈልጋል ። በኀጢአት የምንመላለስ ከሆነ ግን መንፈስቅዱስን እንቃወማለን ። በቅዱስ መፅሐፍም "ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ " (ኤፌ 4÷30) ተብሏል።
#ኃጢአት የሰዎች የባሕርይ ርኩሰት ነው ። "ሁሉ ዐመፁ ፡ በአንድነትም ረከሱ ፣ በጎ ነገርን የሚሰራ የለም ፡ አንድስ እንኳ የለም " ተብሎ ተነግሯል ።
#ኃጢአት መዋረድም ነው ። ሰው ከእግዚአብሔር ልጅነት በመውጣት ተዋርዶ የሰይጣን ልጅ ለመሆን የበቃው በኀጢአት መሆኑን ማስታወስ ያስፈልጋል ።

#የመጨረሻው_ክፍል
#ንስሐ_እንዴት_ይገባል ?
#1ኛ_ከራስ_ጋር_መሆን
ንስሐ መግባት የራስን ፈቃድ ይጠይቃል። ምናልባት ያለህበትን የኀጢአት ባሕርና ጥፋት አልተገነዘብክ ይሆናልና መጀመሪያ ከራስህ ጋር መሆን አለብህ ። ከራሳችን ጋር የሆንን እንደሆነ ድካማችንንና ኀጢአታችንን ለእግዚአብሔር መናገር አይከብደንም ። ማንም ቢሆን በመንፈሳዊ ሕይወቱ በበረታ ቁጥር ሰይጣንም ሊጥለው ከመቼውም የበለጠ ኃይሉን አጠናክሮ ሊፈትነው እንደሚተጋ የተረጋገጠና የማይጠረጠር ነው ።
#2ኛ_ምክንያትንና_ለራስ_ይቅርታ_ማድረግን_ማስወገድ
በንስሐ ሕይወት ለመኖር የምንሻ ከሆነ ለወደቅንበት ኃጢአት ምክንያት መደርደርና ለራሳችን ይቅርታን ለመስጠት መሞከር የለብንም ። ኃጢአትን ከፈፀሙና ከሰሩ በኀላ ለኃጢአት ያበቃ ሌላ ምክንያት ማቅረብና በዚያም አንፃር ለመጽናናት መሞከር በራሱ ኀጢአት ነው ።ስለ ሰራነው ሀጢአት ንስሐ መግባት እንጂ ምክንያት በማበጀት ራስን ነፃ ማድረግ የለብንም ። በዓለም እስካለን ድረስ ሁላችንም ሀጢአትን እንሰራለን ። ወፍጮ ቤት ገብቶ ዱቄት ሳይነካን እንደማንወጣው ሁሉ በዓለምም እስካለን ድረስ እንበድላለን ። ለዚህ ነው አበው ሰው ሆኖ የማይሳሳት፣ እንጨት ሆኖ የማይጨስ ፣ ብረት ሆኖ የማይዝግ የለም የሚሉን ። እግዚአብሔርም ለምን በኀጢአት ወደቅክ አይለንም ለምን አልተነሳህም ነው የሚለን ። ሰለዚህ ንስሐ አባት የሌለን በመጀመሪያ ንስሐ አባት እንያዝ ከዛም ያደረግነውን ሁሉ ዝርዝር አርገን ተናግረን ከሀጢአት የተፈታን ወንዶች የ40 ቀን ህፃን ሴቶች ደሞ የ80 ቀን ህፃን እንሁን ። ሀጢአታችን ምንም ቢበዛም ከእግዚአብሔር ፍቅር ግን አይበልጥም ። የአምላካችን የክርስቶስ ደም ከኀጢአት ሁሉ ሊያነፃን የታመነ ነው ። ማንኛችንም ብንሆን የተወለድንበትን ቀን እንጂ የምንሞትበትን ቀን አናውቅም ። የትኛዋ ቅፅበት የመጨረሻችን እንደሆነች አናውቅምና በቶሎ ንስሐ ገብተን ተዘጋጅተን እንጠብቅ። ስለ #ንስሐ በጥቂቱ ከአቡነ ሺኖዳ መጽሐፍ ላይ ያዘጋጀነው ትምህርት ለዛሬ በዚ አበቃ ነገ ደግሞ ስለ ንስሐ በሌሎች ትምህርቶች እንመለስበታለን ሀሳብ አስተያየት ኢዮአታም ይጠቀሙ