ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
813 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#ትምህርተ_ንስሐ (በአቡነ ሺኖዳ)
#የመጨረሻው_ክፍል
#ንስሐ_እንዴት_ይገባል ?
#1ኛ_ከራስ_ጋር_መሆን
ንስሐ መግባት የራስን ፈቃድ ይጠይቃል። ምናልባት ያለህበትን የኀጢአት ባሕርና ጥፋት አልተገነዘብክ ይሆናልና መጀመሪያ ከራስህ ጋር መሆን አለብህ ። ከራሳችን ጋር የሆንን እንደሆነ ድካማችንንና ኀጢአታችንን ለእግዚአብሔር መናገር አይከብደንም ። ማንም ቢሆን በመንፈሳዊ ሕይወቱ በበረታ ቁጥር ሰይጣንም ሊጥለው ከመቼውም የበለጠ ኃይሉን አጠናክሮ ሊፈትነው እንደሚተጋ የተረጋገጠና የማይጠረጠር ነው ።
#2ኛ_ምክንያትንና_ለራስ_ይቅርታ_ማድረግን_ማስወገድ
በንስሐ ሕይወት ለመኖር የምንሻ ከሆነ ለወደቅንበት ኃጢአት ምክንያት መደርደርና ለራሳችን ይቅርታን ለመስጠት መሞከር የለብንም ። ኃጢአትን ከፈፀሙና ከሰሩ በኀላ ለኃጢአት ያበቃ ሌላ ምክንያት ማቅረብና በዚያም አንፃር ለመጽናናት መሞከር በራሱ ኀጢአት ነው ።ስለ ሰራነው ሀጢአት ንስሐ መግባት እንጂ ምክንያት በማበጀት ራስን ነፃ ማድረግ የለብንም ። በዓለም እስካለን ድረስ ሁላችንም ሀጢአትን እንሰራለን ። ወፍጮ ቤት ገብቶ ዱቄት ሳይነካን እንደማንወጣው ሁሉ በዓለምም እስካለን ድረስ እንበድላለን ። ለዚህ ነው አበው ሰው ሆኖ የማይሳሳት፣ እንጨት ሆኖ የማይጨስ ፣ ብረት ሆኖ የማይዝግ የለም የሚሉን ። እግዚአብሔርም ለምን በኀጢአት ወደቅክ አይለንም ለምን አልተነሳህም ነው የሚለን ። ሰለዚህ ንስሐ አባት የሌለን በመጀመሪያ ንስሐ አባት እንያዝ ከዛም ያደረግነውን ሁሉ ዝርዝር አርገን ተናግረን ከሀጢአት የተፈታን ወንዶች የ40 ቀን ህፃን ሴቶች ደሞ የ80 ቀን ህፃን እንሁን ። ሀጢአታችን ምንም ቢበዛም ከእግዚአብሔር ፍቅር ግን አይበልጥም ። የአምላካችን የክርስቶስ ደም ከኀጢአት ሁሉ ሊያነፃን የታመነ ነው ። ማንኛችንም ብንሆን የተወለድንበትን ቀን እንጂ የምንሞትበትን ቀን አናውቅም ። የትኛዋ ቅፅበት የመጨረሻችን እንደሆነች አናውቅምና በቶሎ ንስሐ ገብተን ተዘጋጅተን እንጠብቅ። ስለ #ንስሐ በጥቂቱ ከአቡነ ሺኖዳ መጽሐፍ ላይ ያዘጋጀነው ትምህርት ለዛሬ በዚ አበቃ ነገ ደግሞ ስለ ንስሐ በሌሎች ትምህርቶች እንመለስበታለን ሀሳብ አስተያየት ኢዮአታም ይጠቀሙ

ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
#ሕይወተ_ወራዙት
#የመጨረሻው_ክፍል
በቀሲስ ህብረት የሺጥላ
#በወር_አበባ_ወቅት_መከልከል_የሚገባው_ከምን_ከምን_ነው ?
#ሀ_ከሩካቤ ፦ የወር አበባን የምታይ ሴት ባለ ትዳር ከሆነች በደሟ ወቅት ምንም እንኳን ባሏም ቢሆን ሩካቤ መፈፀም በመንፈሳዊ ህግ አይፈቀድላትም ። የህክምና ባለሙያዎችም ቢሆኑ በደም ወራት የሚደረግ ሩካቤ በአብዛኛው ለአባላዘር ፣ ለልዩ ልዩ ተላላፊ በሽታዎችና ለኢንፌክሽን በቀላሉ ሊያጋልጥ እንደሚችል ይናገራሉ። መፅሐፍ እንዲህ ይላል "እርሷም በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች ኀፍረተ ሥጋዋን ትገልፅ ዘንድ ሴት አትቅረብ " (ዘሌ 18÷19) ። ምንም እንኳን የወር አበባ በአዲስ ኪዳን መርገም ወይም ርኩሰት ስላልሆነ በዚህ ወቅት ሩካቤ የሚፈፅሙ ሰዎች እንደ ኦሪቱ በድንጋይ ተወግረው ባይሞቱም ተገቢው ቀኖና ግን ይሰጣቸዋል።
#ለ_ከመጠመቅ ፦ ሐዋርያው ጴጥሮስ "ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ... የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም ። ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ " በማለት ተናግሯል ። ( 1ኛ ጴጥ 3÷21) ስለዚህ ጥምቀት ሥጋዊ እድፍ ማስወገጃ ስላልሆነ ከመጠመቅ በፊት ተጣጥበው ከአፍአዊ እድፍ ከጠሩ በሁዋላ መጠመቅ ይገባል ። አንዳንድ ጊዜ በጠና የታመሙ ሴቶች በጠበል ለመፈወስ ክትትል ሲጀምሩ ልዩ ልዩ ፈተና ያጋጥማቸዋል ። ከፈተናዎቻቸውም ውስጥ አንዱና ዋነኛው ያለ ወሩ ያለ ማቋረጥ ወይም በተደጋጋሚ መከሰቱ ነው ። ይህን የመሰለ ነገር ሲከሰት ከሰይጣን ጋር እልህ መጋባትና ዝም ብዬ ብጠመቅ ምን አለበት ? ማለት ሞኝነት ነው ።
#ሐ_ከመቁረብ ፦ ምንም እንኳን ለቁርባን የሚያስፈልገውን ቅድመ ዝግጅት ያጠናቀቁ ቢሆኑም ሴቶች ከደመ ፅጌ ሳይነፁ #ሥጋና_ደሙን መቀበል አይችሉም ። ይህን ሥርዓት ተላልፎ ሴቶችን ከወር አበባ ሳይነፁ ወደ ቤተክርስቲያን እንዲገቡና ሥጋውን ደሙን እንዲቀበሉ ያደረገ ቢኖር ዲያቆን ሆነ ቄስ ከክህነቱ እንዲሻር ፍትሐ ነገስት እንዲህ ሲል ይደነግጋል ። "ከግዳጅዋ ያልነፃችውን ሴት በደሟ ወራት ከቤተ ክርስቲያን አግብቶ ሥጋውን ደሙን ያቀበላት ከመዓርጉ ይሻር " (ፍት.ነገ 6)
#መ_ቤተ_መቅደስ_ከመግባት ፦ የወር አበባ ላይ ያለች ሴት በቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ሆና መማር መፀለይ ትችላለች መቅደስ መግባት ግን ክልክል ነው ።
እነሆ #ሕይወተ_ወራዙትን ጨረስን በቀጣይ ደሞ ሌላ ት/ት እንጀምራለን።

ለአስተያየት 👉ኢዮአታም ይጠቀሙ፡፡
👉ለመቀላቀል 👇👇👇
💚 @zekidanemeheret 💚
💛 @zekidanemeheret 💛
❤️ @zekidanemeheret ❤️
#ፍኖተ_ቅዱሳን
#የመጨረሻው_ክፍል
... ከባለፈው የቀጠለ ...
ከላይ ሁለቱን ደረጃዎች ተመልክተናል ። ወጣኒነትና ማዕከላዊነትን። አሁን ደግሞ የመጨረሻውን ደረጃ ፍፁምነትን እንመልከት ። ይህ የመጨረሻ ደረጃ እንደ መሆኑ መጠን በ2ቱ ደረጃዎች ሰባቱን መዓርጋት ገንዘብ አድርገው ወደዚህ ለመሸጋገር የሚጋደሉትን ሰይጣን በገሃድ ተገልጦ መዋጋት የሚጀምርበት ጊዜ ነው ።ዘንዶና እባብ ፣ አንበሳና ነብር እየሆነ በመምጣት ለማስፈራራት ቢሞክር ያልደነገጡለትን ሽፍታ እየመሰለ መደብደብ ሁሉ ይጀምራል ። መዝ 90 እና መሰል ፀሎትን በመፀለይ ድል ይነሱታል ።መደ ሚቀጥሉት ማዕረጋትም ይሻገራሉ ።
#8ኛ #ንፃሬ_መላዕክት ፦ እዚ ደረጃ ሲደርሱ እነሱን የሚረዷቸውን መላዕክት በየነገዳቸውና በየአለቆቻቸው በሚኖሩባቸው ዓለማተ መላዕክት (በኢዮር ፣ በኤረር ፣ በራማ ) እንዳሉ በዓይነ ስጋ በዐፀደ ስጋ ለመመልከት መብቃት ፣ ምስጋናቸውንም መስማትና ከዚህ ዓለም ፈፅሞ ተለይቶ ከሰማያውያን ጋር መኖርን መጀመር ነው ።
#9ኛ #ተሰጥሞ_ብርሃን ፦ ይህ ደግሞ የእግዚአብሔር የባሕሪ ገንዘብ በሆነው በሚያስደንቀው ብርሃን ውስጥ መዋኘት ነው ። ይህ ብርሃን ፍፁም ልዩ ነው ።ይህም እነርሱ በዛ ብርሃን ውስጥ እያሉ ሌላ ለዚህ ማዕረግ ያልበቃ ሊያየው የማይችል ብርሃን ነው ።ጨለማ የማይሰለጥንበት ፣ እንደዚህ ዓለም ብርሃን የማያቃጥል ፣ በጨረሩ አይንን የማይበዘብዝ ፣ ነፍስን ከስጋ መለየት የሚያስችል ደስታ እስኪሰማ ድረስ ልዩ መዓዛ ያለው ነው ። እነዚህን ፀጋዎች የሚያውቁት የኖሩባቸው ቅዱሳን ናቸው ። እኛ ደሞ ከመፃህፍት ብቻ እንረዳቸዋለን ።
#10ኛ #ከዊነ_እሳት (ነፅሮተ ስሉስ ቅዱስ) ፦ ይህ የመጨረሻው ማዕረግ ነው ። ወደዚ ደረጃ የደረሱ ቅዱሳን ሰውነታቸው ለአጋንንት የሚያቃጥልና የማያስቀርብ ይሆናል ።እነዚህን አጠቃለው የያዙ የልብ ንፅህናን ገንዘብ አድርገዋልና ለነጽሮተ ስሉስ ቅዱስ ይበቃሉ ።ለዚህ መብቃትም ታላቅ ብቃትና ማዕረግ ነው ። በባሕሪው የማይታየውን እግዚአብሔርን ለባሕሪያቸው በሚስማማ መልኩ እስከ ማየት በቅተዋልና።
❖ ተፈፀመ ❖

👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret