ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
813 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#ኦርቶዶክስ_መልስ_አላት
#ክፍል_3
#የይሖዋ_ምስክሮች /ጆቫ ዊትነስ/ *
የይሖዋ ምስክሮች የተባለው የሃይማኖት ተቋም በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ በቻርልስ ራስል የተመሰረተ ሲሆን ራስል ቀደም ባሉት ጊዜያት ክርስቲያን የነበረ ሲሆን በኀለኛው የወጣትነት ዘመኑ በአርዮሳውያን የኑፉቄ ትምህርትና በሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት እንዲሁም በአንዳንድ የክህደት ትምህርት (Atheists) አራማጆች ተፅዕኖ ስር ወደቀ ። እ.ኤ.አ በ1872 አካባቢ ከነዚህ የተበረዙና የተዛቡ አስተምህሮዎች በመነሳት ራስል የራሱን አስተምህሮ (Doctrine) በመቅረፅ በአሜሪካ ውስጥ ለማሳተም ቻለ ።እስቲ ጥቂት እምነታቸውን እንመልከት #1ኛ .ጆቫዎች ቤተክርስቲያንና የአለም መንግስታት ሁሉ የሰይጣን ስራ ውጤቶች ናቸው ብለው ያምናሉ #2ኛ.ዜጎች በወታደራዊ ተቋማት እንዳይገቡ ያደርጋሉ ። ለሰንደቅ አላማ የክብር ሰላምታ መስጠትን እንደ ባዕድ አምልኮ አድርገው ይቆጥሩታል #3ኛ. የሰው ነብስ ትሞታለች ብለው ያምናሉ #4ኛ.የሰው ልጅ ከትንሳኤ ቡሃላ ገነት በምትሆነው ምድር ለዘላለም ይኖራል /ምድር ገነት ትሆናለች/ ብለው ያምናሉ #5ኛ.የይሖዋ ምስክሮች ክርስቶስን ሁሉን ቻይ የሆነ አምላክ ሳይሆን መለኮታዊ ባህሪ ያለው ንዑስ አምላክ ነው ብለው ያምናሉ #6ኛ.የይሖዋ ምስክሮች ሰብአ ሰገል በቤተልሔም በጌታችን ፊት ያደረጉት ስግደት የማይገባና የመራቸውም ኮከብ ከሰይጣን የተላከ እንደሆነ ያምናሉ ። #7ኛ.ጆቫዎች ክርስቶስ አስቀድሞ በሰማይ ከተፈጠረ በኀላ በዚያው ኗሯል ፡ ወደ ምድር እንዲመጣ ያስፈለገበት ዋነኛ ዓላማም ስለ ይሖዋ መንግስት ለመመስከር ነው ይላሉ ። #8ኛ.የይሖዋ ምስክሮች የዳግም ልደቱ መጀመሪያ በሚሆነው ጥምቀቱ ለእግዚአብሔር ልጅነት የተሾመ ነው በዚህም የአብ መንፈሳዊ ልጅ በመሆን የይሖዋ መንግስት ገዢ /ንጉስ/ ሆኗል ብለው ያምናሉ ። #9ኛ.የይሖዋ ምስክሮች ኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ መላዕክት ሚካኤል ነው ብለውም ያምናሉ ። #10ኛ.የይሖዋ ምስክሮች የሰው ልጅ በስጋ ሲሞት ነፍሱም አብራ ትሞታለች። ዘላለማዊነት የይሖዋ ብቻ የተለየ ባህሪ ነው ብለው ያምናሉ ። #11ኛ. የይሖዋ ምስክሮች ኃጢያተኞች ከፃድቃን ተለይተው እንደሚጠፉ እንጂ በሲኦል የሚሰቃዩ መሆናቸውን አይቀበሉም ። ሌላው ቀርቶ ሰይጣን ይጠፉል እንጂ አይሰቃይም አባታችን አዳምም አንዴ ስለሞተ ትንሳኤ አያገኝም ይላሉ ። #12ኛ .መንፈስ ቅዱስ የሥላሴ አንዱ አካል ሳይሆን የይሖዋ ሀይል ነው ብለው ያምናሉ ። #13ኛ. በብዙ ትንሳኤ ያምናሉ ።ማለትም የታናሽ መንጋ ትንሳኤ ፣ምድራዊ ትንሳኤ ፣ የይሖዋ ምስክሮች አባል ላልሆኑትና ፃድቅ ለሆኑት የሚደረግ ትንሳኤ ብለው ትንሳኤን ከፉፍለው ያምናሉ። ወስብሀት ለእግዚአብሔር ።የአብ ፀጋ ፡ የወልድ ቸርነት የመንፈስቅዱስ ህብረት አንድነት ከኛ ጋር ይሁን ለዘለአለሙ አሜን
ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
#ኦርቶዶክሳዊ_የጾታ_ትምህርት
#ክፍል_3
#የፍቅር_አይነቶች(Types of Love)
ብዙ ጊዜ ሰዎች ፍቅር ያዘኝ አፈቀርኩ ሲሉ ይሰማሉ ። እንደ ባለሙያዎች አገላለፅ ከሆነ 12 አይነት ፍቅር አለ ። እነሱን አንድ በአንድ እናያለን ከዛም የተያዘ ሰው የትኛው ፍቅር እንደያዘው እራሱን ያይበታል ። #1ኛ_ሮማንቲክ_ላቭ (Romantic Love ) ፦ ይሄኛው የፍቅር ዓይነት የሚይዛቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ የሰውነትን ቅርፅ ብቻ አይተው የሚያፈቅሩ ሰዎች ናቸው ። ሌሎቹን መሰረታዊ ነገሮች ግምት ውስጥ አያስገቡም ። ለምሳሌ ጥሩ ጸባይ እና ባህሪን፣ የአመለካከት ጥራትን ፣ ሃይማኖትን ፣ ስነምግባርን የመሳሰሉትን ነገሮች አያዩም ።የሚያዩት ተክለ ሰውነትን ብቻ ነው ። ነገር ግን ፍቅር እንደያዛቸው ይናገራሉ ። እንደዚህ አይነት ሰዎች ብዙ ጊዜ ቀናተኛ ናቸው ። ያፈቀሩትን ሰው ከእነሱ ውጭ ከሌላ ሰው ጋር ምንም ዓይነት ጤነኛ (Normal) ግንኙነት እንዲኖረው እንኳን አይፈልጉም ። ይህ ፍቅር ትኩረቱ ብዙ ጊዜ #በሩካቤ ሥጋ መውደቅ እንጂ #ትዳር አይደለም ። ስለዚህ እንደዚህ አይነቱ ፍቅር አይዘልቅም ።
#2ኛ_ፖሽኔት_ላቭ(Possinate Love) ፦ ይህ ፍቅር ስሜታዊ ፍቅር ነው ። ፖሽኔት ላቭ በጣም አስቸጋሪና ከባዱ የፍቅር ዓይነት ነው ። ሕይወትን የመመሰቃቀልና በጣም የማጨናነቅ ባህርይ አለው። ህሊናን እረፍት ከመንሳቱ ጎን ለጎን የወጣቶችን የወደፊትን የሕይወት ምዕራፍ የማጨለም ጉልበት አለው ። ለምሳሌ በስሜታዊ ፍቅር የተያዘ ሰው ትምህርት መማር ሁላ ሊያስጠላው ይችላል ። ከሰው ጋር ተደባልቆ ጊዜውን ከማሳለፍ ይልቅ ያፈቀረውን ሰው እያብሰለሰለ ለብቻው መሆን ይፈልጋል ፤ ምግብ እንኳን ይዘጋዋል አይምሮው ከፍቅር ውጪ ምንም ነገር ማሰብ አይፈልግም ። በመፅሐፍ ቅዱስ ታሪክ በዚህ አይነቱ ስሜታዊ ፍቅር ተይዞ የተሰቃየ ሰው አምኖንን እናውቃለን ። /2ኛ ሳሙ 13/ በዚህ ፍቅር የተያዙ ሰዎች ለጊዜው እውነተኛ ፍቅር እንደያዛቸው ሊያስቡ ይችላሉ ። ማስተዋልን ሳይቀር የሚጋረድበት የፍቅር ዓይነት ነውና። የሚገርመው ደሞ ኀላ ላይ ያስጨነቀውን ያህል ከልብ ውስጥ መጥፋቱ አይቀርም ። እንዲህ አይነቱም ፍቅር ቆይታው ሩካቤ ስጋ እስኪፈፀም ድረስ ብቻ ነው ። ፍቅሩም ከዛች ቅፅበት ጀምሮ ይቆማል ። ይህን በዳዊት ልጅ በአምኖን ላይ ማየቱ ብቻ በቂ ነው ።
#3ኛ_ሎጂካል_ላቭ(Logical Love)፦ በዚህ አይነት ፍቅር የተያዙ ደግሞ የፍቅር መነሻቸው #መመሳሰል ነው ። ብዙ ጊዜ በሎጂክ ሕግ ነው የሚመሩት ። ሲያፈቅሩ በህይወታቸው ውስጥ ከዛ ሰው ጋር የሚያመሳስላቸው አንድ ነገር ስላዩ ነው ። ለምሳሌ እሷ ዲግሪ ካላት የምትመርጠው ዲግሪ ያለውን ነው ። እሷ ስራ አስኪያጅ ከሆነች የምትመርጠው ማናጀር ነው ። እነዚ ከነሱ ጋር የሚያመሳስላቸውን አቻቸውን ማፍቀር የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው ። እንዲህ ሲባል ደግሞ በስራ ጠባይና በት/ት ማዕረግ የተመሳሰሉ ተጋቢዎች ሁሉ እዚህ ፍቅር ውስጥ ናቸው ማለት ግን አንችልም ። ይህ ፍቅር እንደሌሎቹ ሁሉ ዘላቂ አይደለም ። ምክንያቱም ያፈቀረችው ሰው ከእለታት 1 ቀን ያንን ስራ ሊለቅና ሊቀይር ይችላልና ። በዚህ ጊዜ እርሷ የፈለገችው የተመሳሰሉበት መስመር ተቀየረ ማለት ነው ። በተጨማሪም ያቺ ሴት ሥራውን እንጂ ሌሎች ነገሮቹን ስለማታውቅለትና በሕይወቱም ሳትማረክለት የጀመረችው ብዙ ነገር ስላለ ፍቅሩም ላይዘልቅ ይችላል፡፡
🌼🌼🌼ይቆየን

ፍኖተ መንግስተ ሰማያት
ይህ ቻናል ብሂለ አበው፣እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ጽሑፎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች የሚተላለፉበት መንፈሳዊ ቻናል ነው፡፡
ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ ጥያቄና አስተያየት

👉 ኢዮአታም

ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/zekidanemeheret
#ትምህርተ_ንስሐ (በአቡነ ሺኖዳ)
#ክፍል_3
#የንስሐ_መሰናክሎች (እንቅፋቶች)
ሰይጣን ከሚዋጋቸው የድኀነት መንገዶች ውስጥ ንስሐን የሚያክል የለም። ምክንያቱም ንስሐ ጠላት ዲያቢሎስ የክርስቲያኖች ሕይወት ለማጥፋት የገነባውን የኃጢአት ሕንፃ ሁሉ በእግዚአብሔር ቸርነት እንዳልነበር በማድረግ ስለሚያፈርስበት ነው ። ከዚህ የተነሳ የሰው ልጅ ንስሐ እንዳይገባ ፣ ቢገባም ቶሎ እንዳይሆን የተቻለውን ከማድረግ ፈጽሞ አያርፍም ። ከሚጠቀማቸው መሰናክሎች መካከል የሚከተሉት ይገኛሉ ።
#ሀ እንቅፋት መፍጠር ፦ እነዚህ ድንገተኛ ፈተናዎች ወይም አጋጣሚዎች ሊሆኑ ይችላሉ ። እነዚህ አጋጣሚዎች ወይም ፈተናዎች ተነሳሒው በድፍረት ወደ ንስሐ እንዳይመጣና ከኃጢአቱ እንዳይመለስ ተፅእኖ የሚያሳድሩ ናቸው ።
#ለ ኃጢአተኛው ራሱን ከእርሱ የቀለጠ ኃጢአት ሠሩ ከሚላቸው ጋር በማነፃፀር የተሻለ እንደሆነ እንዲገምትና ንስሐም እንደማያስፈልገው ራሱን ማሳመን ፤ #ቅድስና ግን ከኃጢአተኛ ሕይወት ሕይወት ጋር ሊነፃፀር አይገባም ። ኖኀ በብዙ ኃጢአተኞች መካከል ቅዱስ እንደነበር ዮሴፍ፣ ሎጥና ሙሴም በኃጢአተኞች መካከል ቅዱሳን እንደነበሩ እኛም መቀደስ አለብን እንጂ እራሳችንን ማነፃፀር የለብንም ።
#ሐ ከሥጋ ድካም የተነሳ በአካባቢ ተፅእኖ መመራት ፦ ተነሳሒው ሰው በዓለም የማይታለል ጽኑ አቋም እንዲኖረው ያስፈልጋል ። ቅዱስ ጳውሎስ "ይህን ዓለም አትምሰሉ " እንዳለ ። (ሮሜ 12÷2) #ዓሣ ትንሽ ሲሆን ማዕበል በሚያናውጠው ባሕር ውስጥ ይዋኛል ። ክርስቲያንም እንዲህ ሊሆን ይገባዋል ። ደካማ ስጋን ቢለብስም ፈተናውን ተቋቁሞ ለንስሐ መብቃትና በመንፈሳዊ ሕይወት መኖር ይገባዋል ።
#መ መዘግየት ፦ ዲያቢሎስ ንስሐ እንዳንገባ የሚዋጋን በቀጥታ አይደለም ። ነገር ግን የተለያዩ ስውር ፈተናዎችን እየደቀነ እንዳንገባ ያዘገየናል። #መዘግየት ከሚያስከትለው አደጋ አንዱ ለንስሐ የተዘጋጀውን ልቡና መለወጥና ለንስሐ ያለውን ዕድል ማጥፋት ነው ።
#ሠ ተስፋ መቁረጥ ፦ ይህ ንስሐ የማይቻልና ሊደረግ የማይሞከር እንደሆነ አድርጎ ማሰብ ነው። ሰይጣን በኃጢአት ከመውደቃችን በፊት የእግዚአብሔርን ቸርነትና ይቅርታ በማሰብ እንድንሰራ ያደርገናል ፤ ከሰራነው ቡሃላ ደሞ የእግዚአብሔርን ፍርድና ጨካኝ እንደሆነ ያሳስበናል ። ንስሐ እንዳንገባም ተስፋ ያስቆርጠናል ።

💚 @zekidanemeheret 💚
💛 @zekidanemeheret 💛
❤️ @zekidanemeheret ❤️
#ትምህርተ_ንስሐ (በአቡነ ሺኖዳ )
#ክፍል_3
#ለንስሐ_የሚያበረታቱ_ሁኔታዎች
#1 ማንነትህን ካወቅህ ከኀጢአት በላይ ነህ ። ሰው እግዚአብሔር ምን ያህል እንዳከበረው ያወቀ እንደሆነ ራሱን በኃጢአት አያዋርድም ።ሰው ማነው ? አንተ አንቺ ማነህ ?
#ሀ አንተ እግዚአብሔር የሕይወት እስትንፋስ ሰጥቶ የፈጠረህ ፍጥረት ነህ ። አንተ አፈር ብቻ አይደለህም ። ከ4ቱ ባህርያተ ስጋ ከ3ቱ ባህርያተ ነፍስ የተፈጠርክ ሕያው ሰው ነህ ። ሕያው በመሆንህም ለጊዜው በምድር የምትኖር ብትሆንም በክብር ወደ አምላክህ በመሄድ ሰማያዊ ሕይወትን ለመኖር የተፈጠርክ መሆንህን አስብ ። ስለዚህም በመንፈስ ኑር ። ከዓለም ከስጋዊ ስራም ተለይ ።
#ለ አንተ በመልኩና በምሳሌው የተፈጠርክ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ። በእግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠርክ ከሆንክ እንዴት ኃጢአትን ትሰራለህ ? በኃጢአት ወድቀህስ እንዴት የእግዚአብሔር ምሳሌ ልትባል ትችላለህ ? ስለዚህ ነገር ቅዱስ አትናቴዎስ "ሰው በበደለ ጊዜ የእግዚአብሔር ምሳሌ መሆኑ ይቀራል ። ቅድስናውን ያጣልና " በማለት ተናግሯል። ጌታችንም ሰው የሆነው ወደነበርንበት የቅድስና ሕይወት ሊመልሰን ነው ።የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ያወቀ ሰው ኃጢአት አይሰራም ፤ ኃጢአትን ባለመስራትም አባቱን የሚመስል ይሆናልና ። አባቱን የማይመስል ልጅም ልጅ አይደለም። ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጅነትህን ከኀጢአት በመለየት ልታረጋግጥ ይገባሀል። በዚህም አባትህን ትመስላለህና ። "የአብርሃም ልጆች ብትሆኑ የአብርሃምን ሥራ ባደረጋችሁ ነበር " እንደ ተባለ። የእግዚአብሔር ልጆች የኖሩትን የተቀደሰ ሕይወት ካልኖርን የእግዚአብሔር ልጆች አይደለንም ። በመሆኑም በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ ልንል አንችልም ። "... ፃድቅ እንደሆነ ካወቃችሁ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከእርሱ እንደተወለደ ዕወቁ " (1ኛ ዮሐ 2÷29)
#ሐ አንተ የእግዚአብሔር ማደሪያ የመንፈስቅዱስ ቤተ መቅደስ ነህ ። "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ " (ምሳ 20÷26) ይህ አባባል የሰው ልብ የእግዚአብሔር ማደሪያ መሆኑን ያመለክታል። ቅዱስ ጳውሎስም " የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ እንደሆናችሁ ፡ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን ? ማንም የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እሱን ያፈርሰዋል የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ቅዱስ ነውና #ያውም-እናንተ ናችሁ። "(1ቆሮ 3÷16) ። #ዲያቢሎስ_በኃጢአት ሊፈትንህ ወደ አንተ በመጣ ጊዜ
✞ እኔ ለአንተ አይደለሁምና ከእኔ ወግድ በለው
✞ እኔ የእግዚአብሔር መቅደስና የመንፈስቅዱስ ማደሪያ ነኝ በለው
✞ እኔ የሥላሴ ባሪያ ነኝ በለው
✞ እኔ በእኔ ያድር ዘንድና ወደ ልቡናዬ ይገባ ዘንድ እግዚአብሔር ልቤን የሚያንኳኳ ነኝ በለው
✞ እኔ አብና ወልድ ማደሪያቸው ሊያደርጉኝ ወደ እኔ የሚመጡ ሰው ነኝ በለው

💚 @zekidanemeheret 💚
💛 @zekidanemeheret 💛
❤️ @zekidanemeheret ❤️
🇪🇹ክርስቲያናዊ_ሥነ_ምግባር🇪🇹
#ክፍል_3

#1 ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ ወይም አታምልክ {፳÷፪}
🖊እኔ የሁሉ ፈጣሪ አስገኚ እኔ ነኝ ሲል ይህን ትዕዛዝ ወይም ህግ ስለ ውለታው ስለ ቸርነቱ እንድናስበው እንድናመልከው እንድንገዛ ይህን ህግ ሰቶናል።
ማምለክ ሲባል እምነትን ተስፋን ፍቅርን በአምላክ ላይ መጣል ነው ። አንድ ሰው እምነቱን ተስፋውን ፍቅሩን ከእግዚአብሔር ላይ አንስቶ በሌሎች አማልክት ላይ ሲጥል ነው ሌላ አምላክ አመለከ የሚባለው ።
#አምልኮት በተግባር የሚውለው በሚከተሉት ነገሮች ነው ።
፩ እግዚአብሔር መውደድ
፪ በፆም፡በስግደት፡በጸሎት
፭ በጸሎት መስዋዕት
፮ በውዳሴ በዝማሬ
፯ ራስን መገዛት
፰ እግዚአብሔርን በፍርሃት
፱ በምፅዋት ወዘተ
🖊ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ከእግዚአብሔር ውጪ ለሌላ ነገር ብንሰጣቸው ሌላ አመለክን ማለት ነው ። ይህን ህግ የሚያፈርሱ ሰዎች ብዙ ዓይነት በደል ይበድላሉ ። ይኸውም=
#፩ የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር የተባለውን ትዕዛዝ ይለውጣሉ ።
#፪ ከቤተክርስቲያን አንድነት ውጭ ይሆናሉ
#፫ ተስፋ ቢስ ሁሉ የጨለመባቸው ሆነው ይገኛሉ ። 🇪🇹#ሌሎች_አማልክት_የተባሉት🇪🇹
🖊ሰው እንደ እግዚአብሔር የሚያያቸውና ብቸኛውን የእግዚአብሔርን ባሕርይ የሚሰጣቸው ነገሮች ሁሉ አምላክ ሊሆኑበት ይችላሉ ። እነሱም ፦ #፩ ገንዘብ ማቴ ፮:፳፬ ፣የሐዋ ፭÷፩ ፣ ፩ጢሞ ፮÷፲
#፪የሰው ሃይል ት-ኤር ፲፯:፭ ማር ፰÷፴፬
#፫ የሰው ጥበብ እውቀት ት, ኤር ፱:፳፫ ፩ሳሙ፪÷፩-፲
#፬ ሆዳምነት {ራስ ወዳድነት} ፌሊ፫÷፲፱
#፭ የምንታመንባቸው ሰዎች (ባለ ሃብት ባለ ስልጣን) መዝ ፻፵፭÷፫ የሐዋ ፭÷፳፱
#፮ አባትና እናት ማር፲÷፴፯
#፯ ተድላ ደስታ ፪ጢሙ፫÷፬
#፰ ጌጣጌጥ ኦዘፍ ፴፭÷፪-፬
#፱ የተቀረፀ ምስል ዘፀ 20:4 🖊አምልኮ ከእግዚአብሔር ውጪ ለማንም አይሰጥም ። አክብሮትና የጸጋ ስግደት ግን ለቅዱሳን መላዕክት እና ለቅዱሳን ሁሉ ልናደርግ ይገባል ።
🖊መጽሐፍ ቅዱስ ቅዱሳንን #አማልክት ይላቸዋል ። ለምሳሌ ሙሴን ለፈርኦን አምላክ አድርጌሃለው በማለት እግዚአብሔር ነግሮታል ። በቤተክርስቲያናችን ቅዱሳንን እናከብራለን ይህ ከትዕዛዙ ወይም ከህጉ ጋር አይጋጭም የእግዚአብሔርን አምልኮትና አክብሮት ለቅዱሳን አንሰጥምና ። እንዲያውም ለእነርሱ የምንሰጠው ክብር እግዚአብሔርን ማክበር ስለሆነ በብዙ ምስጋና ለእግዚአብሔር እናቀርባለን ።


ይቀጥላል....

ለሌሎች ማጋራትን አይዘንጉ

👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#ፍኖተ_ቅዱሳን
#ክፍል_3
#10ሩ_ማዕረጋተ_ቅድስና
ከባለፈው የቀጠለ ንፅሀ ስጋን ገንዘብ ያደረጉ ሰዎች ቀጥለው የሚሸጋገሩት ወደ ንፅሀ ነፍስ ነው ። ትሩፋተ ስጋን አብዝቶ የሰራ ሰው የሚሸጋገረው ትሩፋተ ነፍስን ወደ መስራት ነውና ። በዚህም መሰረት አንድ ሰው ከንፅሀ ስጋ በሃላ አብዝቶ ትሩፋተ ነፍስ ከሰራ የሚከተሉትን መዓርጋት ገንዘብ ማድረግ ይችላል
#4ኛ #አንብዕ ፦ እንባ ማለት ነው ። የሀዘን እንባ ሰው በደረሰበት ሀዘን ልቡ ተወግቶ ፊቱን አስከፍቶ የሚያለቅሰው ሲሆን የደስታው እንባ ደግሞ ልቡናው በሐሴት ተሞልቶ ሰውነቱ ስሜቱን መቆጣጠር ባቃተው ጊዜ የሚያለቅሰው ነው ። "አንብዕ " ግን ከዚህ ፈፅሞ የተለየ ነው ። ይኸውም ቅዱሳን ሰውነታቸው በሐዘን ሳይከፋ በስጋዊ ሐሴትም ሳይሞላ ሳይሰቀቁ ከዓይናቸው የሚያፈልቁት እንባ ነው ።
#5ኛ #ኩነኔ ፦ ቅዱሳን ከራሳቸው ሰውነት ጋር የሚያደርጉት ( የፈቃደ ስጋና የፈቃደ ነፍስ መጋጨት ) ዋናው ነው ። በዚህ ተጋድሎ ፈቃደ ስጋቸውን ሙሉ ለሙሉ ለፈቃደ ነፍሳቸው ለማስገዛት የበቁ ሰዎች "ለመዓርገ ኩነኔ " በቁ ይባላል ። ኩነኔ ማለት በአጭር ቃል ስጋን ለነፍስ ማስገዛት ማለት ነው ። ስጋ ለነፍስ ተገዛ ማለት ደሞ እንስሳዊ ባህሪያቸው ፍፁም ደክሞ መልአካዊ ባህሪያቸው ሰልጥኖ ይታያሉ ። ለስጋዊ ደማዊ ሰው የሚከብደውን ሁሉ መስራት ይችላሉ ። ለምሳሌ በቅጠላ ቅጠል ብቻ ለብዙ ጊዜ መኖርን ፣ ከእንቅልፍ መጥፋት የተነሳ በትጋሃ ሌሊት ማደርን ፣ በየቀኑ እጅግ ብዙ ስግደት መስገድን ፣ ከስግደትና ከፀሎት ውጪ በሚሆኑበት ሰዓትም ከቅዱሳት መፃህፍት አለመለየት
#6ኛ #ፍቅር ፦ ፍቅር ታላቅ ፀጋ ነው ። እግዚአብሔር ፍቅር ነው የሚባለው የባህሪ ገንዘቡ ስለሆነ ነው ። ሰዎች በተጋድሎ እየበረቱ እግዚአብሔር የፈጠረውን ፍጥረት ሁሉ ሳይንቁ አስተካክሎ መውደድ ነው ። ለዚህ ደረጃ የበቃ ሰው ሌላውን ሰው ኃጥዕ ጻድቅ ፣ አማኒ ከሃዲ ፣ ነጭ ጥቁር ፣ ደቂቅ ልሂቅ ፣ አዋቂ አላዋቂ ሳይል አስተካክሎ መውደድ ነው ።
#7ኛ #ሑሰት ፦ ይህ ደግሞ ነቢየ እግዚአብሔር ኤልሳዕ በኢየሩሳሌም ሆኖ የሶርያው ንጉስ ወልደ አዴር እልፍኙን ዘግቶ ከባለስልጣናቱ ጋር የመከረውን ማንም ሰው ሳይነግረውና ሳይሰማ በሚያውቅበት ፀጋ ካለበት ቦታ ሆኖ ጠፈር ገፈር ሳይከለክለው እንደ ፀሀይ ብርሃን ካሰቡት ደርሶ የፈለጉትን ነገር ማወቅ ማለት ነው ። ይህም በኢየሩሳሌም ሆኖ በቢታንያ የአልዓዛርን ሞት አይቶ የነገራቸውን ጌታን የሚመስሉበት ፀጋ ነው ።
... ይቀጥላል ...

👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
የፖርኖግራፊ መዘዞች
#ክፍል 3

ፖርኖግራፊ መመልከት የሚያስከትለው እጅግ በጣም ብዙ መዘዞች አሉት። ጉዳቶቹም መንፈሳዊ፣ ስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ናቸው። እስኪ የተወሰኑትን እንመልከት።

1. ከእግዚአብሔር ይለያል

በክርስቶስ የተጠራነው ንፁህ እና ቅዱሳን (1ጴጥ 1:10) እንድንሆን እንደመሆኑ በድብቅ የምንሰራቸው ማናቸውም ኃጢያቶች በመንፈሳዊ ሕይወታችን እንድንደክም ያደርጉናል። በፖርኖግራፊ ሱስ ላለ ሰው መፀለይ፤ ቃሉን ማንበብ እና ከሌሎች ክርስትያኖች ጋር ህብረት ማድረግ ከባድ ይሆናል። በዚህ ሱስ ከተጠቁ ወገኖቼ በተደጋጋሚ ከሰማዋቸው ድምጾች ዋነኛው፤ “መጸለይ አልቻልኩም፤ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ከበደኝ፤ ምክንያቱም ፊቴ ላይ የሚመጣው የተመለከትኩት ፖርኖግራፊ ነው” የሚል ነው።
ሀሳብ ከሌላው ሰው የተደበቀ ስለሆነ ብዙ ትኩረት ባይሰጠውም ተጨባጭ ሀጢያት ከመሆን አያግደውም። ፖርኖግራፊ መመልከት ኃጢያት መሆኑ ግልፅ ነው። ጌታችን ኢየሱስ “ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል” (ማቴዎስ 5:28) እንዳለ እናስታውስ። እኔ ፖርኖግራፊ አይቼ በፍጹም አልመኝም የሚል ይኖር ይሆን?
አንድ ሰው ፖርኖግራፊ እያየ ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር ተሰጥቻለሁ ማለት አይችልም። ምክንያቱም በማቴ 6:24 ላይ እንደሚናገረው አንድ ሰው ለሁለት ጌቶች ሊገዛ አይችልም። የስጋን ፈቃድ እየፈፀሙ ክርስቶስን ለማምለክ መሞከር ትርፉ ብቸኝነት፤ ተስፋ መቁረጥ እና ውድቀት ነው። ፖርኖግራፊ መንፈሳዊ ሕይወትን የሚያኮላሽ ነው። ሰው መንፈሳዊነቱን ካጣ ደግሞ ምንም ነገር ቢያገኝ አይረካም። ፖርኖግራፊ ዋና ነገሮቻችንን ያሳጣናል።

2. ድብርት/ጭንቅት

ፖርኖግራፊ ውስጥ የገባ ሰው ያለበት ሕይወት ትክክል እንዳልሆነ ያውቃል። ስለዚህ ከባድ የሆነ ጭንቀት ይሰማዋል። ብዙ ሰዎች በዚህ ምክንያት ሀፍረት ስለሚሰማቸው በራስ መተማመናቸውን ያጣሉ። ስለዚህ በከባድ የድብርት ስሜት ውስጥ ሆነው ራሳቸውን ከሰው ያገላሉ።

3. አቅምን ይገላል

በዚህ ሱስ የተያዘ ሰው በቀን ውስጥ በትንሹ 3 ሰዓት ፖርኖግራፊ በመመልከት ሊያጠፋ ይችላል። ምን ያህል የከበረ ጊዜውን እንደሚያጠፋም አስተውሉ! ከዚህ በተጨማሪ በዚህ ሱስ መጠቃት ኃላፊነትን ቸል ወደማለት ያደርሳል። የፈጠራ ችሎታን ይቀንሳል። በፖርኖግራፊ ምክንያት የአፈጻጸም ብቃታቸው ወርዶ ከስራና ከትምህርት የተባረሩ ሰዎች ጥቂቶች አይደሉም። አስደናቂና ዕምቅ ችሎታ ያላቸው ስንቶችን በፖርኖግራፊ ምክንያት አጥተናቸዋል?

4. ላልተፈለገ ተግባር ያጋልጣል

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ሕጻናትን ከደፈሩ ሰዎች ብዙዎቹ በፖርኖግራፊ ሱስ የተጠቁ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ሰዎች ከማይመለከቱት ጋር ሲነጻጸሩ በ400% ዘማዊ አዳሪዎች ጋር የመሄድ ዝንባሌ አላቸው። የተመሳሳይ ጾታ ፖርኖግራፊ በመመልከታቸው ብቻ ወደ ግብረ ሰዶማዊነት የገቡ ሰዎች እንዳሉም ለማየት ችያለው።

5. የተሳሳተ አመለካከት

በሱሱ የተጠቁ ሰዎች ስለራሳቸው የተሳሳተ አመለካከት ይኖራቸዋል። ‘እኔ አልጠቅምም፤ እኔ ከንቱ ሰው ነኝ፤ እኔ እግዚአብሔር ይጠላኛል፤ እኔ ከሰው አንሳለው፤ መቼም ከዚህ ህይወት መውጣት ስለማልችል ስኬታማ ትዳር አይኖረኝም፤ የሚሉ አሉታዊና ተስፋ የመቁረጥ አመለካከቶችን ያዳብራሉ። እንዲህ አይነቱ ለራስ የሚሰጥ የወረደ ግምት በቶሎ ካልተቀጨ ከባድ ወደሆነ አዕምሮአዊ እና ስነ ልቦናዊ በሽታ ያመራል። ለራሱ የተሳሳተ አመለካከት ያለው ሰው ስለ ሰዎች ትክክለኛ አመለካከት ሊኖረውም አይችልም። ሌላው የተሳሳተ አመለካከት የሚሰጠው ለተቃራኒ ጾታ ነው። እስከ ዛሬ በዚህ ጉዳይ ላይ ያማከርኳቸው ወንድሞችና እህቶች ሁሉም ለማለት በሚያስደፍረኝ ሁኔታ ለተቃራኒ ጾታ ዝቅ ያለ አመለካከት እንዳላቸው ገልጸውልኛል። ብዙውን ጊዜ በፖርኖግራፊ ምስሎች ላይ ሴቶች የወንዶች የወሲብ ፍላጎት አገልጋይ ተደርገው የተሳሉ ሲሆን ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ወንዶችም ልክ እንደዛው ሴቶቹን እንደሚመልከቱ ነግረውኛል። ሴቶች ደግሞ ሁሉም ወንዶች ጨካኝና ለስሜታቸው ብቻ የሚኖሩ እንደሆኑ እንዲያስቡ እንዳደረጋቸው አውርተውኛል። በዚህ የተሳሳተ አመለካከት ምክንያት ጤናማ የሆነ የፍቅር ህይወት ለመጀመር የተቸገሩ ጥቂቶች አይደሉም።

ይቀጥላል.....

🕊👉 @zekidanemeheret

https://t.me/zekidanemeheret
"የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ"
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
👉 የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
"የረቡዕ ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ"
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
👉 የረቡዕ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!