ስንክሳር ወግጻዌ ዘተዋሕዶ
800 subscribers
3.46K photos
104 videos
194 files
1.2K links
የየዕለቱ ስንክሳር እና ግጻዌ የሚቀርብበት ቻናል ነው፡፡

ለማንኛውም አስተያየት እና እርማት
@zetaodokos ላይ ይላኩልን።

👇👇የYoutube Channel ይቀላቀሉ👇👇
https://youtube.com/channel/UCupqpIYe_mMpSM7jMT3Njhw
Download Telegram
#ፍኖተ_ቅዱሳን
#ክፍል_2
(በቀሲስ ደጀኔ ሽፍራው)
#10ሩ_ማዕረጋተ_ቅድስና
መንፈሳዊ ህይወት የቅድስና ኑሮ እንደ መሆኑ መጠን በጥምቀት ጀምሮ ደረጃውን የጠበቀ እድገት ያለበት ሕይወት ነው ።ከዚህም በሃላ እግዚአብሔርን በፍፁም ልቡናቸው ሰውነታቸውና ሕዋሳቶቻቸው እያመሰገኑ አሰረ ፍኖቱን የሚከተሉ ሰዎች ከቅድስና ወደ ከበረ ቅድስና ከሚኖሩበት መንፈሳዊ ኃይል ወደ ሌላ ታላቅ መንፈሳዊ ኃይል ይሸጋገራሉ ። እነዚህ የቅዱሳን የመንፈሳዊ ጉዞአቸው የእድገት ደረጃዎች 3 ናቸው ። እነዚህም #ወጣኒነት (ንፅሀ ስጋ) ፣ #ማዕከላዊነት (ንፅሀ ነፍስ) እና #ፍፁምነት (ንፅሀ ልቡና ) በመባል ይታወቃሉ ። በእነዚህ በእያንዳንዳቸው ስር ደግሞ የተለያዩ ማዕረጋት አሉ ።በንፅሀ ስጋ 3 በንፅሀ ነፍስ 4 በንፅሀ ልቦና 3 ሲሆኑ በጠቅላላው #10ሩ ማዕረጋተ ቅዱሳን በመባል ይታወቃሉ ።
#ንፅሀ_ሥጋ /ወጣኒነት/
ይህ ደረጃ ወጣንያን በባሕርዩ ፍፁም ከኾነው እግዚአብሔር ፍፁም ፀጋን ተቀብለው ለመክበር ቁርጥ ተጋድሎ የሚጀምሩበት ሕይወት ነው ። በዚህም ጊዜ ጠላት የተባለ ሰይጣን የተጋድሎ ሕይወታቸውን የሚያቀጭጭ ፈተና ያመጣባቸዋል ። እነርሱ ግን በፍፁም ተጋድሎ በእግዚአብሔር ፀጋ ከአንዱ ማዕረግ ወደ ሌላው ይሸጋገራሉ ።
#1ኛ #ጽማዌ ፦ ዝምታ ማለት ነው ። ይኸውም አውቆና ፈቅዶ በመናገርና በመቀባጠር ከሚመጣው ኃጢአት መቆጠብ ነው ።ይህን የመጀመሪያውን ደረጃ በዝምታ ማለፍም ታላቁን የሰይጣን ፆር /እሳትን / በተጋድሎ ማጥፋት ነው ።አንደበት እሳት ነውና።
#2ኛ #ልባዌ ፦ ልባዊ ማለት ልብ ማድረግ ፣ ማስተዋል ማለት ነው ። ጌታ በወንጌል "መስማትንስ ትሰማላቹ ነገር ግን አታስተዉሉም " ይላቸው የነበረው ማስተዋል ታላቅ ማዕረግ ስለሆነ ነው ።
#3ኛ #ጣዕመ_ዝማሬ ፦ይህ ደግሞ ሳይሰለቹና ሳይቸኩሉ ምስጢርና ትርጓሜውን እያወጡ እያወረዱ በንቁ ሕሊና ማመስገንና መጸለይ ማለት ነው ። አንድ ሰው የሚፀልየውን ፀሎትና የሚያቀርበውን ምስጋና በትርጓሜና በምስጢር በውሳጣዊ ልቡናው እያዳመጠ የሚያደርሰው ከሆነ ተመስጦን ገንዘብ ማድረግ ይቻለዋል ። ጸጋ መንፈስ ቅዱስንም እየተጎናፀፈ ከዚህ ከስጋዊ አለም ማምለጥ ይቻለዋል።
... ይቀጥላል ...

👉ለመቀላቀል 👇👇👇
@zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret
#ፍኖተ_ቅዱሳን
#ክፍል_3
#10ሩ_ማዕረጋተ_ቅድስና
ከባለፈው የቀጠለ ንፅሀ ስጋን ገንዘብ ያደረጉ ሰዎች ቀጥለው የሚሸጋገሩት ወደ ንፅሀ ነፍስ ነው ። ትሩፋተ ስጋን አብዝቶ የሰራ ሰው የሚሸጋገረው ትሩፋተ ነፍስን ወደ መስራት ነውና ። በዚህም መሰረት አንድ ሰው ከንፅሀ ስጋ በሃላ አብዝቶ ትሩፋተ ነፍስ ከሰራ የሚከተሉትን መዓርጋት ገንዘብ ማድረግ ይችላል
#4ኛ #አንብዕ ፦ እንባ ማለት ነው ። የሀዘን እንባ ሰው በደረሰበት ሀዘን ልቡ ተወግቶ ፊቱን አስከፍቶ የሚያለቅሰው ሲሆን የደስታው እንባ ደግሞ ልቡናው በሐሴት ተሞልቶ ሰውነቱ ስሜቱን መቆጣጠር ባቃተው ጊዜ የሚያለቅሰው ነው ። "አንብዕ " ግን ከዚህ ፈፅሞ የተለየ ነው ። ይኸውም ቅዱሳን ሰውነታቸው በሐዘን ሳይከፋ በስጋዊ ሐሴትም ሳይሞላ ሳይሰቀቁ ከዓይናቸው የሚያፈልቁት እንባ ነው ።
#5ኛ #ኩነኔ ፦ ቅዱሳን ከራሳቸው ሰውነት ጋር የሚያደርጉት ( የፈቃደ ስጋና የፈቃደ ነፍስ መጋጨት ) ዋናው ነው ። በዚህ ተጋድሎ ፈቃደ ስጋቸውን ሙሉ ለሙሉ ለፈቃደ ነፍሳቸው ለማስገዛት የበቁ ሰዎች "ለመዓርገ ኩነኔ " በቁ ይባላል ። ኩነኔ ማለት በአጭር ቃል ስጋን ለነፍስ ማስገዛት ማለት ነው ። ስጋ ለነፍስ ተገዛ ማለት ደሞ እንስሳዊ ባህሪያቸው ፍፁም ደክሞ መልአካዊ ባህሪያቸው ሰልጥኖ ይታያሉ ። ለስጋዊ ደማዊ ሰው የሚከብደውን ሁሉ መስራት ይችላሉ ። ለምሳሌ በቅጠላ ቅጠል ብቻ ለብዙ ጊዜ መኖርን ፣ ከእንቅልፍ መጥፋት የተነሳ በትጋሃ ሌሊት ማደርን ፣ በየቀኑ እጅግ ብዙ ስግደት መስገድን ፣ ከስግደትና ከፀሎት ውጪ በሚሆኑበት ሰዓትም ከቅዱሳት መፃህፍት አለመለየት
#6ኛ #ፍቅር ፦ ፍቅር ታላቅ ፀጋ ነው ። እግዚአብሔር ፍቅር ነው የሚባለው የባህሪ ገንዘቡ ስለሆነ ነው ። ሰዎች በተጋድሎ እየበረቱ እግዚአብሔር የፈጠረውን ፍጥረት ሁሉ ሳይንቁ አስተካክሎ መውደድ ነው ። ለዚህ ደረጃ የበቃ ሰው ሌላውን ሰው ኃጥዕ ጻድቅ ፣ አማኒ ከሃዲ ፣ ነጭ ጥቁር ፣ ደቂቅ ልሂቅ ፣ አዋቂ አላዋቂ ሳይል አስተካክሎ መውደድ ነው ።
#7ኛ #ሑሰት ፦ ይህ ደግሞ ነቢየ እግዚአብሔር ኤልሳዕ በኢየሩሳሌም ሆኖ የሶርያው ንጉስ ወልደ አዴር እልፍኙን ዘግቶ ከባለስልጣናቱ ጋር የመከረውን ማንም ሰው ሳይነግረውና ሳይሰማ በሚያውቅበት ፀጋ ካለበት ቦታ ሆኖ ጠፈር ገፈር ሳይከለክለው እንደ ፀሀይ ብርሃን ካሰቡት ደርሶ የፈለጉትን ነገር ማወቅ ማለት ነው ። ይህም በኢየሩሳሌም ሆኖ በቢታንያ የአልዓዛርን ሞት አይቶ የነገራቸውን ጌታን የሚመስሉበት ፀጋ ነው ።
... ይቀጥላል ...

👉ለመቀላቀል 👇👇👇 @zekidanemeheret @zekidanemeheret @zekidanemeheret