𝚂𝚎𝚢𝚏𝚎𝚕𝙸𝚜𝚕𝚊𝚖 ሰይፈል ኢስላም!
390 subscribers
1.37K photos
136 videos
9 files
309 links
قال ابن تيمية -رحمه الله-:
{قوام الدين كتاب يهدي وسيف ينصر وكفى بربك هادياونصيرا}
مجموع الفتاوى [10/13]
ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት በሚመችዎ የማህበራዊ ሚድያ ይከታተሉኝ!👇
https://heylink.me/AzizoSocialLinks.com/
Download Telegram
#የኢስራኤልናፍልስጤምግጭት_መቼ_እና_እንደት_ጀመረ??
#ታሪካዊዳራ___ክፍል③
"ኢስራኤል በተ/መ/ድ እንደ ሃገር እውቅና ካገኘችበት እ.ኤ.አ.1947 ጀምሮ እስከ ዘመነ ትራምፕ ድረስ ያለው ሁኔታ!!"
________
#የ1947ቱ የተ/መ/ድ የፀጥታው ምክርቤት #ኢፍትሐዊ ውሳኔ፣በርካታ ፍልስጤማዊያንን ክፉኛ ያስቀየመ ከመሆኑም ባሻገር በርካቶችን ተወልደው ካደጉባቸው መንደሮች እንድፈናቀሉ ምክናየት ሆነ።
ይህ ኢፍትሐዊ ውሳኔ የተላለፈበትን ቀን ፍልስጤማውያን በየአመቱ “በናክባ ቀን”አስበውት ይውላሉ።ይህም “ጥፋት” ለሚለው የአረብኛ ቃል የተሰየመ ሲሆን ፍልስጤማውያን ለቀው እንዲወጡ የተገደዱባቸውን ቤቶች ቁልፍ በማመልከት #አሁንም_ተመልሰው_እንደሚኖሩባቸው_ተስፋ_ያልቆረጡባቸውን_ግዛቶች ለመዘከር የታሰበ ነበር።
እ.ኤ.አ. በ1948 የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ፍልስጤማውያን “ #ወደቤታቸው_ተመልሰው_ከአይሁድ_ጎረቤቶቻቸውጋር_በሰላም_ለመኖር_የሚፈልጉሁሉ_በተቻለፍጥነት_ይህን_የማድረግመብት_ሊኖራቸው_እንደሚገባ” በመገንዘብ #ውሳኔ194ን አፀደቀ ፡፡ እስራኤል ምንም እንኳን ይህ በሃይልና በዙልም ከመኖሪያ ቤታቸው ያስለቀቋቸው ነባር ፍልስጤማውያን ወደ መኖሪያ ቤታቸው ተመልሰው ከቤታቸውና ከቀያቸው አስለቅቀው የራሳቸውን መንግስት ከመሰረቱ መጤ አይሁዶች ጋር በጉርብትና እንድኖሩ በሚል ተ/መ/ድ ያወጣውን ውሳኔ፣አድሱ የኢስራኤል መንግስት በቅፅበት ፈቃጅና ከልካይ ሁና" #የፍልስጤሞች_ወደዚህ_መመለስ_ለአዲሱ_የአይሁድ_መንግስት_ተፈጥሮአዊስጋት ነው!"በሚል ሀሳብ ውሳኔውን ላለመቀበልም ዳዳት!
ከአንድ ዓመት በኋላ ለተፈናቀሉ"ፍልስጤማውያን" ወገኖች ድጋፍ ለመስጠት በቅርብ ምስራቅ የሚገኙ የፍልስጤም ስደተኞች #የተባበሩትመንግስታት_የእርዳታ_ስራዎች_ኤጄንሲ( #UNRWA)ተቋቋመ።
በእነዚያ ሁለት ክስተቶች መካከል ባለው ጊዜ እስራኤል #ከአጎራባች አረብ አገሮች ማለትም ከሊባኖስ፣ከሶሪያ ፣ከጆርዳን እና ከግብፅ ጋር የጦር መሣሪያ ስምምነቶችን ተፈራረመች።
ከዚያም እ.ኤ.አ.በ1950 ዮርዳኖስ የዌስት ባንክ አስተዳደራዊ ቁጥጥርን ስትወስድ፣ግብፅ ደግሞ ጋዛን እንድትወስድ ተደረገ።
ይህ ስምምነት እስራኤል እነዚህን ግዛቶች ከዮርዳኖስና ከግብፅ አስለቅቃ ለመውሰድ እንቅስቃሴ እስከጀመረችበትና በዚህም #የ6ቀኑ_የአረብ_ኢስራኤል_ጦርነት እስከተጀመረበት ግዜ ድረስ ቆየ።
(የ6ቱን ቀን የአረብ-እስራኤል ጦርነት ሂደት በሌላ ፅሁፍ እመለስበታለሁ ኢንሻ አሏህ)
ከዚያ በፊትም ብጥብጡ አልፎ አልፎ ቀጥሎ የነበረ ሲሆን፣በ1956 በቃልኪሊያ፣በኩፍርቃሲም እና በሃን ዩኒስ መንደሮች ውስጥ፣እንድሁም በ1966 አስሳሙ በተባሉ ቦታዎች እልቂቶች ተከስተዋል።
#በ1964 #የፍልስጤም_ነፃ_አውጪ _ድርጅት(PLO)ካይሮ ውስጥ የተቋቋመ ሲሆን፣ከሰላማዊ ትግል ይልቅ በትጥቅ አብዮት “ፍልስጤም ነፃ ለማውጣት”የተመሰረተ ነበር።እስራኤልናአሜሪካ ድርጅቱን በአሸባሪነት ቢፈርጁትም፣የፍልስጤም ህዝብ ብቸኛ ተወካይ መሆኑን የአረብሊግ በ1974 እውቅና ሰጠው።
የእስራኤል ወታደራዊ ጦር በጋዛ ሰርጥ፣ በዌስትባንክ፣በጎላን ከፍተኛቦታዎች እና በግብፅ ሲናይ በረሃ፣በ1967 ከፍተኛ ደም መፋሰስ ያስከተለ ሲሆን፣የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት በሃይል ተይዘዋል ብለው ካሰቡዋቸው ግዛቶች እስራኤል ጦሯን እንድታወጣ በማዘዝ #ውሳኔ242 ቢያፀድቅም፣እስራኤል ከቆብ አልቆጠረችውም ነበር።
እስራኤል በ1970 በዮርዳኖስ ውስጥ ከፍልስጤማውያን ወታደሮች ጋር በጥቁሯመስከረም(Black September)ተጨማሪ ውጊያ ማድረጓን ተከትሎ፣"የፀጥታው¡"ምክርቤት የተኩስ አቁም ጥሪ በማቅረብ እና እስራኤል ከ 1967ቱ ወረራ እንድትመለስ በመጠየቅ #ውሳኔ338 አስተላለፈ።
አሁንም እስራኤል እምቢ አለች!
በፍልስጤማውያን"የመሬትቀን"ተብሎ የሚዘከርበት፣ማርች30ቀን1976፣ የእስራኤልን የመሬት ወረራ በመቃወም ከገሊላ ባህር እስከ ኔጌቭ ድረስ ባሉ ከተሞች አመጽ፣አድማ እና ተጨማሪ የኃይል እርምጃዎችን አስከተለ።
እ.ኤ.አ.መስከረም17ቀን 1978፣የእስራኤሉ ጠ/ሚ #ሜናም_ቤገን ከግብፁፕሬዝዳንት #አንዋር_ሳዳት ጋር በፕሬዚዳንት በጂሚ ካርተር ማረፊያ የካምፕ ዴቪድ ስምምነቶችን ለመፈራረም ተገናኙ። ስምምነቱ በሁለቱ ሃገሮች(እስራኤልናግብፅ)መካከል ግንኙነታቸውን ያጠናከረና #የሰላምኖቬል_ሽልማት ያስገኘላቸውሲሆን፣በሌላ በኩል ግን ስምምነቱ የባለጉዳዮቹ ፍልስጤማውያን ውክልና የሌለበት በመሆኑ፣ግጭቱን ከማባባስ የዘለለ የፈየደው አንዳችም ነገር አልነበረም።
የእስራኤል ጦር በጋዛ የሚገኙ 4 ሲቪል ፍልስጤማዊያንን በግፍ በመግደሉ ምክናየት፣December 8, 1987 በፍልስጤምግዛቶች ውስጥ በአይነቱየመጀመሪያ የሆነ ከባድሁከት( #The_First_Intifada)ተነስቶ እስከ መስከረም13,1993 ድረስ ቆየ።
በ1993 #የኦስሎI_ስምምነት(Oslo1) በእስራኤል ጠ/ሚ #ይስሃቅ ራቢንና የ PLO ሊቀመንበር #ያሲር_አራፋት የተፈረመ ሲሆን፣የፍልስጤም ጊዜያዊ የራስገዝ አስተዳደር እንድመሰረትና የእስራኤል ጦር ከተ/መ/ድ እውቅና ውጭ በሃይል ከያዛቸው ቀጠናዎች እንዲወጣ ተደረገ፡፡ነገር ግን ኢስራኤል ስምምነቱን በማፍረሷ
#ሁለተኛው_የኦስሎ_ስምምነት(Oslo2)እ.ኤ.አ.በ1995 ተደረገ።በዚህም በተወሰኑ የዌስትባንክ እና የጋዛ አካባቢዎች የፍልስጤም የራስ ገዝ አስተዳደርን እውቅና ቢሰጥም፣የፍልስጤምን ሉኣላዊ ሃገርነት ግን አሁንም አላፀደቀም ነበር።
በመስከረም28,2000 #ሁለተኛውከባድ አመፅ( #the second Intifada)የተቀሰቀሰ።ዋነኛ ምክናየቱ የእስራኤል ጠ/ሚ #አርኤል_ሻሮን #በአልአቅሷ መስጅድ ጉብኝት ማድረጉ ነበር።
በ2002 እስራኤል ዌስትባንክን ወረረች።ይህም #በ2004_ከያሲር_አራፋት_ሞት ጋር ተዳምሮ ፍልስጤማውያንን ክፉኛ ጎዳቸው።
በ2006 በፍልስጤም በተካሄደ ምርጫ #ሃማስ አብላጫ ድምፅ በመያዝ አሸነፈ።ሆኖም በምርጫ የተሸነፈው ፋታህ(PLO)ውጤቱን ባለመቀበሉ ሃማስናፋታህ #የርስበርስ_ጦርነት አደረጉ።በመጨረሻም ሃማስ ጋዛን ሲቆጣጠር፣ፋታህ ደግሞ ዌስትባንክን ያዘ።
በ2006 እስራኤል በሊባኖስ በሚገኘው"ሂዝቦላህ"የተባለ ቡድን ላይ ጦርነት አወጀች።
አስከትላም በጋዛ በሚገኘው ጅሃድስት ቡድን(ሃማስ)ላይ፣ኦፕሬሽን ካስት ሊድ(2008)፣ኦፕሬሽን የመከላከያ ዓምድ(2012) እና የኦፕሬሽን መከላከያ ጠርዝ(2014)ን ጨምሮ በጋዛ ውስጥ በተደጋጋሚ ጥቃት መሰንዘር ጀመረች፡፡ ይህ ሳያንሳት በ2017 እና በ20018፣ፍልስጤማውያን የናክባ ቀን በሚያስቡበት እለት፣በተ/መ/ድ #የጦርወንጀሎች_ምርመራ የሚያስጠይቅ የሆነ ከባድጥቃት አደረሰች።
በ2017በአሜሪካ በተደረገው ምርጫ #ዶናልድ_ትራምፕ መመረጥ ሁኔታውን ዳግም አገረሸው።ለዚህም ዋነኛ ማሳያ ትራምፕ የአሜሪካን ኤምባሲ #ከቴልአቪቭ_ወደ_ኢየሩሳሌም ማዘወሩ ነበር፡፡ትራምፕ ዓለም አቀፍ ህጎችን በመጣስ፣ #የጎላን ከፍተኛቦታዎችን የእስራኤል መሆናቸውንም አፀደቀ።
ይህም አልበቃ ብሎት አሜሪካ ለUNRWA የምትመድበውን የገንዘብ ድጋፍም አቋረጠ።🔚
የዚህን ፅሁፍ ክፍል①እና②ለማግኘት👉t.me/Abdelaziz_Bin_Muhammed ይጎብኙ።
የመረጃ ምንጮቸ
#አልጀዚራ #ቢቢሲ #ዊኪፔድያ
#ኢንሳይክሎፔድያብሪታኒካ #ዘጋርድያን #ሂስትሪዶትኮም እና ሌሎችም ናቸው።
ጥያቄ/አስተያየት ለመስጠት ከፈለጉ በቴሌግራም t.me/ServantOf_Almighty ላይ ይፃፉልኝ።

t.me/Seyfel_Islam
#የኢስራኤልናፍልስጤምግጭት_መቼ_እና_እንደት_ጀመረ??
#ታሪካዊዳራ___ክፍል③
"ኢስራኤል በተ/መ/ድ እንደ ሃገር እውቅና ካገኘችበት  እ.ኤ.አ.1947 ጀምሮ እስከ ዘመነ ትራምፕ ድረስ ያለው ሁኔታ!!"
____
#የ1947ቱ የተ/መ/ድ የፀጥታው ምክርቤት #ኢፍትሐዊ ውሳኔ፣በርካታ ፍልስጤማዊያንን ክፉኛ ያስቀየመ ከመሆኑም ባሻገር በርካቶችን ተወልደው ካደጉባቸው መንደሮች እንድፈናቀሉ ምክናየት ሆነ።
ይህ ኢፍትሐዊ ውሳኔ የተላለፈበትን ቀን ፍልስጤማውያን በየአመቱ “በናክባ ቀን”አስበውት ይውላሉ።ይህም “ጥፋት” ለሚለው የአረብኛ ቃል የተሰየመ ሲሆን ፍልስጤማውያን ለቀው እንዲወጡ የተገደዱባቸውን ቤቶች ቁልፍ  በማመልከት #አሁንም_ተመልሰው_እንደሚኖሩባቸው_ተስፋ_ያልቆረጡባቸውን_ግዛቶች ለመዘከር የታሰበ ነበር።
እ.ኤ.አ. በ1948 የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ፍልስጤማውያን “ #ወደቤታቸው_ተመልሰው_ከአይሁድ_ጎረቤቶቻቸውጋር_በሰላም_ለመኖር_የሚፈልጉሁሉ_በተቻለፍጥነት_ይህን_የማድረግመብት_ሊኖራቸው_እንደሚገባ” በመገንዘብ #ውሳኔ194ን አፀደቀ ፡፡  እስራኤል ምንም እንኳን ይህ በሃይልና በዙልም ከመኖሪያ ቤታቸው ያስለቀቋቸው ነባር ፍልስጤማውያን ወደ መኖሪያ ቤታቸው ተመልሰው ከቤታቸውና ከቀያቸው አስለቅቀው የራሳቸውን መንግስት ከመሰረቱ መጤ አይሁዶች ጋር በጉርብትና እንድኖሩ በሚል ተ/መ/ድ ያወጣውን ውሳኔ፣አድሱ የኢስራኤል መንግስት በቅፅበት ፈቃጅና ከልካይ ሁና" #የፍልስጤሞች_ወደዚህ_መመለሾ_ለአዲሱ_የአይሁድ_መንግስት_ተፈጥሮአዊስጋት ነው!"በሚል ሀሳብ ውሳኔውን ላለመቀበልም ዳዳት!
ከአንድ ዓመት በኋላ ለተፈናቀሉ"ፍልስጤማውያን" ወገኖች ድጋፍ ለመስጠት በቅርብ ምስራቅ የሚገኙ የፍልስጤም ስደተኞች #የተባበሩትመንግስታት_የእርዳታ_ስራዎች_ኤጄንሲ( #UNRWA)ተቋቋመ።
በእነዚያ ሁለት ክስተቶች መካከል ባለው ጊዜ እስራኤል #ከአጎራባች አረብ አገሮች ማለትም ከሊባኖስ፣ከሶሪያ ፣ከጆርዳን እና ከግብፅ ጋር የጦር መሣሪያ ስምምነቶችን ተፈራረመች።
ከዚያም እ.ኤ.አ.በ1950 ዮርዳኖስ የዌስት ባንክ አስተዳደራዊ ቁጥጥርን ስትወስድ፣ግብፅ ደግሞ ጋዛን እንድትወስድ ተደረገ።
ይህ ስምምነት እስራኤል እነዚህን ግዛቶች ከዮርዳኖስና ከግብፅ አስለቅቃ ለመውሰድ እንቅስቃሴ እስከጀመረችበትና በዚህም #የ6ቀኑ_የአረብ_ኢስራኤል_ጦርነት እስከተጀመረበት ግዜ ድረስ ቆየ።
(የ6ቱን ቀን የአረብ-እስራኤል ጦርነት ሂደት በሌላ ፅሁፍ እመለስበታለሁ ኢንሻ አሏህ)
ከዚያ በፊትም ብጥብጡ አልፎ አልፎ ቀጥሎ የነበረ ሲሆን፣በ1956 በቃልኪሊያ፣በኩፍርቃሲም እና በሃን ዩኒስ መንደሮች ውስጥ፣እንድሁም በ1966 አስሳሙ በተባሉ ቦታዎች እልቂቶች ተከስተዋል።
#በ1964 #የፍልስጤም_ነፃ_አውጪ _ድርጅት(PLO)ካይሮ ውስጥ የተቋቋመ ሲሆን፣ከሰላማዊ ትግል ይልቅ በትጥቅ አብዮት “ፍልስጤም ነፃ ለማውጣት”የተመሰረተ ነበር።እስራኤልናአሜሪካ ድርጅቱን በአሸባሪነት ቢፈርጁትም፣የፍልስጤም ህዝብ ብቸኛ ተወካይ መሆኑን የአረብሊግ በ1974 እውቅና ሰጠው።
የእስራኤል ወታደራዊ ጦር በጋዛ ሰርጥ፣ በዌስትባንክ፣በጎላን ከፍተኛቦታዎች እና በግብፅ ሲናይ በረሃ፣በ1967 ከፍተኛ ደም መፋሰስ ያስከተለ ሲሆን፣የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት በሃይል ተይዘዋል ብለው ካሰቡዋቸው ግዛቶች እስራኤል ጦሯን እንድታወጣ በማዘዝ #ውሳኔ242 ቢያፀድቅም፣እስራኤል ከቆብ አልቆጠረችውም ነበር።
እስራኤል በ1970 በዮርዳኖስ ውስጥ ከፍልስጤማውያን ወታደሮች ጋር በጥቁሯመስከረም(Black September)ተጨማሪ ውጊያ ማድረጓን ተከትሎ፣"የፀጥታው¡"ምክርቤት የተኩስ አቁም ጥሪ በማቅረብ እና እስራኤል ከ 1967ቱ ወረራ እንድትመለስ በመጠየቅ #ውሳኔ338 አስተላለፈ።
አሁንም እስራኤል እምቢ አለች!
በፍልስጤማውያን"የመሬትቀን"ተብሎ የሚዘከርበት፣ማርች30ቀን1976፣ የእስራኤልን የመሬት ወረራ በመቃወም ከገሊላ ባህር እስከ ኔጌቭ ድረስ ባሉ ከተሞች አመጽ፣አድማ እና ተጨማሪ የኃይል እርምጃዎችን አስከተለ።
እ.ኤ.አ.መስከረም17ቀን 1978፣የእስራኤሉ ጠ/ሚ #ሜናም_ቤገን ከግብፁፕሬዝዳንት #አንዋር_ሳዳት ጋር በፕሬዚዳንት በጂሚ ካርተር ማረፊያ የካምፕ ዴቪድ ስምምነቶችን ለመፈራረም ተገናኙ። ስምምነቱ በሁለቱ ሃገሮች(እስራኤልናግብፅ)መካከል ግንኙነታቸውን ያጠናከረና #የሰላምኖቬል_ሽልማት ያስገኘላቸውሲሆን፣በሌላ በኩል ግን ስምምነቱ የባለጉዳዮቹ ፍልስጤማውያን ውክልና የሌለበት በመሆኑ፣ግጭቱን ከማባባስ የዘለለ የፈየደው አንዳችም ነገር አልነበረም።
የእስራኤል ጦር በጋዛ የሚገኙ 4 ሲቪል ፍልስጤማዊያንን በግፍ በመግደሉ ምክናየት፣December 8, 1987 በፍልስጤምግዛቶች ውስጥ በአይነቱየመጀመሪያ የሆነ ከባድሁከት( #The_First_Intifada)ተነስቶ እስከ መስከረም13,1993 ድረስ ቆየ።
በ1993 #የኦስሎI_ስምምነት(Oslo1) በእስራኤል ጠ/ሚ #ይስሃቅ ራቢንና የ PLO ሊቀመንበር #ያሲር_አራፋት የተፈረመ ሲሆን፣የፍልስጤም ጊዜያዊ የራስገዝ አስተዳደር እንድመሰረትና  የእስራኤል ጦር ከተ/መ/ድ እውቅና ውጭ በሃይል ከያዛቸው ቀጠናዎች እንዲወጣ ተደረገ፡፡ነገር ግን ኢስራኤል ስምምነቱን በማፍረሷ
#ሁለተኛው_የኦስሎ_ስምምነት(Oslo2)እ.ኤ.አ.በ1995 ተደረገ።በዚህም በተወሰኑ የዌስትባንክ እና የጋዛ አካባቢዎች የፍልስጤም የራስ ገዝ አስተዳደርን እውቅና ቢሰጥም፣የፍልስጤምን ሉኣላዊ ሃገርነት ግን አሁንም አላፀደቀም ነበር።
በመስከረም28,2000 #ሁለተኛውከባድ አመፅ( #the second Intifada)የተቀሰቀሰ።ዋነኛ ምክናየቱ የእስራኤል ጠ/ሚ #አርኤል_ሻሮን #በአልአቅሷ መስጅድ ጉብኝት ማድረጉ ነበር።
በ2002 እስራኤል ዌስትባንክን ወረረች።ይህም #በ2004_ከያሲር_አራፋት_ሞት ጋር ተዳምሮ ፍልስጤማውያንን ክፉኛ ጎዳቸው።
በ2006 በፍልስጤም በተካሄደ ምርጫ #ሃማስ አብላጫ ድምፅ በመያዝ አሸነፈ።ሆኖም በምርጫ የተሸነፈው ፋታህ(PLO)ውጤቱን ባለመቀበሉ ሃማስናፋታህ #የርስበርስ_ጦርነት አደረጉ።በመጨረሻም ሃማስ ጋዛን ሲቆጣጠር፣ፋታህ ደግሞ ዌስትባንክን ያዘ።
በ2006 እስራኤል በሊባኖስ በሚገኘው"ሂዝቦላህ"የተባለ ቡድን ላይ ጦርነት አወጀች።
አስከትላም  በጋዛ በሚገኘው ጅሃድስት ቡድን(ሃማስ)ላይ፣ኦፕሬሽን ካስት ሊድ(2008)፣ኦፕሬሽን የመከላከያ ዓምድ(2012) እና የኦፕሬሽን መከላከያ ጠርዝ(2014)ን ጨምሮ በጋዛ ውስጥ በተደጋጋሚ ጥቃት መሰንዘር ጀመረች፡፡  ይህ ሳያንሳት በ2017 እና በ20018፣ፍልስጤማውያን የናክባ ቀን በሚያስቡበት እለት፣በተ/መ/ድ #የጦርወንጀሎች_ምርመራ የሚያስጠይቅ የሆነ ከባድጥቃት አደረሰች።
በ2017በአሜሪካ በተደረገው ምርጫ #ዶናልድ_ትራምፕ መመረጥ ሁኔታውን ዳግም አገረሸው።ለዚህም ዋነኛ ማሳያ ትራምፕ የአሜሪካን ኤምባሲ #ከቴልአቪቭ_ወደ_ኢየሩሳሌም ማዘወሩ ነበር፡፡ትራምፕ ዓለም አቀፍ ህጎችን በመጣስ፣ #የጎላን ከፍተኛቦታዎችን የእስራኤል መሆናቸውንም አፀደቀ።
ይህም አልበቃ ብሎት አሜሪካ ለUNRWA የምትመድበውን የገንዘብ ድጋፍም አቋረጠ።🔚
የመረጃ ምንጮቼ:
#አልጀዚራ #ቢቢሲ #ዊኪፔድያ
#ኢንሳይክሎፔድያብሪታኒካ #ዘጋርድያን #ሂስትሪዶትኮም እና ሌሎችም ናቸው።
ጥያቄ/አስተያየት ለመስጠት ከፈለጉ በቴሌግራም t.me/ServantOf_Almighty ላይ ይፃፉልኝ።

t.me/Seyfel_Islam
#የዛሬው_የፍርድቤት_ውሎ!
✍𝓐𝓫𝓭𝓮𝓵𝓪𝔃𝓲𝔃 𝓑𝓲𝓷𝓜𝓾𝓱𝓪𝓶𝓶𝓮𝓭
https://t.me/Seyfel_Islam

⏺መቀመጫውን በኔዘርላንድ ዋና ከተማ #ሄግ ያደረገው ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት እስራኤል በጋዛ ላይ በፈፀመችው የዘር ማጥፋት ወንጀል ምክናየት #ደቡብ_አፍሪካ ባቀረበችው ክስ ላይ ዛሬ January 26/2024 ብይን ሰጥቷል።
“በጋዛ ቀጣይነት ያለው የህይወት መጥፋት በእጅጉ ያሳስበናል!” በማለት የጀመረው ፍርድቤቱ፣ “ደቡብ አፍሪካ እስራኤል በጋዛ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅማለች በማለት ያቀረበችውን ክስ ውድቅ ለማድረግ እስራኤል ያቀረበችው የመከላከያ ክርክር ተቀባይነት አላገኘም!” ብሏል።
“ከ93% በላይ የሚሆነው የጋዛ ሰርጥ ህዝብ ምግብ ማግኘት አልቻለም፤ፍልስጤማውያን የዘር ማጥፋት ወንጀልን ለመከላከል በወጣው ስምምነት መሰረት #ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው ጎሳዎች ናቸው!”በማለት የደቡብ አፍሪካን ክስ ተጋርቷል።
የፍርድቤቱ ዳኛ በማስከተልም “በእስራኤል ላይ የቀረበውን የዘር ማጥፋት ወንጀል  ክስ ውድቅ አናደርግም፣ክሱን ውድቅ ለማድረግ እስራኤል ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም!”ብለዋል።
“በጋዛ ያሉ ፍልስጤማውያንን ከዘር ማጥፋት ድርጊቶች የመታደግ መብታቸውን አረጋግጠናል!”ያሉት የፍርድቤቱ ዳኛ፣
“አሁን ባለው ሁኔታ በጋዛ ምግብ እና ውሃን ጨምሮ መሰረታዊ ፍላጎቶችን የማግኘት እድል የለም!”ብለዋል።

ለዚህ ውሳኔያቸው እንደግብአት የተጠቀሟቸውን ተጨማሪ መረጃዎችንም የጠቀሱት የፍርድቤቱ ፕሬዝዳንት፣
“በጋዛ ሰርጥ እየደረሰ ስላለው የሰብአዊ ሁኔታ መባባስ የ #UNRWA መግለጫም ከግምት ውስጥ አስገብተናል።በተጨማሪም የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ በጋዛ ሰርጥ በሲቪሎች ላይ የደረሰው ጉዳት #የጦር_ወንጀል መሆኑን አመልክቷል።”በማለት ለደቡብ አፍሪካ ክስ አጋዥ መረጃዎችን ጠቃቅሰዋል።
ሌላው ቢቀር የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር ጦርነቱ እንደተጀመረ በሚድያ ቀርቦ “ከሰው መሰል እንስሳት ጋር እየተዋጋን ነው”በማለት የተናገረውን ፀያፍ ንግግር እንኳን ብንወስድ፣በደቡብ አፍሪካ የቀረበውን ክስ ፍርድ ቤቱ ውድቅ ማድረግ አይችልም ብለዋል።
ሁሉም በጋዛ ግጭት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ወገኖች አለም አቀፍ የሰብአዊ ህግጋትን እንዲያከብሩ እና ታጋቾቹን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ያሳሰቡት የዓለም አቀፉ ፍትህ ችሎት ፕሬዝዳንት
በመጨረሻም“እስራኤል በጋዛ ነዋሪዎች ላይ ከግድያ፣ጥቃት እና ውድመት ጋር የተያያዙ #ሁሉንም ነገሮች ለማስወገድ #ቃል_መግባት አለባት!”በማለት ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ ያቀረበችውን ክስ ተቀብሎ በጋዛ ላይ የሚደርሰውን የዘር ማጥፋት መከላከል እንድትችል ጠይቋል።

⏺በመቀጠል ደግሞ ውሳኔውን በተመለከተ ከተለያዩ ሃገራት፣መሪዎችና ድርጅቶች የተሰጡ አስተያየቶች የተወሰኑትን እንይ።
👌በዛሬው የፍ/ቤት ውሳኔ ላይ አስተያየት የሰጡት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ጀግናው #ሲሪል_ራማፎዛ “የዛሬው የአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ውሳኔ የፍትህ ድል ነው።የአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ውሳኔ ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ ቅሬታዋን ማቅረቧ ትክክል እንደነበር አረጋግጧል!”ያሉ ሲሆን፣“የአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ውሳኔ እና የወሰዳቸውን እርምጃዎች በደስታ እንቀበላለን!”ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ራማፎዛ በማስከተልም “እስራኤል ዛሬ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ፊት ቆማለች!ስለዚህ በፍልስጤማውያን ላይ የምትፈጽመው #ወንጀል በግልፅ ይታያል!”ብለዋል።
በመጨረሻም ፕሬዝዳንት ራማፎዛ፣“ከአለም አቀፍ ፍትህ ውሳኔ በኋላ በጋዛ የተኩስ አቁምን ለማሳካት እና የሁለት ሀገር መፍትሄን ለማምጣት ድርድር ለመጀመር የጋራ ጥረት መደረግ አለበት!”ብለዋል።
👌የደቡብ አፍሪካ የአለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትር “በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ሲገደሉ እያየን ዝም ብሎ መመልከት ብቻ አልቻልንም!”በማለት ደቡብ አፍሪካ ክሱን ለመመስረት የተገደደችበትን ፍፁም #ሰብዓዊነት የገለፀ ሲሆን፣
“ፍርድ ቤቱ #የተኩስ_አቁም_ውሳኔ_ቢያወጣ #ደስ_ባለን_ነበር!”በማለት ውሳኔው የጅምላ ጭፍጨፋ እንድቆም እንጅ የተኩስ አቁም እንድደረግ ውሳኔ ባለማሳለፉ የተሰማቸውን ቅሬታ ተናግረዋል።
👌የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም በበኩሉ በጋዛ ውስጥ #የተኩስ_አቁም ከሌለ በስተቀር የዓለም አቀፍ ፍርድቤት ትእዛዝ ተፈፃሚ ይሆናል ብሎ እንደማያስብ ስጋቱንና ቅሬታውን የገለፀ ሲሆን “ለማንኛውም ግን ይሄም ቢሆን የፍትህ ፍርድ ቤቱ ውሳኔዎች እስራኤል ለአለም አቀፍ ህግ ያላትን ቁርጠኝነት #ለመገምገም ጠቃሚ ምልክት እና ፈተና ነው!”ብሏል።
በመጨረሻም “ደቡብ አፍሪካ #ፍልስጤማውያን ትክክለኛ ፍትህ እስከሚያገኙ ድረስ #ከጎናቸው ስለምትቆም በፍፁም #ተስፋ_እንዳይቆርጡ እንጠይቃቸዋለን!”በማለት #ደቡብ_አፍሪካ ምን አይነት የሰብአዊነት ውሃልክ እንደሆነች በአለምህዝብ ፊት ፍልስጤማዊያን መቸም ሊረሱት የማይችሉት ልብ የሚነካ መግለጫ የሰጠው የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ራሷን ብቸኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አድርጋ ስታቀርብ የነበረችውና በጋዛ የዘርማጥፋት ወንጀል #ቀጥተኛ ተሳታፊ የሆነችውን እጅግ መጥፎና አስመሳይ #አሜሪካ ብሎ ሀገር ፕሬዝዳንት ጆባይደን“በጋዛ ህይወትን ለማዳን በሚያበረክተው ማንኛውም የሰብአዊ ስራ ላይ መርዳት አለባቸው!”በማለት በአሽሙር ነካ አድርጎታል!
👌ሌላኛው ስለዛሬው የፍርድቤት ውሳኔ ሀሳብ የሰጠው የደቡብ አፍሪካ አቃቤ ህግ ቡድን“ሁሉም ሀገራት የዛሬውን የፍትህ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲያከብሩ እንጠይቃለን፤ፍርዱ ማንም ሰው ከህግ በላይ እንዳልሆነ ለእስራኤል ግልፅ መልእክት ነው!”ብሏል።
👌አሁንም ከደቡብ አፍሪካ ሳንወጣ በዛሬው የፍርድቤት ውሳኔ ዙሪያ ሀሳብ የሰጡት የደቡብ አፍሪቃ የፍትህ ሚኒስትር በበኩላቸው“እስራኤል የአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ውሳኔን ታከብራለች ብለን ተስፋ እናደርጋለን!”ያሉ ሲሆን በማስከተልም “እኛ ደቡብ አፍሪካዊያን የዘር ማጥፋት ኮንቬንሽኑ ተከላካይ በመሆናችን
የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ በመቃብራቸው ውስጥ ፈገግ የሚሉ ይመስሉናል!”በማለት ባደረጉት ሰብአዊነትና የሞደላቸውን የደቡብ አፍሪካ የነፃነት ታጋይና የመጀመሪያው ፕሬዝዳንታቸውን ኔልሰን ማንደላ ራእይ እውን በማድረጋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።

👌በዛሬው የፍርድቤት ውሳኔ ዙሪያ አስተያየታቸውን ከሰጡ የሀገራት መሪዎች መካከል #የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሆን፣
“የዓለም አቀፉን የፍትህ ፍርድ ቤት ውሳኔ በደስታ እንቀበላለን!እናም የተለያዩ አካላት ፍርድቤቱ ያወጣቸውን ጊዜያዊ እርምጃዎች ተግባራዊ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን!”ብሏል።
ፕሬዝዳንቱ በማስከተልም“ጦርነቱ እንዲቆም፣ታጋቾቹ እንዲፈቱ እና ከእስራኤል ጎን ለጎን #የፍልስጤም_መንግሥት እንዲመሰረት ጥሪያችንን እንቀጥላለን!”ብሏል።

👌ሌላኛው ሀሳባቸውን የሰጡት #የአየርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሆኑ እርሳቸውም “የአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ውሳኔዎችን በደስታ እንቀበላለን! እናም ይህንን ግጭት ማስቆም በሁሉም ወገኖች ሊተገበር የሚገባው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው!”ብለዋል።

👌ከዛሬው የፍ/ቤት ውሳኔ በኋላ ሀሳባቸውን ካስተላለፉት መሪዎች መካከል #የቤልጂየም ጠቅላይ ሚኒስትር በበኩላቸው “እስራኤል በአለም አቀፍ የፍትህ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውስጥ ያሉትን ጊዜያዊ እርምጃዎች ሙሉ በሙሉ እንድትተገብር እንጠይቃለን!”ብለዋል።

👌 #የስኮትላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር በበኩሉ“የፍትህ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ግልጽ ነው!እናም በጋዛ ያለው ግድያ እና ውድመት መቆም አለበት!”ብሏል።