𝚂𝚎𝚢𝚏𝚎𝚕𝙸𝚜𝚕𝚊𝚖 ሰይፈል ኢስላም!
375 subscribers
1.44K photos
150 videos
9 files
329 links
قال ابن تيمية -رحمه الله-:
{قوام الدين كتاب يهدي وسيف ينصر وكفى بربك هادياونصيرا}
مجموع الفتاوى [10/13]
Download Telegram
#የኢስራኤልናፍልስጤምግጭት_መቼ_እና_እንደት_ጀመረ??
#ታሪካዊዳራ___ክፍል
"ኢስራኤል በተ/መ/ድ እንደ ሃገር እውቅና ካገኘችበት እ.ኤ.አ.1947 ጀምሮ እስከ ዘመነ ትራምፕ ድረስ ያለው ሁኔታ!!"
________
#የ1947ቱ የተ/መ/ድ የፀጥታው ምክርቤት #ኢፍትሐዊ ውሳኔ፣በርካታ ፍልስጤማዊያንን ክፉኛ ያስቀየመ ከመሆኑም ባሻገር በርካቶችን ተወልደው ካደጉባቸው መንደሮች እንድፈናቀሉ ምክናየት ሆነ።
ይህ ኢፍትሐዊ ውሳኔ የተላለፈበትን ቀን ፍልስጤማውያን በየአመቱ “በናክባ ቀን”አስበውት ይውላሉ።ይህም “ጥፋት” ለሚለው የአረብኛ ቃል የተሰየመ ሲሆን ፍልስጤማውያን ለቀው እንዲወጡ የተገደዱባቸውን ቤቶች ቁልፍ በማመልከት #አሁንም_ተመልሰው_እንደሚኖሩባቸው_ተስፋ_ያልቆረጡባቸውን_ግዛቶች ለመዘከር የታሰበ ነበር።
እ.ኤ.አ. በ1948 የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ፍልስጤማውያን “ #ወደቤታቸው_ተመልሰው_ከአይሁድ_ጎረቤቶቻቸውጋር_በሰላም_ለመኖር_የሚፈልጉሁሉ_በተቻለፍጥነት_ይህን_የማድረግመብት_ሊኖራቸው_እንደሚገባ” በመገንዘብ #ውሳኔ194ን አፀደቀ ፡፡ እስራኤል ምንም እንኳን ይህ በሃይልና በዙልም ከመኖሪያ ቤታቸው ያስለቀቋቸው ነባር ፍልስጤማውያን ወደ መኖሪያ ቤታቸው ተመልሰው ከቤታቸውና ከቀያቸው አስለቅቀው የራሳቸውን መንግስት ከመሰረቱ መጤ አይሁዶች ጋር በጉርብትና እንድኖሩ በሚል ተ/መ/ድ ያወጣውን ውሳኔ፣አድሱ የኢስራኤል መንግስት በቅፅበት ፈቃጅና ከልካይ ሁና" #የፍልስጤሞች_ወደዚህ_መመለስ_ለአዲሱ_የአይሁድ_መንግስት_ተፈጥሮአዊስጋት ነው!"በሚል ሀሳብ ውሳኔውን ላለመቀበልም ዳዳት!
ከአንድ ዓመት በኋላ ለተፈናቀሉ"ፍልስጤማውያን" ወገኖች ድጋፍ ለመስጠት በቅርብ ምስራቅ የሚገኙ የፍልስጤም ስደተኞች #የተባበሩትመንግስታት_የእርዳታ_ስራዎች_ኤጄንሲ( #UNRWA)ተቋቋመ።
በእነዚያ ሁለት ክስተቶች መካከል ባለው ጊዜ እስራኤል #ከአጎራባች አረብ አገሮች ማለትም ከሊባኖስ፣ከሶሪያ ፣ከጆርዳን እና ከግብፅ ጋር የጦር መሣሪያ ስምምነቶችን ተፈራረመች።
ከዚያም እ.ኤ.አ.በ1950 ዮርዳኖስ የዌስት ባንክ አስተዳደራዊ ቁጥጥርን ስትወስድ፣ግብፅ ደግሞ ጋዛን እንድትወስድ ተደረገ።
ይህ ስምምነት እስራኤል እነዚህን ግዛቶች ከዮርዳኖስና ከግብፅ አስለቅቃ ለመውሰድ እንቅስቃሴ እስከጀመረችበትና በዚህም #የ6ቀኑ_የአረብ_ኢስራኤል_ጦርነት እስከተጀመረበት ግዜ ድረስ ቆየ።
(የ6ቱን ቀን የአረብ-እስራኤል ጦርነት ሂደት በሌላ ፅሁፍ እመለስበታለሁ ኢንሻ አሏህ)
ከዚያ በፊትም ብጥብጡ አልፎ አልፎ ቀጥሎ የነበረ ሲሆን፣በ1956 በቃልኪሊያ፣በኩፍርቃሲም እና በሃን ዩኒስ መንደሮች ውስጥ፣እንድሁም በ1966 አስሳሙ በተባሉ ቦታዎች እልቂቶች ተከስተዋል።
#በ1964 #የፍልስጤም_ነፃ_አውጪ _ድርጅት(PLO)ካይሮ ውስጥ የተቋቋመ ሲሆን፣ከሰላማዊ ትግል ይልቅ በትጥቅ አብዮት “ፍልስጤም ነፃ ለማውጣት”የተመሰረተ ነበር።እስራኤልናአሜሪካ ድርጅቱን በአሸባሪነት ቢፈርጁትም፣የፍልስጤም ህዝብ ብቸኛ ተወካይ መሆኑን የአረብሊግ በ1974 እውቅና ሰጠው።
የእስራኤል ወታደራዊ ጦር በጋዛ ሰርጥ፣ በዌስትባንክ፣በጎላን ከፍተኛቦታዎች እና በግብፅ ሲናይ በረሃ፣በ1967 ከፍተኛ ደም መፋሰስ ያስከተለ ሲሆን፣የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት በሃይል ተይዘዋል ብለው ካሰቡዋቸው ግዛቶች እስራኤል ጦሯን እንድታወጣ በማዘዝ #ውሳኔ242 ቢያፀድቅም፣እስራኤል ከቆብ አልቆጠረችውም ነበር።
እስራኤል በ1970 በዮርዳኖስ ውስጥ ከፍልስጤማውያን ወታደሮች ጋር በጥቁሯመስከረም(Black September)ተጨማሪ ውጊያ ማድረጓን ተከትሎ፣"የፀጥታው¡"ምክርቤት የተኩስ አቁም ጥሪ በማቅረብ እና እስራኤል ከ 1967ቱ ወረራ እንድትመለስ በመጠየቅ #ውሳኔ338 አስተላለፈ።
አሁንም እስራኤል እምቢ አለች!
በፍልስጤማውያን"የመሬትቀን"ተብሎ የሚዘከርበት፣ማርች30ቀን1976፣ የእስራኤልን የመሬት ወረራ በመቃወም ከገሊላ ባህር እስከ ኔጌቭ ድረስ ባሉ ከተሞች አመጽ፣አድማ እና ተጨማሪ የኃይል እርምጃዎችን አስከተለ።
እ.ኤ.አ.መስከረም17ቀን 1978፣የእስራኤሉ ጠ/ሚ #ሜናም_ቤገን ከግብፁፕሬዝዳንት #አንዋር_ሳዳት ጋር በፕሬዚዳንት በጂሚ ካርተር ማረፊያ የካምፕ ዴቪድ ስምምነቶችን ለመፈራረም ተገናኙ። ስምምነቱ በሁለቱ ሃገሮች(እስራኤልናግብፅ)መካከል ግንኙነታቸውን ያጠናከረና #የሰላምኖቬል_ሽልማት ያስገኘላቸውሲሆን፣በሌላ በኩል ግን ስምምነቱ የባለጉዳዮቹ ፍልስጤማውያን ውክልና የሌለበት በመሆኑ፣ግጭቱን ከማባባስ የዘለለ የፈየደው አንዳችም ነገር አልነበረም።
የእስራኤል ጦር በጋዛ የሚገኙ 4 ሲቪል ፍልስጤማዊያንን በግፍ በመግደሉ ምክናየት፣December 8, 1987 በፍልስጤምግዛቶች ውስጥ በአይነቱየመጀመሪያ የሆነ ከባድሁከት( #The_First_Intifada)ተነስቶ እስከ መስከረም13,1993 ድረስ ቆየ።
በ1993 #የኦስሎI_ስምምነት(Oslo1) በእስራኤል ጠ/ሚ #ይስሃቅ ራቢንና የ PLO ሊቀመንበር #ያሲር_አራፋት የተፈረመ ሲሆን፣የፍልስጤም ጊዜያዊ የራስገዝ አስተዳደር እንድመሰረትና የእስራኤል ጦር ከተ/መ/ድ እውቅና ውጭ በሃይል ከያዛቸው ቀጠናዎች እንዲወጣ ተደረገ፡፡ነገር ግን ኢስራኤል ስምምነቱን በማፍረሷ
#ሁለተኛው_የኦስሎ_ስምምነት(Oslo2)እ.ኤ.አ.በ1995 ተደረገ።በዚህም በተወሰኑ የዌስትባንክ እና የጋዛ አካባቢዎች የፍልስጤም የራስ ገዝ አስተዳደርን እውቅና ቢሰጥም፣የፍልስጤምን ሉኣላዊ ሃገርነት ግን አሁንም አላፀደቀም ነበር።
በመስከረም28,2000 #ሁለተኛውከባድ አመፅ( #the second Intifada)የተቀሰቀሰ።ዋነኛ ምክናየቱ የእስራኤል ጠ/ሚ #አርኤል_ሻሮን #በአልአቅሷ መስጅድ ጉብኝት ማድረጉ ነበር።
በ2002 እስራኤል ዌስትባንክን ወረረች።ይህም #በ2004_ከያሲር_አራፋት_ሞት ጋር ተዳምሮ ፍልስጤማውያንን ክፉኛ ጎዳቸው።
በ2006 በፍልስጤም በተካሄደ ምርጫ #ሃማስ አብላጫ ድምፅ በመያዝ አሸነፈ።ሆኖም በምርጫ የተሸነፈው ፋታህ(PLO)ውጤቱን ባለመቀበሉ ሃማስናፋታህ #የርስበርስ_ጦርነት አደረጉ።በመጨረሻም ሃማስ ጋዛን ሲቆጣጠር፣ፋታህ ደግሞ ዌስትባንክን ያዘ።
በ2006 እስራኤል በሊባኖስ በሚገኘው"ሂዝቦላህ"የተባለ ቡድን ላይ ጦርነት አወጀች።
አስከትላም በጋዛ በሚገኘው ጅሃድስት ቡድን(ሃማስ)ላይ፣ኦፕሬሽን ካስት ሊድ(2008)፣ኦፕሬሽን የመከላከያ ዓምድ(2012) እና የኦፕሬሽን መከላከያ ጠርዝ(2014)ን ጨምሮ በጋዛ ውስጥ በተደጋጋሚ ጥቃት መሰንዘር ጀመረች፡፡ ይህ ሳያንሳት በ2017 እና በ20018፣ፍልስጤማውያን የናክባ ቀን በሚያስቡበት እለት፣በተ/መ/ድ #የጦርወንጀሎች_ምርመራ የሚያስጠይቅ የሆነ ከባድጥቃት አደረሰች።
በ2017በአሜሪካ በተደረገው ምርጫ #ዶናልድ_ትራምፕ መመረጥ ሁኔታውን ዳግም አገረሸው።ለዚህም ዋነኛ ማሳያ ትራምፕ የአሜሪካን ኤምባሲ #ከቴልአቪቭ_ወደ_ኢየሩሳሌም ማዘወሩ ነበር፡፡ትራምፕ ዓለም አቀፍ ህጎችን በመጣስ፣ #የጎላን ከፍተኛቦታዎችን የእስራኤል መሆናቸውንም አፀደቀ።
ይህም አልበቃ ብሎት አሜሪካ ለUNRWA የምትመድበውን የገንዘብ ድጋፍም አቋረጠ።🔚
የዚህን ፅሁፍ ክፍል①እና②ለማግኘት👉t.me/Abdelaziz_Bin_Muhammed ይጎብኙ።
የመረጃ ምንጮቸ
#አልጀዚራ #ቢቢሲ #ዊኪፔድያ
#ኢንሳይክሎፔድያብሪታኒካ #ዘጋርድያን #ሂስትሪዶትኮም እና ሌሎችም ናቸው።
ጥያቄ/አስተያየት ለመስጠት ከፈለጉ በቴሌግራም t.me/ServantOf_Almighty ላይ ይፃፉልኝ።

t.me/Seyfel_Islam
#የኢስራኤልናፍልስጤምግጭት_መቼ_እና_እንደት_ጀመረ??
#ታሪካዊዳራ___ክፍል
"ኢስራኤል በተ/መ/ድ እንደ ሃገር እውቅና ካገኘችበት  እ.ኤ.አ.1947 ጀምሮ እስከ ዘመነ ትራምፕ ድረስ ያለው ሁኔታ!!"
____

የመረጃ ምንጮቼ: