STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.9K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ትኩረት...

አሁንም ቢሆን በአንዳንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚበተኑት የማስፈራሪያ ወረቀቶች ቀጥለዋል፡፡ ይህ ጉዳይ ተማሪውን ሰላም ከሚነሱ ጉዳዮች ዋነኛውና አንዱ ቢሆንም እነዚህን ወረቀቶች በሚያዘጋጁና በተደራጀ መልኩ በመማሪያ ክፍል በመኝታ አከባቢ እየተንቀሳቀሱ ማስፈራሪያ የሚያደርጉ አካላት ላይ ትኩረት ያለመደረጉ የታሰበውን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራ እንዳይጀመር ያደርገዋል። በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከዚህ አካባቢ የመጣችሁ አትማሩም፣ ከዚህ ሂዱልን የሚሉ ለሀገር አደጋ የሆነ ድርጊት እየተፈፀመ ይገኛል። ይህ ጉዳይ ከወዲሁ ትኩረት ካልተሰጠው ለዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ሳይሆን ለሀገር አደጋ ነው። ተማሪዎች የሀገሪቱ ሚዲያዎች እያቀረቡት ያሉት ዘገባ እውነታውን የደበቀ እንደሆነ ወቅሰዋል። ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች የሚላኩትን የስጋት መልዕክቶች እንዲሁም ጥቆማዎች እና ችግሮች ለሚመለከታቸው አካላት ለማድረስ ጥረት እያደረግን እንገኛለን።
@nationalexamsresult
Via#ቲክቫህ
@nationalexamsresult
#ኦዳ_ቡልቱም_ዩኒቨርሲቲ

በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ውሳኔ መሰረት ለ15 ቀናት ተቋርጦ የነበረው ትምህርት ሐሙስ ታህሳስ 02 2012ዓ.ም እንደሚጀምር ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል። በዕለቱም መምህራንና ተማሪዎች በመማሪያ ክፍል እንድትገኙ ጥሪ አቅርበል። የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ አያይዞም በ2012 ዓ.ም እና ከዚያ በፊት ባሉት አመታት በሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል ተመድበው በዩኒቨርሲቲው ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ከነበሩ ተማሪዎች ውጪ በማንኛውም ምክንያት ከየትኛውም ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን አቋርጦ የመጣን ተማሪ እንደማያስተናግድ ገልጿል፡፡
@nationalexamsresult
Via #ቲክቫህ @nationalexamsresult
#ባህርዳር_ዩኒቨርሲቲ

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ላይ ያወጣው መግለጫ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል ከባለ ድርሻአካላትና ከባህርዳር ከተማ ወጣቶች ጋር እየሰራ መሆኑን ገልጾ ተማሪዎችም እስከ ታህሳስ 6 ድረስ ሙሉ ለሙሉ ትምህርት እንደሚጀምር ተረድተው እንዲገኙ ጥሪ አቅርቧል፡፡

አሁንም ግን በተለያዩ ቦታዎች የሚሰጡ ማስፈራሪያዎች ተማሪዎችን እየረበሻቸው ይገኛል፡፡ ከማስታወቂያ ጥሪ በተሻለ ተማሪን ማቀራረብና ወጣቱን አስተባብሮ ዘላቂ ሰላም ማስፈን ያስፈልጋል ሲሉ መልዕክታቸውን ለቲክቫህ የላኩ ቤተሰቦቻችን ገልጸዋል፡፡
@nationalexamsresult
Via #ቲክቫህ
@nationalexamsresult
ለተመሳሳይ ችግሮች ተመሳሳይ መፍትሔዎች መወሰድ አለባቸው

አሁንም ደግመን የምንናገረው ቤተሰቦቻችንም በተደጋጋሚ የሚያሳውቁን ጉዳይ አሁንም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ ችግሮችና ስጋቶች በሚፈለገው ልክ አልተወገዱም የአብዛኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ችግር ደግሞ ተመሳሳይ ነው፡፡ ለእነዚህ ለሚስተዋሉ ተመሳሳይ ችግሮች መፍትሔ መምጣት የሚችለው የጋራ መፍትሔዎች ላይ ስናተኩር ብቻ ነው፡፡አሁንም ተማሪዎች በስጋት ከዩኒቨርስቲ እየወጡ ነው አሁንም ወደቤተሰቦቻቸው የሄዱ ተማሪዎች ለመመለስ ፍርሃት አላቸው አሁንም ትምህርት በተጀመረባቸው ዩኒቨርሲቲዎች መማሪያ ክፍሎች ውስጥ የተወሰኑ ተማሪዎች ነው ያሉት እውነት ትምህርት ስላልፈለጉ ነው? መማር ስለሰለቻቸውስ ይሆን?

በተደጋጋሚ ትኩረት የምንለው መንግስትን ብቻ አይደለም የምንናገረው! በርግጥ ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስደው እርሱ ቢሆንም ተማሪዎች፣ የአከባቢው ነዋሪዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ አክቲቪስቶች፣ መምህራን፣ በተለይ የዩኒቨርስቲው የአስተዳደር ሰራተኞች ሁሉም የራሳቸው ድርሻ አላቸው፡፡ ስለዚህ መፍትሔ የጋራ ይሁን የሙከራ ጊዜ ይብቃ ይህ ካልሆነ ከህመማችን ማገገም እንችል ይሆናል መዳን ግን አንችልም፡፡ አሁንም ትኩረት!
@nationalexamsresult
#ቲክቫህ
@nationalexamsresult
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ የኩፍኝ በሽታ መከሰቱን ዩኒቨርስቲው አስታወቀ!

በአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ የኩፍኝ በሽታ ከአንድ ሳምንት በፊት መከሰቱ እና በአሁኑ ሰዓት የህክምና ክትትል እያደረጉ እንደሚገኙ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ተወካይ በድሩ ሂሪጎ በተለይ ለኢቲቪ አስታወቁ።

ሆስፒታል ከገቡ ስድስት ተማሪዎች መካከል ሐዋሳ ከተማ የደም ናሙና ተልኮ የኩፍኝ በሽታ ምልክት የተገኘባቸው 3 ተማሪዎች ናቸው ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓት ለእነዚህ ተማሪዎች በዩንቨርስቲው ልዩ ክትትል እና እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑም ተገልጿል።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አየልኝ ጎሳ በበኩላቸው፣ ዩኒቨርስቲው ከዞኑ ጤና መምሪያ እና ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር በመተባበር ለሁሉም ተማሪዎች የኩፍኝ በሽታ ክትባት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል ሲሉ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት የታመሙት ተማሪዎች በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ እና ከሶስት ቀናት በኋላ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንደሚመለሱ አመልክተዋል።
@nationalexamsresult
(EBC)
@nationalexamsresult
#ቲክቫህ
@nationalexamsresult
በርካታ መልዕክቶች ደርሰውናል ሁሉንም ባናዳርስም ሁሉም መልዕክቶች ተመሳሳይ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡

1. የወጣው ህግ ሰላም የሆኑ ግቢዎችን መጨመሩ ምንም አይነት ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ሲሆን ጭራሽ ወዳልተፈለገ ጭንቀት ውስጥ ይጨምራል፡፡ በሰላም ስንማር የነበርነውን ተማሪዎችንም ከትምህርታችሁ ተዘናጉ እንደማለት ይቆጠራል ብለዋል፡፡

2. የሰዓት ገደቡ የእምነት ተቋማትን የሥርዓት ሁኔታ ያላገናዘበ ነው ሲሉ በርካታ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡

3. በተለይ እየሰሩ የሚማሩ፣ የማታ የሚማሩ ተማሪዎች በግቢ ውስጥ እንዳሉ ይታወቃል ይህ ህግ ሲወጣ እኛ ላይ የህልውና ጉዳይ ነው ካልሰራን መማር አንችልም ሲሉ ገልጸውልናል፡፡

4. ተማሪ ከአራት ሰዓት በፊት ሁሉም ተማሪ ወደዶርም ገብቶ ሁሉም ተማሪ በተሰበበት እንዴት ተደርጎ ይጠናል፡፡ ላይብረሪም እንዴት ተደርጎ ይነበባል ውጪ የምንመገብ ተማሪዎችስ እንዴት ሆነን ልንመለስ ነው፡፡

5. መንግሥት የተሻለ መፍትሔ መውሰድ ይችላል ይሄ ድንገት ማንም ተነስቶ ማድረግ የሚችለው ነገር ነው ሁኔታዎች ተጠንተው ቢደረጉ መልካም ነው፡፡

በአንጻሩ ደግሞ አስተያየታቸውን በበጎ የሰጡም አልጠፉም በተለይ መልዕክታቸውን የላኩልን የተማሪ ቤተሰቦች እኛ በስጋት ልናልቅ ነው፡፡ እንዲህ ጠንከር ያለ እርምጃ መወሰዱ ጥሩ ነው ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ይህ ህግ ከመልካም ጎኑ ብንመለከተውም ጊዚያዊ እንዲሆን አጥብቀን እንመኛለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ ህጉ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ እንደበርካቶቹ ቤተሰቦቻችን ገለጻ ሰላማዊ በሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ተግባረዊ መሆን አይገባውም ሲሉ ጠንከር ያለ አስተያየታቸውን ሰጥተውናል፡፡



#ቲክቫህ_ዩኒቨርስቲ

@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
#JIT

የጅማ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲቲውት የትምህርት ማቆም አድማው አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ የተደረጉ ውይይቶች አሁንም ውጤታማ አልሆኑም፡፡ የሚነሳው ጥያቄም " የኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች በክልልላቸው መጥተው ካልተመደቡ ትምህርት አንጀምርም" የሚል እንደሆነ ለተማሪዎች እየተበተነ ካለው የማስፈራሪያ ወረቀት ላይ ተጠቅሷል፡፡ በዚሁ ወረቀት ላይ "ሁሉም ተማሪዎች ከ22/04/2012 - 25/04/2012 ድረስ ሙሉ ለሙሉ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ " ሲልም ያሳስባል፡፡ ተማሪዎች በበኩላቸው ይህንን መልዕክት በመመልከት መሸበራቸውንና ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ እንደተጋቡ ገልጸውልናል፡፡

ተማሪዎቹ "ነገ የዩኒቨርስቲው ሴኔት ውሳኔ ይሰጣል የሚባል ወሬ ስላለ እሱን ሰምተን እንሄዳለን ብለን ተቀምጠናል" ሲሉ ይናገራሉ፡፡ በሌላ በኩል በርካታ የግቢው ተማሪዎች ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል፡፡ አሁን የሚሰሙት ነገር ምንም አይነት ዋስትና የሌለው እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ ተማሪዎቹ አክለውም " እንዲህ አይነት ማስፈራሪያ ቤታችንም ጭምር ሆነን ይደርሰናል ትምህርታችንን ለመከታተል ብንመጣ ምንም እንደማይደርስብን ዋስትና የለንም ምን ማድረግ እንዳለብን እንኳን አናቅም" ሲሉ ይገልጻሉ፡፡ በየዩኒቨርሲቲው የሚሰራጩ የማስፈራሪያ ወረቀቶች አሁንም ስጋቶች መሆናቸውን ቀጥለዋል፡፡
@nationalexamsresult
#ቲክቫህ
@nationalexamsresult
#semester_project #Hawasa

በ5ኛ አመት የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ electromechanical ተማሪዎች የተዘጋጀ (semester project) የፈጠራ ስራ ለተመልካቾች እየቀረበ ይገኛል

ቦታ 👉 IOT Regstrar

ለዕይታ እየቀረቡ ካሉ ሥራዎች መካከል፡-

- የፈለግነውን አይነት ስእል ወይንም ቅርጽ መሳል የሚያስችል ማሽን

- በአናሎግ እና በ ሞባይል app voice record የሚሠራ የአካል ጉዳተኛ መንቀሳሻ ዊልቸር

- Automatic car parking system

- Heart Beat and Body Temptation monitoring system

- Gesture controled vehicle

- Vehicle forward collision detection warning system

አንዲሁም ሌሎች የፈጠራ ስራዎች እየቀረቡ ይገኛል፡፡ የፈጠራ ባለቤቶቹን ለማግኘት ሙከራ እያደረግን ነው!
@nationalexamsresult
#ቲክቫህ
@nationalexamsresult
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተወሰደ እርምጃ  

-2 ተማሪዎች አንድ አመት ከትምህትር ገበታቸው እንዲታገዱ
- 39 ተማሪዎች ለሁለት አመት ከትምህርት ገበታቸው እንዲታገዱ
- 11 ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ከትምህርት ገበታቸው(ከዩኒቨርሲቲው) እንዲሰናበቱ ተወስኗል፡፡ 
ከዚህም በተጨማሪ

- ለ7 መምህራን ቀላል የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣
- ለ3 መምህራን የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ፣
- ለ3 መምህራን እና
- ለ8 የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም የጤና ባለሙያ ሙሉ በሙሉ ከስራ እንዲሰናበቱ ተወስኗል፡፡ 

ተጨማሪ ያንብቡ 👉 https://telegra.ph/ETH-01-03
@nationalexamsresult
(ጎንደር ዩኒቨርሲቲ )
@nationalexamsresult
#ቲክቫህ
@nationalexamsresult
#ወሎ_ዩኒቨርሲቲ
@nationalexamsresult
በወሎ ዩኒቨርሲቲ ህይወቱ ያለፈው ተማሪ አስከሬኑ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ተልኳል፡፡
@nationalexamsresult
በተማሪው ግድያ የተጠረጠረ አንድ ተማሪ ከነግብረ አበሩ በትናንትናው ዕለት በጸጥታ አካላት ትናንት ምሽት ከ3፡00 ሰዓት ጀምሮ በተደረገ የዶርም ለ ዶርም ጥብቅ ፍተሻ ምሽት 4፡00 ሰዓት አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
@nationalexamsresult
በግድያው የተጠርጣሪውን ተማሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል ከፍተኛውን ድርሻ የተወጡት የግቢው ተማሪዎች ሲሆኑ የተለያዩ የጸጥታ አካላትና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈውበታል ተብሏል፡፡
@nationalexamsresult
ዩኒቨርሲቲው ጥቆማውን ለሰጡት ተማሪዎች ምስጋናውን ያቀረበ ሲሆን ወደፊትም ሁሉም ተማሪ ግቢውን ነቅቶ በመጠበቅና ማንኛውንም ያልተለመደ እንቅስቃሴ ሲያስተውል በመጠቆም ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።
@nationalexamsresult
( ወሎ ዩኒቨርሲቲ )
@nationalexamsresult
Via #ቲክቫህ
@nationalexamsresult
#ዋቻሞ_ዩኒቨርሲቲ

የዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ከታች ባሉት መዳረሻዎች ተማሪዎቹን እንደሚሸኝ አስታውቋል፡-

- አዲስ አበባ
- ጅማ
- አዳማ
- ሀዋሳ
- አርባምንጭ

[#ቲክቫህ]

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን👇
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
#Update

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቻችን ወደ ቤተሰብ ለማጓጓዝ ያቀደው የጉዞ መስመር ይፋ አድርጓል፡፡

1ኛ. ጎንደር - አዲስ አበባ
2ኛ. ጎንደር - ባህር ዳር
3ኛ .ጎንደር - ደሴ
4ኛ. ጎንደር - ደባርቅ

ይህም ከተማሪዎች አደረጃጀት፣ ከጥበቃና ደህንነት እንዲሁም ከትራንስፖርት ዘርፉ ጋር በመመካከር ተፈፃሚ ይሆናል ብሏል፡፡

[#ቲክቫህ]

#SHARE
ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
የሀረማያ ተማሪዎች አሁንም ቅሬታ እያቀረቡ ነው!

" እኛ ስንት ጊዜ ነው በጸጥታ ጉዳይ የተመላለስነው ዩኒቨርሲቲው ይህንን እንኳን ማገናዘብ አልቻለም፡፡ አቅም ያላቸው ሄደዋል አቅም የሌለንን ለምን አይሸኘንም፡፡ ሌሎች ግቢዎች ሙሉ ተማሪዎችን ሲሸኙ የኛ ዩኒቨርሲቲ ከሌሎቹ በምን ይለያል፡፡ እኛስ ተማሪዎች አይደለንም እንዴ አንድ በሉልን እኛ መጉላላቱ በዛብን! "

(#ቲክቫህ)

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSREAULT
#Update

ከሠመራ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቤታቸው ሲሄዱ በደረሰ አደጋ ህይወታቸው ያለፉ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡ የ5ኛ ዓመት ሲቪል ኢንጅነሪንግ ትምህርት ክፍል ተማሪ የነበረው ድሪባ ተፈሪ እና የ1ኛ ዓመት የሶሻል ሳይንስ ተማሪ የነበረው ታፈሰ ሀብታሙ ወደ ቤተሰብ ሲሄዱ በደረሰ ድንገተኛ የመኪና አደጋ በ16/07/2012 ህይወታቸው አልፏል፡፡

ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን!

ምንጭ፡- ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የሬጅስትራር እና አልሙኒ ጽ/ቤት

[#ቲክቫህ]


ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSREAULT
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎቹ ተመሰገነ....

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመላክ ባዘጋጀው መርሀ ግብር መሰረት መጋቢት 18/2012 ዓ.ም በሁለተኛ ዙር የተመደቡትን 12 የአገራችን መዳረሻ ከተማዎች ሸኝቷል፡፡ እነዚህም፡-

ሆሳና፣ ጋምቤላ፣ አሶሳ፣ ደብረ ብርሃን-ከሚሴ፣ አርባ ምንጭ፣ ባህር ዳር-ደ/ማርቆስ፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ወልዲያ፣ ጎዴና ዶሎ አዶ 30 አገር አቋራጭ አውቶቢስና 2 ሚኒባስ እንዲሁም አዲስ አበባ-አዳማ ተጓዦችን የሙቀት መለኪያቸው እየታየ በባቡር ሲላኩ አጠቃላይ 3,262 ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው መልሷል፡፡

የሦስተኛ ዙር ጉዞ በነገው እለትም ወደ ተለያዩ የአገራችን የክልል ከተሞች ተማሪዎችን የመላክ ስራ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ በርካታ ተማሪዎች በላኩልን መሰረት ዩኒቨርሲቲውን ከልብ አመስግነዋል፡፡

[#ቲክቫህ]

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSREAULT
ፎቶ📸| አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር አምርቶ ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ማከፋፈል ጀምሯል፡፡

[#ቲክቫህ]

#SHARE
ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ተቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
@NATIONALEXAMSRESULT
STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
"የሕወሃት ሰራዊት መቀለ ከተማ ገብቷል" ተብሎ ከተነገረበት ሰአት ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል የስልክ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡ ከአዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና መቀለ ዩኒቨርሲቲ ቤተሰቦቻችን ጋርም ያለን ግኑኝነት ተቋርጧል፡፡ በመሆኑም በትግራይ ክልል ወዳሉ ዩኒቨርሲቲዎች መረጃ እንድናቀብላችሁ እጅግ ብዙ ወላጆች እና ተማሪዎች የጠየቃችሁን ሲሆን ምላሽ መስጠት ያልቻልነው በዚህ ምክንያት እንደሆነ ለማሳወቅ እንወዳለን።…
#ቲክቫህ_እንደዘገበው

በመቀለ ከተማ የተመደቡ ፌደራል ፖሊሶች እና የመከላከያ ሰራዊት ከተማውን ለቀው እንደወጡ በሌላ በኩል ደግሞ የትግራይ ክልል ልዩ ሀይል ወደ ከተማው እየገባ እንደሆነ መረጃ ደርሶናል

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግቢው ውስጥ ጥበቃ ያደርጉ የነበሩት ፌደራል ፖሊሶች እና የመከላከያ ሰራዊት ግቢውን እና ከተማውን ለቀው እንደወጡ በሌላ በኩል ደግሞ የትግራይ ክልል ልዩ ሀይል ወደ ከተማው እየገባ እንደሆነ ገልፀውልናል። በትላንትናው ዕለት ወደ መቀሌ ዩንቨርሲቲ የገቡ ተማሪዎችም ትግራይ ክልል ከገቡ በኋላ በትግራይ ክልል ልዩ ሀይል አባላት እንደተፈተሹ ገልፀውልናል።

በአሁኑ ሰዓት የመቀሌ ከተማ ህዝብ የትግራይ ክልል ልዩ ሀይል መመለስን አስመልክቶ ከፍተኛ የደስታ ስሜት ላይ እንደሚገኝ በውስጥ ከደረሱን መረጃዎች እና ከዓለም አቀፍ ሚድያዎች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የሚገኙ ተማሪዎች ከግቢ መውጣትም ሆነ ወደ ግቢ መግባት እንደተከለከሉም ሰምተናል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
@NATIONALEXAMSRESULT
በ " ናዝሬት ትምህርት ቤት " እና በ " አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን " መሃከል የተፈጠረው ምንድነው ?

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው የናዝሬት ትምህርት ቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን መሃከል በተፈጠረ ውዝግብ ምክንያት የናዝሬት ት/ቤት መደበኛ ተማሪዎች ትምህርት መጀመር አለመቻላቸው ተገለፀ።

በሁለቱ አካላት መሃከል የተፈጠረው ውዝግብ የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዳስተጓጎለው ወላጆች ለቲክቫህ ገልፀዋል።

ውዝግቡ እንዴት ሊፈጠር ቻለ ?

- ናዝሬት ትምህርት ቤት ባሳለፍነው 2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በትምህርት ቤቱ ከሚማሩ ተማሪዎች መሀከል 15 ተማሪዎች ውጤት አጭበርብረዋል በማለት በዲሲፕሊን ጉድለት ምክንያት ከትምህርት ገበታ አግዷቸዋል።

- ይህንን ተከትሎ በናዝሬት ትምህርት ቤት ልጆቻቸው የታገዱባቸው የተማሪ ወላጆች ለአራዳ ክፍለ ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

- ቅሬታቸውን የሰማው የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት፤ ልጆቻቸው የታገዱባቸውን ወላጆች እና ናዝሬት ትምህርት ቤትን በጋራ ለማነጋገር ጥሪ አድርጎ ነገር ግን የናዝሬት ትምህርት ቤት የቦርድ አባላት ጉዳዮን ቀርቦ ለማስረዳት እንዳልቻሉ በፃፈው ደብዳቤ ገልጿል።

- የናዝሬት ትምህርት ቤት በበኩሉ "ጉዳዩን ቀርቤ ለማስረዳት ሞክሬ ነበር ነገር ግን የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የታገዱት ተማሪዎች በምን ምክንያት እንደታገዱ ሳይረዳ ተማሪዎቹን ወደ ትምህርት ገበታቸው እንድንመልሳቸው ጫና እያደረገብን ነው" በማለት ለጽ/ቤቱ በፃፉት ደብዳቤ ቅሬታቸውን ገልፀዋል። 

- አለመግባባቱን ተከትሎ የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ጉዳዮን የበላይ አካል ወደ ሆነው የአዲስ አበባ የትምህርትና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን መስሪያ ቤት የወሰደው ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የታገዱ ተማሪዎች ወላጆችን እና ትምህርት ቤቱን በጋራ ለማነጋገር ሞክሮ እንዳልተሳካ ገልጿል።

- ይህንን ተከትሎ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የትምህርት ቤቱን እውቅና ፈቃድ አግዶ የነበረ ሲሆን በነሃሴ 19 2015 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ "ትምህርት ቤቱ የታገዱ ተማሪዎችን ለመመለስ ተስማምቷል" በማለት የእውቅና ፈቃድ እገዳውን ማንሳቱን አሳውቋል።

- ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የእውቅና ፈቃድ እገዳውን አንስቻለሁ በማለቱ ትምህርት ቤቱ የተማሪዎች ምዝገባ ጀምሮ የነበረ ቢሆንም እንደገና ከባለ ስልጣን መስሪያ ቤቱ ምዝገባ አቁሙ የሚል የቃል ትእዛዝ መምጣቱን በመስከረም 4 , 2016 ዓ.ም ለወላጆች በማሳወቅ ምዝገባ በይፋ ማቆሙን አሳውቋል።

በዛሬው እለት የወላጅ ኮሚቴ መደበኛው ትምህርት እንዲጀመር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀራርቦ መነጋገሩ የተገለፀ ሲሆን የወላጅ ኮሚቴ አባል የሆኑት ዶ/ር ወንድወሰን ሙሉጌታ የታገዱት ተማሪዎች ተመልሰው እንዲመዘገቡና አዲስ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ተቋቁሞ ታግደው የነበሩት ተማሪዎች ጉዳይ በድጋሚ እንዲታይ እንደተወሰነ ከቲክቫህ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ አንስተዋል።

የወላጅ ኮሚቴው ከሚመለከተው አካል ጋር ከተነጋገረ በኋላ ፤ በነገው እለት የተማሪዎች ምዝገባ እንደሚጀምር ሲገለፅ ሰኞ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ/ም በይፋ ትምህርት እንደሚጀመር  ትምህርት ቤቱ አሳውቋል።

#ቲክቫህ

@NATIONALEXAMSRESULT
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ.ም አዲስ ገቢ አንደኛ ዓመት እና ለ2015 ዓ.ም ሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ አላደረገም‼️

#ቲክቫህ_ዩኒቨርሲቲ በጉዳዩ ዙሪያ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራርን ጠይቆ ተከታዩን ዘገባ አጋርቷል።

አሁን ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሀገሪቱ ገዢው ፓርቲ ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝና ስልጠናው እስከ ህዳር 30/2016 ዓ.ም እንደሚቆይ ኃላፊው ገልፀዋል።

በመሆኑም በታህሳስ የመጀመሪያ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ጥሪ ሊደረግ እንደሚችል ነው ኃላፊው የገለፁት።

Note:
ከላይ በምስሉ የሚታየው መልዕክት ለነባር መደበኛ ፕሮግራም የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች የተላለፈ መሆኑን ኃላፊው አብራርተዋል።

በነሐሴ 2015 ዓ.ም ወደ ተቋሙ ገብተው የነበሩ የ1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ዓመት ተማሪዎች፥ ወደ 2ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛ ዓመት መዘዋወራቸውን ተከትሎ
የተላለፈ የምዘገባ ጊዜ መልዕክት መሆኑን ገልፀዋል።

[ዘገባው የቲክቫህ ዩንቨርሲቲ ነው]

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#AmboUniversity

አምቦ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች መግቢያ ጥር 23 እና 24/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው 3,022 የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች በ2016 ዓ.ም የተመደቡለት ሲሆን የተማሪዎቹ መግቢያ ጥር 23 እና 24/2016 ዓ.ም እንዲሆን የተቋሙ ሴኔት ትላንት መወሰኑን የዩኒቨርሲቲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር መንግስቱ ቱሉ (ዶ/ር) ለ #ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot