STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.3K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ ፦

#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እለተ ዛሬ 29 ቀን 2013 ዓ.ም በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሃ-ግብር በቅድመ ምረቃ እና በድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 5,310 ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።

#WoldiaUniversity

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ላለፋት ዓመታት በተለያዩ ትምህርት መስኮች ሲያሰለጥናቸው የቆዩ ተማሪዎቹን ዛሬ በሼህ ሙሃመድ ሁሴን አሊ ኣላሙዲን ስታዲየም እያስመረቀ ይገኛል።

በመደበኛው፣ በተከታታይ እና በክረምት መርሃግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 2785 የሚሆኑ እጩ ተመራቂ ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

ከጠቅላላ ተመራቂዎች ውስጥም 926 ሴቶች ናቸው።

#BahirdarUniversity

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መድኮች ሲያስተምራቸው የቆያቸውን 5,117 ተማሪዎችን በፔዳ ካምፓስ በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

4,203 የሚሆኑት የመጀመሪያ ዲግሪ (ቅድመ ምረቃ ፕሮግራም) የተማሩ ናችው። 759 በሁለተኛ ድግሪይ የተማሩ፣10 የፒኤችዲ ተመራቂዎች ይገኙበታል።

በሌላ በኩል በህክምና ስፔሻሊቲ የተመረቁ 40 የሚሆኑ ሰልጣኞች ዛሬ እየተመረቁ ነው።

ከአጠቃላይ ተመራቂዎቹ ውስጥ 1,623 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።

#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 773 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በማስመረቅ ላይ ይገኛል፡፡

#MizanTepiUniversity

ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።

በሌላ በኩል፦

ሂልኮ የኮምፒዩተር ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ኮሌጅ ነገ ጥር 29/2013 ዓ/ም ተማሪዎቹን ያስመርቃል።

@NATIONALEXAMSRESULT
* Congratulations !

በዛሬው ዕለት ብቻ ከተለያዩት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 23,192 ተማሪዎች ተመርቀዋል።

የትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ምን ያህል ተማሪ ? በምን ደረጃ እና የትምህርት ዘረፍ አስመረቁ ? ለጥያቄዎቹ መልስ ይህን አጭር ቁጥራዊ መረጃ አስቀምጠናል።

#HawassaUniversity

- አጠቃላይ 6 ሺህ 793 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 2 ሺህ 158ቱ ወይም 32 በመቶ ሴቶች ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ በመደበኛና ተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

#BahirdarUniversity

- አጠቃላይ 5 ሺህ 586 ተማሪዎች አስመርቋል።
- ከተመራቂዎቹ 1 ሺህ 714ቱ ሴቶች ናቸው።
- በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናሰቁ ናቸው።

#JimmaUniversity

- አጠቃላይ 696 ተማሪዎች አሰመርቋል።
- 450 ወንድ እና 246 ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ 252 ተማሪዎች በአጠቃላይ ሕክምናና በጥርስ ሕክምና የሰለጠኑ ናቸው።
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሶማሊላንድ ሀርጌሳ ካምፓሱ በ 'ኒውትሬሽን' የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን 19 የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎችንም አስመርቋል።

#AdamaScience_and_TechnologyUniversity (ASTU)

- አጠቃላይ 1 ሺህ 298 ተማሪዎች አስመርቋል።
- ሰባቱ በሦሥተኛ ዲግሪ (ፒኤችዲ) ተመራቂዎች ናቸው።
- 215ቱ በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።
- 1 ሺህ 76 ተማሪዎች በመጀመረያ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።

#MettuUniversity

- አጠቃላይ 2 ሺህ 262 ተማሪዎች አስመርቋል።
- 116ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብሮች በመቱ እና በበደሌ ካምፓሶች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

#ArsiUniversity

- አጠቃላይ 831 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- በበቆጂ ካምፓስ የሰለጠኑ ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- በመጀመሪያ እና በ2ኛ ዲግሪ ከተመረቁት መካከል 392ቱ ሴቶች ናቸው።

#AmboUniversity

- አጠቃላይ 4 ሺህ 524 ተማሪዎች አስመርቋል።
- በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ 1 ሺህ 980ዎቹ ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 450 የሚሆኑት የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ሲሆኑ 11 የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ተማሪዎች ይገኙበታል።

#JigjigaUniversity

- አጠቃላይ 1 ሺህ 202 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 336ቱ ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- 233ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን ቀሪዎቹ 969ኙ በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

መረጃውን በማጋራት ላልሰሙ እናሰማ


ለበለጠ ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT
#BahirdarUniversity

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው የህልውና ዘመቻ ምክንያት ከተማሪዎች በመጣ ጥያቄ ትምህርት እንዲቋረጥ ተደርጎ መቆየቱ ይታወሳል; ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ዩኒቨርሲቲው ወስኗል፡፡ ሆኖም ተማሪዎች በሀገሪቱ ወቅታዊ ችግር ምክንያት የስነልቦና ጫና ሊገጥማቸው እንደሚችል ይገመታል፡፡ ስለሆነም ተማሪዎች ከአቀባበል ጀምሮ ስነልቦናን የሚገነቡ ስራዎችን ለመስራት ያስችል ዘንድ 104 ለሚሆኑ የአካዳሚክስ አማካሪ መምህራን በዩኒቨርሲቲው የስልጠና ዳይሬክቶሬት አማካኝነት ታህሳስ 26/2014 ዓ.ም በጥበብ ሕንፃ የመስብሰቢያ አዳራሽ የግማሽ ቀን ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ከጦርነቱ አካባቢ የሚመጡ ተማሪዎች ካለባቸው ተደራራቢ ችግር አንፃር የአንደኛውን ወሰነ ትምህርት ለማጠናቀቅ በተሰጠው የአንድ ወር ጊዜ አጭር በመሆኑ ኮርሶችን በወቅቱ ለማጠናቀቅ ፈታኝ እንደሚሆን ተሳታፊ መምህራን ተናግረዋል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ጦርነቱ ከጉዳቱ ባሻገር ለሀገራችን እና ለህዝባችን አንድነት እና መተሳሰብን እንዲሁም ለሰዎች በጎ ማድረግን ያመጣልን ጥሩ አጋጣሚ በመሆኑ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም መምህራን ጠንክረን በመስራት በፍጥነት ከችግሩ መውጣት እንደሚገባ ተጠቅሷል፡፡ በስልጠናው ላይ የቀረበውን የመወያያ ፅሁፍ መሰረት በማድረግ ከሰልጣኝ መምህራን ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በመጨረሻም በተማሪዎች አቀባበል ዙሪያ ተመሳሳይ ስልጠናዎች በዩኒቨርሲቲው የስልጠና ዳይሬክቶሬት አማካኝነት ለዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ፣ ለዲኖችና ለም/ዲኖች፣ ለትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ ለአስተዳደር ሰራተኞች ዘርፍ ኃላፊዎች እና ለተማሪዎች ህብረት በአጠቃላይ 502 ለሚደርሱ መምህራንና ሰራተኞች ስልጠናው መሰጠቱ ታውቋል፡፡ #ባሕርዳር_ዩኒቨርሲቲ

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#BahirdarUniversity

በ2014 ዓ/ም ከመቐለ ፣ አክሱም፣ ዓዲግራት እና ወልዲያ ዩንቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት ወደ ባህርዳር ዩንቨርሲቲ ለተመደባችሁ የመደበኛ መጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ከየካቲት 21-24/2014 ዓ/ም ባሉት ቀናት የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን (Registration Slip, Student Copy እና Student ID) በሙሉ በመያዝ በየአካዳሚክ ክፍሎች ሬጅስትራር በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ተብሏል።

ማሳሰቢያ ፦

የመጀመሪያ ዓመትን ያላጠናቀቃችሁ ተማሪዎች የምትመጡት የ2014 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ሲጠሩ በምትገቡበት ሴሚስተር መሰረት አብራችሁ የምትመጡ መሆኑን አውቃችሁ የአዲስ ጀማሪ ተማሪዎችን ጥሪ እንድትጠባበቁ ማሳሰቢያ ተላልፋል።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#BahirDarUniversity_College_of_Medicine_and_Health_Sciences

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።

ኮሌጁ ዛሬ 457 ተማሪዎችን እያስመረቀ ሲሆን 383 በቅድመ ምረቃ፣ 24 በማስተርስ እና 50 በሕክምና ስፔሻሊቲ መሆናቸው ተገልጿል።

ከጠቅላላ ተመራቂዎች 187ቱ ሴቶች መሆናቸውን ኮሌጁ ገልጿል።

ኮሌጁ አሁን ላይ ከ2 ሺህ 300 በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT