STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.9K subscribers
11K photos
271 videos
452 files
1.93K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ ፦

#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እለተ ዛሬ 29 ቀን 2013 ዓ.ም በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሃ-ግብር በቅድመ ምረቃ እና በድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 5,310 ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።

#WoldiaUniversity

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ላለፋት ዓመታት በተለያዩ ትምህርት መስኮች ሲያሰለጥናቸው የቆዩ ተማሪዎቹን ዛሬ በሼህ ሙሃመድ ሁሴን አሊ ኣላሙዲን ስታዲየም እያስመረቀ ይገኛል።

በመደበኛው፣ በተከታታይ እና በክረምት መርሃግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 2785 የሚሆኑ እጩ ተመራቂ ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

ከጠቅላላ ተመራቂዎች ውስጥም 926 ሴቶች ናቸው።

#BahirdarUniversity

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መድኮች ሲያስተምራቸው የቆያቸውን 5,117 ተማሪዎችን በፔዳ ካምፓስ በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

4,203 የሚሆኑት የመጀመሪያ ዲግሪ (ቅድመ ምረቃ ፕሮግራም) የተማሩ ናችው። 759 በሁለተኛ ድግሪይ የተማሩ፣10 የፒኤችዲ ተመራቂዎች ይገኙበታል።

በሌላ በኩል በህክምና ስፔሻሊቲ የተመረቁ 40 የሚሆኑ ሰልጣኞች ዛሬ እየተመረቁ ነው።

ከአጠቃላይ ተመራቂዎቹ ውስጥ 1,623 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።

#DebarkUniversity

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 773 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በማስመረቅ ላይ ይገኛል፡፡

#MizanTepiUniversity

ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።

በሌላ በኩል፦

ሂልኮ የኮምፒዩተር ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ኮሌጅ ነገ ጥር 29/2013 ዓ/ም ተማሪዎቹን ያስመርቃል።

@NATIONALEXAMSRESULT
#ጥብቅ_ማሳሰቢያ ‼️
#WolaitasodoUniversity

በትምህርት ሚኒስትር በተደረገ ምደባ መሰረት ከሚያዚያ 27 እስከ 28/2ዐ14 ዓ.ም ባሉት ቀናት ወደ ዩኒቨርሲቲያችን አዲስ ለገቡ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ !

ጉዳዩ፦ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ከግንቦት 1/2014 ዓ.ም ጀምሮ ቅጥ ያጣ የአለባበስ ስርዓት እና የጸጉር አሰራርን _ የማያስተናግድ መሆኑን ስለ ማሳወቅ ይሆናል።

ሙሉ ህገ ደንቡን ከታች ይመልከቱት!!

📭አለባበስና ጸጉርን በተመለከተ ከባድ የዲሲፕሊን ቅጣት የሚያስከትሉ ጉዳዮች:

1. ለሴቶች:
ሆን ተብሎ የተቀደደ ልብስ ወይም አካልን የሚያጋልጥ (ደረት፣ዳሌ) ልብስ ለብሶ መገኘት!

ከጉልበት በላይ የሆነ ቀሚስ ለብሶ መገኘት!

ኮፍያ ማድረግ፣ የጸጉር ቀለም መቀባት፣ እንዲሁም ጸጉርን ማንጨባረር ፈጽሞ የተከለከለ ነው!

ኃይለኛ ሽታ ያለው ቅባቶች እና ሽቶ መቀባት ፈጽሞ የተከለከለ ነው!

የሚረብሽ ድምጽ የሚፈጥሩ ጫማዎችን መማሪያ ክፍል፣ ላይብረሪ እና ላቦራቶሪ አድርጎ መምጣት ፈጽሞ የተከለከለ ነው!
🤟አጠቃላይ የግል ንጽህናን መጠበቅ ግድ ይላል!

2. ለወንዶች:

የወንድ ጸጉር ከ1 ሴ.ሜ ያልበለጠ ሆኖ መስተካከል ግዴታ ነው። ጸጉር ላይ ምንም የተለየ ቅርጽ የሌለውና ንጹህ የሆነ፣ ያልተንጨበረረ ጸጉር ሊኖራቸው ይገባል!

ሆን ተብሎ የተቀደደ ልብስ፣ አካልን የሚያጋልጥ አልባሳት መልበስ ፈጽሞ የተከለከለ ነው!

ኮፍያ ማድረግ፣ የጸጉር ቀለም መቀባት ፈጽሞ የተከለከለ ነው!

🤟አጠቃላይ የግል ንጽህናን መጠበቅ ግድ ይላል!

⚠️ማሳሰቢያ:

🦿 ይህ ህገ ደንብ ለሁለም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የሚሰራ ሲሆን ተግባራዊነቱም ከግንቦት 1/2014 ዓ.ም ጀምሮ የጸና ይሆናል።

🦿ለህገ ደንቡ ተፈጻሚነት የዩኒቨርሲቲው ምድር ግቢ ጥበቃና ደህንነት ሠራተኞች በቁርጠኝነት የክትትል ስራ የሚሰሩ ይሆናል።

🦿ይህን የስነ ምግባር መርሆ (ህገ ደንብ) ተላልፎ በተገኘ አካል ላይ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ጥብቅ የዲስፕሊን እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 4 ሺህ 757 ተማሪዎችን ሐምሌ 09/2014 ዓ.ም ያስመርቃል።

ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብር በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ከዩኒቨርሲቲው የ2014 ዓ.ም 14ኛ ዙር ተመራቂዎች መካከል 574ቱ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች (4 በPhD፣ 8 በሕክምና ስፔሻሊቲ እና 562 በማስተርስ ዲግሪ) መሆናቸው ተገልጿል።

ቀሪዎቹ 4 ሺህ 183 ተማሪዎች የቅድመ ምረቃ እጩ ተመራቂዎች መሆናቸው ተመላክቷል።

በ1999 ዓ.ም የተቋቋመው ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፤ ከ38 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎችን አስመርቋል።

ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰቸጠናቸውን 4 ሺህ 442 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም (HDP)፣
በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በማስተርስ እና በዶክተሬት ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው ለ14ኛ ጊዜ ባካሄደው የምረቃ ስነስርዓት በ HDP 92፣ በመጀመሪያ ዲግሪ 3,776፣ በሁለተኛ ዲግሪ 562፣ በስፔሻሊቲ 8 እንዲሁም በPhD 4 ተማሪዎችን አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብር ከ42 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ እንደሚገኝ
የተቋሙ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ታከለ ታደሰ ገልጸዋል።

የዛሬ ተመራቂዎችን ጨምሮ ዩኒቨርሲቲው በ15 ዓመታት ጉዞው ከ48 ሺህ በላይ ተማሪዎች ማስመረቁን ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል።


ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም #የክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎች ምዝገባ ሐምሌ 20 እና 21/2014 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

የነባር የክረምት ተማሪዎች ቲቶሪያል ከሐምሌ 22 እስከ 25/2014 ዓ.ም እንደሚሰጥ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ጥሪው የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ የክረምት መርሃ ግብር ተማሪዎችን ይመለከታል የተባለ ሲሆን በግብርና፣ በእንስሳት ጤና እና በኅብረት ሥራ ትምህርት ፕሮግራሞች የክረምት ተማሪዎችን አይመለከትም ተብሏል።

( ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል። )

ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም የሁለተኛ እና የሦሥተኛ ዲግሪ አዲስ አመልካቾች የመግቢያ ፈተና ጥቅምት 29/2015 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።

የጤና መርሃ ግብር አመልካቾች ፈተና በኦቶና ካምፓስ ይሰጣል ተብሏል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#WolaitaSodoUniversity

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ ሦሥተኛ ዙር የሕክምና ተማሪዎቹን ቅዳሜ ኅዳር 17/2015 ዓ.ም ያስመርቃል።

ኮሌጁ በዕለቱ በመደበኛ የትምህርት መርሃ ግብር ያስተማራቸውን ከ240 በላይ ተማሪዎች ያስመርቃል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#WolaitaSodoUniversity

በ2015 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ መጋቢት 1 እና 2/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት የሚጀመረው ➧ መጋቢት 4/2015 ዓ.ም

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሄዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➧ መሰናዶ ያለፋችሁበት ሰርተፍኬት፣
➧ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➧ የ8ኛ ክፍል ካርድ፣
➧ አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➧ የሌሊት አልባሳት፣
➧ የስፖርት ትጥቅ፣

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።


የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#WolaitaSodoUniversity

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ወስዳቹህ ማለፊያ ነጥብ በማምጣት ወደ ወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ የተመደባቹህ አዲስ ተማሪዎች፣በ2015ዓ.ም አንደኛ ሴሚስተር ጀምራቹህ በተለያዩ ምክንያቶች Withdrawal የሞላቹህ ተማሪዎች እንዲሁም በ2015ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ(Remedial) ትምህርት ተከታትላቹህ ማለፊያ ነጥብ ያመጣቹህ ነባር የሪሜዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከታህሳስ 03 እስከ 04/2016ዓ.ም መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።

💥 የድህረ ምረቃ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ምዝገባም በተመሳሳይ ቀን ነው‼️

[ተጨማሪ መረጃ ከማስታወቂያው ያንብቡ]

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#WolaitaSodoUniversity

በ2016 ዓ.ም. ወደ መላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሜዲያል/የማሻሻያ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ👉 ከጥር 23-24/2016 ዓ.ም. ለሁለት ተከታታይ ቀናት ብቻ መሆኑን እያሳወቅን ከተጠቀስዉ ጊዜ ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ ዩኒቨርሲቲዉ የማያስተናግድ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትሄዱ

1. የ8ኛ ክፍል ስርተፍክት: ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናዉን እና ፎቶ ኮፒ ይዛችሁ እንድትመጡ፤

2. አንሶላ፣ብርድልብስ፣ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ መምጣት ይኖርባችኋል፡፡

የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#ተራዝሟል
#WolaitaSodoUniversity

በ2016ዓ.ም ወደ ወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ የተመደባቹህ አዲስ የሬሚድያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከጥር 23-24/2016 የነበረዉ ወደ የካቲት 07 - 08 /2016 ዓ.ም. የተራዘመ መሆኑን ዩንቨርሲቲው ዛሬ አሳውቋል፡፡

💥ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትሄዱ

1. የ8ኛ ክፍል ስርተፍክት: ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናዉን እና ፎቶ ኮፒ ይዛችሁ እንድትመጡ፤

2. አንሶላ፣ብርድልብስ፣ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ መምጣት ይኖርባችኋል፡፡

ለ 12ኛ, ለ Remedial እና ለ Freshman ተማሪዎች 🔻  ቻናል👇
https://t.me/+s5S2h_gcBlY0Y2U0
 
            Share share🙏🙏
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
╔═══════════╗
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
♨️ ♦️ @ethiouniversity1  ♨️
╚═══════════╝