STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
40.7K subscribers
11K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
ማስታወቂያ
ለትምህርት ፈላጊዎች አሶሳ ዩኒቨርሲቲ

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
"የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የትምህርት ስርዓቱን መልሶ የመገንባት ሥራ እየተከናወነ ነው።" የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

ሚኒስትሩ በጂንካ ከተማ ከደቡብ ክልል ሁሉም ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ከተውጣጡ የትምህርት ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በዘርፉ ልማት ዙሪያ መክረዋል።

በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ለትምህርት ጥራት ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራል ብለዋል።

''በቅርቡ በተደረጉ ጥናቶች ሶስተኛ ክፍል ከደረሱ ተማሪዎች 65 በመቶ ማንበብ አይችሉም" ያሉት ሚኒስትሩ ፤ ይህም የትምህርት ጥራቱ ደካማ መሆኑን እንደሚያሳይ አመልክተዋል።

የትምህርት ጥራቱ መዳከም በዋናነት ከመምህራን አቅም ጋር የሚያያዝ እንደሆነ ያመላከቱት ሚኒስትሩ ፤
የመምህራንን አቅም መገንባት እንደሚገባ ገልጸዋል።

መምህራን ተገቢውን እውቀት ይዘው ወደ ማስተማሩ ሥራ መግባት እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል።

"የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የትምህርት ስርዓቱን መልሶ የመገንባት ሥራ እየተከናወነ ነው" ብለዋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
Guide_Regarding_Entrance_Examination_and_Interview_of_SPHMMC.pdf
572.5 KB
፨ቅዱስ ፓውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ መወዳደር ለሚፈልጉ ተማሪዎች የቅዱስ ፓውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጁ ነባር ተማሪዎች ያዘጋጁት ፋይል

፨የቅዱስ ፓውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ እስካሁን ድረስ የመወዳደሪያ መስፈርቱን ይፋ አላደረገም‼️

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ❗️

"ሁለቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ 2014 ዓ.ም ለመግባት የዘንድሮው ውጤት ከፍ እንዳለ በተለያየ መንገድ ስትገልፁ እንደነበራችሁ የሚታወቅ ነው፡፡ "

"በመሆኑም የተወሰኑ ማሻሻያዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ነገ ጠዋት በዩቱዩብ ቻናላችን ማስተካከያውን የምናሳውቅ በመሆኑ በትዕግስት ይጠብቁን፡፡"
Link
https://www.youtube.com/channel/UCUpgXuqDCiLfgLPK_FxS-6g


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ዐረፉ።

(ማኅበረ ቅዱሳን ሕዝብ ግንኙነት)

መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ቤት በ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ፤ በማታ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን ከዚህ በታች በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ተቀብሎ ማሠልጠን ይፈልጋል፡፡
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ መረጃዎች
1. የትምህርት መረጃ፡- ሙሉ የትምህርት መረጃ ኦርጅናልና ሁለት (2) ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ሁለት (2) ጉርድ ፎቶ ግራፍ
2. የድጋፍ ደብዳቤ፡- የአመልካቹን ጥንካሬና ባህሪ የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ከመ/ቤት ኃላፊ /ከቀድሞ መምህር/ Recommendation Letter/
3. የመመዝገቢያ ክፍያ፡- የማመልከቻ ክፊያ የ100 ብር ደረሰኝ በመያዝ የማመልከቻ ቅጽ ከቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 210፣ 211 እና ከዩኒቨርሲቲው ድኀረ-ገፅ (www.amu.edu.et) ማግኘት ይችላሉ፡፡
. በመንግሥት /በድርጅት ስፖንሰርነት ለሚማሩ በመስሪያ ቤቱ/ በድርጅቱ ኃላፊ የሚፈረም /Sponsorship Form/ ከዩኒቨርሲቲው ድኀረ-ገፅ (www.amu.edu.et) ማግኘት ይችላለ፡፡
የማመልከቻ፤ የፈተና መስጫ፤ የውጤት ማሳወቂያ፤ የምዝገባ ጊዜ እና ቦታ
የማመልከቻ ጊዜ፡- ከየካቲት 15/2014 ዓ.ም እስከ የካቲት 30/2014 ዓ.ም፤
የማመልከቻ ቦታ፡- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አ/ዳ/ጽ/ቤት ቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 210፣ 211 እና አዲስ አበባ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ጽ/ቤት አራት ኪሎ ሮሚና ካፌ ጎን፤
ለፈተና ያለፉ አመልካቾች ዝርዝር የሚወጣበት ቀን፡- መጋቢት 02/2014 ዓ.ም ፤ ለፈተና ያለፉ አመልካቾች ዝርዝር በውስጥ ማስታወቂያ እና በዩኒቨርሲቲው ድኅረ-ገጽ (www.amu.edu.et) መከታተል ይችላሉ፡፡
የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፡- መጋቢት 5/2014 ዓ.ም
ፈተና የሚሰጥበት ቦታ፡- የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ነጭ ሳር ካምፓስ
ማሳሰቢያ፡-
 ማንኛውም የመግቢያ ፈተና ያለፈ አመልካች ኦፊሻል ትራንስክሪፕት /Official Transcript/ ብቻል በምዝገባ ወቅት ካልሆነ በ60 ቀናት ውስጥ ካልቀረበ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ በጥብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
 በአካል ቀርባችሁ ማመልከት ለማትችሉ አመልካቾች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂ/ቁ 1000021480502 የማይመለስ ብር የ 100 ገቢ ያደረጋችበትን አንድ ኮፒና ሙለ የትምህርት ማስረጃችሁን ኮፒ በማድረግ በ Email አድራሻችን admission@amu.edu.et ማመልከት ትችላላችሁ፡፡
PhD Program - PhD in Public Health
 መደበኛ የፒ ኤች ዲ ተማሪዎች ሁሉም በተመጣጣኝ ክፊያ የዶርም አገልግሎት ያገኛሉ፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር እና አ/ዳ/ጽ/ቤት

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#WolloUniversity

ለወሎ ዩኒቨረሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የሁሉም መደበኛ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች (የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጨምሮ) ምዝገባ የሚከናወነው #መጋቢት 12 እና 13/2014 ዓ.ም ሲሆን ነባሩ መታወቂያ ስለተቀየረ ወደ ግቢ ስትመጡ ለመታወቂያ የሚሆን ሁለት 3×4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ እና ነባሩን መታወቂያ ይዛችሁ እንድትመጡ እያሳሰብን ከመግቢያ ቀን በፊት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግደሆናችንን እናሳውቃለን፡፡

የወሎ ዩንቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ለአዲስ የሕክምና ትምህርት አመልካቾች የምዝገባና ተያያዥ መሥፈርትን በዛሬው ዕለት ይፋ እናደርጋለን ሲል ቅዱስ ፓውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ አሳውቋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር እሑድ መጋቢት 4 ቀን 2014 እንዲፈጸም ሲኖዶሱ ወሰነ።

የካቲት 25/2014 ዓ.ም

ቅዱስ ሲኖዶስ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር እሁድ እንዲፈጸም ውሳኔአሳልፏል፡፡

አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚከናወን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቴሌቪዥን የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ወቅታዊ ሁኔታን ስለማሳወቅ

=============================

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በጥቂት ተማሪዎች የእርስበርስ ግጭት ሐሙስ የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም ረፋድ ላይ ግጭት የተቀሰቀሰ ቢሆንም ብዙም ሳይቆይ በፀጥታ ሀይሎች የጋራ ርብርብ ማረጋጋት ተችሏል።

በግጭቱ ሳቢያ እስካሁን የአንድም ተማሪ ህይወት አለማለፉንና የከፋ አደጋና የንብረት ውድመት አለመድረሱን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።

በግጭቱ ሰቢያ ጥቂት መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ኮምፕሬንስቪ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ሌሎች ተማሪዎች ወደ ማደርያቸው ተመልሰዋል።

ከዚህ ውጪ አንዳንድ አካላት ለጊዜያዊ የፖለቲካ ፍጆታቸው ሲሉ የተዛባና የተሳሰተ መረጃ በአንዳንድ የማህበራዊ የትስስር ገፆች እያሰራጩ እንደሆነ ተደርሶበታል። ይህ የሚለቀቁ የሀሰት መረጃዎች ዩኒቨርሲቲው የሰላም አምባሳደር መሆኑ ያልተመቻቸው እና የራሳቸውን አጀንዳ ለማስረፅ የሚፈልጉ አካላት የሚነዙት የሀሰት ወሬ ነው።

በመሆኑም የሚለቀቁ መረጃዎች የተዛቡና ከእውነት የራቁ መሆናቸውን እየገለፅን በቀጣይ ያሉ መረጃዎችን ከዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ ድረ-ገፅ ብቻ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን።

በዚህ መሠረት ዩኒቨርሲቲው ሰላም መሆኑን እና የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት የዩኒቨርሲቲው አመራርና የሚመለከታቸው አካላት በጋራ በመሆን የተፈታ ሲሆን በቀጣይም ዘላቂ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲካሄድ በጋራ ውይይት እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን መደበኛ የመማር ማስተማር ስራ መቀጠሉን እናሳውቃለን።

ዘገባው የህዝብ ግንኙነት እና ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
የግል_ከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማትና_እውቅና_ፈቃድ_የተሰጣቸው_የትምህርት_መስኮች.pdf
6 MB
#Repost

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እስከ የካቲት 2014 ዓ.ም ድረስ ያጠናቀራቸውን አጠቃላይ የ350 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እና የትምህርት መስኮቻቸውን የእውቅና ፈቃድ የሚገልጽ የተሟላ መረጃ ከላይ ተያይዟል።

ከ350ው 330ዎቹ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲሆኑ 20 ተቋማት በርቀት ትምህርት እውቅና የተሰጣቸው የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በክልል መንግስታት የሚተዳደሩ ተቋማት ይገኙበታል።

የእውቅና ፈቃድ ባልታደሰባቸው የትምህርት መስኮች #አዲስ_ተማሪ_መቀበል_እንዳይችሉ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡

ይህ መረጃ እስከ የካቲት ወር ድረስ ያለውን የእውቅና ፈቃድ ነው።

በሂደት ላይ ያሉ የእውቅና ፈቃድ እና የእውቅና ፈቃድ እድሳት ጥያቄዎች ውሳኔ ሲያገኙ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የእውቅና ፈቃድ ሲሰረዝና በሌሎች ምክንያቶች የውሳኔ ለውጦች በሚኖሩበት ወቅት የመረጃ ለውጥ ሊኖር ይችላል።

በመሆኑም ፦
- ተማሪዎች፣
- ወላጆች፣
- ቀጣሪና የሙያ ፈቃድ የሚሰጡ ድርጅቶች ፣
- የሚዲያና ማስታወቂያ ተቋማት ፣ እንዲሁም መላው ህብረተሰብ የተቋማቱን ወቅታዊ መረጃ በመከታተል ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ተቋማት ይፋ ከተደረገው የእውቅና ፈቃድ መረጃ ውጪ ተማሪ ተቀብለው ቢያስተምሩ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

[ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና እውቅና ፈቃድ የተሰጣቸው የትምህርት መስኮች ከላይ በ #PDF ተያይዟል ]

#ሼር #Share

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት #በሳተላይት_ኮሌጆች በ2014 ዓ/ም ትምህርታችሁን ለመከታተል የመግቢያ ፈተና ለወሰዳችሁ ተማሪዎች በሙሉ

1. የምደባ ቦታችሁ በቀድሞው #የፌደራል_ቴክኒክና_ሙያ_ትምህርትና_ስልጠና_ኤጀንሲ በተመደባችሁበት ሲሆን በSurveying Technology እና በRoad Construction Technology ጀነራል ዊንጌት ተመድባችሁ የነበራችሁ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ #በባህርዳር_ካምፓስ የተመደባችሁ መሆኑን

2. በመጀመሪያው ምደባ በአዲስ አበባ ተግባረዕድ እና ጀነራል ዊንጌት ተመድባችሁ እና የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ወደ ተለያዩ ካምፓሶች ተበትናችሁ የነበራችሁ ተማሪዎች በጥያቄያችሁ መሰረት ወደ መጀመሪያው ምድብ ቦታችሁ ማለትም አዲስ አበባ ተግባረዕድ እና ጀነራል ዊንጌት እንድትመለሱ የተደረገ መሆኑን፤
ነገር ግን በየወሩ ከሚከፈለው ስድስት መቶ ብር ውጪ ምንም አይነት የመኝታም ሆነ የምግብ አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ ራሳችሁን ከወዲሁ እንድታዘጋጁ

3. በማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ በአምቦ እና አሰላ ካምፓሶች ለመማር ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች በቁጥር ማነስ ምክንያት ወደ #አዳማ_ካምፓስ የተመደባችሁ መሆኑን እንድታውቁ

4. በሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት ትምህርታችሁን ለመከታተል በዋናው ጊቢ ፈተና የወስዳችሁ ተማሪዎች ወደ #አርባምንጭ_ሳተላይት ካምፓስ የተመደባችሁ መሆኑን

5. የመመዝገቢያ ቀን ቀድሞ በየሳተላይቶቻችሁ በተገለፀው መሰረት #ከየካቲት_30_እስከ_መጋቢት_1 /2014ዓ/ም ሲሆን በቅጣት የመመዝገቢያ ቀን #መጋቢት_2 /2014 መሆኑን አውቃችሁ በእለቱ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

የሳተላይት ማዕከላት ማስተባባሪያ ዳይሬክቶሬት

@NATIONALEXAMSRESULT
4፤ ከ7 ሺህ በላይ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሰራተኞች ለአንድ ዓመት ያህል ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው መናገራቸውን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ለዜና ምንጩ ቃላቸውን የሰጡ የዩኒቨርሲቲው መምህራን ደመወዝ ባለማግኘታቸው ከእነ ቤተሰባቸው ከባድ ችግር ላይ እንደወደቁ ገልጸው፣ ችግራቸውን ለማቃለል መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የተቀጠሩ እና ሕወሃትን የተቀላቀሉ አንዳንድ መምህራን እንዳሉ ተናግዋል። ትምህርት ሚንስቴር በበኩሉ ከትግራይ ክልል ሸሽተው የወጡ የዩኒቨርሲቲ መምህራንን በሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደመደበ እና ከክልሉ ላልወጡት ግን ማድረግ የሚችለው ነገር እንደሌለ ገልጧል።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ፦

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በግል መደበኛ መርሐ ግብር (Private Regular Program) አዳዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል።
በመሆኑም:-
¥ ቢኤስሲ ነርሲንግ (BSc Nursing)

¥ ቢኤስሲ ሚድዋይፈሪ (BSc Midwifery)

የትምህርት ዘርፎች ወደፊት በሚገለጸው የመመዝገቢያ ቀን እና መስፈርት መሰረት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
ከኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የተሰጠ ማሳሰቢያ

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ መርሀ ግብር ለመማር የሚመዘገቡ ተማሪዎች የሚከተሉትን የቅበላ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

እነዚህም፡-
1. የመሰናዶ ትምህርት ያጠናቀቁ ተማሪዎች ከሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ለትምህርት ዘመኑ ያስቀመጠውን የመቁረጫ ነጥብ ሊያሟሉ ይገባል፡፡

2. ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም የተመረቁ ባለሙያዎች ከሆኑ ከሠለጠኑበት የሙያ መስክ ጋር ተዛማጅነት ባለው የሥልጠና መስክ በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ በደረጃ 4 (ወይም በቀድሞ 10+3 ወይም 12+2) ያጠናቀቁ ሆነው በሙያው ደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ ምዘና (COC level 4) ተፈትነው ያለፉበትን፤ እንዲሁም በሙያው ቢያንስ የሁለት ዓመት ሥራ ልምድ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች በምዝገባው እለት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

3. ከውጭ ሀገር የተገኘ የትምህርት ማስረጃ ለዲግሪ መርሃ-ግብር መግቢያ የሚያገለግለው በባለስልጣኑ የአቻ ግምት ሲሰራለት ብቻ ይሆናል፡፡


4. በየተቋማቱ የሚዘጋጁትን የመግቢያ ፈተናዎች ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፤ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች በምዝገባው ዕለት ማቅረብ ያልቻለ ተመዝጋቢ ህጋዊ ተቀባይነት አይኖረውም።

ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን እና ሌሎች ህጋዊ መመሪያዎችን ጥሶ የተገኘ ተቋም በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የስነ ስርዓት መመሪያ መሠረት በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን እየገለጽን፤ ከህግ ውጪ ገብተው የሚማሩ ተማሪዎችም ሊደርስባቸው የሚችለውን የጊዜ፣ የገንዘብና የስነ-ልቦና ኪሳራ አውቀው አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባለስልጣኑ ያሳስባል። #ETA


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#ASTU #AASTU #ማሻሻያተደርጓል

ሁለቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች (አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ) የ2014 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ ላይ ማሻሻያ አድርጓል።

የመመዝገቢያ መስፈት የሲቪክስ ትምህርትን አይጨምርም‼️

• ለአዳጊ ክልሎች (አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ)

- ኢንጂነሪንግ ~ ለወንድ 375፣ ለሴት 370
- አፕላይድ ሳይንስ ~ ለወንድ 365፣ ለሴት 360

• ለሌሎች ክልሎች

- ኢንጂነሪንግ ~ ለወንድ 380፣ ለሴት 375
- አፕላይድ ሳይንስ ~ ለወንድ 370፣ ለሴት 365

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT