STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
38.8K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.95K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#WolloUniversity

ለወሎ ዩኒቨረሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የሁሉም መደበኛ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች (የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጨምሮ) ምዝገባ የሚከናወነው #መጋቢት 12 እና 13/2014 ዓ.ም ሲሆን ነባሩ መታወቂያ ስለተቀየረ ወደ ግቢ ስትመጡ ለመታወቂያ የሚሆን ሁለት 3×4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ እና ነባሩን መታወቂያ ይዛችሁ እንድትመጡ እያሳሰብን ከመግቢያ ቀን በፊት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግደሆናችንን እናሳውቃለን፡፡

የወሎ ዩንቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት #በሳተላይት_ኮሌጆች በ2014 ዓ/ም ትምህርታችሁን ለመከታተል የመግቢያ ፈተና ለወሰዳችሁ ተማሪዎች በሙሉ

1. የምደባ ቦታችሁ በቀድሞው #የፌደራል_ቴክኒክና_ሙያ_ትምህርትና_ስልጠና_ኤጀንሲ በተመደባችሁበት ሲሆን በSurveying Technology እና በRoad Construction Technology ጀነራል ዊንጌት ተመድባችሁ የነበራችሁ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ #በባህርዳር_ካምፓስ የተመደባችሁ መሆኑን

2. በመጀመሪያው ምደባ በአዲስ አበባ ተግባረዕድ እና ጀነራል ዊንጌት ተመድባችሁ እና የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ወደ ተለያዩ ካምፓሶች ተበትናችሁ የነበራችሁ ተማሪዎች በጥያቄያችሁ መሰረት ወደ መጀመሪያው ምድብ ቦታችሁ ማለትም አዲስ አበባ ተግባረዕድ እና ጀነራል ዊንጌት እንድትመለሱ የተደረገ መሆኑን፤
ነገር ግን በየወሩ ከሚከፈለው ስድስት መቶ ብር ውጪ ምንም አይነት የመኝታም ሆነ የምግብ አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ ራሳችሁን ከወዲሁ እንድታዘጋጁ

3. በማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ በአምቦ እና አሰላ ካምፓሶች ለመማር ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች በቁጥር ማነስ ምክንያት ወደ #አዳማ_ካምፓስ የተመደባችሁ መሆኑን እንድታውቁ

4. በሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት ትምህርታችሁን ለመከታተል በዋናው ጊቢ ፈተና የወስዳችሁ ተማሪዎች ወደ #አርባምንጭ_ሳተላይት ካምፓስ የተመደባችሁ መሆኑን

5. የመመዝገቢያ ቀን ቀድሞ በየሳተላይቶቻችሁ በተገለፀው መሰረት #ከየካቲት_30_እስከ_መጋቢት_1 /2014ዓ/ም ሲሆን በቅጣት የመመዝገቢያ ቀን #መጋቢት_2 /2014 መሆኑን አውቃችሁ በእለቱ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

የሳተላይት ማዕከላት ማስተባባሪያ ዳይሬክቶሬት

@NATIONALEXAMSRESULT
#ArbaMinchUniversity

የተማሪዎች መግቢያ ጥሪ ማስታወቂያ

በ2014 የትምህርት ዘመን ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው ለአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ትምህርት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቅበላ ቀን #የካቲት_29/2015 ዓ/ም፣ የምዝገባ ቀን #የካቲት_30 እና #መጋቢት_01 ቀን 2015 ዓ.ም፣ ትምህርት የሚጀመርበት ቀን መጋቢት 04 ቀን 2015 ዓ.ም ይሆናል፡፡ ስለሆነም የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ትምህርት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች በተጠቀሰው ቀን ወደዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ጊዜ፡-

* የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ኦርጂናልና ሁለት የማይመለስ ኮፒ፣
* ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኦርጂናልና ሁለት የማይመለስ ኮፒ፣
* የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ኦርጂናልና ሁለት የማይመለስ ኮፒ፣
* የፓስፖርት መጠን (Passport Size) የሆነ አራት ጉርድ ፎቶ፣
* አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ እንዲሁም
* ኮቪድ-19ን መከላከል የሚያስችል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል

የምደባ ቦታ
👉 ዓባያ ካምፓስ የተመደባችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ (ዓባያ ግቢ)፣

👉 ጫሞ ካምፓስ የተመደባችሁ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኘው ጫሞ ካምፓስ፣

👉ሳውላ ካምፓስ የተመደባችሁ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ በአካል ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እና የአቅም ማሻሻያ ትምህርት እንድትጀምሩ እናሳስባለን።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት
   
የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot
#GambelaUniversity

በ2015 ዓ.ም በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ ሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ #መጋቢት_8 እና 9/2015 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

፨ዝርዝር መረጃዎችን ከፎቶ ላይ ይመልከቱ።



የተጣሩ ተማሪ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉን
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot