STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.7K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት #በሳተላይት_ኮሌጆች በ2014 ዓ/ም ትምህርታችሁን ለመከታተል የመግቢያ ፈተና ለወሰዳችሁ ተማሪዎች በሙሉ

1. የምደባ ቦታችሁ በቀድሞው #የፌደራል_ቴክኒክና_ሙያ_ትምህርትና_ስልጠና_ኤጀንሲ በተመደባችሁበት ሲሆን በSurveying Technology እና በRoad Construction Technology ጀነራል ዊንጌት ተመድባችሁ የነበራችሁ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ #በባህርዳር_ካምፓስ የተመደባችሁ መሆኑን

2. በመጀመሪያው ምደባ በአዲስ አበባ ተግባረዕድ እና ጀነራል ዊንጌት ተመድባችሁ እና የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ወደ ተለያዩ ካምፓሶች ተበትናችሁ የነበራችሁ ተማሪዎች በጥያቄያችሁ መሰረት ወደ መጀመሪያው ምድብ ቦታችሁ ማለትም አዲስ አበባ ተግባረዕድ እና ጀነራል ዊንጌት እንድትመለሱ የተደረገ መሆኑን፤
ነገር ግን በየወሩ ከሚከፈለው ስድስት መቶ ብር ውጪ ምንም አይነት የመኝታም ሆነ የምግብ አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ ራሳችሁን ከወዲሁ እንድታዘጋጁ

3. በማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ በአምቦ እና አሰላ ካምፓሶች ለመማር ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች በቁጥር ማነስ ምክንያት ወደ #አዳማ_ካምፓስ የተመደባችሁ መሆኑን እንድታውቁ

4. በሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት ትምህርታችሁን ለመከታተል በዋናው ጊቢ ፈተና የወስዳችሁ ተማሪዎች ወደ #አርባምንጭ_ሳተላይት ካምፓስ የተመደባችሁ መሆኑን

5. የመመዝገቢያ ቀን ቀድሞ በየሳተላይቶቻችሁ በተገለፀው መሰረት #ከየካቲት_30_እስከ_መጋቢት_1 /2014ዓ/ም ሲሆን በቅጣት የመመዝገቢያ ቀን #መጋቢት_2 /2014 መሆኑን አውቃችሁ በእለቱ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

የሳተላይት ማዕከላት ማስተባባሪያ ዳይሬክቶሬት

@NATIONALEXAMSRESULT