STUDENTS NEWS CHANNEL (የተማሪዎች ዜና መስኮት)
39.7K subscribers
11.1K photos
272 videos
452 files
1.94K links
የተማሪ እና ተማሪ ነክ መረጃዎች ይቀርቡበታል፡
Download Telegram
#AASTU

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የማዕድን ምህንድስና ተማሪዎች የነበሩና ወደ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ምዝገባ ታህሳስ 21 እና 22/2014 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት ብቻ የመጨረሻ ሴሚስተር ግሬድ ሪፖርት በመያዝ በተቋሙ ሬጅስትራር ጽ/ቤት በመገኘት እንዲመዘገቡ ተብሏል።

የግል መገልገያ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ ተቋሙ አሳስቧል።

ሁለት መምህራን ለመቅጠር እንዲሁም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ያስተምሩ የነበሩ የትምህርት ክፍሉ መምራንን ለማስመደብ ጥረት እየተደረገ አንደሆነና ይህም የተማሪዎቹን ምዝገባ እንዳዘገየው የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ታረቀኝ ብርሀኑ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ገልጸዋል።

 ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#AASTU

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋረጡ 45 የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የማይኒንግ ምህንድስና ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ መሆኑን ገልጿል።

የዩኒቨርሲቲው የማይኒንግ ትምህርት ክፍል ከ2ኛ እስከ 5ኛ ዓመት የሆኑ 45 የማይኒንግ ምህንድስና ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል።

ለሰባት ወራት ትምህርት አቋርጠው የቆዩት ተማሪዎቹ ታኅሳስ 21 እና 22/2014 ዓ.ም ምዝገባ ማከናወናቸው ተገልጿል፡፡

የማካካሻ ትምህርትና አጫጭር የማጠናከሪያ ኮርስ በመስጠት የ5ኛ ዓመት ተማሪዎቹን ለማስመረቅ በተለየ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ሦሥት የአክሱም ዩኒቨርሲቲ መምህራንን ተቀብሎ ሥራ እንዳስጀመረም አሳውቋል።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
በ2013 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው ወደ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት ተላልፏል።

ሁለቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ የተማሪዎች ቅበላን የሚያከናውኑት በሀገር አቀፍ ደረጃ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባው ውጤት ከተወሰነ በኃላ ነው፡፡

ይህንን ሂደት ተከትሎም ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች የመመዝገቢያ እና ለፈተና ብቁ የሚያደርገውን ውጤት የሚወስኑ ሲሆን ምዝገባውም በኦንላይን ብቻ የሚከወን ይሆናል፡፡

በመሆኑም አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በሚወጣው መስፈርት መሰረት ለመግባትና ለመማር የምትፈልጉ ተማሪዎች ቀጣይ ሂደቶችን በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ይገለፃል ተብሏል።

#AASTU

መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#ASTU #AASTU

ሁለቱ የኢትዮጵያ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈትነው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስገባ ነጥብ ያዝመዘገቡ ተማሪዎችን ለመቀበል በዛሬው ዕለት ጥሪ አቅርበዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የ2014 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ በዛሬው እለት አውጥተዋል።

የመመዝገቢያ መስፈርቱ የሲቪክስ ትምህርትን ሳይጨምር የስድስት ትምህርት ድምር ውጤት ከዚህ በታች እንደተገለፀው ነው።

ለታዳጊ ክልሎች (አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤ/ጉሙዝ ፣ ጋምቤላ) ፦

- ኢንጂነሪንግ ለወንድ 395 ለሴት 390
- አፕላይድ ሳይንስ ለወንድ 385 ለሴት 380


ለሌሎች ክልሎች ፦

- ኢንጂነሪንግ ለወንድ 400 ለሴት 395
- አፕላይድ ሳይንስ ለወንድ 390 ለሴት 385


የምዝገባ ጊዜው ከየካቲት 21 ቀን 2014 ዓ/ም እስከ የካቲት 30 /2014 ዓ/ም ሲሆን ምዝገባው የካቲት 30 /2014 ዓ/ም ከለሊቱ 6 ሰዓት ላይ ይጠናቀቃል ተብሏል።

ከላይ የተቀመጠውን የምዝገባ መስፈርት የሚያሟሉ ተማሪዎች በማንኛውም ስፍራ ሆነው በኢንተርኔት www.aastu.edu.et እና www.astu.edu.et ላይ መመዝገብ ይችላሉ።

ፈተናው መጋቢት 7 ቀን 2014 ዓ/ም እንደሚሰጥ ተነግሯል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል)

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#ASTU #AASTU #ማሻሻያተደርጓል

ሁለቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች (አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ) የ2014 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ ላይ ማሻሻያ አድርጓል።

የመመዝገቢያ መስፈት የሲቪክስ ትምህርትን አይጨምርም‼️

• ለአዳጊ ክልሎች (አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ)

- ኢንጂነሪንግ ~ ለወንድ 375፣ ለሴት 370
- አፕላይድ ሳይንስ ~ ለወንድ 365፣ ለሴት 360

• ለሌሎች ክልሎች

- ኢንጂነሪንግ ~ ለወንድ 380፣ ለሴት 375
- አፕላይድ ሳይንስ ~ ለወንድ 370፣ ለሴት 365

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#ASTU #AASTU

በኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2014 ዓ.ም መግቢያ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገባችሁ ተማሪዎች የመለማማጀ ፈተናዎች ለማግኘት በተከታዩ ሊንክ በመግባት ማግኘት ይቻላል፦

http://cba.astu.edu.et/stu_download_demo_exam.php

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
Edited student list by center alemshet .xls
256 KB
#ASTU #AASTU

በ 2014 ዓ.ም ወደ ሁለቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ለመግባት ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች

ከታች በተዘረዘሩት የመፈተኛ ጣቢያዎች የተመዘገባችሁ ተማሪዎች ከላይ የተያያዘውን የኤክስ ኤል ፋይል በመክፈት የመፈተኛ ጣቢያችሁን በአድሚሽን ቁጥራችሁ አማካይነት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

1. አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
2. አአዩ ጥቁር አንበሳ መፈተኛ ጣቢያ(ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል)
3. ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
4. ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
5. ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
6. ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
7. ጎንደር ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
8. ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
9. ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
10. ወለጋ ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
11. ወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ካምፓስ መፈተኛ ጣቢያ
12. አምቦ ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ
13. አአዩ አራት ኪሎ መፈተኛ ጣቢያ(አራት ኪሎ)
14. አአዩ FBE campus (6 killo)
15. አአዩ (EIABC) መፈተኛ ጣቢያ( ልደታ ፍርድቤት ጎን)
16. አአዩ አምስት ኪሎ መፈተኛ ጣቢያ(አምስት ኪሎ)
17. አአዩ ኮሜርስ መፈተኛ ጣቢያ(ኮሜርስ)
18. አሶሳ ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ

©አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESUL
#Update #ASTU #AASTU

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ለመግባት ላመለከቱ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ዛሬ መሠጠት ተጀምሯል።

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ የመፈተኛ ጣቢያዎች እየተሰጠ ያለውን ፈተና እያስተባበረ እንደሚገኝ ገልጿል።

የፈተና አሰጣጡ በተሳካ ሁኔታ እየሄደ እንደሚገኝ ነው ዩኒቨርሲቲው የገለጸው።


ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#Update #ASTU #AASTU

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ለመግባት ያመለከቱ 6 ሺህ 179 ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ወሰደዋል።

መስፈርቶችን ያሟሉ 6 ሺህ 179 ተማሪዎች በ38 የመፈተኛ ጣቢያዎች የመግቢያ ፈተናውን መውሰዳቸው ተገልጿል።

2 ሺህ 696 ተማሪዎች በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት በ20 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለፈተናው ሲቀመጡ 3 ሺህ 483 ተማሪዎች በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት በ18 የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናውን ወስደዋል።

የፈተና አሰጣጡ ከጥቂት ግድፈቶች በስተቀር በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ነው የተገለጸው።

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESUL
#AASTU

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ላለፉት አስር ዓመታት ሲጠቀምበት የቆየውን አርማ ለውጧል።

ዩኒቨርሲቲው አዲሱን አርማ/ሎጎ ቅዳሜ ሰኔ 25/2014 ዓ.ም በይፋ አስተዋውቋል፡፡

አዲሱ አርማ የተቋሙን የአስር ዓመት ስትራቴጂክ ፕላን መሰረት በማድረግ መዘጋጀቱን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

አዲሱ ሎጎ ዩኒቨርሲቲው የሚጠቀምባቸውን የእንግሊዘኛ እና የአማርኛ ፊደላት አይነት፣ ምጣኔ እንዲሁም ለህትመት፣ ለማስታወቂያ እና ለሌሎች አገልግሎት የሚውል የደረጃ ይዘቶችንም የያዘ ነው፡፡

አቶ ቲዎፍሎስ መኮንን የተባሉ ግለሰብ አዲሱን ሎጎ በነፃ ሰርተው ለዩኒቨርሲቲው ማስረከባቸው ተገልጿል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#AASTU

የጸጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች " ትምህርት ስለተጠናቀቀ ግቢውን ለቃችሁ ውጡ እንደተባሉና ችግር ላይ መሆናቸውን" ገልጸውልናል።

በተለይ ከትግራይ ክልል የመጡ የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመመለስ ትራንስፖርት አለመኖሩ እንዲሁም ሌሎች ምክንያቶችን በማንሳት መቸገራቸውን ያስረዳሉ።

በጉዳዩ ዙሪያ የጠየቅናቸው የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም ዐቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አለምእሸት ገብረወልድ ተከታዩን ምላሽ ሰጠውናል።

"መደበኛ ነባር ተማሪዎች እስካሁን በግቢው ነው የሚገኙት። ማንም የወጣ ተማሪ የለም።"

"የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በጉዳዩ ዙሪያ እየመከሩ ነው። የትኞቹ ተማሪዎች ናቸው መቆየት ያለባቸው በሚለው ላይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እየተወያዩ ነው።"

"ዩኒቨርሲቲው የጸጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች የትኞቹ ናቸው የሚለውን ማጣራት ካደረገ በኋላ ውሳኔው እንደሚያሳውቅ" ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።


ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#AASTU

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ምዝገባ ሊጀምር ነው።

ስርዓቱ በመንግስት እና የግሉ ዘርፍ አገልግሎቶች ላይ ግልጽነት እና የተጠያቂነት አሰራርን እንደሚያበረታታ ታምኖበታል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ማከናወን የሚጠበቅባቸውን ዝርዝር አሳውቋል፦

~ ሁሉም ተማሪዎች (የቅድመ እና ድህረ-ምረቃ)፣
~ መምህራን (በሥራ ላይ እና በሀገር ውስጥ
ትምህርት ላይ የሚገኙ) እና
~ የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች (ቋሚ ቅጥር፣ ኮንትራት ቅጥር ወይም ጊዚያዊ ቅጥር ሰራተኞች)

የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ የዲጂታል ምዝገባ የሚያደርጉበት የጊዜ ሰሌዳን በቀጣይ ይገለጻል ተብሏል።

ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የተመደቡ ባለሙያዎች የዲጂታል መታወቂያውን እንደሚያዘጋጁ ታውቋል።

መንግስት በ2014 ዓ.ም በተመረጡ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ለማካሄድ እቅድ መያዙ ይታወሳል።

ተማሪ ነክ መረጃ እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#AASTU

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለ189 ተማሪዎች የስቴም ትምህርት ስልጠና ነገ መስጠት ይጀምራል።

የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና ሒሳብ ትምህርቶች ማበልፀጊያ ማዕከል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ከ8ኛ-12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡

ስልጠናው ሐምሌ 30/2014 ዓ.ም ይጀምራል ተብሎ የነበረ ሲሆን ያመለከቱ 400 ተማሪዎችን ለማጥራት በአንድ ሳምንት ወደፊት እንደተገፋ ተመላክቷል።

ስልጠናው ከነገ ነሐሴ 07/2014 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርቱ የሚሰጠው ቅዳሜ እና እሁድ ጠዋት ከ2:30-7:30 ሲሆን ዩኒቨርሲቲው የትራንስፖርት አገልግሎት ማዘጋጀቱን ገልጿል።

(ለስልጠናው የተመረጡ ተማሪዎች ስም ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን
@NATIONALEXAMSRESULT
#AASTU

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ፦

➤ የመጀሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች
     ➭ ጥቅምት 24 እና 25/2015 ዓ.ም

➤ 4ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ የማታ ተማሪዎች
     ➭ ጥቅምት 26 እና 27/2015 ዓ.ም

➤ ነባር የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች
     ➭ ጥቅምት 28 እና 29/2015 ዓ.ም

➤ አዲስ የድኅረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች
     ➭ ጥቅምት 30 እና ህዳር 01/2015 ዓ.ም

➤ ሁሉም የድኅረ ምረቃ የማታ ተማሪዎች
     ➭ ህዳር 3 እና 4/2015 ዓ.ም

አዲስ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች ለምዝገባ መያዝ የሚያስፈልጋቸው፦

• ፓስፖርት መጠን ያለው ፎቶግራፍ (3)

• በመንግስትና በግል ድርጅት ስፖሰርነት የምትማሩ ተማሪዎች የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ

• የግል ተማሪዎች የከፈላችሁበት ደረሰኝ

• የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው

• የሦሥተኛ ዲግሪ ተማሪዎች የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው

የአንደኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ትምህርት ጥቅምት 24/ 2015 ዓ.ም ይጀምራል፡፡

ተማሪ ነክ መረጃዎችን ያግኙ
@NATIONALEXAMSRESULT

Click here for advertisement
@studentsnewsadv35bot