TIKVAH-ETHIOPIA
1.44M subscribers
55.9K photos
1.4K videos
202 files
3.77K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#iSonXperiences

ከትላንት ጀምሮ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የጥሪ ማዕከል ሰራተኞች የሥራ ማቆም አድማ ላይ መሆናቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ የደረሰው መልዕክት ያሳያል።

ሰራተኞቹ የሥራ አድማውን ያደረጉት መስሪያ ቤታችን ቅሬታችንን ሊመልስልን አልቻለም በሚል መሆኑን ገልጸዋል።

ሰራተኞቹ ካቀረቡት ጥያቄዎች ዋነኛው " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የጥሪ ማዕከል ሰራተኞቹን በራሱ ሥር ያካተን ፤ በኤጀንት ለምን ያሰራናል ? " የሚል ነው።

በተጨማሪ ፦

➢ ለሙያው ከሚገባውና ካለው የሥራ ጫና አንጻር ተገቢ ያልሆነ የደመወዝ አከፋፈል ፤ ደመወዝ አላግባብ ተቆራርጦ መድረስ እና በጊዜው አለመግባት

➢ ለሰራተኛ የሚገባውን የሕይወትና የአካል ጉዳት ኢንሹራንስ አለመግባት፤

➢ ሰራተኛው ለማጁን የሰለጠነበት የምስክር ወረቀት አለመስጠት፤

➢ ድርጅቱ በተለያዩ የቀን እና የለሊት ፈረቃ ለሚሰሩ ሰራተኞች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ፍትሃዊ የመጓጓዣ አገልግሎት ጉድለት የሚሉና #ሌሎችም ቅሬታዎች አሏቸው።

ቲክቫህ ከቤተሰቦቹ እንደተረዳው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የጥሪ ማዕከል ሰራተኞች በቀጥታ የተቀጠሩት በሳፋሪኮም ሳይሆን ISON Xprience በተባለ ድርጅት አማካኝነት ነው።

ከሰራተቹ ጥያቄ ጋር በተያያዘ የ " ISON Xprience " የሥራ አመራሮች ህዳር 1 ቀን ከሰራተኛ ተወካዮች ጋር ስብሰባ አካሂዶ ነበር።

በዚህ ስብሰባ ላይ ክፍያን በተመለከተ ፤ " በኢትዮጵያ ህግ ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን ስለሌለ ደመወዝ በድርድር / በድርጅቱ የደመወዝ ስኬል የሚወሰን ነው።" ሲል ገልጿል።

ከቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የደረሱን ቅሬታዎች ይዘን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ለማነጋገር እና ምላሽ ለማግኘት ጥረት አድርገናል።

ሳፋሪኮም ፤ " የጥሪ ማዕከላችንን በሚያስተዳድርልን ድርጅት (ISON Xprience) እና በሰራተኛው መካከል አለመግባባቶች እንዳሉ ተረድተናል። " ያለን ሲሆን " በደርጅቱ ሥራ አስፈጻሚዎችና ሰራተኞች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ተፈትቶ መደበኛ የሥራ እንቅስቃሴዎች እንደሚቀጥሉ ተስፋ እናደርጋለን " ብሏል።

በዚህ ወቅት፤ ለደንበኞቹ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች እንደከዚህ ቀደሙ ፤ በተለመደው መልኩ እንደ ቀጠለ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አሳውቆናል።

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/ISON-Xprience-11-16