TIKVAH-ETHIOPIA
1.38M subscribers
54.6K photos
1.35K videos
197 files
3.61K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update “ ከታገቱ ሚያዚያ 19/2016 ዓ/ም ሰባት ወራት ይሆናቸዋል። እንደቀላል ነገር በወጡበት ቀሩ ” - የታጋች ባለቤት ከ6 ወራት በፊት ወደ ባቱ (ዝዋይ) ለስራ ጉዳይ እየተጓዙ በታጣቂዎች ታገቱ ከተባሉ 6 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች መካከል 3ቱ ቢለቀቁም 3ቱ ግን እንዳልተለቀቁ ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልም የሚችለውን ሁሉ…
#Update

“ በታጣቂዎች ከታገቱ 9 ወራት አለፉ፤ ያሉበትን እንኳ አናውቅም። ወደ ማን እንጩህ ? ”- የታጋች ባለቤት

መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም በታጣቂዎች ታግተው የተወሰዱ 3 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች ደብዛቸው እንደጠፋ መሆኑን የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

ወደባቱ ለስራ እየተጓዙ በነበረበት ወቅት በታጣቂዎቸ ታገቱ የተባሉት ሠራተኞቹ ያልተለቀቁት አጋቾቹ ገንዘብ ጠይቀው ከ2.8 ሚሊዮን ብር ከተላከ በኋላ እንደሆነ የታጋች ቤተሰቦች ከዚህ ቀደምም ገልጸው ነበር።

አሁንስ ምን አዲስ ነገር አለ ? 

- አቶ ልዑል አስፋወሰን
- አቶ ሰይፉ እንዳለ
- አቶ አብዩ ደገፋው የተባሉ ሠራተኞች በህይወት ይኑሩ አይኑሩ አይታወቅም።

ትላንት ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ 2 የታጋች ቤተሰቦች ስለ 3ቱም ታጋቾች ምንም የሰሙት ፍንጭ እንኳ እንደሌለ ገልጸዋል።

አንዷ የታጋች ባለቤት “ በታጣቂዎች ከታገቱ 9 ወራት አለፉ ፤ ያሉበትን እንኳ አናውቅም። ወደ ማን እንጩህ ? ” ሲሉ ሀዘን ያጀበው ጥያቄ አንስተዋል።

የሰው ልጅ ለ9 ወራት ያህል ያለበት እንኳን አለማወቅ ከባድ ሀዘን መሆኑን ፤ ኤሌክትሪክ ኃይልን በቅርቡ ቢጠይቁም ካቅሙ በላይ እንደሆነበት መግለጹን ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን እየተሰራ እንደሆነ ጥያቄ ያቀረበለት የኤሌክትሪክ ኃይል ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት መግለጹ ይታወቃል።

#TikvahEthiopaFamilyAA

@tikvahethiopia