TIKVAH-ETHIOPIA
1.38M subscribers
54.5K photos
1.35K videos
197 files
3.61K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #Sudan የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ እና ሱዳንን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ በአረብኛ ቋንቋ ባሰራጩት መልዕክት የሱዳንና የኢትዮጵያ ህዝቦች ወንድማማቾች መሆናቸውን ገልፀው በሁለቱ ሀገራት መካከል ችግር መኖሩ ግልፅ ነው ብለዋል። ነገር ግን ሁለቱ ሀገራት እነዚያን ችግሮች ለመፍታት ሊጥሩ እና ሊተባበሩ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። ኢትዮጵያ እና ሱዳንን ለማጋጨት የሚፈልጉ…
#Update #Ethiopia #Sudan

" መረጃው ውሸት ነው " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

" በእግረኛ የሚመጡ ከሆነ የአካባቢው ታጣቂ በተጠንቀቅ ቆሟል " - አቶ አብራራው ተስፋ

" ሱዳን ትሪቡን " የተባለው የሱዳን ሚዲያ የሱዳን ጦር ሰራዊት ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ኃይሎች ተወሰደብኝ ያለውን እርምጃ ለመበቀል የይገባኛል ጥያቄ በሚናሳበት የአልፋሽጋ አካባቢ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ስር የነበሩ " ካላ ላባን " እና " በረከት " የተባሉ አካባቢዎችን ተቆጣጥሯል ሲል ዘግቧል።

በዘገባውም ላይ የሱዳን ጦር በርካታ የኢትዮጵያ የጦር ተሸከርካሪዎች ላይ ጉዳት እንዳደረሰ  / እንዳቃጠለ ፣ ወታደሮችንም እንደማረከ ገልጿል።

ዛሬ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ቃላቸውን የሰጡት የኢፌድሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስተር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ መረጃው #ውሸት እንደሆነ አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል በም/ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የሱዳን ጦር አካባቢው እንዳይለማ አልሞ አሁንም ድረስ ከእርቀት መድፍ እየተኮሰ እንደሆነ የወረዳው የሰላምና ደህንነት ኃላፊ አቶ አብራራው ተስፋ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ገልፀዋል።

አንድ የአካባቢው ነዋሪም የሱዳን ጦር ትንኮሳውን በአካባቢው ትናንት ማምሻውን ቀጥሎ እንደነበር አስረድተዋል፡፡ 

መድፍ ከእርቀት ከመተኮስ ያለፈ ነገር እንደሌለ የሚናገሩት የወረዳው የሰላምና ደህንነት ኃላፊ ፥ " በእግረኛ የሚመጡ ከሆነ የአካባቢው ታጣቂ #በተጠንቀቅ_ቆሟል ነው " ያሉት፡፡ 

ህብረተሰቡ በሚተኮሱት ከባባድ መሳሪያዎች ከመደናገጥ ይልቅ ተደራጅቶ ዘልቀው የሚመጡ ከሆነ እየጠበቀ እንደሆነ ነው ለሬድዮ ጣቢያው ያስረዱት፡፡

@tikvahethiopia
#Sudan #June30March

ዛሬ በሱዳን ከፍተኛ ተቃውሞ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ዛሬ #June30 በጎረቤት ሱዳን በሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን የሚመራውን ወታደራዊ ጁንታን በመቃወም ከፍተኛ የሆነ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

በተቃውሞ ሰልፉ ወታደራዊው ክንፍ በመፈንቅለ መንግስት የያዘውን ስልጣን ለሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክብ እና የሲቪል መንግስት እንዲቋቋም ይጠየቅበታል ነው የተባለው።

ተቃውሞውን ተከትሎ የፀጥታ ኃይሎች የተለያዩ መንገዶችን ዘግተዋል። በተጨማሪ የፀጥታ ኃይሎች ሰልፍ የሚያስተባብሩትን አክቲቪስቶች እያደኑ እያሰሩ ነው ተብሏል።

የሱዳን ወታደራዊ ክንፍ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ከተቆጣጠረ በኃላ በሱዳን ዜጎች የሚደርስበት ተቃውሞ እስካሁን የቀጠለ ሲሆን ስልጣኑን ለሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክብ ግፊት እየተደረገበት ይገኛል።

እስከዛሬ ድረስ በነበሩት ተቃውሞዎች የመንግስት ፀጥታ ኃይሎች በወሰዷቸው እርምጃዎች ብዙ ሰዎች ሞተዋል፤ በርካቶችም ቆስለዋል።

@tikvahethiopia
#Sudan

ሱዳን በጋረጠችው የፀጥታ ችግር ሳቢያ በምዕራብ አርማጭሆ አንድ ጋሻ የሚጠጋ የእርሻ መሬት ለ1 ዓመት ያህል ሳይታረስ መቆየቱ ተገልጿል።

የሱዳን ኃይሎች የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው መግባት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ነው መሬቱ ያልታረሰው።

የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ም/ል ኃላፊ ደሴ ዘውዓለ ለአሐዱ በሰጡት ቃል፤ በምዕራብ አርማጭሆ ኢንቨስትመንት ቀጠና በስፋት ጥጥ፣ አኩሪ አተር፣ ማሽላና ሰሊጥ ይመረታል ብለዋን።

በ2013/14 የምርት ዘመን በአካባቢው የእርሻ ስራ ማከናወን ባለመቻሉ በርካታ ገንዘብ ስለመታጣቱን አንስተዋል፡፡

በተመሳሳይ በዞኑ መተማ ወረዳ በሱዳን ኃይሎች ሳቢያ በ2013 ዓ.ም ከእርሻ ስራ የወጡ 76 ባለሃብቶች መኖራቸውን የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ምህረቱፍቃድ ገላው ተናግረዋል፡፡

የሰሞኑን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ ግን ከእርሻ ስራቸው የተፈናቀሉ ባለሃብቶች አለመኖራቸውን አስረድተዋል፡፡

በወረዳው ደለሎ በሚባለው የኢንቨስትመንት ቦታ ከሱዳን የሚተኮሰው መሳሪያ በእርሻ ስራ ላይ #ከስጋት ባለፈ ያስከተለው ጉዳት እንደሌለ ገልፀዋል።

የሚተኮሰው መሳሪያ የሚያርፈው ከኢንቨስትመንት ስፍረው በ500 ሜትር ርቀት ላይ መሆኑን ነው የጠቀሱት፡፡

በመተማ ወረዳ በ3 የኢንቨስትመንት ቀጣና 256 ባለሃበቶች ተሰማርተው የቆዩ ቢሆንም ሱዳን ገፍታ በመምጣቷ ሳቢያ በአሁኑ ወቅት 76ቱ ከስራ ውጭ ናቸው፡፡

የሱዳን ኃይሎች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ከገቡበት ዕለት አንስቶ እስካሁን በምዕራብ ጎንደር ዞን 276 የሚደርሱ ባለሃብቶች ከስራቸው ተፈናቅለዋል።

መንግስት የጉዳዩን አሳሳቢነት በመመልከት የተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ ስራዎችን በመስራት የተስተጓጎሉ የእርሻ ስራዎች እንዲቀጥሉ ማድረግ እንደሚገባው የወረዳው ባለስልጣናት ጥሪ ማቀረባቸውን አሐዱ ቲቪ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#SUDAN #DrWorknehGebeyhu

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በሱዳን የአንድ ቀን የስራ ጉብኝት አድርገዋል።

ዋና ፀሀፊው በስራ ጉብኝታቸው ከሱዳን ጦር አዛዥ እና የሃገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን አሳውቀዋል።

በውይይቱ ኢጋድ ማክሰኞ ዕለት በኬንያ፣ ናይሮቢ ስለሚያካሂደው ስብሰባ የተነሳ ሲሆን ዶ/ር ወርቅነህ ከውይይቱ በኃላ በሰጡት መግለጫ በኢጋድ ስብሰባ ላይ የሁሉም አባል ሀገራት መሪዎች እንደሚገኙ ማረጋገጠናቸውን ገልፀዋል።

ስብሰባው እጅግ በጣም በወሳኝ ሰዓት የሚደረግ ስብሰባ ነው ተብሏል።

ስብሰባውን በተመለከት ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ፤ " እጅግ በጣም ወሳኝ ስብሰባ ነው " ያሉ ሲሆን " የሁሉም አባል ሀገራት መሪዎች እንደሚመጡ አረጋግጠውልናል ፤ የቀጣናው ጉዳይ በመሪዎችችን አማካኝነት ይመከርበታል ይህ እጅግ በጣም ትልቅ ዜና ነው " ብለዋል።

" መሪዎቻችን ቀጠናውን በሚያሳስቡ ጉዳዮች ላይ ፣ ለሰላም እና ደህንነት እንቅፋት ስለሆኑ ጉዳዮች ፣ በድርቁ ሁኔታ ላይ " ይመክራሉ ሲሉም ገልፀዋል።

ሱዳን የወቅቱ የኢጋድ ሊቅመንበር መሆኗ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#SUDAN

ሲቪል አስተዳደሩን ገልብጠው ሙሉ በሙሉ ስልጣን ከተቆጣጠሩ ጊዜ አንስቶ በሱዳናውያን ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ እያስተናገዱ ያሉት ሌ/ጄነራል አብዳልፈታህ አልቡርሃን ጦሩ ቦታውን እንደሚለቅ ተናግረዋል።

ትላንት ሰኞ ሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን በቴሌቫዥን ቀርበው የሱዳን ጦር ኃይል አገሪቱ ወደ ሲቪል አስተዳደር እንድትመለስ ለማድረግ ቦታውን ይለቃል ብለዋል።

የአገሪቱ ጦር ኃይል ሱዳን ወደ ዴሞክራሲ ለምታደርገው ሽግግር እንቅፋት እንደማይሆንና ምርጫ እንዲደረግ ወስኖ እየሰራ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ጨምረውም በአገሪቱ ያለውን ፖለቲካዊ ቀውስ ለማብቃት ከሲቪል ቡድኖች ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ ጦር ሠራዊቱ የሚያደርገውን ተሳትፎ እንደሚያቋርጥ አሳውቀዋል።

ነገር ግን አገሪቱ ውስጥ ምርጫ ስለሚደረግበት እንዲሁም ጦር ኃይሉ ሥልጣን ስለሚያስረክብበት ሂደት የጊዜ ሰሌዳ ምንም አላሉም።

በሱዳን ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲመሰረት የሚጠይቁት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ሠራዊቱ ከፖለቲካው እንዲወጣ በመጠየቅ ለወራት የዘለቀ ተቃውሞ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል ሲል ቢቢሲ ፅፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update እጅግ በጣም በወሳኝ ሰዓት ይደረጋል ያተባለው የኢጋድ ስብሰባ ዛሬ ይካሄዳል። በዚሁ ስብሰባ ላይ የአባል ሀገራት መሪዎች ናይሮቢ እየገቡ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል። ናይሮቢ ከደረሱ መሪዎች መካከል የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የሱዳኑ ወታደራዊ አስተዳደር መሪ እና የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ይጠቀሳሉ። ከኢጋድ ስብሰባ ጎን ለጎን ጠ/ሚ ዶ/ር…
#SUDAN #ETHIOPIA

የኢትዮጵያ እና የሱዳን ጉዳይ !

ኢትዮጵያ እና ሱዳን በመካከላቸው ያሉ ያልተፈቱ ቀዳሚ ጉዳዮቻቸውን በሰላማዊ መንገድ በውይይት ለመፍታት ቁርጠኛ መሆናቸው ገለፁ።

ኬንያ ፤ ናይሮቢ የሚገኙት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከጄኔራል አብዱል ፈታሕ አል-ቡርሃን ጋር ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱን ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ " ሁለቱ ሀገራት በሰላማዊ መንገድ ሊሠሩባቸው የሚችሉ በርካታ የትብብር መሠረቶች እንዳሏቸው አረጋግጠናል " ብለዋል።

" ያለን ትሥሥር ከየትኛውም መከፋፈል የሚበልጥ ነው " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " ሁለታችንም ያልተፈቱ ቀዳሚ ጉዳዮችን #በሰላማዊ መንገድ በውይይት ለመፍታት ቁርጠኝነታችንን ገልጸናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
#Sudan

በጎረቤት ሀገር ሱዳን ፤ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በሚቀርበው ብሉናይል ግዛት ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 31 ሰዎች ሲገደሉ 39 ሰዎች ለጉዳት መዳረጋቸው በርካቶችም ሰላም ፍለጋ መሸሻቸው ተሰምቷል።

ግጭቱ የጎሳ ግጭት እንደሆነ ተገልጿል።

በበርቲ እና ሃውሳ ጎሳዎች መካከል በተነሳ የመሬት ውዝግብ ምክንያት በሮሰሪስ ከተማ ውስጥ ከትናንት በስቲያ በተፈጠረው ግጭት ቢያንስ 31 ሰዎች ሲገደሉ፣ 39 ሰዎች ቆስለዋል በርካታ ሱቆች ተቃጥለዋል።

በሁለት ግለሰቦች መካከል የተነሳ አለመግባባት ሳቢያ አንድ ሰው (በግብርና ስራ የሚተዳደር) ከተገደለ በኃላ ግጭቱ ወደ ጎሳ ግጭት ተቀይሮ ነው የበርካቶችን ህይወት የቀጠፈው ተብሏል።

ምንም እንኳን ሱዳን በአካባቢው ተጨማሪ ወታደሮችን ብታሰማራም ግጭቱ እስከ ትላንት ከሰአት በኋላ ቀጥሎ መዋሉ ታውቋል።

መንግስት ደም አፋሳሹን ግጭት ለማስቆም ችግር ባለባቸው ቦታዎች ላይ የምሽት ሰዓት እላፊ አውጇል።

#CGTNAFRICA #AlJazeera #AP

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sudan በጎረቤት ሀገር ሱዳን ፤ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በሚቀርበው ብሉናይል ግዛት ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 31 ሰዎች ሲገደሉ 39 ሰዎች ለጉዳት መዳረጋቸው በርካቶችም ሰላም ፍለጋ መሸሻቸው ተሰምቷል። ግጭቱ የጎሳ ግጭት እንደሆነ ተገልጿል። በበርቲ እና ሃውሳ ጎሳዎች መካከል በተነሳ የመሬት ውዝግብ ምክንያት በሮሰሪስ ከተማ ውስጥ ከትናንት በስቲያ በተፈጠረው ግጭት ቢያንስ 31 ሰዎች ሲገደሉ፣…
#Update #SUDAN

ለኢትዮጵያ ድንበር በሚቀርበው የሱዳን ብሉናይል ግዛት ውስጥ በተቀሰቀሰው ደም አፋሳሽ የጎሳ ግጭት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 70 መደረሱ ሪፖርት ተደርጓል።

በበርቲ እና ሃውሳ ጎሳዎች መካከል በተነሳው የመሬት ውዝግብ ምክንያት በተፈጠረው ግጭት ቢያንስ 70 ሰዎች ሲገደሉ ከ200 በላይ ሰዎች ቆስለዋል (አብዛኞቹ በጥይት እና በስለት የቆሰሉ ናቸው) በርካታ ሱቆች ተቃጥለዋል ፤ 150 ሰዎች ተፈናቅለዋል።

በሁለት ግለሰቦች መካከል የተነሳ አለመግባባት ሳቢያ አንድ ሰው (በግብርና ስራ የሚተዳደር) ከተገደለ በኃላ ግጭቱ ወደ ጎሳ ግጭት ተቀይሮ ነው የበርካቶችን ህይወት የቀጠፈው ተብሏል።

Photo Credit : Darfur Monitors

@tikvahethiopia
#SUDAN

በትግራይ ክልል ጦርነት ሲቀሰቀስ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ሱዳን መግባታቸው ይታወሳል።

እነዚህ ኢትዮጵያውያን ተፈናቃዮች በነበሩባቸው የሱዳን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ #የግዳጅ የውትድርና ምልመላ ይካሄድ እንደነበረ መረጃ እንዳለው የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ለቢቢሲ በሰጠው ቃል አሳውቋል።

ተቋሙ ከወራት በፊት ከስደተኞቹ መካከል አንዳንድ ጊዜ በኃይል ጭምር ተዋጊዎችን ለመመልመል የሚደረጉ ጥረቶች እንደነበሩ " ተአማኒ ሪፖርቶች "  ደርሶኛል ብሏል ለቢቢሲ በሰጠው ቃል።

ተቋሙ ይህን ካወቀ በኃላ ምን አደረገ ?

የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን " ወታደራዊ ምልመላ መኖሩን እንደተገነዘብኩኝ ጉዳዩን ለሱዳን ማዕከላዊ መንግሥትና ለአካባቢ ባለሥልጣናት ስጋቴን ገልጫለሁ " ብሏል።  ይህንም ተከትሎ ሁኔታዎች የተሻሻሉ ይመስሉ ነበር ሲል መልሷል።

ምልመላውን ማነው የሚያደርገው ?

ይኸው የተመድ ተቋም " ወታደራዊ ምልመላውን ለማካሄድ #ከኢትዮጵያ የሚመጡ ሰዎች እንደነበሩ እና ይህንንም ከስደተኞች መረዳቱን ይገልጻል። ነገር ግን የትኛው ወገን ምልመላውን እንዳካሄድ " ማረጋገጥ አልቻልኩም"  ብሏል።

NB : ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግሥት ሰደተኛ ነን ብለው ወደ ሱዳን የገቡ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ከህወሓት ጋር በመሆን ሲዋጉ እንደነበር መግለፁ ይታወሳል።

ያንብቡ : telegra.ph/BBC-09-07

@tikvahethiopia
#SUDAN

በሱዳን ያሉ ኢትዮጵያዊያን ከግጭት አከባቢዎች እንዲርቁና ከእንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ ተለለፈ።

ካርቱምን ጨምሮ በተለያዩ የሱዳን ግዛቶች ግጭት ተፈጥሯል።

ከተፈጠረው ግጭት ጋር በተያያዘ ሊያጋጥም ከሚችል አደጋ እራስን መጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ከግጭት አካባቢዎች በመራቅና ከእንቅስቃሴ በመቆጠብ እራሳቸውን ከአደጋ እንዲጠብቁ በካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#SUDAN

ሱዳን ውስጥ እየተደረገ ያለው ግጭት መቀጠሉን ለማወቅ ተችሏል።

በተለይም በዋናነት በካርቱም ሰሜናዊ አቅጣጫ ግጭት እየተካሄደ እንደሆነ ተሰምቷል።

ከትላንት አንስቶ በነበረው ግጭት የሟቾች እና የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል። እስካሁን ባለው 56 ሰላማዊ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

የፈጣን ድጋፍ ሰጭ ኃይሎች በፖርት ሱዳን ጦራቸው #ከውጭ_አውሮፕላኖች ጥቃት እንደረሰበት ገልጸዋል። እነዚህ የውጭ ኃይሎች እነማን እንደሆኑ በግልፅ አልተነገረም።

የውጭ ኃይሎች ከጣልቃ ገብነት እራሳቸውን እንዲያርቁ እና እጃቸውን እንዲሰበስቡ RSF አስጠንቅቋል።

የሱዳን ጦር በRSF ይዞታዎች ላይ የአየር ላይ የቦንብ ጥቃቶችን ስለማድረሱ ለመስማት ተችሏል። ዋና ዋና የሚባሉትን የጦር ሰፈሮችንም መቆጣጠሩ እየተነገረ ነው።

የRSF አዛዥ ጀነራል መሐመድ ሀምዳን ደጋሎ ለሚዲያ በሰጡት ቃል ፤ እስካሁን ከ "አል-ቡርሃን" ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ገልጸዋል። " አል-ቡርሃን ተከቧል " ያሉት ዳጋሎ " ያለው አማራጭ እጅ መስጠት ብቻ ነው " ብለዋል።

ሱዳን ውስጥ የምትገኙ ቤተሰቦቻችን ነገሮች እስኪረጋጉ እራሳችሁን እንድትጠብቁ የሚወጡ ትዕዛዞችንም እንድትፈፅሙ አደራ እንላችኃለን።

ቪድዮ ፦ በሱዳን ከተማ ውስጥ ሲቪል ሰዎች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች የሚደረጉ ከፍተኛ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ያሳያሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በጎረቤት ሱዳን ያለው ውጊያ ዛሬ ለሶስተኛ ቀን መቀጠሉን ለማወቅ ተችሏል። ከካርቱም ጨምሮ ከሌሎች ከተሞች በወጡ መረጃዎች ዛሬም በከባባድ መሳሪያ የታገዘ የከተማ ውስጥ ውጊያ እየተካሄደ ነው። በተለይም በካርቱም ሰሜናዊ እና ደቡባዊ ክፍል የከባድ መሳሪያ ውጊያ እንዳለ ተነግሯል። የሠራዊቱ ጠቅላይ ዋና መሥሪያ ቤት በር ፊት ለፊት ውጊያ እየተካሄደ ሲሆን አርኤስኤፍ (RSF) ከቅዳሜ ጀምሮ…
#Sudan

በሱዳን የአሜሪካ ኤምባሲ ተሽከርካሪ በጥይት ተደበደበ።

በሱዳን ፣ ካርቱም የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ብረት ለበስ ተሽከርካሪው " ሆን ተብሎ " በጥይት መደብደቡን አስታወቀ።

ድርጊቱን የፈፀመው ሄሜቲ የሚመሩት RSF ቡድን መሆኑን ኤምባሲው ለአል አረቢያ ገልጿል።

ኤምባሲው ተሽከርካሪው በ100 ጥይት መደብደቡን ገልጾ ድብደባው ያደረሰው ምንም ጉዳት የለም ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ የአሜሪካ መንግሥት ጦርነት ውስጥ ካለችው ሱዳን ዜጎቹን የማስወጣት እቅድ እንደሌለው ዋይትሃውስ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#SUDAN

በሱዳን የEU አምባሳደር ጥቃት ተፈፀመባቸው።

በሱዳን ካርቱም ሚገኙት የአውሮፓ ህብረት (EU) አምባሳደር በመኖሪያ ቤታቸው ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ተሰማ።

አምባሳደሩ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ያሳወቁት የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ዲፕሎማት ጆሴፕ ቦሬል ናቸው (በትዊተር ገፃቸው)።

ቦሬል ስለ ጥቃቱ ምንም አይነት ዝርዝር ነገር ባይገልጹም አምባሳደሩ ግን " ደህና ናቸው " ብለዋል።

የዲፕሎማቲክ ቦታዎችን እና ሰራተኞችን ደህንነት ማስጠበቅ የሱዳን ባለስልጣናት ቀዳሚ ኃላፊነት ነውም ሲሉ ገልጸዋል።

ምንም እንኳን ቦሬል ፤ በሱዳን የአውሮፓ ህብረት አምባሳደርን ስም ባይፅፉም ስማቸው አይዳን ኦሃራ የሚባሉ ሲሆን የ #አየርላንድ ዲፕሎማት ናቸው።

ቦሬል ካርቱም ውስጥ የተፈፀመው ጥቃት ፤ በሌሎች ሀገራት የሚሰሩ ዲፕሎማቶች ጥበቃን የሚደነግገውን የተመድ ስምምነት የ " ቪይና ኮንቬንሽን " በእጅጉ የጣሰ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ የአውሮፓ ህብረት ቃል አቀባይ ናቢላ ማስራሊ ለAFP በሰጡት ቃል " የሰራተኞች ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው " ብለዋል፤ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ቡድን ከካርቱም እንዲወጣ እንዳልተደረገ ተናግረዋል።

ቃል አቀባይዋ ፤ በሱዳን ያለው የፀጥታ እና ደህንነት ሁኔታ እየተገመገመ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሱዳን ጦር በ72 ሰዓታቱ የተኩስ አቁም ተስማማ። ጦሩ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀን ድረስ ዜጎች የኢድ አልፈጥር በዓልን እንዲያከብሩ፣ እና ለሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት መሳለጥ ሲባል የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማቱን ዛሬ ማምሻውን አሳውቋል። በጄነራል ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር " አማፂያን " ሲል የጠራቸው የRSF ኃይሎች የተኩስ አቁሙን እንዲያከብሩና ይህንን የሚያደናቅፉ ማንኛውም ወታደራዊ…
#SUDAN

የሱዳን ተዋጊ ኃይሎች የተኩስ አቁም ቢያውጁም ውጊያው አሁንም መቀጠሉ ታውቋል ፤ ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሱዳን ለማስወጣት ሩጫ ላይ ናቸው።

ትላንት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ የ72 ሰዓታት የተኩስ አቁም ማወጁ፤ የሱዳን ጦርም ምሽት ላይ በተኩስ አቁሙ እንደተስማማ አሳውቀው እንደነበር ይታወሳል።

ነገር ግን ዛሬም በሱዳን የተለያዩ ቦታዎች ውጊያ መኖሩ ተሰምቷል። በካርቱም ካለፉት ቀናት ጋር ሲነፃፀር በተለየ መልኩ የተኩስ ድምፅ ቀንሶ ታይቷል።

በሌላ በኩል ፤ ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሱዳን ለማስወጣት ሩጫ ላይ ናቸው። ተዋጊ ኃይሎቹም የውጭ ዜጎች እንዲወጡ ለማመቻቸት ቃል ገብተዋል ተብሏል።

የሱዳን ጦር ፤ የውጭ ዜጎች እና ዲፕሎማቶች ከአሜሪካ ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ እና ቻይና በጦር አውሮፕላኖች ከካርቱም ኤርፖርት የማስወጣት ስራ በሰዓታት ውስጥ ይጀምራል ብሏል።

ከዚህ ባለፈ በሀገሪቱ የሚገኙ የሳዑዲ አረቢያ ዲፕሎማቶች ከካርቱም ወደ ፖርት ሱዳን ከዚያም ወደ ሳዑዲ አረቢያ እንዲወጡ መደረጉን አስታውቋል። የጆርዳን ዲፕሎማቶችም ዛሬ ወደበኃላ ላይ በተመሳሳይ መንገድ ከአገሪቱ ይወጣሉ ሲል ገልጿል።

በሱዳን የተካሄደ ያለው ውጊያ እጅጉን የከፋው በትልልቅ ከተሞች፣ የዜጎች የመኖሪያ መንደሮች፣ የስራ ቦታዎች ላይ እየተደረገ መሆኑ ሲሆን የሀገሬው ዜጋ እና የሌሎችም ሀገራት ዜጎች ያለ ውሃ ፣ ምግብ ፣ መብራት ቤታቸው ውስጥ ከሳምንት በላይ እንዲቀመጡ አድርጓል።

@tikvahethiopia
#Sudan

የጎረቤት ሱዳን ዜጎች በሰላም እጦት ሳቢያ የገዛ ሀገራቸውን ለቀው እየተሰደዱ ይገኛሉ።

ሱዳን አሁንም በጦርነት እየታመሰች ሲሆን ተዋጊዎቹ ኃይሎች ውጊያ የማቆም ፍላጎት እያሳዩ አይደለም።

በተደጋጋሚ በተለያዩ ሀገራት ጥረት የተኩስ አቁም እንዲደረግ እንዲሁም ዳጋሎ እና አል ቡርሃን ችግሩን እንዲፈቱ ጥረት ቢደረግም ውጤት አላስገኘም።

ዛሬም በርካቶች የሱዳን ዜጎች ሀገራቸውን ጥለው እየሸሹ ናቸው። የውጭ ሀገር ዜጎችም ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የሱዳንን ምድር እየለቀቁ ይገኛሉ።

በሱዳን ጦርነት ምክንያት እስካሁን ወደ ኢትዮጵያ በመተማ በኩል ፤ የ61 ሀገራት ዜጎች የሆኑ 7726 ሰዎች ገብተዋል።

@tikvahethiopia
#SUDAN

" ወደ ተኩስ አቁም ለማምራት መደላደል ነው " የተባለ ስምምነት በሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) መካከል ተፈረም።

በሱዳን ወጊያ ላይ የሚገኙት ሁለቱ ተፋላሚ ኃይሎች ሳዑዲ አረቢያ ፣ ጅዳ ሄደው ባካሄዱት ድርድር የመጀመሪያ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተነግሯል።

" የቅድሚያ ስምምነት መርሆች " መፈራረማቸውን የዘገበው አል አረቢያ  ሁለቱም ወገኖች ለሱዳን ሉዓላዊነትና አንድነት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል ብሏል።

ሁለቱ ኃይሎች የሱዳን ወዳጆች የሚያደርጉትን ጥረት በደስታ እንቀበላለን ማለታቸውንም ተነግሯል።

በመጀመሪያው ስምምነት መሰረት ፤ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት ከሚያደርሱ ጥቃቶች እንደሚታቀቡ ፤ በሱዳን ያሉ ሲቪሎች ያሉባቸውን አካባቢዎች ለቀው እንዲወጡ ያስገድዳል።

ተፋላሚ ኃይሎቹ በሱዳን የመንግስትና የግል ተቋማትን ለቆ ለመውጣት፣ የህክምና ባለሙያዎችን እና የህዝብ ተቋማትን መጠበቅ፣ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት መፍቀድ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ስምምነቱን በደስታ መቀበሉን ገልጾ፤ የጅዳ ድርድር በሁለቱ ወገኖች መካከል እስከ 10 ቀናት የሚቆይና የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ እንደሚያተኩር አስታውቋል። 

" የደህንነት እርምጃዎቹ በአሜሪካ፣ በሳዑዲ አረቢያ እና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚደገፍ የተኩስ አቁም ቁጥጥር ዘዴን ያካትታል " ብሏል።

የአሜሪካ መንግስት በሰጠው መግለጫ ስምምነቱ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዳልሆነ ተናግሯል። የጂዳ ስምምነት ወደ ተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያመራ መደላደል እንደሆነም ተነግሯል።

መረጃው የአል አረቢያ ቴሌቪዥን እና አል አይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
#Sudan

የጎረቤት ሀገር ሱዳን ጦርነት #ሰላማዊ መፍትሄ እንዲገኝ ኢጋድ በኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ  የሰላም ስምምነት እንዲጀመር ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ታውቋል።

በሱዳን ሚያዚያ ወር የጀመረው ጦርነት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን በርካቶች ህይወታቸውን እያጡ ፣ ከቤታቸው እየተፈናቀሉ፣ ንብረትም እየወደመ፣ የሀገሪቱ ኢኮኖሚም እየወደቀ ይገኛል።

ተፋላሚዎቹ የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሹ (RSF) ካርቱም ላይ ከሚያደርጉት ጦርነት ባሻገር ጦርነቱ የዳርፉር ክልልን ጨምሮ ወደ ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች የተስፋፋ ሲሆን በምዕራብ ዳርፉር ውስጥም የጎሳ ግጭት መቀስቀሱ ታውቋል።

ትላንትም የሱዳን መንግሥት ጦር ሠራዊት በኦምዱርማን በፈጸመው የአየር ጥቃት ቢያንስ ህፃናት እና ሴቶችን ጨምሮ 22 ሰዎች ሲገደሉ፣ በርካቶች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በሱዳን ያለውን አስከፊ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ አሜሪካ እና ሱዑዲ አረቢያ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካም። ተፋላሚዎቹ የተኩስ አቁም ለማድረግ ይስማሙና በሰዓታት ውስጥ ግጭቱን እንደሚቀጥሉ ከዚህ ቀደም በተዳጋጋሚ ታይቷል።

አሁን ላይ ደግሞ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) በሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች መካከል የሚደረግ የሰላም ስምምነት እዚህ አዲስ አበባ ላይ ሰኞ  ለመጀመር ጥረት እያደረገ መሆኑ ተሰምቷል።

ነገር ግን የሱዳን ጦር ኃይሎች አዛዥ ጄኔራል አል ቡርሐን በሰላም ንግግሩ ላይ " አልመጣም " ማለታቸውን ቃል አቀባያቸው መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#SUDAN

ዛሬም ድረስ አሸናፊም ሆነ ሰላማዊ የሆነ መፍትሄ ያልተገኘለት የጎረቤት ሀገር ሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት አራት ወራት ሊያስቆጥር ተቃርቧል።

በዚህ ጦርነት ምክንያት ከ24 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ይህ ማለት ከሀገሪቱ አጠቃላይ ዜጎች ውስጥ ግማሹ ያህሉ የምግብ እና ሌሎች ዕርዳታ እንዲፈልጉ አድርጓቸዋል።

ነገር ግን በአሰቃቂው ጦርነት እና የገንዘብ ድጋፍ እጦት ምክንያት 2.5 ሚሊዮን ዜጎች ብቻ ናቸው ድጋፍ ያገኙት ተብሏል።

እንደ ተመድ መረጃ ድጋፍ ከሚፈልጉ ዜጎች 14 ሚሊዮኑ ህፃናት ናቸው።

በአጠቃላይ እስካሁን በጦርነቱ ከ3000 የሚልቁ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ከ6000 በላይ ተጎድተዋል ፤ ሚሊዮኖችም ሀገራቸውን ጥለው ተሰደዋል፤ የሀገሪቱ ኢኮኖሚም ክፉኛ ተጎድቷል፣ የዜጎች ደህንነትም ጠፍቷል።

ተመድ ፤ በጦርነቱ ምክንያት በሱዳን ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ ጥረት ቢያደርግም ከአጠቃላይ ድጋፍ ፈላጊው መድረስ የቻለው ለ2.5 ሚሊዮኑ ብቻ ነው ፤ አሁን ላይ ሱዳን እጅግ አደገኛ ከሚባሉ ቦታዎች መካከልም መድቧታል።

በሱዳን ጦር መሪ ጄነራል አልቡርሃን እና በፈጥኖ ደራሽ በሚባለው ኃይል መሪ ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ወይም ሄምቲ መካከል ጦርነት የተቀሰቀሰው ሚያዝያ 7/ 2015 ዓ.ም ነበር ዛሬም ድረስ አንዱ አሸናፊ ሳይሆን የሰላም መፍትሄም ሳይገኝ ሀገሪቱ የከፋ ውድቀት ውስጥ እንደገባች ቀጥላለች።

@tikvahethiopia
#IGAD

ዛሬ በኡጋንዳ፣ ኢንቴቤ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት (ኢጋድ) መሪዎች ስብሰባ ይደረጋል።

ስብሰባው ትኩረት ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች አንዱ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ነው።

ሌላው የሱዳን ጦርነት ነው።

ለኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ እስካሁን ድረስ በታወቀው ፦

የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የጅቡቲው ፕሬዜደንት ኢሳሜል ኦማር ጌሌህ

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሙሐሙድ

የደቡብ ሱዳን ፕሬዜዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መሪ መሃመድ ሃምዳን ደጋሉ ካምፓላ ይገኛሉ።

#Sudan : የሱዳንን ብሔራዊ ጦር የሚመራው የሱዳን መንግሥት ኢጋድ የተፋላሚውን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል አዛዥ በስብሰባው እንዲሳተፉ መጋበዙ ‘የሃገሪቱን ሉላዊነት ጥሷል’ በሚል ውንጀላ ከኢጋድ ጋር ያለውን ግንኙነት አቋርጧል።

የኢጋድ አባል ሀገራት እነማን ናቸው ?
🇪🇹 ኢትዮጵያ
🇰🇪 ኬንያ
🇺🇬 ኡጋንዳ
🇸🇩 ሱዳን
🇩🇯 ጅቡቲ
🇪🇷 ኤርትራ
🇸🇸 ደቡብ ሱዳን
🇸🇴 ሶማሊያ ናቸው።

@tikvahethiopia
#Sudan #Ethiopia

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፤ ሱዳን ከኢትዮጵያ በቀን የምትወስደው የኤሌክትሪክ ኃይል ከ200 ሜጋዋት ወደ 50 ሜጋዋት መውረዱን ገለጸ።

በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያለችው ሱዳን ከኢትዮጵያ የምትወስደው የኤሌክትሩክ ኃይል በእጅጉ መቀነሱን ተነግሯል፡፡

ሱዳን #ጦርነት_ውስጥ_ከመግባቷ_በፊት ከኢትዮጵያ የምትገዛው የኤሌክትሪክ ኃይል በቀን እስከ 200 ሜጋዋት የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን 50 ሜጋዋት እና ከዚያ በታች ሆኗል ሲል አገልግሎቱ አስረድቷል፡፡

ለሱዳን የሚቀርበው ኃይል ከመውረዱም በላይ " ለተጠቀሙት የኤሌክትሪክ ኃይል እየከፈሉ አይደለም " ብሏል።

በታሰረው ውል መሰረት #ለተጠቀሙበት_ካልከፈሉ አገልግሎቱን ማቋረጥ የሚቻል ቢሆንም ግንኙነቱ እንዳይሻክር ኢትዮጵያ ይህንን አላደረገችም ሲል ገልጿል።

ኢትዮጵያ ከሱዳን ከጅቡቲ እና ከኬኒያ የኃይል ትስስር ያላት ሲሆን በቀን እስከ ሁለት ቴራ ዋት ሀወር ለሶስቱ ሀገራት ኃይል እንምድታቀርብ ተነግሯል።

ጅቡቲ የምትጠቀመው የኤሌክትሪክ ኃይል አብዛኛው ከኢትዮጵያ የሚሄድ ሲሆን ኬኒያም ከምትጠቀመው የኤሌክትሪክ ኃይል 10 ከመቶ ከኢትዮጵያ የሚሄድ ነው ተብሏል፡፡

#ShegerFM

#Sudan #Ethiopia

@tikvahethiopia