ኢዴፓ ቀጣዩ አገራዊ ምርጫ እንዲራዘምለት ጠየቀ!
የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ 5ኛው አገራዊ ምርጫ የማይራዘም ከሆነ በአዲስ አበባ ብቻ እንደሚወዳደርም አስታውቋል። ፓርቲው በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።
እንደ ፓርቲው መግለጫ 5ኛው አገራዊ ምርጫ በተያዘለት ጊዜ የሚካሄድ ከሆነ በአዲስ አበባ ብቻ እንደሚወዳደር ገልጿል።
ፓርቲው ከምርጫ ቦረድ ጋር በገባው ግጭት ያለአግባብ ታግጄ መቆየቷ ለቀጣዩ ምርጫ በአገር አቀፍ ደረጃ መዘጋጀት አልቻልኩም ብሏል።
ከሰኔ 2011 ዓ.ም ጀምሮ ምርጫ ቦርድ እገዳውን ስላነሳልኝ ለምርጫው ዝግጅቴን ጀምሬያለሁ የሚለው ይህ ፓርቲ ምርጫው እንዲራዘምለትም ጠይቋል።
ከእገዳው መነሳት በኋላ ፓርቲው ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ አቶ አዳነ ታደሰን የፓርው ሊቀመንበር ወ/ሪት ፅጌ ጥበቡን ደግሞ ምክትል ፕሬዝደንት አድርጎ መምረጡንና ይሄንንም ለምርጫ ቦርድ አሳውቂያለሁ ብሏል፡፡
ኢዴፓ በመግለጫው ከምርጫ ቡርድ ከተሰጠው ምላሽ በኃላ ልዩና አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ ከፓርቲው መልቀቂያ ሳይወስዱ በለቀቁ የፓርቲው የስራ አስፈጻሚ አባላት ምትክ የማሟያ ምርጫ ማድረጉን ተናግሯል፡፡
Via #ETHIO_FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ኢትዮጲያ በመጀመሪያ ድግሪና ከዚያ በላይ የተመረቁ ወጣት ሙያተኞችን ወደ አውሮፓና ጃፓን ለመላክ ዝግጅት መጀመሯ ተገለጸ። አገሪቱ ከአራት የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ጋር የስራ ውል ስምምነት ልትፈጽም መሆኑም ተገልጿል፡፡
በሃገራችን በአሁኑ ሰዓት ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ስራ አጥ ዜጎች ያሉ ሲሆን በያመቱ 3 ሚሊዮን የሚሆኑ ወጣቶች የስራ ዓለሙን ይቀላቀላሉ፡፡ በተመሳሳይም በያመቱ ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ድግሪና ከዚያ በላይ ይመረቃሉ፡፡
የኢትዮጵያ ማሪታይም ኢንስቲትዩት ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያሰለጠናቸው የማሪን ኢንጅነሪንግ ተመራቂዎች በመካከለኛው ምስራቅና አውሮፓ ኩባንያዎች ተቀጥረው ውጤታማ መሆናቸው ታይቷል። አሁን ደግሞ በተለይም የሙያ ነክ ትምህርት መስኮች ተመራቂዎችን ከአውሮፓና ጃፓን አገራትና ኩባንያዎች ጋር በመነጋገር ለመላክ ዝግጅት መጀመሩ ተገልጿል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት ሃገሪቷ ከሊባኖስ፣ ኩዬት፣ ባህሬንና ኦማን ጋር የስራ ስምሪት ስምምነት ለመፈጸም ድርድር እያደረገች መሆኑ ተገልጿል። ድርድሩ በቅርቡ ተጠናቆ ስምምነት ከተፈጸመ በኋላ ሰራተኞችን ወደነዚህ አገራት መላክ ይጀመራል ተብሏል፡፡
በተጨማሪም በቀጣይ በክህሎት የዳበሩ ዜጎችን ወደ አውሮፓና ጃፓን መላክ የሚያስችል የስራ ስምሪት ስምምነት ለመፍጠር እቅድ መኖሩን የሚኒስቴሩ ኮምዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ታዬ ነግረውናል፡፡ የኢትዮጲያ የውጪ ሃገር የስራ ስምሪት አዋጅ 923/2008 የስራ ስምሪት ማድረግ የሚቻለው ከኢትዮጲያ ጋር የስራ ስምምነት ከፈጸሙ ሃገራት ጋር ብቻ መሆኑን ይደነግጋል፡፡

#update የኢትዮጵያ ሲምካርድ ከአገር ውጪ በዝቅተኛ ክፍያ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረጉን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ። ድርጅቱ በሮሚንግ አገልግሎት ላይ የክፍያ ማሻሻያ ማድረጉን ገልጿል። የሮሞንግ አግልግሎት ኢትዮጵያዊያን ወይም የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ለስራ፣ ለትምህርት እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች ከሀገር ሲወጡ ሲም ካርድ መቀየር ሳያስፈልጋቸው በሄዱበት ሀገር በዓለም አቀፍ ደረጃ መጠቀም የሚያስችል አገልግሎት ነው፡፡ አገልግሎቱ ከዚህ በፊትም የነበረ ቢሆንም ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህ ቀደም ደንበኞች ይህ አገልግሎት ውድ ነው በሚል ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያነሱበት ነበር። ኢትዮ ቴሌኮም ይሄነን ቅሬታ ለመፍታት ከተለያዩ ሀገራት ኦፕሬተሮች ጋር በመነጋገር የክፍያ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
Via #ETHIO_FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #ETHIO_FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ያለበትን 151 ሚሊዮን ብር እዳ ባለመክፈሉ ምክንያት የላብራቶሪ ምርመራ አገልግሎት አቋረጠ። ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የላብራቶሪ መመርመሪያና ሌሎች የህክምና ግብዓት የሚቀርቡለት የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ነበር። ኤጀንሲው ከዚህ በፊት ለዚህ ሆስፒታል ያቀረበለትን ገንዘብ ባለመከፈሉ ምክንያት ግብዓት አላቀርብም በማለቱ ሆስፒታሉ ለጊዜው የላብራቶሪ ምርመራ አገልግሎትን እያካሄደ አይደለም። በዚህ ምክንያት ደግሞ ታካሚዎች ህክምና በላብራቶሪ ግብዓት እጥረት ምክንያት ለሳምንታት እየተንገላቱ መሆኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
Via #ETHIO_FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #ETHIO_FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SUDAN
በሱዳን የዳቦ ዋጋ መናርን ተከትሎ በተቀሰቀሰው የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት የቀድሞውን ፕሬዘዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽርን ከስልጣን በማውረድ ብቻ አልተጠናቀቀም ነበር።
ተቃውሞን ተከትሎም የአገሪቱ ወታደራዊ ጦር ስልጣን መቆጣጠሩን ተከትሎ በሱዳን ድጋሚ የፖለቲካ ቀውስ ተከስቶ ነበር። በዚህ ምክንያት ነበር የአፍሪካ ህብረት በወቅቱ የአገሪቱን ስልጣን ተቆጣጥሮ የነበረው ወታደራዊ የሽግግር መንግስት ስልጣኑን ለሲቪል እንዲያስረክብ ያዘዋል። ይሁንና የሽግግር መንግስቱ ስልጣኑን በተባለው ጊዜ ባለማስረከቡ ምክንያት ህብረቱ ሱዳንን በጊዜያዊነት አገደ።
አሁን ላይ የሽግግር መንግስቱና #የተቃዋሚ ሃይሎች በመስማማታቸው የፕሬዘዳንትነቱን ስልጣን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት የጠቅላይ ሚኒስትርነትና የተወሰኑ የሚኒስትርነት ቦታዎችን ከተቃዋሚዎች በሚመረጡ ሹመኞች እንዲያዝ ተስማምተዋል።
የቀድሞው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ምክትል ሃላፊ የነበሩት ኢኮኖሚስቱ ዶክተር አብደላ ሃምዶክ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ተደርገው የተሾሙ ሲሆን ካቢኔያቸውን ከትናንት በስቲያ አዋቅረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሱዳን የፖለቲካ ታሪክ የመጀመሪያዋን ሴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ሾመዋል። በሱዳን የነበረው የፖለቲካ ቀውስ እየረገበ በመምጣቱና ወታደራዊ ጦሩ ስልጣኑን በከፊል በማስረከቡ የአፍሪካ ህብረት በሱዳን ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ ማንሳቱን አስታውቋል።

#ADDISABEBA
በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ አትክልት ተራ አካባቢ አንድ የ20 ዓመት ወጣት ከፖሊስ #በተተኮሰ ጥይት #መሞቱ ተገለጸ። የ20 ዓመቱ ታዳጊ ወጣት ጅብሪል አህመድ በአትክልት ተራ አካባቢ የተለያዩ አትክሎትችን በመቸርቸር ስራ ህይወቱን ይመራ እንደነበር ኢትዮ ኤፍ ኤም በአካባቢው ከሚኖሩ ሰዎች አረጋግጫለሁ ብሏል። እናቱን በቅርቡ በሞት በማጣቱ ምክንያት ታናናሾቹን አንድ ወንድምና እህቱን ከዚሁ ስራ በሚያገኘው ገቢም ያስተዳደር ነበር። ይሁንና በትናንትናው ዕለት ጧት ላይ ከአንድ ሰው ጋር ግጭት ውስጥ ይገባሉ።
በሁለቱ ግገለሰቦች ምክንያት በአካባቢው የነበሩ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊሶች እንደመጡ በወጣት ጅብሪል አህመድ ላይ ሶስት ጥይት ተኩሰው እንደገደሉት የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል። ወጣት ጅብሪል ወዲያውኑ ወደ አቤት ሆስፒታል ቢወሰድም ህይወቱን ማትረፍ አልተቻለም። የሟች አስከሬንም ዛሬ ለአካባቢው ነዋሪዎች በመሰጠቱ ስርዓተ ቀብሩ በኮልፌ ሙስሊም መቃብር አካባቢ ተፈጽሟል። ፖሊስ ጉዳዩን በሚገባ ሳያጣራ ጥይት መተኮሱም በተለይም በስፍራው የነበሩ ሰዎችን አስቆጥቷል።
ነዋሪዎቹ እንዳሉት ፖሊስ ጉዳዩን ሳያጣራ ነው ልጁ ላይ የተኮሰበት፣ መንግስት ጉዳዩን አጣርቶ በህግ ተጠያቂ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል። በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ በጉዳዩ ዙሪያ መልስ እንዲሰጡን ተደጋጋሚ ሙከራ ቢደረግም ምላሽ ሊሰጡ አልቻሉም ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል።

#BREAKING
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ወይም ማለፊያ ነጥብን ይፋ አደረገ።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን እንዳስታወቁት የ2012 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ወይም ማለፊያ ነጥብ
1. የሶሻል ሳይንስ ሴቶች መግቢያ ውጤት 164 እና በላይ
2. የሶሻል ሳይንስ ወንዶች መውጤት ውጤት 174 እና በላይ
3. የናቹራል ሳይንስ ወንዶች መግቢያ ውጤት 176 እና በላይ
4. የናቹራል ሳይንስ ሴቶሽ መግቢያ ውጤት 166 እና በላይ
5. ለግል ተፈታኞች ለወንዶች 190 እና ከዚያ በላይ
6. ለግል ተፈታኞች ሴቶች 185 እና ከዚያ በላይ
7. ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች ናቹራል ወንዶች 166
8. ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች ናቹራል ሴቶች 156 እና ከዚያ በላይ
9. ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ማህበራዊ ሳይንስ ወንዶች 164 እና ከዚያ በላይ ሴቶች ደግሞ 154 እና ከዚያ በላይ መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም መስማት ለተሳናቸው በተፈጥሮ ሳይንስ ወንዶች 120 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች 115 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ማየት ለተሳናቸው ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ወንዶች 110 እና ከዚያ በላይ ሴቶች ደግሞ 105 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም በመንግስት እና በግል ተቋማት በግላቸው ከፍለው ለሚማሩ ተፈታኞች በሁለቱም መስክና ጾታ 140 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተፈታኞች መማር ይችላሉ ተብሏል።
በአጠቃላይ በዘንድሮው ዓመት 142 ሺህ 821 ተማሪዎች ወደ መንግስት ዩንቨርሲቲዎች ይገባሉ ተብሏል።

ግብፅ❓
"...አሁን ቢሆን እንድትገነባ አንፈቅድላትም" አብዱል ፋታህ አልሲሲ
የግብጹ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን የጀመረችው አሁን ቢሆን እንድትገነባ አንፈቅድላትም ነበር አሉ። ፕሬዘዳንቱ ኢትዮጵያ ከ8 ዓመት በፊት የተካሄደውን የግብጽ አቢዮት ተጠቅማበታለች ሲሉ ተናግረዋል።
ፕሬዘዳንቱ ይሄንን ያሉት በትላንትናው እለት በካይሮ በተደረገ ብሔራዊ የወጣቶች መድረክ ላይ ነው። ግብጻዊያን ከ8 ዓመት በፊት የሆስኒ ሙባረክን አገዛዝ ለመገርሰስ ወደ አደባባይ በወጡበት ወቅት ኢትዮጵያ ይሄነን አጋጣሚ በመጠቀም የህዳሴውን ግድብ መጀመሯን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ የጀመረችው አሁን ቢሆን ኖሮ እንከለክላት ነበር ሲሉ ለተሰብሳቢዎቹ መናገራቸውን የአገሪቱ የህትመት ሚዲያ አህራም ኦን ላየን የተሰኘው የእንግሊዘኛ ጋዜጣ አስነብቧል። ግብጽ በአብዮቱ ጊዜ የሰራችው ስህተት ዋጋ እያስከፈላት ነው ያሉት ፕሬዘዳንት አልሲሲ ተመሳሳይ ስህተት ለመስራት የሚፈልጉ ግብጻያን ወጣቶች እንዳሉም ተናግረዋል።
#ETHIO_FM
https://telegra.ph/ETH-09-15

5ሺ ዶላር የሚየሸልም ውድድር ይፋ ተደረገ!
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 5ሺ የአሜሪካን ዶላር የሚያሸልም ውድድር ይፋ አደረገ። ሚኒስቴሩ ከአይቢኤ ኢትዮጲያ ከተሰኘ የግል ኩባንያ ጋር በመተባበር አህጉራዊ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ንቅናቄ ‹‹አፍሪካ ኢኖቬሽን ሳምንት›› በሚል ከጥቅምት 17 እስከ ጥቅምት 22ቀን 2012 ድረስ በአዲስ አበባ አካሂዳለሁ ብሏል፡፡
ስለሆነም ችግር ፈቺ፤ ሀብት ፈጣሪና ወደ ምርትና አገልግሎት ሊቀየር የሚችል የፈጠራ ስራ ያላችሁ በዚህ አህጉራዊ መድረክ ላይ ሀገራችሁን ወክላችሁ እንድትወዳደሩና የፈጠራ ውጤቶቻችሁን ለውጭና ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶች፤ ለቬንቸር ካፒታል ተቋማት እና ለሌሎች የፋይናስ ምንጮች በማስተዋወቅ ወደ ምርትና አገልግሎት እንድትቀላቀሉ ይጋብዛል፡፡ በዚህ ውድድር አሸናፊ የሆኑ አምስት ከፍተኛ የፈጠራ ወይም የምርምር ስራዎች እያንዳንዳቸው 5ሺ የአሜሪካን ዶላር ተሸላሚ ይሆናሉ ተብሏል፡፡
ሌሎችም ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ #ሽልማቶች እንደሚበረከትላቸው በተገለጸው በዚህ ውድድር ላይ ለመካፈል ዘመናዊ ከተሞች እና አዳዲስ የመኖሪያ ቴክኖሎጂዎች፤ ዲጂታላይዜሽን፤ የኢንተርኔት ንግድ ስርዓት፤ የግብርና፤ የጤናና የህክምና ቴክኖሎጂ፤ መስተንግዶና ቱሪዝም፤ የማምረቻና እና የማዕድን ኢንደስትሪ አመልካቾች የፈጠራ ስራ ፕሮፖዛላችሁን ስከ መስከረም 16ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብላችኋል።
በዚህ ውድድር ላይ የመወዳደሪያ ሀሳባችሁን Registration@africaninnovationweek.com ላይ በመላክ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል።

#update የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን በማስመልከት ለማካሄድ ላቀደው ህዝበ ውሳኔ የምርጫ ምልክቶችን ይፋ አደረገ። ቦርዱ በመጪው ህዳር 3 ቀን 2012 ዓ.ም የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን በማስመልከት ለማካሄድ ላቀደው ህዝበ ውሳኔ አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እያከናወነ ይገኛል።
Via #ETHIO_FM
@tsrgabwolde @tikvahethiopia
Via #ETHIO_FM
@tsrgabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbaba
በአዲስ አበባ የትግራይ ተወላጅ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ከጸጥታ አካላት እና ከአዲስ አበባ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያዩ።
ውይይቱ ትኩረቱ የነበረው በአ/አ ከተፈጠረው ክስተትና ከንግድ ቤት መታሸግ ጋር በተያያዘ ነበር።
የትግራይ ተወላጅ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የንግድ ቤቶቹ መታሸግ ከማንነት ጋር የተያያዘ አንድምታ እየፈጠረባቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
መከላከያ ሰራዊቱ መቐለ ከተማን ሰኔ 21 ቀን 2013 ለቅቆ መውጣቱን ተከትሎ በአዲስ አበባ በሚገኙ ፣ ሆቴሎች ፣ መጠጥ ቤቶች እና ምሽት ቤቶች ብጥብጥ ለማስነሳት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦችን በመደገፍ የተጠረጠሩ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል።
እርምጃ የተወሰደባቸው ቤቶች በከተማዋ የዘር ፍጅት እንዲከሰት ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች በሆቴል ቤታቸው በማስቀመጥ ድጋፍ አድርገዋል በሚል ሲሆን ከነበረው ክስተት ጋር በተያያዘ መንግስት ከ8 በላይ ባለ ኮከብ ሆቴሎች እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ክለቦች እንደዚሁም ምግብ ቤቶችን ጨምሮ በድርጊቱ ተሳትፎ የነበራቸው ከረንቦላ ቤቶች ታሽገዋል።
ከትግራይ ተወላጅ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ጋር በተካሄደው ውይይት የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ የሴክተር ተቋማት ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት ሰለሞን ኃይሌ ፥ ሰላማዊ የሆነው የንግዱ ማህበረሰብ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ መብቱ ይጠበቃል ፤ ከንግዱ ማህበረሰብ የሚጠበቀው እራሱን ከህወሓት ቡድን ማራቅ ብቻ ነው ብለዋል፡፡
"የትግራይ ተወላጅ የሆነ በሙሉ በሀገር የተከሰተውን ህመም ሊጋራ ይገባል" ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ያንብቡ : telegra.ph/Addis-Ababa-07-28
Credit : #ETHIO_FM
@tikvahethiopia