TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BOLIVIA

ቦሊቪያ ውስጥ ወታደሮች የሀገሪቱን ፕሬዜዳንት ቤተመንግሥት በኃይል ሰብረው በመግባት መውረራቸው ተሰማ።

እንቅስቃሴው " መፈንቅለ መንግሥት " ሳይሆን እንዳልቀረ ተነግሯል።

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሉዊስ አርሴ የሀገሪቱን ጦር " መደበኛ ያልሆነ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው " በማለት አውግዘዋል።

ወታደሮቹ በአስቸኳይ ከቤተመንግሥት እንዲበተኑ ጠይቀዋል።

በቦሊቪያ ቴሌቪዥን ላይ የተሰራጨው ቪዲዮ አርሴ ከሠራዊቱ ዋና አዛዥ ጄነራል ጁዋን ጆሴ ዙኒጋ ጋር በቤተ መንግሥቱ ኮሪደር ላይ ሲፋጠጡና ሲነጋገሩ ታይተዋል።

አርሴ ፤ " እኔ የአንተ አለቃ ነኝ፣ ወታደሮቹንም እንድታስወጣ አዝዤሃለሁ እናም ለትዕዛዜ መገዛት አለብህ !! " ሲሉ ተደምጠዋል።

ዙኒጋ ወታደሮቹን ይዘው ወደ ቤተመንግሥት ሳይገቡ በፊት ውጭ ላይ ለሪፖርተሮች በሰጡት ቃል ፥ " ማጥፋት ይቁም፣ ሀገራችንን ወደ ድህነት መምራት ይቁም ፣ ሰራዊታችንን ማዋረድ ይቁም " ብለዋል።

የጦሩ አዛዥ ዙኒጋ ፥ " አዲስ የሚኒስትሮች ካቢኔ ይዋቀራል ፤ በእርግጠኝነት ነገሮች ይቀየራሉ፣ ሀገራችን ከዚህ በኋላ አሁን ባለው ሁኔታ መቀጠል አትችልም " ሲሉ ተደምጠዋል።

ፕሬዜዳንት አርሴ በቪድዮ ባሰራጩት መልዕክት ፥ ሀገሪቱን ከሚታየው የመፈንቅለ መንግሥት እንቅስቃሴ ለመታደግ ህዝቡ ተሰባስቦ እና ተደራጅቶ ወደ ጎዳና እንዲወጣና ዲሞክራሲውን እንዲታደግ ጥሪ አቅርበዋል።

#Bolivia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

በቦሊቪያ የተሞከረው መፈንቅለ መንግሥት ከሸፈ።

ሙከራው ሰዓታትን እንኳን አልቆየም።

የፕሬዜዳንቱን ቤተመንግሥት በኃይል ሰብረው ገብተው የወረሩት ወታደሮች ከቤተመንግሥቱ አካባቢ መሄዳቸው ተሰምቷል።

ፕሬዜዳንት ሉዊስ አርሴ ፤ ወታደሮችን እየመሩ ቤተመንግሥት የገቡትን የሠራዊቱን አዛዥ ጄነራል ጁዋን ጆሴ ዙኒጋን ከስልጣን አውርደው በሌላ ተክተዋል።

አዲሱ የሠራዊት አዛዥ ጆሴ ዊልሶን ሳንቼዝ ሁሉም ቤተመንግሥት የመጡ ወታደሮች ወደ የመጡበት ወታደራዊ ሰፈር /ክፍል እንዲመለሱ አዘዋል።

ይህን ተከትሎም ወታደሮቹ ከስፋራው ለቀው ሄደዋል።

ፕሬዝዳንት አርሴ አዲስ የአየር ኃይል አዛዥ እና የባህር ኃይል አዛዥም ሾመዋል።

ፕሬዝዳንቱ ወታደሮች ቤተመንግሥቱን ሰብረው መግባታቸውን እና መውረራቸውን ተከትሎ ህዝቡ በነቂስ ተደራጅቶ ወደ ጎዳና እንዲወጣና የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እንቅስቃሴውን እንዲያከሽፍ እና ዴሞክራሲውን እንዲያስጠብቅ ጥሪ አቅርበው ነበር።

በዚህም በርካቶች የሀገሪቱን ባንዲራ ይዘው በቤተመንግሥቱ አካባቢ ተሰብሰበው ነበር።

ፕሬዝዳንቱ ሙከራው መክሸፉን ተከትሎ ህዝቡን  በእጅጉ አመስግነዋል።

ወታደሮችን እየመሩ ቤተመንግሥት የገቡት ጄነራል ጁዋን ጆሴ ዙኒጋን ምንም እንኳን የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪ ነኝ ብለው በግልጽ ባይናገሩም ፥ " ጥፋት ይቁም ፤ ሀገራችንን ወደ ድህነት መምራት ይቁም፣ ሠራዊታችንን ማዋረድ ይቁም " ሲሉ ተደምጠው ነበር።

ጦሩ ዴሞክራሲን ወደነበረበት ለመመለስ እና የፖለቲካ እስረኞችን ነጻ ለማድረግ እንደሚጥርም ሲናገሩ ተደምጠዋል።

ዙኒጋን አዲስ የሚኒስትሮች ካቢኔ እንደሚቋቋም ከአሁን በኃላ ሀገሪቱ አሁን ባለው መንገድ እንደማትቀጥልም ገልጻው ነበር።

ጄነራል ዙኒጋን ከሽፏል ከተባለው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በኃላ ቀጣይ ዕጣፋንታቸውን እና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለጊዜው አልታወቀም።

ቦሊቪያ 🇧🇴 ፦ በደቡብ አሜሪካ የምትገኝ ከ12 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖሩባት ሀገር ናት።

#Bolivia
#failedcoup

@tikvahethiopia