TIKVAH-ETHIOPIA
1.37M subscribers
54.4K photos
1.34K videos
192 files
3.6K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

" ... አሁንም ቢሆን ለያዥ እና ገናዥ አስቸጋሪ የሆነው የመንግስት አቋም ነው " - መረራ ጉዲና (ፕሮፌሰር)

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ( #ኦፌኮ ) ሊቀመንበር መረራ ጉዲና (ፕ/ር) በሀገራችን ጉዳይ ላይ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

Q. በተለያዩ ቦታዎች ያለውን የጸጥታው ችግር እንዴት ትገመግሙታላቹ ? መፍትሄውስ ምንድን ነው ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" ብሔራዊ እርቅ እና ብሔራዊ መግባባት የሚባለውን እኮ ከኢህአዴግ መጀመሪያ ዓመት ጀምሮ እስከ 30 ዓመታት ስንጠይቅ ቆይተናል።

አሁንም ቢሆን መልክ አልይዝ እያለ ያስቸገረው / ለያዥና ለገናዥ አስቸጋሪ የሆነው የመንግስት አቋም ነው።

ስልጣንን በMonopoly መያዝ ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ እንደ ባህል ተይዟል። አሁንም ቀጥሏል። የኢትዮጵያ መሪዎች ከዛ አልወጣ አሉ። ውጤቱ ደግሞ የታወቀ ነው። 

ደርግ ወጣቶችን ጨፍልቆ ነው የሄደው ፤ ኢህአዴግ ለ27 ዓመታት አገሪቱን ቀላል ያልሆነ ቀውስ ውስጥ ከቷት ነው ጡረታ የወጣው ፤ ብልጽግናም በባሰ መንገድ ይህንኑ ሁኔታ እየተከተለ ነው።

የኢትዮጵያ ጸጥታ ሁኔታ ' ከድጡ ወደ ማጡ ' ተብሎ የሚገለጽበት ደረጃ ላይ ነው።  መፍትሄው ቁጭ ብሎ መወያዬት ነው።

ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን #ከመገዳደል ፓለቲካ ወደ #መደራደር ፓለቲካ ማምጣት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። "

Q. በየጊዜው የንጹሐን ሕይወት በግፍ እየተቀጠፈ ነው። ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ መስራትም የሞት ጊዜን እንደማፋጠን ሆኖ ይስተዋላል።  መፍትሄ እንዲመጣ ምን እየሰራችሁ ነው ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና፦

" ለ30 ይሁን ለ6ቱ ዓመታት በዴሞክራሲ የሚደረገው ለውጥ በተለይ ዴሞክራሲያዊ ምህዳርን እንዲያሰፉ ደጋግመን ስንጠይቅ ነበር።

አሁንም ያን መጠየቅ ቀጥለናል። ሜዳው / ምህዳሩ ግን በተቃራኒው እየጠበበ፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎች በአገሪቷ ላይ እየተንሰራፉ የመጡበት ሁኔታ ነው ያለው።

ምህዳሩ ካልሰፋ፣ ለዴሞክራሲ የሚደረገው ትግል መልክ ካልያዘ፣ ወጣቱንም ወደ ጫካ እየተገፋ የትም አያደርሰንም። "

Q. ከመንግስት የሚደርስባችሁ ጫና ምንድን ነው ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" ከኦነግ ቀጥሎ ከፍተኛ ጫና ያለበት የእኛ ፓርቲ ነው።

ለምሳሌ የዛሬ 4 ዓመት ከ200 በላይ ቢሮዎች ነበሩን፤ አሁን ያሉን 3 ብቻ ናቸው። አባሎቻችን #ግድያ እና #እስራት ይፈጸምባቸዋል። 

ለምሳሌ ፦ የምሥራቅ ወለጋ የቢሮ ኃላፊ ከተወሰደ የት እንደገባ አላወቅንም 2 ዓመታት ሊሆነው ነው።

የምሥራቅ ሸዋ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላችን ለዚያውም የዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ታስሯል።

አምቦ 4 ወጣቶች ታስረው 2 ሳምንታት ሆኗቸዋል። "

Q. #ብልሹ_አሰራርና #ሙስናን በተመለከተ ኢትዮጵያ በምን ደረጃ ትገኛለች ? መፍትሄውስ ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" በኢትዮጵያ ታሪክ የተለዬ/የከፋ የሙስና ደረጃ ነው ያለው።

መንግስትና ተቋማቱ የአንድ ቡድን ጉዳይ አስፈጻሚ ሆነው ሲዋቀሩ እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ይፈጠራሉ።

አሁንም መንግስት ተጠያቂነት ባለው መንገድ እንደገና ካልተዋቀረ በስተቀር፣ ከዚህ በሽታ የምንወጣበት መንገድ ያለ አይመስለኝም።

Q. የኑሮ ውድነቱ ሕዝቡን በእጅጉ አማሮታል። ፓርቲያችሁ ለመንግስት ያላችሁ ግምገማን ቢያጋሩ ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" ዜጎች እጅግ አስቸጋሪ ፣ ፈታኝ ሁኔታ ላይ ደርሰዋል።

መንግስት አስፈላጊ እርምጃ እንዲወስድ በተደጋጋሚ ተይቀናል።

መንግስት ግን ጆሮ ያለው አይመስልም። ችግሩ ግን እጅግ በጣም ፈታኝ ነው። "

Q. በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ተመራጭ ሆኖ ለመቅረብ ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ?

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

" የፓለቲካ ምህዳር ለማግኘት የመገዳደል ፓለቲካው እንዲቆም እየጠየቅን ነው። ምርጫ ከዚያ በኋላ የሚመጣ ነው።

ለነፃና ፍትሃዊ ምርጫ አስቻይ የሆነ ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም።

ትልልቆቹ አማራና ኦሮሚያ ክልሎች ጦርነት ውስጥ ናቸው። በዚህ ሁኔታ ምን አይነት ምርጫ እንደሚካሄ የምናየው ነው። መደራጀቱን ቀጥለናል። "

#TikvahEthiopiaFamilyAA

#ቲክቫህኢትዮጵያ
#የፖለቲካ_ፓርቲዎች_ምን_ይላሉ?

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 " አሁን ላይ ያሉ ችግሮች ምፍትሄ እስካላገኙ  ስለ ምርጫ ማሰብ #ቀልድ ነው " - አቶ ግርማ በቀለ የሕብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሕብር) ሊቀ መንበር አቶ ግርማ በቀለ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ቆይታ አድረገዋል። Q. የዜጎች በሕይወት የመኖር መብት ጥሰትን በተመለከተ ስለሚነሱ ጉዳዮች የፓርቲዎ ግምገማ ምን ይላል ?   አቶ ግርማ…
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

“ ... ያለፉትን ዘመናት እኮ #እንደ_ቅንጦት እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው ” - ጎጎት ፓርቲ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ' #የፖለቲካ_ፓርቲዎች_ምን_ይላሉ ? ' በሚል በህጋዊ መንገድ ተመዝገበው ለሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች እያቀረበ ያለውን ወቅታዊ ሀገራዊ ጥያቄዎች በመቀጠል ጎጎት ፓርቲን አነጋግሯል።

የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ጀሚል ሳኒ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

Q. ከዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት አንፃር የፓርቲዎን ግምገማና መፍትሄውን ቢገልጹ ?

አቶ ጀሚል ሳኒ፦

“ ሰዎች በተደጋጋሚ ሕይወታቸውን እያጡ ነው። በዋና ከተማዋ ሲይቀር ሰዎች እየታሰሩ፣ እየታገቱ ነው።

የትኛውም ዜጋ የደህንነት ስሜት እየተሰማው አይደለም። 

መንግስት #በዋነኛነት የተመሠረተበትና እንዲሰራው ኃላፊነት የተሰጠው ስራ ከየትኛውም ቅድሚያ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ የተዘነጋ የሚመስልበት ዘመን ላይ ነን።

በመወያየትና በመነጋገር ጦርነትን ማስቆም ይገባል።

ሰላምን ከማስፈን ይልቅ #ስልጣንን_የመጠበቅ ፣ የፕሮፓጋንዳ ስራ በመስራት ነው አብዛኛው አቅም እየባከነ ያለው።

ከዚያ ይልቅ አገሪቱን በሚያሻግሩ ሀሳቦች ላይ አተኩሮ መስራት ያስፈልጋል።

ያለፉትን ዘመናት እንደ ቅንጦተ እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው። ”

Q. በሙስና ተዘፍቀው ስለሚገኙ ባለስልጣናት እንዲሁም በአጠቃላይ ስለብልሹ አሰራር ፓርቲዎ ምን ይላል ?

አቶ ጀሚል ሳኒ ፦

“ አሁን ላይ #ሀዘኔታዎች_የጠፉበት ፣ ሌላው ይቅርና የዜጎች ቤቶች ‘ሕገ ወጥ ናቸው’ ተብለው ቤታቸው የሚፈርስባቸው ሰዎች ላይ ገንዘብ የሚጠየቅበት ሁኔታ ነው ያለው። 

ከኢትዮጵያ Norm ሁላ ያፈነገጠበት ወቅት ላይ ነው ያለነው። በአብዛኛዎቹ መስሪያ ቤቶች የተለመደውን አይነት አሰራር ከመስራት ይልቅ ከእግሮች እጆች እየቀደሙ ነው።

#ሙስና_በግልጽ_እየተጠየቀ ፣ ቢሮ ውስጥ ሥራ አስፈጻሚዎች #በግልጽ_ድርድር እያደረጉበት ያለበት ሂደት ነው አሁን ያለው።

አለ የተባለ የትኛውም ችግርን ለመቅረፍ ላይከብድ ይችላል ፤ ነገር ግን ከተንሰራፋ የትኛውንም ችግር ልቅረፍ ማለት የማይታሰብ ይሆናል። 

ሙስና የሀገር ተቋርቋሪነትን፣ ስሜትን ያጠፋል።

እያየነው ያለውም ይሄው ነውና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።”

Q. እንደ ፓርቲ የሚደርስባችሁ ጫና ምንድን ነው ?

አቶ ጀሚል ሳኒ ፦

“ የምስረታ ጉባዔ ባደረግንበት፣ የጉባዔውን ውጤትና የምርጫ ቦርድ ኮሮጆ ጭምር ይዘን በነበረበት ሰዓት ነው እስር የተጀመረው። ክፍለ አገርም አዲስ አበባም እስሮች አሉ። 

በአባል ደረጃ አንድ የፓርቲው አባል ከ5 ወራት በላይ ያለ ክስና ዋስትና በእስር ላይ ይገኛሉ። ከአባላቶች እስራትና ተንቀሳቅሶ ከመስራት ጋር ዘተያያዘ ያለፉትን ዘመናት እንደ ቅንጦት እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው።

ፓርቲውን የሚደግፉ አባላት #ወጣቶች_እየተላኩ ማስፈራሪያ ያደርሱባቸዋል።

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ሕገ መንግስቱን ያልከተለ በመሆኑ ምስረታው እንዲታገድ፣ ኢ - ሕገ መንግስታዊ ስራዎች በሰሩ ባለስልጣናት ላይ የመሰረትነው ክስ በቀጠሮ እየተጉላላ ነው ያለው። ”

Q. ሕዝቡ በኑሮ ውድነቱ ተማሯል። ለዚህም “ መንግስት ትኩረት አልሰጠም  ” የሚሉ ወቀሳዎች ይቀርባሉ። የፓርቲዎ ግምገማ ምንድን ነው ?

አቶ ጀሚል ሳኒ ፦

“ የኑሮ ውድነት በራሱ የሚፈጠር ነገር አይደለም። እስካሁን ከላይ የተነጋገርንባቸው ነገሮች ናቸው እየገፉ የሚያመጡት። 

አንዲት አገር #በጦርነት ላይ ሆና ሚሊዮን ዶላሮችም ለጦርነት እያወጣች ፣ አርሶአደር ማምረትና በሰላም ወጥቶ መግባት ባልቻለበት ፣ የመልካም አስተዳደር ፣ የአቅም ፣ የብቃት ጉዳዮች የመጨረሻ ውጤታቸው የኑሮ ውድነቱ ማምጣት ነው።

እነዚህን ችግሮች ማጥፋት፣ መቀነስ ካልተቻለ የኑሮ ውድነቱን ማረጋጋት፣ የተረጋጋ ኢኮኖሚ ማስፈን አይቻልም። ”

Q. ስለምርጫ ያላችሁ አስተያዬት ምንድን ነው ? በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ተመራጭ ሆኖ ለመቅረብ ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ?


“ ከምርጫ ጋር በተገናኘ ትኩረት ተደርጎ የሚሰራው፣ አጀንዳውም የሚያዘው ከሚደረገው #የፓርላማ እና #የክልል_ምክር_ቤቶች ጋር በተገናኘ ነው። 

ይሄ ስርዓቱን ለመቀየር የሚያስችል ብቸኛው መንገድ አይደለም። ከዚህ ይልቅ ምርጫ በየአካባቢው ማድረግ ያስፈልጋል። የአካባቢ ምርጫ የተደረገው ከ8 ዓመታት በፊት ነው።

የአካባቢ ምርጫ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

አሁን ባለንበት ሁኔታ ላይ #ምርጫ ሊደረግ ይችላል ብሎ ማለት ትንሽ አዳጋች ነው። ”

◾️በቀጣዩ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፓርቲ የሰጠው ቃል ይቀርባል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia