TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.2K photos
1.42K videos
206 files
3.92K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ - ዛሬ⬇️

🔹1

ዛሬም በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች #ስንደቅ_አላማ በመስቀልና የከተማዋን ጎዳናዎች በማቅለም ዙሪያ አለመግባባቶች ታይተዋል። #አዲሱ_ገበያ አካባቢ የኦነግን አርማ ይሰቀል/ይቀባ በሚሉና ቀድሞ የተሰቀለው አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ስንደቅ #አናስነካም ባሉ ወጣቶች መካከል ግብ ግብ ተነስቶ ፖሊስ ጣልቃ ገብቷል። በአስለቃሽ ጭስ ወጣቶቹን መበተን ያቃተው ፖሊስ ጥይት ወደ ስማይ #ተኩሷል። ኋላም በዶፍ ዝናብ ምክንያት ወጣቶቹ #ተበትነዋል
.
.
🔹2

የአዲስ አበባ ወጣቶችም ሆኑ የኦነግ ደጋፊዎች ከጠብ #አጫሪነት እንዲቆጠቡ ይህ ካልሆነ ግን ፖሊስ የህዝቡን ደህንነት ለማስከበር #እርምጃ እንደሚወስድ የፌደራል ፖሊስ ኮምሽነር ዘይኑ ጀማል አስታወቁ። ባለፉት ሁለት ቀናት ለንብረት ውድመት ምክንያት የሆኑ ግጭቶች መከሰታቸውንና ሁኔታው ተባብሶ በፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ጉዳት ለማድረስ ሙከራ መደረጉን የተናገሩት ኮምሽነር ዘይኑ ማናቸውም ዜጋ ያመነበትን የፖለቲካ ድርጅት አርማ ይዞ #የመውጣትና ተገቢ በሆኑ አካባቢዎች የመስቀል መብቱ የተከበረ ሲሆን፣ ጎዳናዎችንና የጋራ መገልገያዎችን #ቀለም መቀባት ግን ተገቢ አለመሆኑን አስረድተዋል።
.
.
🔹3

#የኦነግ አቀባበል ኮሚቴ በሰጠው መግለጫ የድርጅቱ ደጋፊዎች ከግጭት እራሳቸውን በማራቅ በሰላማዊ መንገድ እንዲንቀሳቀሱ #አሳስቧል

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፌደራል ፖሊስ-አልታገስም አለ⬆️

ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ የድርጅት አመራሮችን ለመቀበል በሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ላይ በወጣቶች መካከል እየተፈጠረ ያለውን ግጭትና ህገወጥ ተግባር ከዚህ በኋላ #እንደማይትገስ የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ከአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ኢብሳ ነገዎ ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው ላይም ኮሚሽነር #ዘይኑ_ጀማል፥ በትናንትናው እለት እና ዛሬ ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ የድርጅት አመራሮችን ለመቀበል በሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ላይ በወጣቶች መካከል ግጭት መፈጠሩን አስታውቀዋል።

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራውን #የኦነግ ቡድን ለመቀበል እየተደረገ ባለ ቅድመ ዝግጅት ወቅት ወጣቶች የድርጅቱን አርማ ለመስቀል ዝግጅት እያደረጉ ነበር፤ ይህንን የከለከላቸው አካል የለም ያሉት ኮሚሽነር ዘይኑ፥ ሆኖም ግን አስፋልትን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትን እንዳያቀልሙ ተከልክው፤ ይህንንም ተወያይተን እሺ ብለው ተቀብለው ትተው ነበር ብለዋል።

ሆኖም ግን ማንም ያልፈቀደላቸው አካላት የእነሱን ባንዲራ አውርደው የሌላ ለመስቀል ሲሉ ግጭት ተፈጥሯል ሲሉም ገልፀዋል።

ግጭቱ ለማንም ጠቃሚ አይደለም ያሉት ኮሚሽነር ዘይኑ፥ ችግሩን #በውይይት መፍታት ሲቻል ወደ አላስፈላጊ ግጭት መግባት ተገቢ አይደለም ሲሉም ተናግረዋል።

ፖሊስ የህግ የበላይነትን የማስከበር ሀላፊነት ስላለበት ከዚህ በኋ እንዲህ አይነት #ግጭቶችን በትእግስት እንደማያልፍም ኮሚሽነር ዘይኑ አሳስበዋል።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር #ብርሃኑ_ነጋ፥ የዴሞክራሲ ስርዓትን እንገንባ ብለን ስንሰና ስርዓቱን ለመገንባት የሚያስፈልግ እነዚህን ባህሪያትን ተቀብለን ካልተነሳን ግን ስርዓቱን መገንባት እንችልም ብለዋል።

የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ውስጥ ልዩነቶችን መቀበል የግድ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፥ ልዩነቶቹ ደግሞ ሀሳቦችን፣ አርማዎችን እና ባንዲራዎችን ሊያጠቃልል ይችላል ብለዋል።

ትናንትና እና ዛሬ በአዲስ አበባ የተስተዋሉ ችግሮች ደግሞ ከዚህ ጋር የሚፃረሩ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፥ ማንኛውም አካል ስሜቴን ይገልፅልኛል ያለውን አርማ የመያዝ እና የማውለብለብ #መብት አለው ሲሉም ተናግረዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ #ኢብሳ_ነገዎ በበኩላቸው፥ ሰሞኑን በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ የተስተዋለው ችግር #ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አንስተዋል።

ወጣቱም ከዚህ አይነት እንቅስቃሴዎች ሊቆጠብ እንደሚገባም አቶ ኢብሳ ጥሪ አስተላልፈዋል።

አሁን ላይ እየታየ ያለው ግጭት እና ያልተገባ #ፉክክር ድርጅታቸውን የማይወክል መሆኑንም ነው አቶ ኢንብሳ ተናግረዋል።

©Fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል‼️

ባለፈው ሳምንት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ያሶ ከተማ በፈፀመ ጥቃት #ስምንት የአንድ ቤተሰብ አባላት #መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች ለቢቢሲ ተናገሩ።

ህዳር 11 ቀን 2011 ማታ ከሶስት ሰዓት በኋላ ታጣቂዎች የቤተሰብ አባላቱን በጥይት ገድለው ቤታቸውንም እንዳቃጠሉ በጥቃቱ ባለቤታቸውንና የባለቤታቸውን ወንድሞች ያጡት የስምንት ልጆች እናት ወ/ሮ #ልኪቱ_ተፈራ ይናገራሉ።

"መጀመሪያ ተኩስ ከከፈቱብን በኋላ ቤት ውስጥ ጭድ ጨምረው እሳት ለኮሱብን። እኔና ልጆቼ በጓሮ በር በኩል አመለጥን። ሌሎቹ ግን እዚያው ተቃጠሉ" በማለት ሁኔታውን ያስታውሳሉ።

ልጃቸው አቶ ወጋሪ ፈይሳ በመኖሪያ ቤታቸው በወቅቱ ሃያ አንድ የቤተሰብ አባላት እንደነበሩና ቤታቸውም ፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያ በመሆኑ ደህንነት ተሰምቷቸው እንደነበር ይናገራል።

ነገር ግን ያልጠበቁት ነገር መከሰቱንና በተፈጠረው ነገርም ህፃናት ልጆች ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ እንዳሉም ይገልፃሉ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሳ አህመድ ከተማው ውስጥ ግድያ ስለ መከሰቱ መረጃ እንዳላቸው ነገር ግን ዝርዝር ጉዳዮችን እንደማያውቁ ገልፀዋል።

ከጥቃቱ የተረፉ የቤተሰቡ አባላት ሸሽተው የተጠለሉበት አዋሳኝ የምሥራቅ ወለጋ ሃሮ ሊሙ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጋሮማ ቶሎሳ ግድያው ስለመፈፀሙ ማረጋገጫ እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

"አባቴ ፈይሳ ዲሳሳ፣ ወንድሙ ዲንሳ ዲሳሳን ጨምሮ ስምንት የአጎቶቼ ልጆችን አጥተናል። ግድያው በጣም አሰቃቂ ነበር" ይላሉ አቶ ዋጋሪ።

በተመሳሳይ እለት የቤተሰብ አባላቱን ግድያ ጨምሮ በያሶ ከተማ በተፈፀመ ጥቃት አርባ የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን ኗሪዎችና የአዋሳኝ ወረዳ አስተዳዳሪው ቢናገሩም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊው አቶ ሙሳ ግን አስር ሰው ብቻ ስለመገደሉ መረጃ እንዳላቸው ይገልፃሉ።

ሆኖም ግን ጉዳዩን በሚመለከት ተጨማሪ መረጃ እንደሚያስፈልጋቸው "መንገድ በመዘጋቱ ነገሮችን በቅርበት ማጣራት አልቻልንም" በማለት ተናግረዋል።

አቶ ሙሳ እንደሚሉት የረቡዕ ጥቃት ከመፈፀሙ ከጥቂት ቀናት በፊት ሁለት የመንግሥት ሰራተኞች ተገድለዋል። አርብ እለትም ደግሞ በካማሼ ሌሎች ሦስት ሰዎች መሞታቸውንም ገልፀዋል።

በያሶ ጥቃቱን የፈፀሙት ታጣቂዎች ከመሆናቸው በዘለለ ስለታጣቂዎቹ እስካሁን ምንም የተረጋገጠ መረጃ እንደሌለ አቶ ሙሳ ይናገራሉ።

'ያፈነገጡ የኦነግ ታጣቂዎች' ለአካባቢው ስጋት እየሆኑ እንደሆነ አቶ ሙሳ ቢናገሩም ያነጋገርናቸው ኗሪዎች እና የአዋሳኝ ወረዳ ሃላፊዎች ግን በአካባቢው #የኦነግ ታጣቂ እንደሌለ ገልፀዋል።

በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ አራት የካማሺ ዞን ሃላፊዎች አሶሳ ከተማ ስብሰባ ቆይተው ወደ ካማሺ በመመለስ ላይ ሳሉ በተከፈተባቸው ተኩስ ህይወታቸው ማለፉን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት ብዙዎች መገደላቸውንና ወደ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ከቀያቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅት ግን ነገሮችን #ለመቆጣጠር በያሶ ከተማ ፌደራል ፖሊስ፤ በካማሽ ደግሞ መከላከያ ሠራዊት እንደገባ አቶ ሙሳ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በምእራብ ወለጋ #የኦነግ ማሰልጠኛ ካምፕ ናቸው ተብለው በተጠረጠሩ ቦታዎች ላይ ዛሬ ጥዋት #የአየር_ጥቃት መፈፀም መጀመሩን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።
.
.
የአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ...

Ethiopia Defense Force begins #airstrike in western Oromia; says targets are OLF military training #camps. Ethiopian National Defense Force (ENDF) has began airstrikes in Qellem Wellega and its environs in western Oromia, a military source told Addis Standard. According to our source, the army’s targets are “military training camps run by OLA”, the armed group of the Oromo Liberation Front – Shane Group (OLF-SG). The airstrikes have began this morning; it is unclear how long the army will conduct the operation. It follow yesterday’s #bank_robbery of the state owned Commercial Bank of Ethiopia and the Cooperative Bank of Oromia.

©Addis Standard
@tsegabwolde @tikvahethiopi
TIKVAH-ETHIOPIA
ኦነግ ላይ #ተሰነዘረ ስለተባለው የአየር ጥቃት! #ጋዜጠኛ_ኤልያስ_መሰረት(AP) ሰሞኑን አንዳንድ የሀገር ውስጥ ሚድያዎች በኦነግ ማሰልጠኛ ካምፖች ላይ የአየር ጥቃት መድረሱን ሲዘግቡ ሰንብተዋል። አንድ የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን ትናንት ምሽት anonymously የነገሩኝ ግን ፈፅሞ የተለየ ነበር፦ "ያው እንደምታውቀው መከላከያ የራሱ ስርአት ስላለው እና እኔም ወታደር ስላልሆንኩ ዝም ብዬ በነሱ…
"የአየር ጥቃት ተፈፅሟል" ኦነግ‼️

ዕሁድ ጠዋት የሀገር መከላከያ በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ የኦነግ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች ላይ የአየር ጥቃት ሰንዝሯል የሚል መረጃ በስፋት ተሰራጭቶ ነበር።

የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ #ገመቺስ_ተመስገን በጉዳዩ ላይ BBC የአማርኛው አገልግሎት አስተያየታቸውን ጠይቆ፤ ''ይህ መረጃ እስካሁን አልደረሰኝም። በምዕራብ ኦሮሚያ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ይንቀሳቀሳል። በተለያዩ አጋጣሚዎችም ከኦነግ ሠራዊት ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርጓል። ዕሁድ ዕለት የአየር ጥቃት ተሰንዝሯል ወይም #አልተሰነዘረም ማለት #አልችልም'' ብለዋል።

በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የአየር ጥቃት የተፈጸመው በቤጊ እና ጊዳሚ ወረዳዎች አዋሳኝ ድንበር ላይ መሆኑ በስፋት ተነግሯል። ይሁን እንጂ BBC ያነጋገራቸው የአከባቢው ነዋሪዎች "የአየር ጥቃት ተፈጽሟል ሲባል ሰማን እንጂ ያየነው ነገር የለም" ይላሉ።

ነዋሪዎቹ እንደሚሉት፤ የአየር ጥቃት ሲፈጸም #ባይመለከቱም በአከባቢው የጦር ሄሊኮፕተሮች በብዛት ስለሚመላለሱ ከፍተኛ ስጋት ገብቷቸዋል።

#የኦነግ_ሸኔ የሥራ አሰፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ #ሚካኤል_ቦረና ግን መንግሥት በቤጊ እና ጊዳሚ ወረዳዎች ውስጥ የአየር ጥቃት #እየሰነዘረ ነው ሕዝቡም እየተጎዳ ነው ብለዋል። አቶ ሚካኤል እንደሚናገሩት፤ የኦነግ ጦር የነበረበትን ስፍራ ሳይለቅ እራስን #የመከላከል እርምጃ እየወሰደ ነው።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አየር ሃይል‼️

‘በምዕራብ ኦሮሚያ በኦነግ ሸኔ ላይ በአየር ኃይል የታገዘ ጥቃት ተፈጽሟል’ ተብሎ በማህበራዊ ድረ-ገጾች የሚናፈሰው ወሬ #ሃሰተኛ መሆኑን የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል #ይልማ_መርደሳ ገለጹ።

ብርጋዴር ጄኔራሉ በምዕራብ ኦሮሚያ የጸጥታ ችግር መኖሩንና መንግስት ብዙ ትዕግስት ማሳየቱን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።

መንግስት የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ እርምጃ መውሰድ የጀመረ ቢሆንም በማህበራዊ ድረ-ገጾች ‘በአየር ኃይል የታገዘ ጥቃት ተፈጽሟል’ ተብሎ የሚነዛው ወሬ ሃሰተኛ መሆኑን አስታውቀዋል።

በአካባቢው ከምድር ውጊያና የሰፈር ግጭት ያለፈና አውሮፕላን መጠቀም የሚያስገድድ ሁኔታ አለመኖሩንም ነው የገለጹት።

ምንጭ፦ ኢዜአ
.
.
.
ምንም እንኳን መንግስት የአየር ጥቃት አልተፈፀመም፤ የሚናፈሰው ወሬም ሀሰት ነው ቢልም ከቀናት በፊት ቢቢሲ ያነጋገራቸው #የኦነግ_ሸኔ የሥራ አሰፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ #ሚካኤል_ቦረና መንግሥት በቤጊ እና ጊዳሚ ወረዳዎች ውስጥ #የአየር_ጥቃት እየሰነዘረ ነው ሕዝቡም #እየተጎዳ ነው ብለዋል። አቶ ሚካኤል እንደሚናገሩት፤ የኦነግ ጦር የነበረበትን ስፍራ ሳይለቅ እራስን #የመከላከል እርምጃ እየወሰደ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሃገር ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረውን #የኦነግ ታጣቂ ወደ ካምፕ ለማስገባት የተሰራው ስራ ላይ የማጠቃለያ ሪፖርት ቀረበ። ሪፖርቱ በመንግስትና በኦነግ የዕርቀ ሰላም ኮሚቴና የሃገር ሽማግሌዎች አማካኝነት፥ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እና የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በተገኙበት ነው የቀረበው።

ከሪፖርቱ በኋላ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የኦነግ አመራሮች፥ የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነትና አንድነት ለማረጋገጥ በጋራ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል። ኦነግ የክልሉ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚሰራቸውን ስራዎች እንደሚደግፍም ሊቀ መንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ተናግረዋል።

Via #BBC
ፎቶ፦ ጃዋር መሃመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia