TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የፐርፐዝ ብላክ አካውንቶች ታገዱ። የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ አካውንቶች በመንግስት ታግደዋል። ድርጅቱ አካውንት ሲታገድብኝ ይህ በዓመት ለ3ኛ ጊዜ ነው ብሏል። የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጰያ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶክተር ፍስሐ እሸቱ ፥ የድርጅቱ አካውንቶች ለምን እንደታገዱ ምክንያቱን እንደማያውቁት ገልጸዋል። በአመት ውስጥ ምክንያቱ  ሳይታወቅ ለሶስት ጊዜ አካውንታቸው መታገዱን አመልክተዋል። ስለ…
#Update

" መጀመሪያ 250 ሚሊዮን ብር ከዛ 200 ሚሊዮን ብር ጉቦ ጠየቁን " - ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ

የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሀገር ጥለው አሜሪካ መግባታቸው ተሰምቷል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ ዛሬ አሜሪካ ሆነው መግለጫ ሰጥተዋል።

" ከሀገረ የወጣሁት በግፈኞች ምክንያት ተገድጄ ነው " ብለዋል።

ባልፈው የግላቸውን ጨምሮ የድርጅቱ የባንክ አካውንቶች በሙሉ በመንግስት መታገዱን መግለጻቸው ይታወሳል።

ይህን በተመለከተ በሰጡት ቃል፥ " አካውንቶቹ የታገዱት ጽንፈኛ የፋኖ ታጣቂ ኃይሎችን በመርዳት፣መሳሪያ በማዘዋወር በሙስና ወንጀል፣ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር በሚል እና በሌሎች ነው  " ብለዋል።

" እኛ ምርመራ ይደረግ እያልን ነበር በኃላ እውነቱ ጫና የሚደረገው ብላክሜል ለማድረግ እና አስፈራርቶ የሚፈልጉትን ነገር ለመቀበል ነበር " ሲሉ ተደምጠዋል።

ዶ/ር ፍስሃ መጀመሪያ 250 ሚሊዮን ብር ከዛ ግን 200 ሚሊዮን ብር ጉቦ ክፈሉ እንደተባሉ ተናግረዋል።

ለዚህም " የስልክ እና ሌሎች ማስረጃዎች አሉን " ብለዋል።

" መቼ እና እንዴት ገንዘቡ እንደሚከፈል ፣ በምን ሁኔታ እንደሚከፈል ጭምር ፣ መቼ ገንዘቡ እንደሚወጣ ጭምር ነው ትዕዛዝ የተሰጠን " ሲሉ ገልጸዋል።

" ሰዎቹ ልክ ቼኩን እንደወሰዱ በማግስቱ ሁሉም እግድ እንደሚነሳ ቃል ገብተው ነበር " ብለዋል። 

" ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋርም እናገናኛችኋለን ስብሰባም ትቀመጣላችሁ ብለው ነበር " ሲሉ ጠቁመዋል።

የተጠየቀው ጉቦ የማይሰጥ/ የማይከፈል ከሆነ ግን ከማሰር እስከ መግደል የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ዛቻና ማስፈራሪያ እንደተሰነዘረባቸው ገልጸዋል።

አጠቃላይ በጠራራ ጸሀይ እንዝረፋችሁ የሚል " የማፊያ " ስራ ነው የተሰራው ሲሉ አክለዋል።

" ሆን ተብሎ በደረሰብኝ ጫና፣ ማስፈራራትና ዛቻ እኔን አጥቅቶ ገንዘብ ለማግኘት ፣ ድርጅቱንም ለመቆጠር በሚሰራው ስራ ሀገር ለቄቄ ወጥቻለሁ " ብለዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው ፤ " ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄ ሁሉ ሲደረግ ያውቃሉ ብዬ አላስብም ፤ በእሳቸው የአመራር ዘመን እንደዚህ አይነት በአፍሪካ ሆነ በዓለም የሚዘገንን የዝርፊያና ሙስና ስራ ሲሰራ ዝም ብለው ያያሉ ብዬ አላምንም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" እኛ ከቢዝነስ ውጭ ምንም የፖለቲካ ፍላጎት የለንም ፤ ' ፅንፈኞችን ይደግፋሉ ፣ መሳሪያ ያዘዋውራሉ ' የሚለው ክስ በሬ ወለደ ነው ከኛ ጋር አይገናኝም " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩም ያለው ችግር በሰላም ይፈታ ዘምድ መፍትሄ እንዲፈልጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

" ከአሁን በኃላ ከማንም ጋር መስራት አንፈልግም ፤ በሚኒስትር ደረጃ ያሉትን አነጋግረናል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ውጭ  መፍትሄ የሚሰጠን የለም " ብለዋል።

" ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ለደህንነታችን ዋስትና ይስጡንና ስራችንን በሰላም እንስራ " ብለዋል።

" ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ውጭ ችግራችንን የሚፈታልን የለም ፤ ከሳቸው ውጭ ያየነው ነገር ቢኖር ከፍተኛ ሙስና የማፊያ ሰራ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከእሳቸው ውጭ ባሉት የበታች ሰዎች ምንም እምነት የለንም " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ ሽምግልና እንደሚሞከር ጠቁመው አስፈላጊ ከሆነም የአሜሪካ ኤምባሲ ጣልቃ ገብቶ እንዲያግባባ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ  " ሰዎቹ " እያሉ የጠሯቸው (200 ሚሊዮን ብር ጉቦ የጠየቋቸው) እነማን እንደሆኑ ፣ የስልጣን ደረጃቸው ፣ የተቋም ኃላፊነታቸው ምን እንደሆነ በግልጽ #ስማቸውን_ጠቅሰው አልተናግሩም።

" በደረሰብኝ የእስርና ግድያ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ሀገር ለቅቄ ወጥቻለሁ " ያሉት የኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ  ከሀገር ሲወጡ የገጠማቸው ነገር ስለመኖሩ የሰጡት ቃል የለም።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia