TIKVAH-ETHIOPIA
1.44M subscribers
55.9K photos
1.4K videos
202 files
3.77K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ስለ ህዳሴ ግድብ...

- የሲቪል ስራው (በሳሊኒ እየተሰራ ያለ) 82 ፐርሰንት ደርሷል።

- የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራው (ለረጅም ግዜ በሜቴክ ስር የነበረ) 25 ፐርሰንት ላይ ይገኛል።

- በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ወደ 65 ፐርሰንት ገደማ ላይ ነው።

- እስካሁን የተበየደው ያ ሁሉ ብረታ ብረት ልክ ነው አይደለም የሚለው ጥያቄ ውስጥ ገብቷል።

- ብዙ ኮንትራቶችን እንደ አዲስ እየተደራደርን ሲሆን በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በሙሉ ሀይል ወደ ስራ እንገባለን።

- ለሜቴክ የተሰጠው ክፍያ 65 ፐርሰንት ሲሆን የፈፀመው ስራ ግን 25 ፐርሰንት ገደማ ነው። ይህም ትልቅ ችግር እና imbalance አስከትሏል።

- ያለፈው አልፏል። #ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር የለም።

Via-Elias Meseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ሂርጳ 'ዳግም' ሞቱ‼️

ከሁለት ወራት በፊት የሞትን ብርቱ ክንድ አሸንፈው ተነሱ የተባሉት አቶ #ሂርጳ_ነገሮ ሞተው ሳሉ የገጠማቸውን ለቢቢሲ አጫውተው የነበረ ሲሆን ከ70 ቀናት በኋላ ትናንት 'ዳግም' ማረፋቸውን ከሁለት ጊዜ ገናዣቸው ተሰምቷል።

መቃብር ፈንቅለው ከወጡ በኋላ ጤናማ የነበሩት አቶ ሂርጳ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ግን በፅኑ ታመው ከፈሳሽ ውጭ ምንም ነገር ይወስዱ እንዳልነበር BBC ከቤተሰቦቻቸው ማረጋገጥ ችሏል። እሳቸው አይሆንም ቢሉም ቤተሰቦቻቸው ነቀምት ሆስፒታል ወስደዋቸው ነበር። ቤተሰቦቻቸው አቶ ሂርጳ ዳግም መቃርብር ፈንቅለው ይነሳሉ የሚል #ተስፋ እንደሌላቸው ገልፀዋል።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia