The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#የእግዚአብሔር_ልጅ"

ውጥረት እና ግርግር ከማያጣት አዲስ አበባ አምልጬ በሚስቴ ትምህርት ሰበብ በውቧ የእስኮትላንድ መዲና ኤድንብራ ከልጆቼ ጋር ያሳለፍኳቸው እና የተረጋጉ አመታትን ያስታውሱኛል።

ወደ ተለያዩ የብሪታኒያ ከተሞች በየሰንበቱ የማደርጋቸው የአገልግሎት ጉዞዎች ትዝ ይሉኛል። የጌታ ቸርነት እና የሚያስቡልን ወገኖች ፍቅር ይታወሰኛል። በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ምጥ የበረታባትን መከረኛ አገሬን በልቤ ተሸክሜ ነበር።

(ከመጽሐፉ ተቀንጭቦ የተወሰደ)

አስተማሪ፡ ሰባኪ፡ አቃቤ-እምነት፡ ፀሐፊና ተርጓሚ ነው ጳውሎስ ፍቃዱ።

በተለያዩ መጣጥፎቹ የምናውቀው ወንድም ጳውሎስ ፈቃዱ ከ 10 በላይ መጽሐፍትን የተረጎመ ከመሆኑ ባሻገር ያልተንኳኩ በሮችና የብርሃን አንጓዎች የተሰኙ ሁለት መጽሐፍትን ከዚህ ቀደም ጽፎ አበርክቶልናል፡፡

ወንድማችን ጳውሎስ ፍቃዱ በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያንን በትጋት እያገለገሉ ካሉ ወንድሞቻችን መሃል አንዱ ነው። በሚዛናዊ እይታው እና የአንድን የመፅሃፍ ቅዱስ እውነታ ፈልፍሎ ለማውጣት በሚጥረው ስራው ይታወቃል። ህዝበ ክርስቲያኑን በተለያዩ ዘርፎች እያገለገለ ሲሆን ሶስተኛውንና "የእግዚአብሔር ልጅ" የተሰኘውን ድንቅ መጽሐፍ ደግሞ ነገ መስከረም 23 ከቀኑ 9 ሰዓት የተቀባ የእግዚአብሔር ቃል ቤ/ክ ይመረቃል።

ለማንኛውም ነገ ሁላችሁም በ9:00 ተጋብዛችኋል። ከአዲስ አበባ ውጪ በተለያየ አለም ለምትገኙ ቤተሰቦች ደግሞ የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ሙሉ መረጃውን አጠናክረን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።

ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/
የመሰረተ ክርስቶስ #ቤተክርስቲያን #ግማሽ_ሚሊዬን ብር ድጋፍ አደረገች።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከየካቲት 30 እስከ መጋቢት 2/2015 ዓም ድረስ በቦረና አካባቢ ያሉትን ወገኖች ጎብኝታለች።

በቦረና ከተከሰተው ድር ቅ የተነሣ ለካፋ ችግር ለተጋለጡ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች እና ሌሎች ወገኖች ግማሽ ሚልዮን ብር ወጭ በማድረግ በጊዜያዊነት እርዳታ አድርጋለች።

በሌላ በኩል በአከባቢው #የእግዚአብሔር_የእርዳታ_እንዲገለጥ በጋራ ጸሎት ከማድረጋቸውም በተጨማሪ ከተለያዩ የቦረና አከባቢዎች ከተውጣጡ የቤተክርስቲያን መሪዎች ጋር የቤተክርስቲያንቷ ፕሬዚዳንት የወደፊት የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ላይ ምክክር አድርገዋል።

እግረ መንገዳቸውንም የዲላ አጥቢያን ጨምሮ የተለያዩ አጥቢያ ቤተክርስቲያናትን መጎብኘታቸውን እና ለቦረና አከባቢ ጸሎት እና የምግብ እህል ድጋፍ እንዲደረግ ማሳሰባቸውን የቤተክርስቲያኒቱ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አሳውቋል።
#live እየገባችሁ በልሳን የምትፀልዮ ሰዎች ስህተት ውስጥ ናችሁ። ዘማሪት ሶፊያ ሽባባዉ

#መጽሀፍ #ቅዱስ ድርጊታችሁን ስህተት ነው ስለሚል እኔም ስህተት ነው እላለሁ።

በየ ሚዲያውና በየ ቲቪ ቻናሎች በልሳን የሚጸለይበት አላማው ምንድነው? ይህን በማድረጋችሁ እምነቱን ከማሰደብና ማላገጫ ከማድረግ ውጭ አንዳች የምታመጡት ጥቅም የለምና እባካችሁ ስሜታዊነትን አስወግዱና ቃሉ እንደሚል እንሁን።

የሚመለከታቸው #ክርስቲያን #ሁሉ #አሜን እያለ ከማደፋፈር ይልቅ ልክ አለመሆናቸውን በማሳወቅ ማስተው ያስፈልጋል። ማንም ሰው ከቃሉ አይበልጥም።

አንዳንድ አገልጋዮች የማያምኑ ሰዎች በጉባኤው እንዳሉ እያወቁ እስኪ ሁላችሁ በልሳኖቻችሁ ጸልዩ ብለው ጭራሽ ትዛዝ ሲሰጡ ግራ ይገባኛል።ሰውም እነሱ ያሉትን ተከትሎ በሚያምንም በማያምንም ፊት በልሳን እየጮኸ ይጸልያል።

#የእግዚአብሔር #ቃል ነው መከበር ያለበት ወይስ የአገልጋዩ ትዕዛዝ? የሁልጊዜ ጥያቄዬ ነው።

1ቆሮንጦስ 14:23
እንግዲህ ማኅበር ሁሉ አብረው ቢሰበሰቡ ሁሉም በልሳኖች ቢናገሩና ያልተማሩ ወይም የማያምኑ ሰዎች ቢገቡ፡— አብደዋል አይሉምን?
#ኑ #የእግዚአብሔርን #ቤት በጋራ እንስራ!!!

ለብዙዎች መጠለያ የሆነችው እና ለአርሲ ዩንቨርስቲ አሰላ ካምፓስ ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት ማምለኪያ የሆነችው የአሰላ አርዱ ቁጥር 2 #ሙሉ #ወንጌል ቤተክርስትያን #ዛሬ የሁላችንን እገዛ ትፈልጋለች።

#አሁን የምትገኝበት የማምለኪያ አዳራሽ የአምልኮ ፕሮግራም ለመካፈል የሚመጡትን አማኞች መያዝ ስላልቻለ እና እንዲሁም የአሁኑ አዳራሽ እየፈረሠ ስለሚገኝ ከአጥቢያዋ በረከት የተካፈላችሁ በዓለም ዙሪያ እንዲሁም በሃገር ውስጥ የምትገኙ የአሰላ አርዱ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ቤተሰቦች ወዳጆች እንዲሁም #የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ለዚህ ስራ እጆቻቸሁን እንድታበረቱ ስንል በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን።

ከዚህም ጋር ተያይዞ ከመጋቢት 6 እስከ 8/2016 ዓ.ም በአጥቢያዋ የተዘጋጀ #ልዩ ኮንፍራንስ ስላለ በቦታው በመገኘት በዚህ የወንጌል ስራ እንድትሳተፉ #በጌታ #ፍቅር እንጠይቃለን።

በተጨማሪም በቦታው መገኘት የማትችሉ ከታች በመተቀመጠው የቤተክርስቲያኒቷ አካውንት እጆቻችሁን ትዘረጉ ዘንድ በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን።

1000515969962 ንግድ ባንክ
1600860054837 ብርሃን ባንክ

የአሰላ አርዱ ሙሉ ወንጌል #ቤተክርስቲያን
ፍትህ #ግን ይወጣል ከሰማይ ...😭😭😭
አበጥሮ ሁሉን ከሚያይ ...
የጊዜ ጉዳይ እንጂ #ሁሉ ነገር
ከፍርድ የለም ሚቀር
ከፈጣሪ ወንበር ከሰማዩ መንበር
ስታይ ከዙፋን የለም አንድም ሚቀር
#ፍትህ ይወጣል ከሰማይ

#ልጆች #የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናቸው። እናቶች የምድር በረከቶች ናቸው። እናቶች ብዙ ጊዜ ከመጽናናት ከሚከብዳቸው ነገሮች መካከል አንዱ የልጆችን ሃዘን መቋቋም ይከብዳቸዋል።

መጽሃፍ ቅዱስም “ #እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን ፈጽሞ እንቢ አለች።” ይላል።

የእናትየዋን መሪር ሃዘን ሳይ ጥፋተኞቹ ከጥፋታቸው በላይ #አሁን በድጋሜ ለሌላ ጥፋት እየተሰናዱ መሆናቸው የበለጠ እንዳሳመማት ያሳያል።

የመጽናናት አምላክ የሆነ #እግዚአብሔር ለእናትዬው መጽናናት ይስጥ። ፍትህ ግን ተጓድላ አትቀርም።