The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#የዛሬ_እንግዳችን
#ነብይ_ሱራፌል_ደምሴ
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

ተወልዶ ያደገው በመዲናችን አዲስ አበባ "ጉርድ ሾላ" አከባቢ ነው። ወላጅ ቤተሰቦቹን በ10ዓመቱ አጥቷቸዋል። በመሆኑም ወደ አያቶቹ ሃዋሳ ሄደ። ምንም እንኳን ቤተሰቦቹ በጌታ ቢሆኑም ጌታን ያገኘው ግን ቆይቶ ነው።

ወደ ጌታ እና ወደ አገልግሎት የመጣው በፌሎሺፕ አማካኝነት ነው። ወደ ጌታ እንዲመጣ ምክንያት የሆነችው ደግሞ ተወዳጇ ባለቤቱ መስክራለት ነው።

ጌታን ከተቀበለ በኋላ በሃዋሳ ተወዳጅ እና ትልቅ በሆነችው የሃዋሳ ህይወት ብረሃን ቤተ ክርስቲያን ነው።

ነብይ ሱራፌል ደምሴ ዛሬ የፕረዘንስ ኦፍ ጋር አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን መስራች እና ባለራዕይ ነው።

ከተወዳጁ ዘማሪ ይሳቅ ሰዲቅ ጋር በአንድ ፌሎሺፕ የማገልገል እድል ነበረው። በፌሎሺፕ ቆይታቸው በግቢ ውስጥ (አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ) ዛምሬዎችን በማዘገጅት እና ሲዲ በጋራ በማዘጋጀት 11 ተማሪዎች ሊረዱ ችለዋል።

ከግቢ ቆይታው በኋላ "የዜማ ጊዜ ደረሰ" የሚል መጠሪያ ያለው የዝማሬ አልበም ለበረከት ይሆን ዘንድ አደረሰን።

ከአገልግሎት ከጠፋ ከሁለት አመት በኋላ (ለሌላ አገልግሎት በጸሎት ቆይታ ውስጥ) ሲመለስ

"ክብረ ጌትዬ ክበር አባባ
ጠላቴ ዛሬ ግራ ይጋባ

የተሰኘ ዝማሬን ይዞ በርካቶች እንዲጽናኑ እና እንዲባረኩ ምክንያት ሆኗል። የዛሬዋን የፕረዘንስ ኦፍ ጋድ ቤተክርስቲያንን ከመጀመሩ በፊት በቤተክርስቲያን መሪዎች ተጽልዮለት እና እንዲከናወን (በአገልግሎቱ እንዲሳካለት) ተባርኮ ነው ወደ አገልግሎት የገባው።

በተለያዩ ጊዜያት ከመንፈሳዊ አገልግሎት ባሻገር ብዙዎችን በመደገፍ ይታወቃል። የትላቱ ተወዳጅ ዘማሪ የዛሬው ነብይ ሱራፌል ደምሴ።
#አሳዛኝ_መረጃ
The Christian News - የክርስቲያን ዜና
#ነብይ_ብረሃኑ_ዳና_አረፉ

ከ20ዓመታት በላይ ጌታን ያገለገሉት ለሰው የማይቻል ለእግዚያብሄር ይቻላል የጸሎት እና የተዓምራት አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን አገልጋይ እና ባለ ራዕይ ነብይ ብረሃኑ ዳና ህይወታቸው እንዳለፈ ተሰምቷል።

በከንባታ እና ወላይታ ብሄረሰቦች መካከል በምትገኘው ሃዳሮ በምትባል ከተማ ተወልዶ ያደገው ነብይ ብረሃኑ ዳና ምንም የአካል ጉለት እና የጤንነት እክል ሳያግደው ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ወንጌልን በገጠር በከተማ ያገለገለ አገልጋይ ነው ።

ነብይ ብረሃኑ ዳና በወጣትነቱ ምንም እንኳን እግር ኳስ ተጫዋች የመሆን እቅድ ቢኖረውም በኋላ ላይ በአከባቢው በነበረው እንጨት እላዩ ላይ በመገልበጥ አደጋ ደርሶበታል።

ነብዩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለአገልግሎት ወደ ደቡብ አፍሪካ የተጓዘ ቢሆንም በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ በገጠመው የጤንነት ችግር ምክንያት በድንገተኛ ህይወቱ ልታልፍ ችላለች።

በመላው አለም የምትገኙ ውድ የክርስቲያን ዜና አድማጭ ተመላካቾቻችን የክርስቲያን ዜና ለመላው ቤተሰቦቹ እና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን እንመኛለን።
#ይቅርታ 🙏 #ሰሞኑን_በለቀኩት_የድመት_ቪዲዮ_ዙሪያ 🐈
👉 #ነብይ ሔኖክ ግርማ ይህን ብሏል...

ሰሞኑን በዩትዩብ ቻናላችን ስለተለቀቀው የድመትዋ ምስክርነት ጌታ የሰራው ድንቅ ስራ ቢሆንም የእህታችንም ደስታ ደስ ብሎን ደግሞም “ጻድቅ ሰው ለእንስሳቱ ይራራል፤ ክፉዎች ራሩ ቢባል እንኳ ዞሮ ዞሮ ሥራቸው ጭካኔ ነው።

"ምሳሌ 12 : 10 በሚለው የአምላካችን ቃል ክፋ ስላልሆን እንጂ ለጌታም ምንም ከመምጣቱ በፊት እድሜያችንን ለሰጠንለት ወንጌል ክብርና ፍቅር አጥተን አይደለም::

ቢሆንም በዚህ ምክንያት ያሳዘንነውን ሁሉ ይቅርታ እንጠይቃለን!
JPS TV WORLDWIDE

"እኔ ግን እጅግ በጣም የሚገርመኝ የመሪዎቹ ሳይሆን የምዕመናኑ ነው። አንዳንድ መሪዎች ጥፋታቸውን አምነው እንዲህ ይቅርታ ሲጠይቁ ምዕመናን ግን ዛሬም ባሉበት ናቸው። ይመቻቸው" (የግል ሃሳብ)
#እንኳን #አደረሳችሁ
#ውድ ቤተሰቦቻችን በአዲሱ አመት ተወዳጅ ፕሮግራሞች መካከል በBetachn ቤታችን Tv ተሰናድቶ በኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥኝ የተላለፈው የተወዳጁ #ነብይ አበበ ሃ/ማርያም እና ቤተሰቦቹ ይዘንላችሁ ቀርበናል ሀሳብ አስተያየታችሁን እንድታጋሩን ግብዣችን ነው።

በድጋሜ #መልካም አዲስ አመት ፕሮግራሞችን በሙሉ ለማግኘት ሊንኩን ይጠቀሙ

ክፍል 03 https://www.youtube.com/watch?v=XNtG-SFvD8Y
ክፍል 02 https://www.youtube.com/watch?v=lf2y9vTps-I
ክፍል 01 https://www.youtube.com/watch?v=Iz-3D7CkfK8
#መልካም #እለተ ሰንበት ይሁንልን 🙏🙏🙏

ቴክኒካሊ ብልጥ ሆነን የማናልፍበት ዘመን መጥቷል።

ዘመኑን ለማለፍ መንፈሳዊ መሆን የግድ ነዉ። እሱም ከኢየሱስ ጋር #ብቻ መሆን #ነዉ የሚያዋጣዉ።

በመፅሐፍ #ቅዱስ #ብዙ ታሪክ የሰሩ ሰዎችን ብንመለከት #እንኳን አለም እነሱን አይታ ተሸናፊዎችነዉ ያለቻቸዉ። ማንም አይፈልጋቸዉም ነበር።

በዘመናቸዉ #ሁሉ #ኢየሱስ ሲሉ ነበር ካለፉ በኋላ ግን ሁሉም ሰዉ ስለ ኢየሱስ ከ2ሺህ ዘመናት በላይ ይናገራል።

ኢየሱስ ካልክ የዚህ ድንቅ መፅሐፍ አካል ትሆናለህ። መፅሐፍ ቅዱስ የአንድ ታሪክ መፅሐፍ ነዉ። እነዚህ ሁሉ ሰዎች ስለ አንድ ታሪክ ሲናገሩ ነዉ የታሪክ አካል የሆኑት።

#ነብይ ጥሌ
#ኢየሱስ ላውድልህ ሃገሩን
#ዘማሪ ይድኔ

ኢየሱስ ላውድልህ ሃገሩን የዘማሪ ይድነቃቸው ተካ የዝማሬ ድግስ #ቅዳሜ መጋቢት 7 ከቀኑ 7 ሰዓት #ጀምሮ በሚሊኒየም #አዳራሽ ይካሄዳል።

ይሄንኑ ድግስ በተመለከተ ዘማሪው ከአጋር አካላት #ጋር ለሚዲያዎች #ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን ዘማሪ ይድነቃቸው ተካ፡ የሙዚቃ አቀናባሪ ዳዊት ለሚ፡ የድግሱ ብቸኛ አጋር ኤል ሃዳር ኢንጂነሪንግ፡ የጸጥታ አካል ዘጸዓት ሴኩሪቲ እና አስተባባሪዎች መግለጫውን በጋራ ሰጥተዋል።

በሮች ከ4 ሰዓት ጀምሮ ክፍት ይሆናሉ። የተባለ ሲሆን ዘማሪ ይድነቃቸው፡ ከኢየሱስ አልበም እና ቸኮለብኝ አልበኖች ዝማሬዎችን ያቀርባል።

#ነብይ ጥላሁን ጸጋዬ #በእግዚአብሔር ቃል የሚያገለግል ሲሆን ምንም አይነት የመግቢያ ክፍያ እንደሌለዉም ተጠቅሷል።

ከዳዊት ለሚ ባንድ ጋር ለ3 ወራት ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን የጠቀሰዉ ዘማሪ ይድኔ ድግሱ ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ከተሞችም ይካሄድ ተብሏል።

ኢየሱስ #2 አልበም ከ5 ወራት ፊት ነበር የተለቀቀው። ቸኮለብኝ #1 አልበም 2003 መለቀቁ ይታወሳል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በመግለጫዉ ላይ ተገኝተን ዝርዝሩን አሰናዳንላችሁ።

#ሙሉ ጋዜጣዊ መግለጫዉን ከደቂቃዎች በኋላ በቪዲዬ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።