Seid Social
9.14K subscribers
2.26K photos
332 videos
6 files
1.43K links
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል
Download Telegram
" ይህንን ብታደርጊ አንላቀቅም "
ይላል የዛሬው የቱርክ መግለጫ ።
ቱርክና እስራኤል በመካከላቸው ያለው ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እየተካረረ ይገኛል ። ሁለቱ ሀገራት እየተፏከሩ ነው ።
በተለይ ደግሞ ዛሬ እስራኤል በቱርክ ኳታርና ሊባኖስ የሚገኙ የሀማስ መሪዎችን እገድላለሁኝ ማለቷን ተከትሎ ቱርክ " አድርጊውና እንተያያለና " ስትል አስታውቃለች ።

የቱርክ የደህንነት መስሪያቤት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ይህንን ነገር እስራኤል ብትፈፅም የሚያስከፍላት ዋጋ እጅግ ከባድ ነው ብሏል ።
ቱርክ የሀማስ የፖለቲካ መሪዎች መኖሪያ ከሆኑ ሀገራት አንዷና ዋነኛዋ ነች ። ሀማስ በሀገር ደረጃ መንቀሳቀስ የሚችለው በኳታርና ቱርክ ሲሆን እነዚህ ሀገራት ለጋዛ የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ በመስጠትም ቀዳሚ ናቸው ። እናም የሀማስ መሪዎች በነዚህ ሀገራት እየተንቀሳቀሱ ትግላቸው ግብ የሚመታበትን ስትራቴጂ ይቀይሳሉ ።

በዚህ የቱርክና የኳታር ድርጊት የተበሳጨቺው እስራኤል የሀማስን አመራሮች ሀገራቱ ውስጥ እገድላለሁኝ ማለቷ በተለይ ከቱርክ በኩል " እንግዲያውስ ይለይልናል " የሚል ምላሽን አስከትሏል ።
ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ስለፍልስጤማዊያን ከኳታሩ አሚር ተሚም ጋር ለመነጋገር ዛሬ ኳታር ዶሀ የገባ ሲሆን በምእራባውያን የምትታገዘውን የእስራኤልን ጭፍጨፋ ለማስቆም ሙስሊሙ አለም በአንድነት እንሰለፍ ሲልም ጥሪ አቅርቧል !

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
ለመረጃ ያክል !
ኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘቧን ከዶላር አንፃር በእጥፍ ለማዳከም ወስናለች ። ይህንንም በቅርብ ጊዜ ይፋ ታደርጋለች ።
ያ ማለት የአንድ አሜሪካ ዶላር ዋጋው ከ 110 ብር በላይ ይሆናል ማለት ነው ።
ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ስላጋጠማትና ይህንንም ለማለፍ ከ IMF የግደታ ብድር ማግኘት አለባት ። ይህንን ብድር ካላገኘች ግን መንግስት እንጥፍጣፊ ዶላር አይቀረውም - ይሟጠጣል ። ብድሯን መክፈል ተስኗት አበዳሪዎችን እየተማፀነች ለምትገኘው ኢትዮጵያ አበዳሪዎቿ ተነጋግረው የሁለት ወራት እፎይታ የሰጧት ሲሆን ይህንን ብድር ለመክፈል ደግሞ የግደታ ከ IMF መበደር አለባት ። ተበድሮ ለአበዳሪ መመለስ !

IMF ለኢትዮጵያ የሁለት ቢሊዮን ዶላር ብድር ለማፅደቅ የተቃረበ ሲሆን ይህንን ብድር ለማግኘት ግን ኢትዮጵያ የብር አቅሟን በእጥፍ እንድታዳክም ቅድመ መስፈርት የጣለባት በመሆኑ ይህንን ለማድረግ ወስናለች ። በመሆኑም የብር የመግዛት አቅም ከሳምንታት በሗላ በግማሽ ይወርዳል ።
ሪፖርተር ይዞት በወጣው መረጃ መሰረት ብሔራዊ ባንክ የብርን ያግዛት አቅም ከብላክ ማርኬቱ ጋር እኩል ወይንም ተቀራራቢ ለማድረግ ወስኗል ።

ይህ የብር ማዳከም ህዝብን ማጣፊያ ያሳጣውን የኑሮ ውድነቱን በእጥፍ እንዳያጉነው ተሰግቷል ። በተለይም ደግሞ ለተቀጣሪውና ሰፊው ማህበረሰብ ጉዳቱ እጅግ የከፋ እንዳይሆን ያሰጋል !
እንኳን ዘንቦብሽ እንዲሉ የውጭ ምንዛሬዋን ጦርነት ሙጥጥ አድርጎ የበላባት የድሆቹ መኖሪያ ኢትዮጵያ አሁን መንግስት ብድር ለማግኘት ብለው የሚወስደው እርምጃ ህዝባችንን መቀመቅ የሚከት ነው ።

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
በአለም አቀፍ ህግ መሰረት የህዝብ እንደራሴዎች ወይንም ተወካዮች ፤ ድፕሎማቶችና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣናት ከመከሰስ ነፃ ናቸው they are immune from jurisdiction.

ህግም ሞራልም ምግባርም የማይገዛውና በብረት ብቻ የሚያስበው የብልፅግና መንግስት ግን በአለም አቀፍም ህግም ሆነ በኢትዮጵያ ህገመንግስት ያለመከሰስ ያለመያዝ መብት ያላቸውን የህዝብ ተወካዮች ካለምንም ክስ አፍኖ ወስዶ እንደዚህ ማዋረድ ማሰቃየቱ ሀገሪቱ ህግ በማያውቅ እብሪተኛ አገዛዝ ስር መሆኗን ማረጋገጫ ነው ።

አንድ የህዝብ ተወካይ ላለመታሰር የግደታ የገዥውን መንግስት አስተሳሰብ መቀበል የለበትም ። የህዝብ ተወካዮች ፊትለፊት ቀርበው መንግስትን ስለሞገቱ የሚታሰሩባት ኢትዮጵያ የዜጎቿ ሲኦል ሆና ቀጥላለች ።

ይሄ እንደ ሀገር ክሽፈት ብቻ ሳይሆን ህዝብ ህግ የሚባል ነገር እንደሌለ እንዲያስብ ሆን ተብሎ የሚደረግ ሀገርን ስርአት አልባ የማድረግ አደገኛ አካሔድ ነው !

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
" አሜሪካ እስራኤል እና ሳኡዲ አረቢያ ጥቃት ሊፈፅሙብን ይችላሉ ግና ለሁሉም ነገር ዝግጁ ነን " ይላል የዛሬው የየመን አንሷሩሏህ ሁቲዎች መግለጫ !

ሶስቱ ሀገራት በትብብር እየሰሩ ይገኛሉ በኛም ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ እናውቃለን የሚሉት የመኖቹ ግና ለሁሉም ዝንጁ መሆናቸውን ገልፀዋል ። የመኖች ወደ እስራኤል ያስወነጨፉት ሚሳኤል በአሜሪካና ሳኡዲ አረቢያ ተመቶ ቢወድቅም እነርሱ ግን ትግላቸውን አላቆሙም ። ከቀናት በፊትም የሁለቱን ሀገራት ፀረሚሳኤሎች ጥሰው የእስራኤሏን ኢላት ከተማን መምታት ችለዋል ።

" ስለፍልስጤማዊያን ወንድሞቻችን ከነዚህ ሀገራት ለሚመጣብን ጥቃት ሁሉ ሁሉንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ይህ ለእኛ ክብራችን ነው ስለወንድሞቻችን መሰዋታችን ልቅናችን ነው " በማለት እርግጡን ተናግረዋል - የመኖቹ !!!

ሳኡዲን በተመለከተ በሰጡት መግለጫቸው " ሳኡዲ ከአሜሪካና እስራኤል ጋር አብራ ሚሳኤሎቻችንን መትታ ጥላለች ከዚያ አልፎ የመንን እደበድባለሁ ብትል ግን የነዳጅ ማምረቻ ጣቢያዎቿን በሚሳኤሎቻችንና በድሮኖቻችን እናወድማቸዋለን " ብለዋል ።

የመኖች በእርግጠኝነት ያሰመሩበት ሌላኛው ነገር በቀይባህርና በኤደን ባህረ ሰላጤ የእስራኤል መርከቦች ዝር እንዲሉ አንፈቅድላቸውም ብለዋል ። እስካሁን ሶስት የእስራኤል መርከቦችን የተቆጣጠሩት የመናዊያኑ ከዚያ በተጨማሪ ሶስት የእስራኤል መርከቦች ላይ ጦር ከፍተው መርከቦቹን የአሜሪካ ጦር አድኗቸዋል ። ይህ የእስራኤልን የባህር ነፃነት በእጅጉ አደጋ ውስጥ የከተተ መሆኑ አሜሪካን አሳስቧታል ።

የየመኖቹን ጥቃት ለመከላከል አሜሪካ ከአጋሮቿ ጋር እየመከረች ሲሆን በየመን ሁቲዎች ላይ ጦርነት መክፈት ከኢራን ጋር የቀጥታ ጦርነት ያስገባል በሚል ስጋት አቅባ ይዛዋለች ። አሜሪካ ለሀማስ ጥንካሬም ፤ ለሂዝቡላህ ሀያልነትም ሆነ ለየመናዊያን ጠንካራ የጦር አደረጃጀት ተጠያቂዋ ኢራን ናት የምትል ሲሆን በዚህም ጦርነቱ እንዳይሰፋ በሚል ከሙሉ እርምጃዎች መታቀቧን ገልፃለች ።

የመኖችም የእስራኤል መርከቦችን ማሳደድ ቀጥለዋል !!!

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
ሌተናል ኮሎኔል ቶመር ግሪንበርግ የጎላን ብርጌድ 13ኛ ባታሊዮን ዋና አዛዥ ፤ ሌተናል ኮሎኔል ይሳቅ ቤን ባሺት የፋረን ብርጌድ ዋና አዛዥን ጨምሮ 13 የእስራኤል ጦር አመራሮችና ወታደሮች አዳራቸውን በሀ**ማ-*ስ ተገድለው አድረዋል ።

እስራኤል የሚደርስባት ወታደራዊ ኪሳራ ከ
እየጨመረ ሲሆን የምታደርገውም ግራ ገብቷታል ። አሜሪካ በበኩሏ እስራኤል ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እያሳደረችና ጫናዋን እያበረታች ትገኛለች ።
አሜሪካ ሁለት አቅጣጫዎችን በእስራኤል ላይ አስቀምጣለች ። አንደኛው ጦርነቱን በአስቸኳይ እንድታጠናቅቅ ሲሆን ሌላው ደግሞ የመንግስት ለውጥ እንድታደርግ ።
ባይደን ለኔታኒያሁ ደውሎ በአስቸኳይ የመንግሰት ለውጥ እንዲያደርግ ማዘዙም ሌላኛው አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኗል ።

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
እስራኤል የሀማስ ዋሻዎችን በውሀ መሙላት ይቻላታል ??

ጦርነቱ ባልጠበቀቺውና ባላሰበቺው መንገድ ሲሄድ ፤ ደካማ ሀማስን አልማ ክንደ ብርቱ ሙጃሂድ ሲገጥማት እስራኤል የምታደርገው ቢጠፋባት በርግጥ አይፈረድባትም ።
እስራኤል ጋዛ ስትገባ የሀማስን የመሬት ውስጥ መተላለፊያ ዋሻዎች በቀላሉ አፈራርሳ ሀማስን ከምድረገፅ አጥፍታ ሀሌሉያህ እያለች እየጨፈረች መመለስ ነበረ ሀሳቧ - ቅዤት ሆኖ ቀረባት እንጅ !!!
የሀማስ ዋሻዎችን መቅረብ የሞት ዋሻ ውስጥ መግባት ቢሆንባት ወታደሮቹ ዋሻዎቹን መግባት ቀርቶ መጠጋት ቢፈሩ እስራኤል አንድ ነገር አደርጋለሁ አለች - ዋሻዎቹን በሜድትራንያን ውሀ መሙላት ። የማይሳካ የቅዤት ህልም !

የሀማስ ዋሻዎች እጅግ የተራቀቁ ናቸው ። የትኛውም አለም ላይ የሀማስን ያክል እጅግ የተራቀቀ የምድር ውስጥ ዋሻ መገንባት የቻለ ሀይል የለም - የትኛውም አለም ላይ ! በምድር ላይ 360 ኪሎሜትር የሚረዝሙት ዋሻዎቹ መግቢያ መውጫቸውን ከሀማስ ውጭ የሚያውቅ ከቶ አንድ እንኳ የለም ። አንድ የእስራኤል ወታደር እንደምንም ብሎ ዋሻዎቹ ውስጥ ቢገባ መልሶ መውጣት አይችልም - ሀማስ እንዲወጣ ቢፈቅድለት እንኳ !! እናም ከገቡ አይወጡም ! ዋሻዎቹ ወደመሬት 30 ሜትር የሚጠልቁ መሆናቸው አሜሪካ ሰራሾቹ የእስራኤል ሚሳኤሎችም ሊያገኟቸው አልቻሉም ። እናም በውሀ ለምን አልሞክርም ነው የእስራኤል ቅዤት !

ግና ይህ የሚሆን አለመሆኑ ነው እውነታው ! ሀማስ እነዚህን ዋሻዎች በጋዛ መሬት ውስጥ እንዲገነባ ሀሳብ ያቀረቡትና ያረቀቁት ሁለት ሰዎች ነበሩ ። ሁለቱም በአሜሪካ የተቀነባበረ የአየር ጥቃት ተገድለዋል !
አንዴኛው የዚህ ሀሳብ አመንጪ የኢራኑ አብዮታዊ ቁድስ ጦር ዋና አዛዥ የነበረው ጄኔራል ቃሲም ሱለይማኒ ነበር ። ጄኔራል ቃሲም የሀማስ መሪዎችን ሰብስቦ የእስራኤልን የአየርና የሚሳኤል ጥቃት ለመመከት ከመሬት ውስጥ መተላለፊያ መገንባት እንዳለባቸው ነገራቸው ። ለዚያም ኢራን ድጋፏን እንደምታደርግ በመግለፅ የዋሻዎቹ ግንባታ ተጀመረ ። ፐርሺያዊያን የጦር ጠበብትነታቸው በርግጥ አያስገርምም ። ያኔ ከ 1,400 አመት በፊት ሰልማኑል ፋሪስ ለነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም የነገራቸውን የጦር ታክቲክ ከቶ ማን ይረሳል ። የሚገርመው ግን ያኔም ጦርነቱ የነበረው ከአይሁዳውያን ጋር ጭምርም የመሆኑ መገጣጠም ነበር !

ሁለተኛው የሀማስ ዋሻዎች ኢንጅነር አርቃቂ ደግሞ የሂዝቡሏሁ ወታደራዊ ጠበብት ኢንጅነር ኢማድ ሙግኒያህ ነው ! ኢንጅነሩ የሀማስ ዋሻዎች በምን መልኩ ቢሰሩ የወራሪዋን ጥቃቶች ይመክታሉ በሚል በሰራው እጅግ አስደናቂ ንድፍ መሰረት ሀማስ ዋሻዎቹን ገነባ ። ታዲያ ዋሻዎቹ ሲገነቡ ውሀ ቢለቀቅ ፤ ከፍተኛ ዝናብ ጥሎ ማእበል ቢመጣ ፤ ከላይ ሚሳኤል ቢዘንብባቸው ፤ የኬሚካል መሳሪያ ቢለቀቅ ፤ የጠላት ወታደሮች ወደ ዋሻዎቹ ቢገቡ ወዘተ የሚሉ እጅግ አንገብጋቢ ስጋቶችን ሁሉ ከግምት ውስጥ አስገብቶ የተሰሩ መሆናቸው እስራኤልን ምንም እንዳታደርግ እጇን ሽባ አድርጓታል ።

የእስራኤል ጦር ወደ ጋዛ ሲገባ ዋሻዎቹን የሚያፈራርሱ ኢንጅነሮችን ይዞ ነበር የገባው ። ኢንጅነሮቹ ግን እዚያ ሲደርሱ በእጅጉ ተደንቀው ፈዘዋል ። የኢንጅነሮቹ ዋና ሀላፊ ለአሜሪካ ሚዲያዎች በሰጠው መግለጫ " እኛ ተራ ዋሻዎች እንደሆኑ አስበን ነበር የገባነው ግና ያየነውን ነገር ማመን አልቻልንም እንደዚህ የተራቀቀ ግንባታ አይተን አናውቅም ይህንን የሰሩት ኢንጅነሮች እጅግ ድንቅ ናቸው " በማለት ነው አግራሞቱን የገለፀው ።

እናም የእስራኤል ውሀ እለቃለሁ ማስፈራሪያ ከማስፈራሪያነት አይዘልም !!!!

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
አንድ ምስጢር ልንገራችሁ !!
ፍልስጤማዊያን አረቦች አይደሉም !

ፍልስጤማዊያን አረቦች አይደሉም ። ይልቁንስ ከነአናውያን ነበሩ ። ከነአኖች ደግሞ " ማርና ወተት የሚፈስበት " የሚባለውን ግዛት ያስተዳደሩ የመሩ እጅግ በርካታ ስልጣኔዎችን የገነቡ የመካከለኛው ምስራቅ ቀደምት ነባር ህዝቦች ነበሩ ።

ከነአናውያን ታላቋን ቅዱሷን የአለም ስልጣኔና ሀይማኖቶች ሁሉ አስኳል ከተማ የሆነቺውን ኢየሩሳሌምን የመሰረቱ ህዝቦች ናቸው ። ዛሬ አይሁዶችም ክርስታያኖችም ሙስሊሞችም ቅዱሷ ከተማችን የሚሏት ኢየሩሳሌም ወይንም ቁድስ የተመሰረተቺው በሶስቱም ሀይማኖት ተከታዮች ሳይሆን የራሳቸውን ባህላዊ አምልኮ በሚያመልኩት በከነአናዊያን ወይንም ለፍልስጤማውያን ነው ። ፍልስጤሞች የከነአኖች አንድ አካል የነበሩ ህዝቦች ሲሆኑ ከፍልስጤሞች ሌላ ሰባት የከነአን ህዝቦችም ነበሩ ።

እስራኤላውያን በንጉሳቸው ጆሹዋ ወይን ዮሸእ ቢን ኑን እየተመሩ ፍልስጤማዊያንን እስኪያሸንፉ ድረስ ኢየሩሳሌም የፍልስጤማውያን ነበረች ። የዚያ ጦርነት ጊዜ ግን እስራኤላውያን በጆሹዋ እየተመሩ በጎሊያድ የሚመራውን የፍልስጤም ጦር ገጥመው አሸነፉና ኢየሩሳሌምን ተቆጣጠሩ ።

ጎሊያድን ወይንም በኢስላማዊ አጠራር ጃሉት በዚያ ጦርነት የጆሹዋ ወታደር በነበረው በዳዊት ወይንም በዳውድ ሲገደል የመካከለኛው ምስራቅ ታሪክ ሙሉ ለሙሉ ተቀየረ ። አምላክ ያዳላላቸውና አሸናፊ እንዲሆኑ ያደረጋቸው እስራኤላውያን የከነአን ህዝቦችን ብዙዎችን አጥፍተው ኢየሩሳሌምን ለበርካታ መቶ አመታት ካስተዳደሯት በሗላ እነርሱም ሌላ ወራሪ መጥቶባቸው ስደት እጣፈንታቸው ሆኗል ።

የከነአን ህዝቦች ሲጠፉ የተረፉት ፍልስጤማዊያን እና ሊባኖሳዊያን ብቻ ሆነው ቀሩ ። እነርሱም ኢስላም በነብዩ ሙሀመድ ሶ.ዐ.ወ መልእክተኛነት አካባቢውን ሲያዳርስ እስልምናን ተቀብለው ባህላቸውንና የአኗኗር ዘይቤያቸውንም ወደ አረባዊነት በመቀየር አረቦችን መስለው እስካሁን እየኖሩ ይገኛሉ ።

ፍልስጤሞችና እስራኤሎች ጦርነታቸው ገና ከዛሬ 2,500 አመት ገደማ በፊት ጀምሮ ሲሆን እስካሁን እየተገዳደሉ አሉ ። እናም አሁን ፍልስጤሞች ከአረቦች ጋር ቢመሳሰሉም ቋንቋና ባህላቸውም በአረቦች ቢዋጥም ኢስላም ከሌላው ህዝብ ጋር ቢያዋህዳቸውም መነሻቸው ግን ከነአናዊየነት ነበር ።
ከአመት በፊት የፍልስጤም ፕሬዚዳንት ማህሙድ አባስ " እኛ የከነአን ልጆች ነን" ማለቱ ይታወሳል ።

ምናልባትም አረቦች አሁን ፍልስጤማዊያንን እርግፍ አድርገው የተዋቸው አረቦች ስላልሆኑም ጭምር ነው ። በዝምድናና በዘር ለአረቦች ከፍልስጤማውያን ይልቅ እስራኤሎች ይቀርቧቸዋል ።
በአሁን ጊዜ በዝምድና ለፍልስጤሞች የሚቀርቡት ህዝቦች ሊባኖሳዊያን ብቻ ናቸው ።

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
ዛሬ አሜሪካ ከየመን ጋር ስትዋጋ ነው የዋለቺው !
በዚህ ዛሬ አሜሪካ በአየር ሀይሏ ከየመን ባህር ሀይል ጋር ባደረገቺው ፍልሚያም 10 የመናዊያን መስዋዕት ሆነዋል ።

የየመን ሁቲዎች ለጋዛ ፍልስጤማዊያን ወንድሞቻቼው አጋርነት ባወጁት ትግል ወደ እስራኤል የሚሄዱ መርከቦች ላይ ከፍተኛ ጥቃት በመሰንዘር እስራኤልን እና ግብፅን ከፍተኛ ጭንቅ መክተታቸው ይታወቃል ። እናም አሜሪካ ሁለቱን ወዳጅ ሀገሮቿን ለመርዳት 10 አባል ሀገራት ያሉት የጦር ግንባር መስርታ ከየመን ሁቲዎች ጋር ስትዋጋ መሰንበቷ ይታወሳል ። ዛሬ የየመን ተዋጊ ጀልባዎች ላይ በፈፀመቺው የአየር ጥቃት ነው አሜሪካ 10 የመናዊያን ወታደሮችን መግደል የቻለቺው ።

የሁሲ ቃል አቀባይ ማምሻውን በሰጠው መግለጫም መላው የመናዊያን ለአሜሪካ ጦር እንዲዘጋጁ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን መላው ነፃው አለምም እንዲቀላቀላቸው ጥሪውን አስተላልፏል። አሜሪካ የመን ጋር ጦርነት ከገጠመች አፍጋኒስታን እና ቬትናም ላይ ከደረሰባትም የከበደ ኪሳራና ሽንፈት እንደሚጠብቃት ሁቲዎች መዛታቸው አይዘነጋም ።
እንደ የመን ሁሲ መግለጫ ለፍልስጤማውያን ወንድሞቻቼው ሲሉ የሚከፍሉት መስዋዕትነት ለነርሱ ልቅና መሆኑን አስምረውበታል ።

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
ሳኡዲ አረቢያ የየመን ሚሳኤሎች እስራኤልን እንዳይመቱ ላደረገቺው አስተዋፅኦ ጀርመን የዩሮፋይተር የጦር ጄት እንዲሸጥላት ፈቀደች ።

የጀርመኗ ውጭጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ቤርቦክ ዛሬ እስራኤል ትገኛለች ። ሚኒስትሯ አቀባበል የተደረገላትም በወረራ በተያዘቺው ኢየሩሳሌም ሲሆን እዚያም ለእስራኤል ከፍተኛ አጋር ለሆነቺው ሳኡዲ አረቢያ ከፍ ያለ ምስጋናዋን አቅርባለች ።

ኢየሩሳሌም ከእስራኤል ፕሬዚዳንት እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ሆና የጀርመኗ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቤርቦክ እንድህ የሚል መግለጫዋን ለአለም አስተላለፈች
" ከ October 7 ( ሀማስ እስራኤል ላይ ጥቃት ከፈፀመ) በሗላ የመካከለኛው ምስራ ሀገራት አሰላለፍ በአስደናቂ ሁኔታ ተለውጧል ። መካከለኛው ምስራቅ ሌላ አለም ሆኗል ። ሳኡዲ አረቢያ የየመን ሁቲዎች በእስራኤል ላይ ሊያደርሱ የነበረውን የሚሳኤል ጥቃት መከላከልና መመከት ችላለች ይሄ ትልቅ ለውጥ ነው ።
ለዚህ የሳኡዲ አረቢያ በጎ ሚናም ጀርመን የዩሮፋይተር የጦር ጄት እንዲሸጥላት ትፈቅዳለች " በማለት ሳኡዲ አረቢያና እስራኤልን ያስደሰተ መግለጫ ሰጥታለች ።

አሁን ጦርነቱ ግልፅ ነው ። ጦርነቱ እስራኤል ወዳጆቿ የአረብ ሀገራት እና ምእራባውያን በአንድ ግንባር ተሰልፈው በተቃራኒው ደግሞ ሀማስ ፣ ሂዝቡሏህ ፣ የየመን ሁቲዎች እኛ ኢራን በሌላ ጎን ተሰልፈው የሚዋጉበት ጦርነት ሆኗል ።

ልክ እንደ እስራኤል ሁሉ የምእራባውያን በተለይም የእንግሊዝ ስሪት የሆኑት ሳኡዲ አረቢያን የመሳሰሉ የአረብ ሀገራት ከእስራኤል ጎን ሆነው ይፋለማሉ ብሎ በርግጥስ ማን የጠበቀ ነበር ??!!!
ለዚያ ነው የጀርመኗ ሴት አረቡ አለምን " ፍፁም ያልተጠበቀ ሌላ አለም " በማለት ያሞካሸቺው ።


#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
የፍርድ ክርክሩ ሊጀመር ዝግጅቱ ተጠናቋል !

ከተለያዩ ሀገራት የተውጣጡት የአለም አቀፉ የፍትህ ፍርድቤት 15 ዳኞች ተሰይመዋል ። ከነርሱ በተጨማሪ አንድ ዳኛ ከደቡብ አፍሪካ አንድ ዳኛ ደግሞ ከእስራኤል ተመድበዋል ምክንያቱም ከሳሽና ተከሳሽ ናቸውና !!!

የጥቁር ህዝቦች ብቻ ሳይሆን የነፃነት ወዳዶች ሁሉ ኩራት የሆነቺው ደቡብ አፍሪካ እስራኤል ስለ ፍልስጤማዊያን ሆና ልትሞግት ኔዘርላንድ ሄግ ተሰይማለች ። ደቡብ አፍሪካ እንደ ሌሎቹ የአለም ሀገራት የእስራኤልን የዘር ማጥፋት ወንጀል በዝምታ ማለፍ ባለመቻሏ ይሄው እስራኤልን በዘርማጥፋት ወንጀል ከሳ ልትሟገት ወገቡን ጠበቅ አድርጋ ቀርባለች ። ፍልስጤም የአረቡ አለም በአጠቃላይ የሙስሊሙ አለም ቢጥላት ደቡብ አፍሪካ ግን ያን ማድረግ አልቻለችም - በአፓርታይዳዊ ስርአት መገዛት ምን አይነት ህመም እንደሆነ ታውቃለችና !!!

ደቡብ አፍሪካ ይህንን ውሳኔ ወስና የፍልስጤም ወኪል ሆና የጋዛዎች ጠበቃ ሆና በአለምአቀፋዊው ፍርድቤት ስትሟገት የሚደርስባትን ፈተና ወይንም የምትከፍለውም ዋጋ ጠንቅቃ ታውቀዋለች ግና ይህ ለደቡብ አፍሪካ ለፍትህ ከመቆም በላይ አይደለምና እስከመጨረሻው ልትሟገት ይሄው ነገ ቀጠሮው ነው ።

እስራኤል ከደቡብ አፍሪካ ክስ አልሸሽም ብላለች ። ይልቁንስ " ተሟግቼ ንፅህናየን አረጋግጣለሁ የተከሰስኩበት ወንጄል እጅግ ከባድ ነው ስለሆነም ወንጄለኛ እንዳልሆንኩ በፍርድ ቤቱ ቀርቤ እሟገታለሁ እንጅ አላፈገፍግም " ብላለች ። ለዚህ የሀገሪቱን ቁንጮ ዳኞች አዘጋጅታለች ። ከዚያ በተጨማሪም ከህሎከስት ( የናዚ ጭፍጨፋ ) የተረፉ እስራኤላውያንን ይሟገቱላት ዘንዳ ወደ ሄግ ልካለች ።

አለም የፍርደገምድሎችና የሀያላኖች ብቻ በሆነችበት ተጨባጭ በፍርድ ቤት ክርክር የተበዳይ በደል አይወጣ ይሆናል ። ግና ለታሪክ ፍርድ ፤ ለአለምም ተእይንት ፤ ለእውነትም ግብአት ይሆን ዘንዳ ደቡብ አፍሪካ የሰራቺው ስራ የፈፀመቺው ገድል ሁሌም በታሪክ መዝገብ ላይ ስለ ፍትህ ውግንናዋ እንድትወሳ የሚያደርግ ነው ።

ያኔ ሶሀቦች ተሰደው ያስጠጋቻቼው ኢትዮጵያ እና መሪዋ ሁሌም እንደሚወደሱት ሁሉ ደቡብ አፍሪካም ሁሌም የሚያስወድሳትን ድርጊት ፈፅማለች ።

አንድ ቀንኮ ፍልስጤማዊያን ነፃ ይወጣሉ ! ያሸንፋሉ ! ሙስሊሙም አለም ከተኛበት ይነሳል !
ያኔ ደቡብ አፍሪካ ምን ተብላ ውለታዋ እንደሚወሳ አስቡት !!!

ፍልስጤሞች ጠበቃ ባጡ ሰአት ጠበቃ የሆነቻቼው ደቡብ አፍሪካ በልቤ ትልቅ ቦታ አላት !!!

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
ዛሬ ተአምር ነው የተሰራው !
እንደዚህ አይነት የፍርድ ውሎ በታሪክ ተሰምቶም ታይቶም አይታወቅም !
ደቡብ አፍሪካ የፍርድ ሂደቱን ይመሩላት ዘንዳ አዲላ ሀሰንን እና ቴምቤካ ንጉካይቶቢን ከፊት ሰይማለች ።

ደቡብ አፍሪካ ለ 3 ሰአት የዘለቀ ክሷን 15 የአለም ዳኞች በተሰየሙበት አሰማች ። ከውጭ ለፍልስጤማውያን መብትና ክብር የተሰለፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ኔዘርላንዳዊያን የፍርድቤቱን ዙሪያ ሞልተው ድምፃቸውን እያሰሙ ነው ። ኩነቱ ሁሉ ልብን ሰቅዞ የሚይዝ ነበር ።

የተባበሩት መንግስታትና የአለም አቀፍ ታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር አላና ኦማሌይ የፍርድ ሂደቱን " ከዚህ በፊት ያልታየ ታሪካዊ " ያሟካሹታል ።

ደቡብ አፍሪካ እጅግ የተራቀቀ ሰነድን መረጃን የህግ ትርጓሜዎችን ታሪኮችን ያጣቀሰ ክሷን ስታሰማ የታሪክ ተመራማሪዎች የህግ ጠበብቶች ፈዝዘው አሰየተመለከቱ ነበር ። ሶስት ሰአት የፈጀው የክስ ንባብ ሶስት ደቂቃ የቆየ ሳይመስል ነበር የተጠናቀቀው ። እስራኤል ተሸማቀቀች አፈረች ። የሰየመቻቼው ዳኞች የሚያወሩበት ምላስ ተጎላደፈባቸው ! ያሰቡት ሁሉም ተነነባቸው !!!

ደቡብ አፍሪካ ምን አይነት ሀገር ነች !!! ምን አይነት መባረክ ነው !!

ፍርዱ እየተካሔደ እዚህ ደቡብ አፍሪካ መሪ ክቡር ሲሪል ራማፎዛ ለአለም መልእክታቸውን እያስተላለፉ ነበር ። " ሀገሬ በፍልስጥኤማውያን ላይ የሚደረገውን ዘር ማጥፋትና ጭፍጨፋ እስከ መጨረሻው ትታገላለች " አሉ ጥቁሩ አልማዝ !! ክቡር የክቡር ልጅ !

" እስራኤል በየሳምንቱ ከ 6,000 በላይ ቦንቦችን በጋዛ ላይ ታርከፈክፋለች ! በዚህ የቦንብ ናዳ የሚተርፍ አንድ እንኳ የለም ! የተወለዱ ህፃናት ሳይቀር የሚሳኤል ሰለባ ሆነዋል ! ጋዛን ተመድ ራሱ " የህፃናት መቃብር " ሲል ገልጿታል ። የተከበረው ፍርድቤት ሆይ ሴቶችን ተኩሶ መግደል ፤ ህፃናትን አናጣጥሮ መግደል ፤ ንፁሀን ወንዶችን መጨፍጨፍ ፤ ምንም አይነት ሰብአዊ እርዳታ እንዳይገባ ዘግቶ መክበብ እነዚህ ሁሉ በፍልስጥኤማውያን ላይ በእስራኤል የሚፈፀም የዘር ማጥፋት ነው!
የተከበረው ፍርድ ቤት ክብሯን ዳኞች የእስራኤል ባለስልጣናት በይፋ የጋዛን ህዝብ እንደሚያጠፉ ሲዝቱ አይታችሗል ! ይህንን የባለስልጣናቱን የዘር ማጥፋት ዛቻም ወታደሮቹ በተግባር ሲፈፅሙትም አይታችሗል ...." እያለ የደቡብ አፍሪካ ክስ ህግና ታሪክን እያጣቀሰ ይቀጥላል ።

ደቡብ አፍሪካ በዘር ለማይዛመዷት ፣ በቀለምም ለማይገናኟት ፣ በሀይማኖትም ለማይመሳሰሏት ፣ በመልክአምድርም ለማይቀራረቧት ፤ ምንም አይነት የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ ትርፍ ለማታገኝባቸው ለነዚያ ምስኪን የነፃነት ታጋይ ፍልስጤማዊያን እንደዚህ ክንዷን ገትራ ስትሟገት ስትፋለጥና ከምእራባውያን ጋር ስትጋፈጥ ሳይ በጣም በጣም ገርሞ ገርሞ እንደገና ይገርመኛል !

አለም በአስመሳዮችና ጨቋኞች በተሞላችበት ደቡብ አፍሪካ ግን ብቻዋን የምታበራ የነፃነት ቀንድል ሆና እንደቀጠለች አለች !

ምን ማለት እችላለሁ አላህ ልቅናና ሀያልነትን ያጎናፅፋት እንጅ !
መሪዎቿንም ሂዳያውን ወፍቆ በጀነቱ ያቀማጥላቸው እንጅ !!

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
አሜሪካና እንግሊዝ የመንን ሲደበድቡ አድረዋል !

በባህሬን ካናዳና ኔዘርላንድ ተባባሪነት በሳኡዲ አረቢያ የአየር ክልል ፈቃጅነት በተፈፀመውና በአይነቱ ከፍተኛ በተባለው የአየር ጥቃት አሜሪካና አጋሯ እንግሊዝ የየመን ዋና ከተማ ሰነአን ከጦር ጄቶቻቼውና ከጦር መሬከቦቻቼው በሚወነጨፉ ሚሳኤሎች ሲደብድቧት አምሽተዋል ።

አስፈሪው ጦርነት እየመጣ ይመስላል። ቀጠናው ወደለየለት ትርምስ እንዳይገባ አስፈርቷል ። የየመን ሁቲዎች ላይንበረከኩ ብቻ ሳይሆን በፅናት የበቀል ጦርነታቸውን አፋፍመው ሊቀጥሉ ምለው ተገዝተዋል ። ሁቲዎች ባወጡት መግለጫ አሜሪካና እንግሊዝን ብቻ ሳይሆ አጋሮቻቼውን እነ ሳኡዲ አረቢያና ባህሬይንን እንደሚበቀሉ አስታውቀዋል ። ወደ እስራኤል የሚጓዙ መርከቦችንም አንዱንም እንደማያሳልፉ እንደዚያው !!

የየመንን የጦር ማከማቻና ማስወንጨፊያዎችን ማውደምን ኢላማ ባደረገው በዚህ የእንግሊዝ እና የአሜሪካ የጦር ዘመቻ ብዙዎችን ያስደነገጠ ሳይሆን የአሜሪካ ኮንግረስ አባላትም " እንደት እኛ ሳንጠየቅ ባይደን ይህን ለማድረግ ደፈረ " በማለት እያወገዙት ነው ።

የሆነው ሆኖ አሜሪካና ኢራን ጦርነት ለመግጠም አንድ እርምጃ ብቻ ይቀራቸዋል ።
በዚህ ውጥንቅጡ በወጣ ቀጠና ጦርነቱ ከተስፋፋ ሀገራችንን ጨምሮ በርካታ የቀጠናው ሀገራት በሰላምና ኢኮኖሚ ቀውስ ይመታሉ ።

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
የእስራኤልን የስለላ መስሪያቤት ኢላማ ያደረገው የኢራን የሚሳኤል ጥቃት !

በዛሬው እለት ኢራን በፈፀመቺው የሚሳኤል ድብደባ በኢርቢል የሞሳድን ዋና መስሪያ ቤት አውድማለች ። 11 ሚሳኤሎችን በተኮሰችበት በዚህ ልዩ የኢራን ወታደራዊ ተልእኮ የስለላ ተቋሙን ማውደምና እስራኤልን መበቀልን ኢላማ ያደረገ ነበር ።

ጦሯን " የኢስላም አብዮታዊ ዘብ " በማለት የምትጠራው ኢራን በፈፀመቺው የባላስቲክ ሚሳኤል ጥቃት ኢራቅና ሶሪያ በፍንዳታ ሲናጡ ውለዋል ። ሚሳኤሉም በአሜሪካ የጦር ሰፈር አቅራቢያ በሚገኙ የሞሳድ ማሰልጠኛና እዝ መስጫ ማእከል ላይ አርፎ በዚያ ያሉ በርካታ ሰዎችን ገድሏል ። ከዚህም ውስጥ ኩርዳዊው ቢሊየነር ፓሽራው ዲዛየና ቤተሰቦቹ ተገድለዋል ።

ኢራን የሚሳኤል ጥቃቱን የፈፀመቺው በሰሜናዊ ኢራቅ የኩርድ ራስገዝ አስተዳደር ላይ ሲሆን የኩርዱ ፕሬዚዳንት መስሩር ባርዛኒ ጥቃቱን " በኩርድ ህዝብ ላይ የተፈፀመ ጥቃት " በማለት ኢራንን አውግዘዋል ።
ኢራቅ አምባሳደሯን ከኢራን የጠራች ሲሆን አሜሪካና እንግሊዝ ደግሞ " የኢራቅን ሉአላዊነት የጣሰ ግድየለሽ ጥቃት " በማለት ኢራንን አውግዘዋል ።

በቱርክና ኢራን በሽብርተኝነት የተፈረጁትና ከሁለቱም ሀገራት ጋር የሚዋጉት የኩርድ ታጣቂዎች ከአሜሪካና እስራኤል ጋር ጠንካራ ወዳጅነት አላቸው ። እናም እስራኤል ኢራንን ለመሰለልና በኢራን ላይ ወታደራዊ ጥቃት የሚፈፀምበትን ሁኔታ ለማመቻቼት የኩርድ ታጣቂዎችንና የኩርድ ግዛትን ትጠቀማለች ። አሜሪካም ለኩርድ ታጣቂዎች ከፍተኛ የመሳሪያ እና የፋይናንስ ድጋፍ የምታደርግ ሲሆን ይህ ድርጊቷ ከቱርክ ጋር ጥርስ እንዳናከሳት ቀጥሏል ።

ኢራን ዛሬ የሚሳኤል ጥቃት የፈፀመቺው በኢርቢል ብቻ አይደለም ። በሶሪያ በሚገኙ የአይኤስ አይኤስ ኢላማዎችም ላይ ከፍተኛ የሚሳኤል ጥቃት ፈፅማለች ። ኢራን ይህንን ያደረገቺው ከሳምን በፊት አኤይስ በደቡባዊ ኢራን የሟቹን ጄኔራል ቃሲም ሱለይማኒን ሙት ለማሰብ በተሰባሰቡ ኢራናዊያን ላይ በፈፀመው የፈንጅ ጥቃት ከ 110 በላይ ኢራናዊያን መገደላቸውን ተከትሎ ለዚያ በቀል ነው ።

የኢራን ኢስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ከጥቃቱ በሗላ በሰጠው መግለጫ " ኢራንን አጥቅቶ በየትኛውም አለም ያለ ሀይል ከቅጣታችን እንደማያመልጥ ለህህዝባችን እናረጋግጣለን " ብሏል ።

ዘገባውን ከአልጀዚራ ፣ ቴህራን ታይምስና ሲኤንኤን አጠናቀርኩላችሁ ።

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
ኢራንና እስራኤል በሰው ሀገር ሜዳ ደግሞም በእጅ አዙር እየተፋለሙ አቅምም እየተለካኩ ነው ።

ኢራን በሶሪያ ወታደራዊ ይዞታ አላት በሽር አልአሳድ ደግሞ የኢራን አጋር ነው ። እስራኤል በኢራቋ ኩርድ የስለላና ወታደራዊ ማእከላት አሏት ። የኩርድ ነፃ አውጭ ተዋጊዎች አጋሯ ናቸው ። ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ኤርዶጋን በነገር በወጋው ቁጥር ዘሎ " የኩርዶች ጠላት " ካላለው ስድቡን የመለሰ አይመስለውም ።

ለነገሩ የኢራቁም ሆነ የሶሪያ ኩርድ ግዛቶች የምእራባውያን የጦር ሰፈሮች የስለላ ተቋማት መነሀሪያ ናቸው ። PKK , YPJ እና PYDን የመሳሰሉ የኩርድ ነፃ አውጭ ታጋዮች የአሜሪካና የእስራኤል አጋር ወዳጅ የቀጠናው ተልእኮ ፈፃሚዎች ናቸው ። አላማቸውም አንድት ውህድ የኩርድ ሀገርን መመስረት ነው ።
ኩርድ በአራት ሀገራት ማለትም በቱርክ ፣ በኢራቅ ፣ በሶሪያ እና ኢራን ተበትነው የሚኖሩ በአንድ ወቅት የአለም ሀያል የነበረው የአዩቢድ ስርወመንግስት ባለቤትና የሰልሀዲን አልአዩቢ ውልዶች የነበሩ ህዝቦች ናቸው - የዛሬን አያድርገውና !

ወደ አጀንዳው ስመለስ እስራኤል ኢራንን በቀጥታ መምታት የሚያመጣባትን መዘዝ ስለምታውቅ ኢራንን ለመጉዳት ስትፈልግ ጥቃት የምትሰነዝረው በሶሪያ በሚገኙ ወታደራዊ ይዞታዎቿ ላይ ነው ። ከዚያ አለፍ ሲልም የበሽር አልአሳድ አገዛዝን ኢላማዎች በአየር በመደብደብ ኢራን ላይ ምላሱን እያወጣች ትጉነትላታለች ። አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ነገው ነገሩ !

ኢራንም እንደዚያው ናት ! እስራኤልን በቀጥታ መግጠምም ሆነ በቀጥታ ጥቃት መሰንዘር አትፈልግም ። የምትከፍለውን መራር ዋጋ ታውቀዋለችና ። እስራኤል ብትለቃት አሜሪካ አትለቃትምና ! እናም ኢራን እስራኤልን ማጥቃት ስትፈልግ እስራኤል በሌላ ሀገራት ላይ ያሏትን ኢላማዎች ነው የምትመታው ልክ ትላንት እንዳደረገቺው ።

ከዚያ በተጨማሪ ግን ኢራን ክንደ ፈርጣማ ታጣቂ ቡድኖችን በመመስረትና በማገዝ እስራኤልን ትመታለች ። ከነዚህ ውስጥ ዋነኞቹ የሊባኖሱ ሂዝቡሏህና የየመኑ ሁቲ ናቸው ። እናም ኢራን በነዚህ ቡድኖች አማካኝነት እስራኤልን ብቻ ሳይሆን ምእራባውያንን ጭምር ትፋለማለች ። ኢራን ሂዝቡሏህ የሚባል ሌላ ታጣቂ ሀይልም ኢራቅ ውስጥ አላት ። ይህ ሀይል ነው በአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ላይ የድሮንና የሮኬት ጥቃት የሚፈፅመው ።

ሰሞኑን ኢራን የፈፀመቻቼው ከፍተኛ የሚሳኤል ጥቃቶች አላማቸው እነዚህን አካባቢዎች መምታት ብቻ አይደለም ። ይልቁንስ እስራኤል በኢራን የሚሳኤል ጥቃት ክልል ውስጥ መሆኗንም ለማሳየት ጭምር እንጅ ! የኢራን ሚሳኤሎች ልክ እንደምእራባዊያኑ ሁሉ አላማቸውን ሳይስቱ መምታት እንደሚችሉ ማሳየት ጭምር እንጅ!

ኢራን የሀማስ ዋነኛ ወታደራዊ ደጋፊ ናት ። ሀማስ በእስራኤል ላይ የሚያሳየው የወታደራዊና የመሳሪያ አቅም ዋነኛ ምንጭ ኢራን ናት ። በዚህ ሀማስም ኢራንም ደስተኛ ናቸው ። በዚያ ላይ የጋራ ጠላት አላቸውና እስራኤል ታስተሳስራቸዋለች ።

በዚያም ተባለ በዚህ ኢራንና እስራኤል በእጅ አዙር መፋተግ መፋለም ከያዙ ዋል አደር ብለዋል ። ለመሆኑ ይህ ፍልሚያቸው ወደ ቀጥታ ጦርነት ይወስዳቸው ይሆን ወይንስ እንደ አሜሪካና ሶቭየት ህብረት ተፈራርተው ይቀሩ ይሆን ?
ጊዜ የሚነግረን ይሆናል !

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
ፓኪስታን ኢራንን በሚሳኤል ስትደበደብ ዋለች !

የሁለቱ ሀገራት ግዴለሽ ጦርነት የት ያደርሳቸው ይሆን ?

ከትላንት በስቲያ ኢራን ፓኪስታንን በሚሳኤል ከደበደበች በሗላ ዛሬ ፓኪስታን በአፀፋው በድሮንና በሚሳኤል በተቀናጄ ተኩስ የኢራን ግዛቶችን ስታደባይ ውላለች ። ሁለቱም ሀገራት ስለ ጥቃታቸው ኢላማ ሲናገሩ " አሽባሪ ድርጅቶችን ለመምታት ብለው " ይገልፃሉ ።

ኢራንና ፓኪስታን እርስበርሳቸው የሚደባደቡባቸው አሸባሪ የሚሏቸው ድርጅቶች ደግሞ የባሎችስታን ነፃ አውጭ ቡድኖችን ነው ። ባሎችስታን ልክ እንደ ኩርዶች አይነት ህዝቦች ሲሆኑ በፓኪስታን አፍጋኒስታንና ኢራን ተበትነው የሚገኙ ሶስቱንም ሀገራት የሚያጎራብቱ ህዝቦች ናቸው ።

ኢራን ጦርነት የምትከፍተው ፓኪስታን ውስጥ በሚገኘው የባሎችስታን ነፃ አውጪ ተዋጊ በሆነው ጀይሽ አልአድል ላይ ሲሆን ፓኪስታን ደግሞ ሚሳኤሏን ያስወነጨፈቺው በኢራን በሚገኘው የባሎችስታን ነፃ አውጭ ማርግ ባር ሳርማቻር ላይ ነው ። ሁለቱም ሀገራት በባሎችስታን ተዋጊዎች ላይ ይተኳኮሳሉ ። ይህ ለባሎች ህዝቦች አሳዛኝ ክስተት ነው ።

ኢራን የፓኪስታንን ድርጊት ያወገዘች ሲሆን ከፍተኛ የፓኪስታን ድፕሎማትንም ጠርታ አነጋግራለች ።

ፓኪስታን በበኩሏ በሰጠቺው መግለጫ ውጥረቱ እንዲፋፋም እንደማትፈልግ ገልፃ አላማዋ የሽብር ቡድኖች ብቻ መሆኑን አስታውቃለች ።
የሚያሳዝነው ሀቅ ቢኖር በሁለቱ ሀገራት የእርስበርስ ሚሳኤል መጠቃቃት በርካታ ንፁሀን መሞታቸው ነው ። ሚሳኤልን ያክል ከባድ ነገር እንድህ በቀላሉ መወናጨፍም የሚያስደንቅ ነገር ነው ።

ቻይና ሁለቱን ሀገራት አነጋግራ እንደምታስታርቃቸው ዛሬ አስታውቃለች ።

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
መረን የለቀቀው የጎዳና ላይ ስብከት ሊቆም ይገባል !

መቼስ ይህቺ ሀገር ሁሉ ነገር መረን የለቀቀባት ሆናለች ። የሀይማኖት ሰባኪያን ገሪ አጥተው በመነገድም በአደባባይም በስራ ቦታም አላስቀምጥ አላላውስ ካሉ አስርት አመታት ተቆጠሩ ። ከጩኸት ውጭ ጠብ የሚል ልብን የሚያረጥብ ነገር ለማውጣት አንደበታቼው ያልታደለው ጯሂዎች ህዝባችንን አስመርረውታል ። በጪከትና እርበሻ የድምፅ ብክለት እንጅ የነፍስ ቀለብ አይገኝምና እነዚህ ጯሂዎች በቃችሁ ሊባሉ ይገባል ።

እንደ ሰውኮ ነፃነቱን ተገፈፈ ። መኪና እንኳ በሰላም መሰለፍ ተቸገረ ። አሁንማ በመኪና ስፒከር ላይ ደቅነው ከተማውን ሁሉ በሚያናጋ ድምፅ እየናጡት ነው ። አለቅጥ መረን ተለቀቀና ወደሌላ አቅጣጫ ሳይሄድ እንዲቆም ቢደረግ መልካም ነው ።

ሰው ሀይማኖቱን ማስተማር ከፈለገ በየሀይማኖት ተቋሙና በየሚዲያዎቹ ያስተምር እንጅ ሴኩላር የሆነና ብዝሀ ሀይማኖት ባለበት ህዝብ መካከል እየመጡ ይሄንን ካልተቀበልክ ከስረሀል ጠፍተሀል እያሉ መጮህ ሌላ የብጥብጥ ስጋትን ይደቅናል ።

አሁንማ ሆስፒታል አልቀረ የትምህርት ማእከላት አልቀሩ በቃ የሰበካ ወይንም የጩኸት ዘመቻ ተከፍቶ ህዝባችን እየተሳቀቀ ነው ።

መንግስት ይህንን መረን የለቀቀ ሰበካ ማስቆም አለበት ። እየተደረጉ ያሉ ትንኩሳዊ ስብከቶች በሗላ ከቁጥጥር የወጣ ቀውስን እንዳያመጡ እሰጋለሁ ።

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

👉 t.me/Seidsocial
👉 t.me/Seidsocial
ሁለት ዜናዎች የየመን ሁቲዎችን በተለመለከተ

1 የመኖች በዛሬው እለት ሁለት የአሜሪካና የእንግሊዝ መርከቦችን በሚሳኤልና ድሮኖች ቅንጅት ደብድበዋል ። አሜሪካና እንግሊዝ በየመን ላይ የአየር ድብደባቸውን አጠናክረው ቢቀጥሉም ሁቲዎችን ግን ማስቆም አልቻሉም ። የመኖችም እኛ ጥቃታችንን የምናቆመው የፍልስጤም ወንድሞቻችን ጥቃት ሲቆም ብቻ ነው በማለት ትግላቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል ። በዛሬው እለትም ሁለት የእንግሊዝ እና የአሜሪካ መርከቦችን በሚሳኤሎቻቼው ደብድበዋል ።

2 የየመን ሁቲዎች አሜሪካና እንግሊዝ በየመን ላይ የሚያደርጉትን ድብደባ ካላቆሙ የአለም የመገናኛ ኢንተርኔት መስመርን እንደሚቆርጡት አስጠንቅቀዋል ። ይህ ምስራቁን ከምእራቡ አለም የሚያገናኘው የኢንተርኔት መስመር የተዘረጋው በቀይባህር እና ህንድ ውቅያኖስ ስር ሲሆን መስመሩም ሁቲዎች እንደፈለጉ የሚንቀሳቀሱበት መስመር ነው ። እናም ሁቲዎች ይህንን መስመር ከቆረጡት የአለም የኢንተኔት ግንኙነት ሊቋረጥ ይችላል ።
ከ 90% በላይ የሚሆነው የበይነመረብ መስመሮች የተዘረጉት በባህር ውስጥ መሆኑ ይታወቃል ።

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
ለአለም መርገምትን አውርሰው ያለፉት የባጢኒያ ሺአዎች !! Assassination and Mafia መነሻቸው !
የሀሰን ሳባህ በደም የተጨማለቁ እጆች ሲታወሱ !

ጊዜው በአባሲድ ኸሊፋና በሰልጁቅ ሱልጧኔትነት ጊዜ ነው ። በአባሲድ ኸሊፋ ስር ሱልጁቅ ሱልጧኔት አለመል ኢስላምን ሲመራ በነበረበት ወቅት ። ታላቁ አሊም አንነይሳቡሪይ ሶስት ሰዎችን ጠሩና ለታላቅ ኢስላማዊ ሀላፊነት አጯቸውና ቃል አጋቧቸው እነርሱም ኒዟመል ሙሉክ ፣ ሀሰን ሳባህና ታላቁ ሊቅ ኡመር ኻያም ነበሩ ።

ግና ሀሰን ሳባህ በኒዟመልሙሉክ ይቀና ነበርና እርሱን ለመግደል መንቀሳቀስ ጀመረ ። በይፋ ሙስሊም መስሎ በድብቅ ደግሞ ባጢኒያ ሆኖ የሰልጁቅና የአባሲድ ባለስልጣናትን ማሳደድ አሳዶ መግደልም ተያያዘው ። ባጢኒያነት ስውርነት ነው ። ባጢኒያዎች ቁርአን ሁለት ትርጉም አለው ብለው ያምናሉ አንዱ የዟሂር ትርጉም ሲሆን ይህም ቁርአን ከላይ በቀጥታ ያለው ትርጉም ነው ። ሌላኛው ትርጉሙ ደግሞ የባጢን ትርጉም ነው ። ይህ ለባጢኒ ኡለሞች እንጅ ለማንም ያልተገለጠ ማንም ምንም ቢደክም የማያገኘው ከፈጣሪ በቀጥታ በሚደረግ ግንኙነት የሚገኝ ብቻ ። ልክ እንደ አሁኑ የፕሮቴስታንት ሀሰተኛ ነብያት በሏቸው ።

እናም በባጢኒ ሀራሞች ሁሉ ሀራም ሀላሎች ሁሉም ሀላል አይደሉም ። አንድ መጥፎ ነገር መጥፎ የሚባሉ ለተመልካቹ ሊሆን ይችላል በባጢን ግን የተፈቀደ ይሆናል ። ሌላው መገለጫቸው አንድ ሰው የባጢኒ ኢስማኢሊያን ለማስፋፋት ተልእኮውን ለመወጣት ምንም ማድረግ ምንም መሆን ይችላል ። ክርስቲያን መሆን ይችላል ፓጋን መሆን ይችላል ሱኒ መሆን ይችላል ግና ብቻ የተባለለትን አላማ ተመሳስሎ መግደል አለበት ኸላስ !

በኢስላም ታሪክ ከታዩ አስቀያሚ ግሩፖች ውስጥ ናቸው እነዚህ ባጢኒዮች ። እናም እነ ኒዟሙል ሙሉክን ጨምሮ በርካታ የኢስላም ስብእናዎችን መግደል ተሳካላቸው ኢስላሙ አለምን አዳከሙት ሰልጁቅ ኢምፓየርን ገዘገዙት ። ሱልጧን መሊክሻህ ሊያጠፋቼው ቢሞክርም ፍፁም ከማንም ጋር ተመሳስለው በመኖራቸው ጭራሽ አስቸጋሪ አደረገበት። መሊኽ ሻህ ሲሞት ልጁ አህመድ ሳንጃር ዋና መቀመጫቼውን አላሙትን አፈራርሶ ሀሰን ሳባህን ሊገድለው ሲል የሳንጃርን አገልጋይ ሴት አንገቷ ላይ ስለት በመደገን ከተንቀሳቀስክ አንገቷን እቆርጠዋለሁ በማለቱ እሷን መያዦ አድርጎ አምልጧል ።

#Assassins !

በሀሰን ሳባህ የሚመሩት ባጢኒዎች ለአለም ካበረከቱት ነገር አንዱ እራስን አጥፍቶ ማጥፋት ነው ። ለዚህም ባጢኒዎች መግደል የማፈልጉትን ባለስልጣን ገድለው ራሳቸውን ይገድላሉ ። አንዳዴም ምስጢር እንዳያወጡ ምላሳቸውን ተቆርጠው ወደ ተልእኮ ይዘምታሉ ። ከሀሰን ሳባህ ለዚህም ጀነት ቃል ይገባላቸዋል ። የውሸት የቅጥፈት ጀነት !!
ታድያ ሀሰን ሳባህ ይህን አይነት ጭካኔ እንድሂ እንዲወስኑ አያደርጋቸውም ። ከፍተኛ የሆነ ሀሽሽ ያስወስዳቸዋል ። በሀሽሽ ከደነዘዙ በሗላ የፈለገውን ነገር ያሰራቸዋል ። ፈንጆችም ባጢኒያዎችን Hashashin ሲሉ ጠሯቸው ። Hashashin ከሚለው ቃልም Assassin የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል ተፈጠረና የእነርሱን ተግባር መፈፀም Assassination ተብሎ ተጠራ ። አይገርማችሁም ??!!
እናም ራስን ሰውቶ የፈለጉትን ዝነኛ ሰው አዋቂና ባለስልጣን መግደል ከነርሱ ተወሰደ ማለት ነው ።

#Mafia

ሌላው ባጢኒያ ሺአዎች የፈጠሩት ነገር ማፊያነትን ነው ። ታላቁ ሱልጧን ሰላሂድን አልአዩቢ ፋጢሚዶችን አሸንፎ ግብፅን ሲቆጣጠር የባጢኒ ሺአዎች ወደ ጣሊያኗ የሲሲሊ ከተማ ፈለሱና እዚያ በድብቅ የራሳቸውን የምስጢር እንቅስቃሴ ፈጠሩ ። ያም መግደልን መዝረፍን ማገትን እና ሌሎችም ዘግናኝና አስፈሪ እርምጃዎችን ይወስዱ ነበር ። እንቅስቃሴያቸውንም #መህፊያ ብለው ጠሩት ። በአረብኛ ምስጢር እንደማለት ነው ። እናም መህፊያ ከሚለው ቃል ማፊያ ተወለደ ማለት ነው ። ጣሊያንም ከዚያ ጀምሮ ማፊያዎች የተወለዱባት ሀገር ሆነች ። እናም በሱሰኝነት የማነዳው ማፊያ በዚህ መልኩ አለምን ተዋወቀ ።

ባጢኒዮች አብዛኛው ኢላማቸው ሙስሊሞች ነበሩ ። ለዚህም ከመስቀል ጦረኞች ጋር አብረው ይሰሩ ነበር ። የመስቀል ጦረኞች በባጢኒያዎች በጣም ይደነቁና ይገረሙ ነበር ። ብዙ የጭካኔ ተግባሮቻቼውንም ኮረጄው ወስደዋል ።
ባጢኒያ ወታደሮች ተአማኝነታቸውን ለሰይዳቸው ሀማሳየት የራሳቸውን አንገት ጭምር ይቀሉ ነበር ። ለሀሰን ሳባህ ታማኝነት መተኪያ የሌለው መስፈርት ነው ። ሀሰን ሳባህ ሁለት ልጆቹን ሳይቀር የገደለ ጉድ ያለው ሰው ነበረ ።

ባጢኒያዎችን ከፍተኛ ውድመት አድርሶ የበታተናቸው የሞንጎል ጦር ነበር ። በሁላጉ ኻን የሚመራው የሞንጎል ጦር ባጢኒዎችን ደምስሶና በታትኖ የተረፉት ጥቂቶች ወደ አዘርባጃን እና አናቶሊያ እንዲሰደዱ አድርጓቸው ነበር ።

የኢራኑን ሳፋቪድ ዳይናስቲን የመሰረተው ኢስማኢልም አስተምህሮቱን የወሰደው ከነዚህ ከሞት ከተረፉ ባጢኒዎች ነበር ። ባጢኒዎች ከኢስላም ያፈነገጡ ቡድኖች ነበሩ ።

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
#ክንፍ_ያሉት_ወዳጆች_ዘልአለማዊ_ጠላትነትን¶የተጋቡባት_ቀን !
የኢራን ኢስላማዊ አብዮት ሲታወስ !
1941 እ.ኤ.አ እንግሊዝና ሶቭየት ሩሲያ በጋራ ኢራንን ወረሩ ። የወረራቼው ምክንያት ደግሞ ኢራን የጋራ ጠላታቼውን የናዚ ጀርመንን ተፅእኖ መቋቋም አልቻለችም በሚል ነበር ። ይህች ምክንያት ነበረች ። ዋና አላማቼው ግን በጋራ የኢራንን ነዳጅ መቆጣጠር ነበርና አደረጉት ። ያንጊዜ ሩሲያና እንግሊዝ እንደዛሬው ጠላት ሳይሆኑ አብረው የሚዋጉ አብረው የሚወሩ ወዳጆች ነበሩ ። ያው በፖለቲካው ዘላቂ ጥቅም እንጅ ዘላቂ ወዳጅ የለም አይደል የሚባለው ።

እናም እንግሊዝና ሪሲያ ኢራንን ወረሩና የሀገሪቱን መሪ ሬዛ ልጁን ሙሀመድ ሬዛን ተላላኪ መሪያቼው አድርገው አስቀመጡት ። ከዚያ በሗላ ሁለቱ ሀገራት ኢራንን መጋጥ ተያያዙት ። በዚህ ጊዜ በኢራን ባለስልጣናት የሚመራ ተቃውሞ ተነሳ ። ተቃውሞውም የውጭ ሀይላት ከሀገራችን ይውጡ ኢራን የኢራናዊያን ትሁን የሚል ነበረ ። ተቃውሞው ሲበረታ እንግሊዝ ጦሯን ከኢራን አስወጣች ሩሲያ ግን ለተቃውሞ ደንታ የሌላት ሀገር ናትና በኢራን ተተክላ ቀጠለች ። ይህ ያበሳጫት አሜሪካም ለሩሲያ ማስጠንቀቂያ ስትልክ ሩሲያም ከኢራን ጦሯን አስወጣች ። ይሁን እንድ እንግሊዝ ከኢራን ብትወጣም የኢራንን ነዳጅ በአንግሎ-ኢራን የነዳጅ ኩባንያዋ አማካኝነት ሙጥጥ አድድጋ ትወስድ ነበር ። ይህ ድርጊት ያበሳጨውና የኢራንን ጠቅላይ ሚኒስትርነት የተቆናጠጠው ሙሀመድ መስደቅ የእንግሊዝን ውል በማቋረጥ ምእራባውያንን አስከፋ ።

በዚህ ጊዜ ነበር አሜሪካና እንግሊዝ የተላላኪያቼዌን የሻህ ሙሀመድ ሬዛን ስልጣን ለመጠበቅ አንድ አደገኛ የደህንነት ተቋም ማቋቋም እንዳለባቼው በማመን SAVAK የተሰኘ ምስጢራዊ ቡድን ያቋቋሙት ። SAVAK የንጉሱን ስልጣን ለመጠበቅና ጠላት ያላቼውን አሳዶ ለመግደል 60,000 ሰላዮችን ይዞ መንቀሳቀስ ጀመረ ። ሳቫክ በዋናነት ኢስላማዊ ንቅንቄ የሚያደርጉ አካላትን በሙሉ እያደነ መግደል ማሰቃየትን ተራቀቀበት ።

ከማሰቃያ መንገዶቹ ውስጥ በጅምላ አስገድዶ መድፈር ፤ ጥፍር መንቀል ፤ ከፍተኛ የሆነ የኤሌክትሪክ ሾክ በብልት ውስጥ መልቀቅ ይጠቀሳሉ ። አሜሪካና እንግሊዝ ከስለላው በተጨማሪ በገንዘብም በማጠናከር ኢራንን እያለቡ ሻሁን እያፈረጠሙ የኢራንን ህዝብ የበይ ተመልካች አደረጉት ።

በዚህ የልብ ልብ የተሰማው ሻህ ሙሀመድ ሀይማኖታዊ እሴቶች በሙሉ ከሀገሪቱ እንዲጠፉ ወሰነ ። ስልጣን ላይ ሲወጡ በቁርአን መማልን ከለከለ ። የአውሮፓ እሴቶች በሙሉ የኢራን እሴቶች እንዲሆኑ በማድረግ ዳግማዊው አታቱርክ ሆኖ ተነሳ ። በዚህ ጊዜ ነው አያቱሏህ ኹመይኒ ሌሎች አጋር ኡለሞችንና ህዝባቼውን አስነስተው አመፅ የገቡት ።

አያቱሏህ ኹመይኒ ከታሰሩ በሗላ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሰን አልመንሱር ፊት ቀረቡ ። ገማል አብዱልናስር ሰይድ ቁጥብን ይቅርታ ጠይቅ እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትሩም ለኢማም ኹመይኒ " አጥፍቻለሁ ይቅርታ አድርጉልኝ " በል አላቸው ። ኢማሙ ግን እምቢ አሉ ።በዚህ ጊዜ ጠቅላይሚኒስትሩ ተነሳና በጥፊ ደረገማቸው ። ከኢራን እንዲሰደዱም ወሰነባቼው ። በርግጥ እንደ ሰይድ ቁጥብ አለመግደሉም ደግ ነገር ነው ። ኹመይኒ ዝም አሉ ! የኢራን ህዝብ ግን ዝም አላለም ነበር ። ያንን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሳደድ ያዘ ። ይህንን ካደረገ ከሳምንታት በሗላ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን አልመንሱር ከነ ባልደረቦቹ ተገደለ ። ለኹመይኒ ጠላቶች ሁሉ ጆሮ ጭው የሚያደርግ ዜና ነበረ ።

ኹመይኒ በስደት ሆነው ትግሉን ማቀጣጠል ያዙ ። የእንግሊዝ የስለላ ተቋማትና የአሜሪካው ሲአይኤ ሻሁን ለማዳንና አብዮቱን ለመልበስ የቻሉትን ሁሉ ቢያደርጉም ሊሳካላቼው ሳይችል ቀረና ህዝቡ ንቅል ብሎ ተሰለፈ ። ሻህ ሙሀመድ ከስልጣን ሳይወርድ ኹመይኒ ወደ ኢራን በረራ ጀመሩ ። እኔ ብሞትም ትግሉ በተከታዮቼ ይቀጥላል ብለው ኢራን አየር ላይ ሲደርሱ የንጉሱ ባለስልጣናት ለሁለት ተከፈሉ ። ግማሾቹ ኢማም ኹመይኒ አየር ላይ ይመቱ ሲል ግማሾቹ ይህን ካደረግን የኢራን ህዝብ ይበላናል አንዳችንም አንተርፍም ብሎ ሲሟገቱ በ 1979 በትላንትናዋ እለት ኹመይኒ ቴህራን ደረሱ ። ያኔ ኢራን በታሪክ አይታ በማታውቀው የሰው ጎርፍ ማእበል ተጥለቀለቀች ። " ሞት ለአሜሪ ! ሞት ለእንግሊዝ ! " በሚል መፈክር የኢራን ምድር ተንቀጠቀጠ ። የሻህ ሙሀመድ ሬዛ ስልጣንም የኢራንና የምእራባውያን ወዳጅነትም የዚያን ቀን አበቃ ።

ይህንን የተረዳቺው አሜሪካም ኢራንን መምታት አልያም ማዳከም አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው አለች ። እናም ኢራንን ለመደብደብ የጦር ጄቶቿን ወደ ኢራን ብትልክም ሁሉም ተከስክሰው ቀሩ ።

በዚህ ጊዜ አሜሪካ የኢራቁን ሰዳም ሁሰይንን በማስታጠቅና ከፍተኛ የስለላና የስትራቴጂ ድጋፍ በማድረግ ኢራንን እንዲወር አበረታቺው ። ሳዳምም በአሜሪካ እየታገዘ በአረብ ሀገራት ፔትሮዶላር እየተንቆረቆረለት ኢራንን ወረረ ። የጀመረው ግና ያልጨረሰው ጦርነት ለ ሰባት አመታት ተዋግቶ በመጨረሻም ተሸንፎ ከስሮ ከኢራን ተመለሰ ። ከዚያ ሲመለስ ለእዳው ማካካሻ ኩዌይትን መውረሩ ከወዳጆቹ አሜሪካና አረቦች ጋር ሲያላትመው ጊዜ እንግሊዝ እና አሜሪካ ዘመቱበትና መጨረሻውም አሳዛኝ ሆኖ ቀረ ። ከዚያ በሗላ የኢራቅ እጣፈንታ በአሜሪካ እና በኢራን ውስጥ ገባና ዛሬ የምናያትን ኢራቅን ዛሬ የምናያትን ኢራንን ለማየት በቃን ።

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
" ሀማስ የማይችለውን ጦርነት ከፍቶ ፍልስጤሞችን አስጨረሳቸው "

ይህ የፈሪዎቹ ወቀሳ ነው ! ይህ የደንታቢሶቹ ክስ ነው ! ይህ የኢስላም ልቅናም የሙስሊሞች ክብርና ህልውናም የማያሳስባቸው የግደለሾች ክስ ነው !!

ሀማስ የተመሰረተው በ 1987 ነው ከዛሬ 36 አመት በፊት ። እስራኤል ፍልስጤማዊያንን ካለአንዳች መከላከል እንደፈለገች ስትጨፈጭፍ ህይወታቸውን ሰውተው ህዝባቸውን ለማዳን የኢስላም ሸአኢሮችን ለመጠበቅ ሞትን ላይፈሩ ተማምለው የመሰረቱት የሙጃሂዶች ስብስብ ነው ። ይህ የነ ሸይኽ አህመድ ያሲን የነ አብዱአዚዝ አልረንቲሲ የህይወት መስዋእትነት ውጤት ነው ።

ሀማስ ባይኖር በአሁኑ ሰአት አንድም ፍልስጤማዊ በፍልስጤም ምድር አይገኝም ነበር ። ጋዛ ዌስት ባንክ የሚባሉ የፍልስጤም መኖሪያዎችንም አናይም ነበር ። የእስራኤልን እጅግ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ የሚታገል ብቸኛው የሙጃሂድ ቡድን ሀማስ ብቻ እንጅ ሌላ አይደሉም ።

ሀማሶች ከላይ ሚሳኤሉ ቢዘንብባቸው ከታች ታንክና መድፉ ቢያጓራባቸው እንኳን የሚፈራ የሚደነግጥ ልብ የሌላቸው ተዋርዶ ከመኖር በክብር ሸሂድ መሆንን የሚናፍቁ ሙጃሂዶች ፤ መላው አረብ ተንቦቅቡቆ ከእስራኤልና ምእራባውያን ጋር ሲሽለጠለጥ እነርሱ ግን ከተራራ በገዘፈ ኢማናቸው ተመክተው እነዚህን የገጠሙ የሶሀቦች ትውስታ ትክክለኛ ኸሊፋዎቻቼው ናቸው ። ሀማሶች አንድም ቀን ተመችቷቸው ኖረው አያውቁም ። ሁሌም ከምድር በታች እየቆፈሩ ከምድር በታች እየኖሩ አፈር ለብሰው ድንጋይ ተንተርሰው ይሄንን የሞተ ኡማ ሩህ አለው የሚያስብሉ የኡማውን ቀንደኛ ጠላት እስራኤልን እያቃዡ የሚያስጨንቁ እነርሱ የሙሀጅርና አንሷሮች ኩትኩት የውዱ ነብያቸውም ፈለግ እውነተኛ ተከታይ ፤ ኢስላምን በቃል ሸንገላ ሳይሆን በተግባር የሚኖሩት ፤ ጅሀድን በቂርአት ሳይሆን በህይወትና ንብረታቸው የሚማሩት የወቃሽን ወቀሳ ሳይሰሙ ስለኢስላማቸው ስለህዝባቸው ፍግም የሚሉ እነርሱ ህያዋን ናቸው ።

የፈሪ ፈሪዎቹ ግን አህያውን ፈርቶ ዳውላውን እንዲሉ እስራኤልን ሲፈሩ ሀማስን ይወቅሳሉ ! ሀማስን ያወግዛሉ !  ይህ ንፍቅና ነው ! ይሄን በቃል መግለፅ አልችልም !!

እነዚህ ደንታቢሶች ሀማስን " ካለአቅሙ እስራኤልን እየተዋጋ " ብለው ጀግኖቹን ለማውገዝ ሲሞክሩ አይሰቀጥጣቸውምን ? በአቅምማ ቢሆን የሳኡዳ አረቢያ የኢኮኖሚ አቅም የእስራኤልን ሁለት ሶስት እጥፍ ይበልጥ ነበረ ! የግብፅ ወታደር ብዛት የእስራኤልን ሶስት እጥፍ ይበልጥ ነበረ ! የቱርክና የፓኪስታን ወታደራዊ አቅም ከእስራኤል ይልቅ ነበረ !
ግና ከነርሱ ጋር የኢኮኖሚና ወታደራዊ አቅም እንጅ የሀማሶች ሪጃልነት የለም !! ሪጃልነትን አላህ መርጦ የሰጠው ለሀማሶች ናቸውና ! የእርሱን ጅሀድ ይዋደቁ ዘንዳ የተመረጡት ሀማሶች ናቸውና !!
ሌላውማ መይት ነው ! ኢራንና ሂዝቦላህ ለሙስሊሞች ክብር ያላቸውን መቆጨት ለምእራባዊያን ያላቸውን ትግል 1% እንኳ የላቸውም !!

አህሉል ሩዞችና አህላል ፊራሾች አህለል ጅሀዶችን ሲያንጓጥጡ እንደማየት የሚያሳፍር የለም !

ሀማስ ይህንን ጦርነት የጀመረው እስራኤል መስጅደል አቅሷን ጨርሳ ጠቅልላ ለመውሰድ እየተዘጋጀች ባለችበት ነበር ። እናም የአይሁድ አማኞች መስጅዱን ሊረከቡ ዝግጅታቸውን እየጨረሱ ሳሉ ነበር ሀማስ እኛ በህይወት እያለን ይህንን አንፈቅድም በማለት ጦርነት ያወጀው ።

ሀማስ ጦርነቱን ሲከፍት እስራኤል በወረራ በያዘቻቼው የጋዛ ድንበሮች ላይ ምእራባውያን ሙጅሪሞችን ጨምሮ የእስራኤል ሰፋሪዎች በጋዛ ድንበር ተሰባስበው እየጠጡ እየጨፈሩ ነበር ። ሀማስ እንደ መብረቅ ወረደባቸው ። በመቶዎች የሚቆጠሩ የእስራኤል ወታደሮችንም ወደ ጀሀነም ላካቸው ። ከዚያ በሗላ ይሄው ጦርነቱ ተፋፍሞ ቀጥሏል ።
እስራኤል አቅሟ ንፁሀን ላይ ነውና ንፁሀንን በአየር እየጨረሰች ነው ። ይህንን ከምስረታዋ ጀምሮ የምታደርገው ነው ። ሀማስ ስለመጣ እስራኤል ጦርነት የከፈተች የሚመስላቸውን ገልቱዎች ማስረዳት ከባድ ነው ።

አላህ ድልን ለሙጃሂዶቹ ያጎናፅፋል !
ቃሉንም ይሞላል !

ያኔ መናፍቃንም አዱወሎሆችም ያፍራሉ ይሸማቀቃሉ ኢንሻአላህ !!!!

#seid_mohammed_alhabeshiy

t.me/Seidsocial