Seid Social
9K subscribers
2.18K photos
320 videos
6 files
1.37K links
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል
Download Telegram
" ሀማስ የማይችለውን ጦርነት ከፍቶ ፍልስጤሞችን አስጨረሳቸው "

ይህ የፈሪዎቹ ወቀሳ ነው ! ይህ የደንታቢሶቹ ክስ ነው ! ይህ የኢስላም ልቅናም የሙስሊሞች ክብርና ህልውናም የማያሳስባቸው የግደለሾች ክስ ነው !!

ሀማስ የተመሰረተው በ 1987 ነው ከዛሬ 36 አመት በፊት ። እስራኤል ፍልስጤማዊያንን ካለአንዳች መከላከል እንደፈለገች ስትጨፈጭፍ ህይወታቸውን ሰውተው ህዝባቸውን ለማዳን የኢስላም ሸአኢሮችን ለመጠበቅ ሞትን ላይፈሩ ተማምለው የመሰረቱት የሙጃሂዶች ስብስብ ነው ። ይህ የነ ሸይኽ አህመድ ያሲን የነ አብዱአዚዝ አልረንቲሲ የህይወት መስዋእትነት ውጤት ነው ።

ሀማስ ባይኖር በአሁኑ ሰአት አንድም ፍልስጤማዊ በፍልስጤም ምድር አይገኝም ነበር ። ጋዛ ዌስት ባንክ የሚባሉ የፍልስጤም መኖሪያዎችንም አናይም ነበር ። የእስራኤልን እጅግ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ የሚታገል ብቸኛው የሙጃሂድ ቡድን ሀማስ ብቻ እንጅ ሌላ አይደሉም ።

ሀማሶች ከላይ ሚሳኤሉ ቢዘንብባቸው ከታች ታንክና መድፉ ቢያጓራባቸው እንኳን የሚፈራ የሚደነግጥ ልብ የሌላቸው ተዋርዶ ከመኖር በክብር ሸሂድ መሆንን የሚናፍቁ ሙጃሂዶች ፤ መላው አረብ ተንቦቅቡቆ ከእስራኤልና ምእራባውያን ጋር ሲሽለጠለጥ እነርሱ ግን ከተራራ በገዘፈ ኢማናቸው ተመክተው እነዚህን የገጠሙ የሶሀቦች ትውስታ ትክክለኛ ኸሊፋዎቻቼው ናቸው ። ሀማሶች አንድም ቀን ተመችቷቸው ኖረው አያውቁም ። ሁሌም ከምድር በታች እየቆፈሩ ከምድር በታች እየኖሩ አፈር ለብሰው ድንጋይ ተንተርሰው ይሄንን የሞተ ኡማ ሩህ አለው የሚያስብሉ የኡማውን ቀንደኛ ጠላት እስራኤልን እያቃዡ የሚያስጨንቁ እነርሱ የሙሀጅርና አንሷሮች ኩትኩት የውዱ ነብያቸውም ፈለግ እውነተኛ ተከታይ ፤ ኢስላምን በቃል ሸንገላ ሳይሆን በተግባር የሚኖሩት ፤ ጅሀድን በቂርአት ሳይሆን በህይወትና ንብረታቸው የሚማሩት የወቃሽን ወቀሳ ሳይሰሙ ስለኢስላማቸው ስለህዝባቸው ፍግም የሚሉ እነርሱ ህያዋን ናቸው ።

የፈሪ ፈሪዎቹ ግን አህያውን ፈርቶ ዳውላውን እንዲሉ እስራኤልን ሲፈሩ ሀማስን ይወቅሳሉ ! ሀማስን ያወግዛሉ !  ይህ ንፍቅና ነው ! ይሄን በቃል መግለፅ አልችልም !!

እነዚህ ደንታቢሶች ሀማስን " ካለአቅሙ እስራኤልን እየተዋጋ " ብለው ጀግኖቹን ለማውገዝ ሲሞክሩ አይሰቀጥጣቸውምን ? በአቅምማ ቢሆን የሳኡዳ አረቢያ የኢኮኖሚ አቅም የእስራኤልን ሁለት ሶስት እጥፍ ይበልጥ ነበረ ! የግብፅ ወታደር ብዛት የእስራኤልን ሶስት እጥፍ ይበልጥ ነበረ ! የቱርክና የፓኪስታን ወታደራዊ አቅም ከእስራኤል ይልቅ ነበረ !
ግና ከነርሱ ጋር የኢኮኖሚና ወታደራዊ አቅም እንጅ የሀማሶች ሪጃልነት የለም !! ሪጃልነትን አላህ መርጦ የሰጠው ለሀማሶች ናቸውና ! የእርሱን ጅሀድ ይዋደቁ ዘንዳ የተመረጡት ሀማሶች ናቸውና !!
ሌላውማ መይት ነው ! ኢራንና ሂዝቦላህ ለሙስሊሞች ክብር ያላቸውን መቆጨት ለምእራባዊያን ያላቸውን ትግል 1% እንኳ የላቸውም !!

አህሉል ሩዞችና አህላል ፊራሾች አህለል ጅሀዶችን ሲያንጓጥጡ እንደማየት የሚያሳፍር የለም !

ሀማስ ይህንን ጦርነት የጀመረው እስራኤል መስጅደል አቅሷን ጨርሳ ጠቅልላ ለመውሰድ እየተዘጋጀች ባለችበት ነበር ። እናም የአይሁድ አማኞች መስጅዱን ሊረከቡ ዝግጅታቸውን እየጨረሱ ሳሉ ነበር ሀማስ እኛ በህይወት እያለን ይህንን አንፈቅድም በማለት ጦርነት ያወጀው ።

ሀማስ ጦርነቱን ሲከፍት እስራኤል በወረራ በያዘቻቼው የጋዛ ድንበሮች ላይ ምእራባውያን ሙጅሪሞችን ጨምሮ የእስራኤል ሰፋሪዎች በጋዛ ድንበር ተሰባስበው እየጠጡ እየጨፈሩ ነበር ። ሀማስ እንደ መብረቅ ወረደባቸው ። በመቶዎች የሚቆጠሩ የእስራኤል ወታደሮችንም ወደ ጀሀነም ላካቸው ። ከዚያ በሗላ ይሄው ጦርነቱ ተፋፍሞ ቀጥሏል ።
እስራኤል አቅሟ ንፁሀን ላይ ነውና ንፁሀንን በአየር እየጨረሰች ነው ። ይህንን ከምስረታዋ ጀምሮ የምታደርገው ነው ። ሀማስ ስለመጣ እስራኤል ጦርነት የከፈተች የሚመስላቸውን ገልቱዎች ማስረዳት ከባድ ነው ።

አላህ ድልን ለሙጃሂዶቹ ያጎናፅፋል !
ቃሉንም ይሞላል !

ያኔ መናፍቃንም አዱወሎሆችም ያፍራሉ ይሸማቀቃሉ ኢንሻአላህ !!!!

#seid_mohammed_alhabeshiy

t.me/Seidsocial
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አረፋ በሙጃሂዶቹ ምድር በእውነተኞቹም መአሪክ እንደዚህ አለፈ።
ተልቢያውም ተክቢራውም እዚያ መእረካ ላይ !!!

አላህ ሆይ እኔ አንተ የምትወደው አይነት ስራ የለኝም ። ግና እነዚህን በቃልህ ያደሩ ደጋግ ባሮችህን እወዳለሁ !!!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢድ አልአድሀ ሶላት በጋዛ ምድር እንድህ ተሰገደ 💔
በፍርስራሹ ውስጥ ባልተሞተው ኢማን ፤ በፈራረሰው ቤተሰብም ባልፈረሰው ኡኽዋ ፤
ተስፋ በሚያስቆርጠው ሁኔታ ውስጥ ባልሞተው ተወኩልና የቂን ፤ ከአፈር በበዛ ጠላት ውስጥ ባልተሰበረው ወደጀሊሉ የመጠጋት ፅናትና ኢስቲቃማ ሁሉንም ችለው ሁሉም አልፎባቸው ይህችን ቀን እንድህ አሳለፏት😢

ሁሉም ሙስሊም አለም ቢረሳቸው አላህ ግን እንደማይረሳቸው እርግጠኞች ናቸው!

ከድቅድቁ ጨለማ ከሚያስፈራው ጭጋግ ባሻገር ዛሬ በዱኒያ ባይሆን ነገ በአኼራ አላህ እንደሚክሳቸውና የተስፋን ብርሀን እንደሚያፈግግላቸው ለቅፅበትም ተጠራጥረው አያውቁምና ህይወትና መስዋዕትነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ሆነውባቸው ቀጥለዋል።

ወዴት ይደረሳል ??????
ሸህ ጦሀን ወይ የኢድ አሰጋጅ ባያደርጉት ወይንም ደግሞ ተረጋግቶ እንዲያሰግድ ቢያሳምኑት ምናለ ???

እንደት ሰው ከሗላው በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሰጋጆችን አስከትሎ እንደዚህ ይጣደፋል ? የት ለመድረስ ነው ?
ሰው አላህ አክበር ብሎ ገና ሩኩእ እየወረደ እርሱ ከቅፅበት ይነሳል ። ከዚያ መልሶ ወደ ሱጁድ እየወረደ እያለ እርሱ አጣድፎት ይነሳል ። ቆይ ምን ማለት ነው ?

ሁሌ በአንድ ሰው ምክንያት እንደተወዛገብንና እንደተጣደፍን መስገድ አለብን እንዴ ?
በጣም ያናድዳል !

እንደት አንድ አሰጋጅ እንደዚህ አሮጋንት ይሆናል ? እርሱ እያሰገደ አንድ ቀን በትክክል ሰው ሰግዶ አያውቅም ። ግማሹ ሩኩእ ግማሹ ሱጁድ ብትንትን ያደርገዋል።
አሁን ሁለት ረከአ ሶላት አረጋግቶ ማሰገድ የሚያስቸግር ነገር ሆኖ ነው ? ለመእሙሙ ትንሽ አይታሰብም ?

ለነገሩ የተያዘው ሰጋጁ በአንድ ተሰብስቦ አድስ አበባ ስቴዲየም እንዳይሰግድ ማድረግ ይመስላል ። ደግሞም እየተሳካላቸው ነው።

ጠራራ አያስቸግር ምን አያስቸግር ሁሌ ግማሹን ጀመአ እየቆረጡ ህዝቡን ማስቀየሙን ቀጥለውበታል።

t.me/Seidsocial
የሳኡዲ አገዛዝን የበሰበሰ አካሔድ ስተች አህባሻቸውን የባረኩላቸው የሚመስላቸው ብዙ ሰዎች አሉ !
በጭራሽ እንዳታስቡት!!

የሙስሊሙን አንድነት ለመናድ ከየትኛውም ጠላት ጋር ተሰልፈው ለመታገል የማይወገዱ ፤ የላኢላሀ ኢለሏህ ሙስሊም ወንድሞቻቼውን ስለጠሉ ብቻ " ውሀብያ " የሚል ስም በግድ እየለጠፉ ከአይሁድም በላይ ጠላቶቻችን ናቸው ከሚሉ ፤ የሙስሊም ጠላቶች ሲሞቱ ሶስት ሰው ያለቀሰለት ጀነት ይገባል እነርሱም የጀነት ናቸው እያሉ የሚቀጥፉ ፤ ሙስሊሞች እስከተመቱላቸው ድረስ ከአፄያዊያን ጋር ጭምር አብረው የሚሰለፉ ፤ በፊቂሀዊ መሰአላ ሙስሊምን የሚያከፍሩ ፤ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብትና የእኩልነት ጥያቄ ላይ ደንቀራና እንቅፋት ሆነው ስንት ዋጋ ያስከፈሉ ፤ በሀሰት እየመሰከሩ ስንት ወንድሞቻችንን ያሳሰሩ ያስገደሉ ስንቱን የቲም ያደረጉ ፤ ስንት ጥብቅ እህቶቻችን የሙጅሪሞች መጫወቻ እንዲሆኑ ያስደረጉ ! ኧረ ስንቱ ... ከነርሱ ጋር ከምሆን ብቻየን ኖሬ ብቻየን መሞትን እመርጣለሁ !!!

አንዱን ፅንፈኛ ስተች ሌላኛውን ፅንፈኛ ሆንኩ ማለት አይደለም !!!

አህባሾች ላደረሱብን ግፍና ንፍቅናዊ ተላላኪነት የአይን ምስክር ነኝና ማንም ሊያሳምነኝ አይቻለውም !

t.me/Seidsocial
" እንዴ ወንድ መከላከል ያልቻልከውን እንደሴት አትነፋረቅ "

የኢስላማዊት ስፔይን የመጨረሻ ሰአታትና የግራናዳ ሱልጧኔት ፍፃሜ አሳዛኙ ክስተት በአጭሩ ሲታወስ !

https://youtu.be/kg-FAo4Ny8c?si=JpkQmyLF7BXtxRDd
አህባሽ የሚባል የለም ዝም ብሎ የተለጠፈ ስም ማጥፊያ ነው አህባሽን ፈልገነው አጣነው የሚሉ አስቂኞች አሉ። የት ፈልጋችሁት ነው የምታጡት ?
አህባሽ ሊባኖስ ውስጥ በፖለቲካውም በሀይማኖቱም በስፋት የሚንቀሳቀስ ትልቅ እንቅስቃሴ ነው።

አህባሽ የፖለቲካ ክንፍና የሀይማኖት ክንፍ ያለው ሲሆን የፖለቲካ ክንፉ በሊባኖስ ፓርላማ ውስጥ በምርጫ ይፎካከራል። በ 1992 የሊባኖስ የፓርላማ ምርጫ ተወዳድሮ ከሂዝቡላህ ጋር ጥምረት በመፍጠር መቀመጫ ወንበሮችን ማሸነፍ ችሎም ነበር። በ 2018 ምርጫም የአህባሽ ተወካይ አድናን ትራቡልሲ የፓርላማ ምርጫን አሸንፎ ገብቷል።
አህባሽ ሴኩላሪዝምን የሚያቀነቅን ሲሆን ሀይማኖትና መንግስት መለያየት አለባቸው ብሎ ያምናል።

አህባሽ ከሌሎች ሀይማኖቶች ጋር ማለትም ከአይሁድ ከክርስትና ወዘተ መቀራረብ መነጋገር በአንድ መስራት አለብን ብሎ የሚያምን ሲሆን ከሌሎች እርሱ በጠላትነት ከሚፈርጃቸው ኢስላማዊ ቡድኖች ጋር ግን በፍፁም የመግባባትም የመነጋገርም ልምድ የለውም። ከዚያ ይልቅ በወሀብይነትና በኢኽዋንነት የፈረጃቸውን በሙሉ ያከፍራል ከእስልምናም ያስወጣል።

ይሄ ፅንፍ የረገጠ አካሔዱም ከሊባኖስ ውጭ ብዙ እንዳይስፋፋ አድርጎታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስዜናዊና ይህንን አንጃ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለመጫን በርካታ ጥረት ያደረገ ሲሆን ሰፊ ተቀባይነት ባያገኝም የተወሰኑ ተከታዮችንና ፅንፈኛ አስተማሪዎችን ማፍራት ችሏል።

ከሚኖርባቸው መንግስታት ጋር ተቆራኝቶ መስራት መገለጫው የሆነው የአህባሽ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ በኢህአዴግ አገዛዝ ለደረሰው ከፍተኛ ጉዳትም ተጠያቂ ነው።

ቡድኑ ከላባኖስ በተጨማሪ በአሜሪካ በስፋት ይንቀሳቀሳል።

ከታች የምታዩት ምስል የአህባሽ ይፋዊ ሎጎ ነው።

t.me/Seidsocial
እኔና አባቴ

ለመጨረሻ ቤተሰብ ጋር የሄድኩ ግዜ ቤት በረንዳ ላይ ቁጭ ብለን ረዥም ሰአት አወጋን። ያመው ስለነበር ትንሽ ሰውነቱ ቀንሷል። ቀን ሲከፋ ግዜ ከእድሜ ቀድሞ ያስረጅ የለ እርሱም ላይ የእርጅና ምልክቶቹ መታየት ጀምረው ነበር።

ከልጅነቴ ጀምሮ ኑሯችንን ደግመን ደጋግመን እየቃኘን ብዙ ተጫወትን። አልፎ አልፎ ሁለታችንም በዝምታ በሀሳብ ባህር ውስጥ እንነጉዳለን። የቀዶ ህክምና ት/ቴን እና ውጭ ሀገር ህክምና ለማጥናት ፈቃድ የሚያስገኝልኝን ፈተና (USMLE) እኩል እያስኬድኳቸው እንደሆነና ሁሉም ጥሩ እየሄዱ እንደሆነ ነገርኩት።

"አንተ እያመለጥክ ነው። ህይወት አምርራ ብትታገልህም እያሸነፍካት ነው"አለኝ። ከልጅነቴ ጀምሮ ሁሌም የሚለኝ ነገር "ተማር ልጄ" ነበር። "ተማር ልጄ ወገን ዘመድ የለኝ ሀብት የለኝም ከጄ "የሚለውን ይወደዋል ... ታዳ ዛሬም ድረስ ድምፁ ይሰማኛል።

እኔም "አንድ ቀን ሁሉም መልካም ይሆናል። ህይወት መስመር እየያዘችልኝ ይመስለኛል" ብየው ትንሽ ዘወርወር ማለት ስለፈለኩ ወጣ ብየ ልምጣና ኋላ እናወራለን ብየው ተነሳሁ።

"በቀጣይ ስትመጣ አንዲት መኪና ይዘህ መትህ አብረን ደግሞ እንዞራለን" አለኝ። ውስጤን ደስ አለው። እሱ በኔ ተስፋ ሲኖረው የኔ ደግሞ የጋራ ህልማችንን የማሳካት ፍላጎቴ ይጨምራል። መኖርህስ ትርጉም የሚኖረው የምትኖርለት አላማ የምታስደስተው ሰው ሲኖርህ አይደል።

ከቤት ወጥቼ ከቅዳሜ ገበያ ት/ቤት እስከ ፒያሳ በእግሬ አዘገምኩ።ፒያሳ ከሚገኝ አንድ ካፌ ውስጥ ብቻየን ገብቼ በረንዳ ላይ ቁጭ ብየ ማኪያቶ እየጠጣሁ በሀሳብ ከወጭ ወራጁ ጋር እየተመምኩ እኔም አንድ ቀን ከሱ ጋር ከላይ ከታች እንደምል በህሊናየ እያሰላሰልኩ አምሽቼ ምሽቱ አይን ያዝ ማድረግ ሲጀምር ወደ ቤቴ ተመለስኩ።

ከለታት በአንዱ ቀን በደረሰብኝ የመኪና አደጋ ከአርቲፊሻል መተንፈሻ መሳሪያው ተላቅቄ ትንሽ ማገገም ስጀምር ዘመድ አዝማድ በተሰበሰቡበት እንዳረፈ ነገሩኝ።

ስለ ሁኔታው ጠየኳቸው

እኔ አድስ አበባ ሆስፒታል ስገባ እርሱ በተመሳሳይ ቀን ደሴ ሆስፒታል ገብቶ እንደነበር ነገሩኝ፤

ስለ እኔ ሰምቶ ነበር አልኳቸው?

"እኛ መናገር አልፈለግንም ነበር። መጀመሪያ የሰማው ሊጠይቁት ከሚመጡት ሰወች ነበር።" አሉኝ

"እና እሱ ጋር ማን ነበር። ሁላችሁም እኔ ጋር አድስ አበባ ከነበራችሁ?"

"አንተን እንጅ እርሱ ይቀድማል ብሎ ያሰበ ሰው ማንም አልነበረም። ቢሆንም ግን ግማሻችን አንተ ጋ ግማሻችን ደግሞ እሱ ጋር ነበርን አሉኝ።

"ምን አለ መጎዳቴን ሲሰማ?"ብየ ስጠይቅ

ብዙ አያወራም ነበር። አልፎ አልፎ ብቻ "ልጄ ምንም አይሆንም። እርሱ ገና ልጅ ነው ፤ እኔ ለሱ ፊዳ እሆናለሁ ፣እኔ የርሱን ሞት እሞትለታለሁ" ይል ነበር አሉኝ።

በዛ በክረምት እኔም ቀን ሊወጣልኝ ነው ስል ሌላ ጨለማ ውስጥ ዳግም የገባሁበት አባቴም ከዚች አስከፊ የህይወት ውጣ ውረድ ለዘላለሙ ያረፈበት ክረምት ሆኖ አለፈ።

የለፋሁበት የደከምክምበት ድንገት እንደ ማለዳ ጤዛ በኖ ሲጠፋ በህልሜ ላይ ቀዝቃዛ ውሀ ሲቸለስበት፣ ጉልበት ሲከዳኝና አቅም ሳጣ፣ ፍራቻና ጭንቀት ቤታቸውን ሊሰሩብኝ ዱብዱብ ሲሉ በሰወች መሀል ተከበቤ ብቸኝነት ሲሰማኝ የመናር ትርጉሙ ሲጠፋብኝና የመኖር ጉጉት ሲለየኝ፣ በሀዘንና በደስታየ በከፍታና በዝቅታየ፣ ፍራቻየንና ጭንቀቴን የማዋየው ሰው ድንገት ሲለየኝ ስሜቱን መግለፅ ከባድ የነበረ ቢሆንም ከወደኩበት የጨለማ ዋሻ ወጥቼ ድጋሜ እንደ ንስር ለመብረር "ህይወትን ብቻህን ሁነህ ለመጋፈጥ እንዳትፈራ፣ ለራስህ ከራስህ በላይ ማንም የለህም፣ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ተስፋ እንዳትቆርጥ፣ከምንም በላይ ወደ አላህ ራስህን አስጠጋ" ብሎ የመከረኝ ምክር ለመከራ ግዜ ስንቄ፣ የድካም ግዜ ምርኩዜ፣ የጨለማ ግዜ መብራቴ ከመሆኑም በላይ ነገሮችን ቀለል አድርጌ እንዳይ፣ መንፈሰ ጠንካራና የማይሰበር ማንነት እንዲኖረኝ በአለማዊም በመንፈሳዊም ህይወት ላለኝ የዛሬ ማንነት ትልቅ አሻራውን ጥሎ ያለፈ ለጀግና አባቴ ስል ምንም እንዳልተፈጠረ ነገሮችን ተቀብየ ጉዞየን ቀጥየ ዛሬ ላይ ደርሻለሁ... ስለ ነገ ነገ ራሱ ያውቃል እያልኩ በልቤ ውስጥ ህያው የሆነውን አባቴን ዛሬ በአደባባይ ላመሰግነው ወደድኩ!

እንዲሁም ለመላው የእስልምና ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

Dr. Nuru Ahmed: MD, Surgeon

© Hakim

t.me/Seidsocial
አሜሪካ በቻይና ላይ የንግድ እቀባ ጥላለች። አሜሪካ ይህን እርምጃ የወሰደቺው ቻይና የኡይጉር ሙስሊሞችን የሰብአዊ መብት እየጣሰች ነው በማለት ነው።

በመሆኑም በኡይጉር ብዝበዛ የሚመረቱ የትኛውም ምርቶችን ቻይና ወደ አሜሪካ መላክ እንዳትችል ማእቀብ ጥላለች። አሜሪካ የኡይጉር ሙስሊሞችን መብት ቻይና እንድታከብርም አሳስባለች።

መቼስ የሀያላኑ ቁማርና ንፍቅና ገርሞ ገርሞ ይገርማል።
ከፍልስጤም እስከ አፍጋሃኒስታን ለሚሊን ሙስሊሞች ጭፍጨፋ ዋነኛ ተጠያቂ የሆነቺዋ አሜሪካ ለፖለቲካ ትርፏ ስትል ቻይና የሀገሯን ሙስሊሞች መብት እንድታከብር መጠየቋ ይደንቃል።
የኡይጉር ሙስሊሞች በቻይና ከፍተኛ ሲስተማቲክ የዘር ማፅዳት እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ይታወቃል

ንፍቅናቸውን ለመግለጽ ቃል ያጥራል!

t.me/Seidsocial
የኡይጉር ሙስሊሞች ማን ናቸው ?
ኢስላምን እንደት ተቀበሉ ?
የቻይና ኡይጉሮችን ወደ ቻይናነት የመቀየር በቴክኖሎጂ የተራቀቀ ዘር ማጥፋት ምን ይመስላል ?
ይሳካላትስ ይሆን ??

ብታዳምጡት ጠቃሚ መረጃዎችን ታገኛላችሁ


https://youtu.be/6aQPRJh-6YA?si=YrWNtY-g9Lr-0EpI
የጫካ ፕሮጀክት ጫካ ሙሉ ጉዶች !

ብልፅግና የ 10 ቢሊዮን ዶላር ቤተመንግሥት እየገነባ ነው ወደ ብር ሲቀየር 600 ቢሊዮን ብር ገደማ ማለት ነው።። በዚህም የአብይ አህመድ ቤተመንግስት 10 ቢሊዮን ዶላር ያወጣ በአለም እጅግ ውዱ እጅግ ቅንጡው ቤተመንግስት ያደርገዋል። ይህ ቤተመንግሥት በአለማችን ላይ እስከዛሬ ውድ ተብሎ የተመዘገበውን የእንግሊዙን ቡኪንግሀም ቤተመንግስት በውድነት በ 10 እጥፍ ይበልጠዋል። ቡኪግንሀም ተገንብቶ የተጠናቀቀው በ 1 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ነውና። ስሙንም የጫካ ፕሮጀክት ብሎታል።

የአብይ አህመድ ቤተመንግሥት በሰፊው የየካ ክፍለከማ እየተገነባ ሲሆን ተገንብቶ ሲጠናቀቅ በዘንባባ ዛፎች የተዋቡ 3 ሰው ሰራሽ ሀይቆች ፤ ሰው ሰራሽ ፏፏቴዎችና ወንዞች ፤ ቅንጡ ሆቴሎች ፤ የሀገራት መሪዎችን መቀበያ በጣም የተቀናጡ ዘመናዊ እንግዳ ማረፊያወች፤ የእንሰሳት ፓርኮች ፤ ቅንጡ የባለስልጣናት መኖሪያ አፓርትመንቶች ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከነቤተሰባቸው የሚኖሩባቸው የተለዩ እጅግ ውድ ቤቶችን አካቶ የሚሰራ በከተማ ውስጥ ሌላ ከተማ ፤ ኢትዮጵያዊያን ሳይሆኑ ኢትዮጵያን የሚገዙ ብቻ የሚኖሩበት ከተማ እየገነባ ነው።

ይህ ቤተመንግሥት ድንገት መፈንቅለ መንግስት ቢያጋጥም በምድር ውስጥ የሚያሾልክ ዋሻንም ከመሬት በታች እየተገነባለት ነው ። ቤተመንግሥቱ በአለም ላይ አለ በተባ የደህንነት ቴክኖሎጂ እጅግ በሰለጠኑ የደህንነት ሀይሎችም እንዲጠበቅ ይደረጋል።

የኢትዮጵያ አጠቃላይ አመታዊ በጀት 17 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ይህ ፕሮጀክት ብቻውን 10 ቢሊዮን ዶላር ቅርጥፍ አድርጎ ይበላል። ያ ማለት የሀገሪቱን አጠቃላይ በጀት 59% ያክልን ይወስዳል ማለት ነው።ብልፅግና ይህንን ፕሮጀክት በዋናነት ከኢማራት በሚገኝ ድጋፍ የሚሰራ ሲሆን ለዚህም ኢትዮጵያን ለኢማራት ቀብድ አሲዟል።

ከዚያ ውጭ ብልፅግና የተለያዩ ባለሀብቶችንና ድርጅቶችን በግድ እያስከፈለ ሲሆን ይህን በማያደርጉ ላይ ከገበያ የማስወጣት ስራም እየሰራ ይገኛል።
ቤተመንግስቱ ከሚያርፍበት ከየካ ክፍለከተማ የተፈናቀሉ በመቶሺህ የሚቆጠሩ ነዋሪዎችም ብሔራቸው እየተለየ አማራ የሆኑት ወደ ደብረብርሃን ኦሮሞ የሆኑት ደግሞ ወደ ወለጋ እንዲሄዱ ተደርገዋል።
የአብይ አህመድ ጫካ ቤተመንግሥት በጀት 5 የህዳሴ ግድቦችን በመቶ የሚቆጠሩ ኢንዱስትሪዎችን መክፈት ይቻለዋል።
ኢትዮጵያ ከ IMF ለመበደር እየለመነች ያለቺው 3.5 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ይህም አብይ አህመድ ለቤተመንግሥት እያወጣው ያለውን ውጪ 1/3ኛ ብቻ ነው የሚሆነው። ይሁንና IMF የብር ዋጋ ከዶላር አንፃር እንዲወርድ ካላደረግሽ አላበድርም በማለት ኢትዮጵያን እምቢ ብሏል።
በአብይ አህመድ አነሳሽነት ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ አዲስ አበባ ቦሌ ላይ እየገነባው ያለው ቤተመንግሥት ብቻውን አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚፈጅ ሲሆን በዚህም በአለም ላይ የሚበልጠው የእንግሊዙ ቡኪንግሀም ቤተመንግስት ብቻ ነው።

40 ሚሊዮን ዶላር እዳዋን መክፈል ያልቻለች ሀገር ፤ ከ 20 ሚሊዮን በላይ ህዝቦቿ በረሀብ ውስጥ እየኖሩ ባሉባት ሀገር ፤ ከአድስ አበባ ውጭ በሁሉም አቅጣጫ ሰቅጣጭ ጦርነትና የጅምላ ግድያ ባለባት ሀገር ፤ መንግስት ሰራተኞቿ በልተው ማደር በማይችሉባት ሀገር ፤ ከ 3 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ ጎዳና ላይ በሚኖሩባት ሀገር ፤ የኑሮ ውድነቱ የስራ አጥነቱ ህዝቡን እያስለቀሰ ባለባት ሀገር ማንም ሀገር ያላደረገውን 10 ቢሊዮን ዶላር አውጥታ ቤተመንግሥት እየገነባች ነው ብንባል እንደት አድርገን ልንቀበል እንችላለን ?? ያው ለነገሩ ባንቀበልስ ምን ምን ታመጣላችሁ ብሎን የለ !!

እንደዚህ መንግስት ህዝብ የናቀ በህዝቡ ሰቆቃ ያላገጠ ያፌዘ ጨካኝ መንግስት አይቼ አላውቅም።

ኢትዮጵያ የቁልቁለት ጉዞዋን ተያይዛዋለች።
መሪዎቿ ግን የራሳቸውን አለም እየገነቡ ነው።

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
" ኑሮ የከበዳቸው የመንግስት ሰራተኞች የምሳ ሰአትን በቤተ እምነቶች እያሳለፉ ነው "
ይላል የሪፖርተር ዘገባ ። ዘገባው በንኡስ ርእሱም " የቤት ኪራይ መክፈል ያልቻሉም ተደብቀው ቢሮ ውስጥ እያደሩ ነው " ይላል።

ብዙ የመንግስት ሰራተኞች ከስራ ሲወጡ ማንነታቸውን ቀይረው ልመና ላይ ጭምር ተሰማርተዋል። የዩኒቨርስቲ መምህራኖች ራሳቸውን በምግብ መቻል ባለመቻላቸው ዩኑቨርስቲዎች ምገባ እየጀመሩ ነው ።

ከዚህ በላይ የአንድ ስርአት ውድቀት ማሳያ የለም። ይህንን መራር ውድቀት የውሀ ፎንቴንንና የሳር ፓርክ ስለሰራህ አትሸሽገውም።

የሀገሪቱ ዋና ዋና ሴክተሮች የቁልቁለት ጉዞውን አፍጥነውታል። የትምህርት ስርአቱማ ሙቷል ማለት ይቻላል።

ብልፅግና ሀገሪቱን አሪፍ አድርጎ እያወላለቃት ነው !

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት የሞቱ የሀጂ ተጓዦች ከ 900 ማለፉ ተገለፀ።
ከ 46 ድግሪ ሴንቲግሬድ በላይ ሙቀት ያስተናገደቺው ሳኡዲ አረቢያ በሙቀቱ ምክንያት የሟቾች ቁጥር እያሻቀበ ይገኛል።
እስካሁን 922 ሁጃጆች መሞታቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 600 ዎቹ ሁጃጆች ግብፅ ናቸው።
የሙቀቱ መጠን መካ ላይ ከ 51.8 ድግሪ በላይ እንደደረሰም ተገልጿል።

ከግብፅ በመቀጠል ኢንዶኔዥያ ፤ ህንድ ኢራን የመሳሰሉ ሀገራት ከፍተኛ ሁጃጆች የሞቱባቸው ናቸው።
ሳኡዲ አረቢያ ሙቀቱን ለመቆጣጠርና በሁጃጆች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዳያደርስ አሉ የተባሉ ቴክኖሎጂዎችን ሁሉ የተጠቀመች ቢሆን ከአቅም በሗላ በሆነ ሁኔታ የዚህ ሁሉ ተጓዦች ህይወት ሊያልፍ ችሏል።

ሌሎች ሟቾችንም የመፈለግ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

👉 t.me/Seidsocial
የእስራኤሉ መከላከያ ሚኒስትር ቃልአቀባይ ዛሬ ለእስራኤል አስደንጋጭ የሆነ መግለጫ ሰጥተዋል ለመሆኑ ምን አሉ ? ኔታኒያሁ ብቻውን እየቀረ ይሆን ?
የሂዝቦላሁ መሪ ሀሰን ነስረላህ የጦርነት አዋጅና የሂዝቦላህ የደህንነት መረጃ ስለምን እስራኤልን አስደነገጠ ?
ቆጵሮስ ምን ነካት ?

ሁሉንም ስለጋዛ የተሰሙ አዳድስ መረጃዎችን ተከታተሉኝ

https://youtu.be/vQBB8r3klhU?si=B57xrWMUTbBx8aI-
ሲሪል ራማፎዛ በድጋሜ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት በመሆን ቃለመሀላ ፈፅመዋል።
ፕሬዚዳንት ራማፎዛ ምንም እንኳ ፓርቲያቸው ANC መንግስት መመስረት የሚያስችለውን ድምፅ ማግኘት ባይችልም ምርጫውን በአሸናፊነት ማጠናቀቁ ይታወቃል። እናም ከ DA ፓርቲ ጋር ጥምረት በመፍጠር በቀጣይ ደቡብ አፍሪካን የሚመራ ይሆናል።

ፕሬዚዳንት ራማፎዛ በቃለመሀላቸው ወቅት በገቡት ቃል አድስ የከፍታ ምእራፍ ለደቡብ አፍሪካ ለመክፈት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።
ፕሬዚዳንት ራማፎዛ በፍልሥጤም ጠበቃነታቸው የሚታወቁ ሲሆኑ እስራኤልን በአለምአቀፉ ፍርድቤት በዘር ማጥፋት ወንጀል Genocide ከሰው እየተሟገቱ ይገኛሉ።

👉 t.me/Seidsocial
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን በሰሜን ኮሪያ የተደረገላቸው አቀባበል እጅግ ልዩ ነበር።
እንደዚህ አይነት ወታደራዊ ትርኢት አስፈሪ የወታደር ሰልፍ አንድን መሪ ለመቀበል ሲደረግ ምናልባትም ፑቲን የመጀመሪያው ሳይሆኑ አይቀሩም።

ፑቲን ከኪም ጆንግ ኡን ጋር ባደረጉት የጦር ስምምነት ከሁለቱ ሀገራት አንደኛው ላይ ወታደራዊ ጥቃት ቢፈፀም ሁለቱም ላይ እንደተፈፀመ እንደሚቆጠርና ሁለቱም በጋራ ጦርነት እንደሚያውጁ የሚያትት የጦር ስምምነት ተፈራርመው ነው ፕሬዚዳንት ፑቲን የሰሜን ኮሪያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው የተመለሱት