Seid Social
11K subscribers
2.58K photos
463 videos
6 files
1.7K links
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል
Download Telegram
ለአለም መርገምትን አውርሰው ያለፉት የባጢኒያ ሺአዎች !! Assassination and Mafia መነሻቸው !
የሀሰን ሳባህ በደም የተጨማለቁ እጆች ሲታወሱ !

ጊዜው በአባሲድ ኸሊፋና በሰልጁቅ ሱልጧኔትነት ጊዜ ነው ። በአባሲድ ኸሊፋ ስር ሱልጁቅ ሱልጧኔት አለመል ኢስላምን ሲመራ በነበረበት ወቅት ። ታላቁ አሊም አንነይሳቡሪይ ሶስት ሰዎችን ጠሩና ለታላቅ ኢስላማዊ ሀላፊነት አጯቸውና ቃል አጋቧቸው እነርሱም ኒዟመል ሙሉክ ፣ ሀሰን ሳባህና ታላቁ ሊቅ ኡመር ኻያም ነበሩ ።

ግና ሀሰን ሳባህ በኒዟመልሙሉክ ይቀና ነበርና እርሱን ለመግደል መንቀሳቀስ ጀመረ ። በይፋ ሙስሊም መስሎ በድብቅ ደግሞ ባጢኒያ ሆኖ የሰልጁቅና የአባሲድ ባለስልጣናትን ማሳደድ አሳዶ መግደልም ተያያዘው ። ባጢኒያነት ስውርነት ነው ። ባጢኒያዎች ቁርአን ሁለት ትርጉም አለው ብለው ያምናሉ አንዱ የዟሂር ትርጉም ሲሆን ይህም ቁርአን ከላይ በቀጥታ ያለው ትርጉም ነው ። ሌላኛው ትርጉሙ ደግሞ የባጢን ትርጉም ነው ። ይህ ለባጢኒ ኡለሞች እንጅ ለማንም ያልተገለጠ ማንም ምንም ቢደክም የማያገኘው ከፈጣሪ በቀጥታ በሚደረግ ግንኙነት የሚገኝ ብቻ ። ልክ እንደ አሁኑ የፕሮቴስታንት ሀሰተኛ ነብያት በሏቸው ።

እናም በባጢኒ ሀራሞች ሁሉ ሀራም ሀላሎች ሁሉም ሀላል አይደሉም ። አንድ መጥፎ ነገር መጥፎ የሚባሉ ለተመልካቹ ሊሆን ይችላል በባጢን ግን የተፈቀደ ይሆናል ። ሌላው መገለጫቸው አንድ ሰው የባጢኒ ኢስማኢሊያን ለማስፋፋት ተልእኮውን ለመወጣት ምንም ማድረግ ምንም መሆን ይችላል ። ክርስቲያን መሆን ይችላል ፓጋን መሆን ይችላል ሱኒ መሆን ይችላል ግና ብቻ የተባለለትን አላማ ተመሳስሎ መግደል አለበት ኸላስ !

በኢስላም ታሪክ ከታዩ አስቀያሚ ግሩፖች ውስጥ ናቸው እነዚህ ባጢኒዮች ። እናም እነ ኒዟሙል ሙሉክን ጨምሮ በርካታ የኢስላም ስብእናዎችን መግደል ተሳካላቸው ኢስላሙ አለምን አዳከሙት ሰልጁቅ ኢምፓየርን ገዘገዙት ። ሱልጧን መሊክሻህ ሊያጠፋቼው ቢሞክርም ፍፁም ከማንም ጋር ተመሳስለው በመኖራቸው ጭራሽ አስቸጋሪ አደረገበት። መሊኽ ሻህ ሲሞት ልጁ አህመድ ሳንጃር ዋና መቀመጫቼውን አላሙትን አፈራርሶ ሀሰን ሳባህን ሊገድለው ሲል የሳንጃርን አገልጋይ ሴት አንገቷ ላይ ስለት በመደገን ከተንቀሳቀስክ አንገቷን እቆርጠዋለሁ በማለቱ እሷን መያዦ አድርጎ አምልጧል ።

#Assassins !

በሀሰን ሳባህ የሚመሩት ባጢኒዎች ለአለም ካበረከቱት ነገር አንዱ እራስን አጥፍቶ ማጥፋት ነው ። ለዚህም ባጢኒዎች መግደል የማፈልጉትን ባለስልጣን ገድለው ራሳቸውን ይገድላሉ ። አንዳዴም ምስጢር እንዳያወጡ ምላሳቸውን ተቆርጠው ወደ ተልእኮ ይዘምታሉ ። ከሀሰን ሳባህ ለዚህም ጀነት ቃል ይገባላቸዋል ። የውሸት የቅጥፈት ጀነት !!
ታድያ ሀሰን ሳባህ ይህን አይነት ጭካኔ እንድሂ እንዲወስኑ አያደርጋቸውም ። ከፍተኛ የሆነ ሀሽሽ ያስወስዳቸዋል ። በሀሽሽ ከደነዘዙ በሗላ የፈለገውን ነገር ያሰራቸዋል ። ፈንጆችም ባጢኒያዎችን Hashashin ሲሉ ጠሯቸው ። Hashashin ከሚለው ቃልም Assassin የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል ተፈጠረና የእነርሱን ተግባር መፈፀም Assassination ተብሎ ተጠራ ። አይገርማችሁም ??!!
እናም ራስን ሰውቶ የፈለጉትን ዝነኛ ሰው አዋቂና ባለስልጣን መግደል ከነርሱ ተወሰደ ማለት ነው ።

#Mafia

ሌላው ባጢኒያ ሺአዎች የፈጠሩት ነገር ማፊያነትን ነው ። ታላቁ ሱልጧን ሰላሂድን አልአዩቢ ፋጢሚዶችን አሸንፎ ግብፅን ሲቆጣጠር የባጢኒ ሺአዎች ወደ ጣሊያኗ የሲሲሊ ከተማ ፈለሱና እዚያ በድብቅ የራሳቸውን የምስጢር እንቅስቃሴ ፈጠሩ ። ያም መግደልን መዝረፍን ማገትን እና ሌሎችም ዘግናኝና አስፈሪ እርምጃዎችን ይወስዱ ነበር ። እንቅስቃሴያቸውንም #መህፊያ ብለው ጠሩት ። በአረብኛ ምስጢር እንደማለት ነው ። እናም መህፊያ ከሚለው ቃል ማፊያ ተወለደ ማለት ነው ። ጣሊያንም ከዚያ ጀምሮ ማፊያዎች የተወለዱባት ሀገር ሆነች ። እናም በሱሰኝነት የማነዳው ማፊያ በዚህ መልኩ አለምን ተዋወቀ ።

ባጢኒዮች አብዛኛው ኢላማቸው ሙስሊሞች ነበሩ ። ለዚህም ከመስቀል ጦረኞች ጋር አብረው ይሰሩ ነበር ። የመስቀል ጦረኞች በባጢኒያዎች በጣም ይደነቁና ይገረሙ ነበር ። ብዙ የጭካኔ ተግባሮቻቼውንም ኮረጄው ወስደዋል ።
ባጢኒያ ወታደሮች ተአማኝነታቸውን ለሰይዳቸው ሀማሳየት የራሳቸውን አንገት ጭምር ይቀሉ ነበር ። ለሀሰን ሳባህ ታማኝነት መተኪያ የሌለው መስፈርት ነው ። ሀሰን ሳባህ ሁለት ልጆቹን ሳይቀር የገደለ ጉድ ያለው ሰው ነበረ ።

ባጢኒያዎችን ከፍተኛ ውድመት አድርሶ የበታተናቸው የሞንጎል ጦር ነበር ። በሁላጉ ኻን የሚመራው የሞንጎል ጦር ባጢኒዎችን ደምስሶና በታትኖ የተረፉት ጥቂቶች ወደ አዘርባጃን እና አናቶሊያ እንዲሰደዱ አድርጓቸው ነበር ።

የኢራኑን ሳፋቪድ ዳይናስቲን የመሰረተው ኢስማኢልም አስተምህሮቱን የወሰደው ከነዚህ ከሞት ከተረፉ ባጢኒዎች ነበር ። ባጢኒዎች ከኢስላም ያፈነገጡ ቡድኖች ነበሩ ።

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial