ISLAMIC SCHOOL
12.6K subscribers
371 photos
166 videos
7 files
1.07K links
ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group
Download Telegram
እጠብቅሻለሁ ፨
አሞሽ ነው ተኝተሽ ስጣራ ዝም ያልሽ
እማ ልደግፍሽ እጄን ያዢ ተነሽ
ወይ በይኝ ስጠራሽ ልጄ አለሁ በይኝ
ድምፅሽን አሰሚኝ በጣም ነው የራበኝ
ልጥባ ጡትሽን ስጪኝ
በለጋው እድሜዬ ሜዳ ላይ አጣይኝ
እርቃ ሄዳለች በቃ ተዋት አሉኝ
አሰማም ሞታለች ሰዎች ሁሉ ሲሉኝ
አልገባኝም እኔ እማ እስኪ አስረጂኝ
ምን ማለት ነው ሞት?
ተኝቶ መነሳት?
ወይስ በዛው መቅረት?

። "ጥሪኝ" እማ
አትሙቺ እማ ልሙትልሽ እኔ ፣
ከሠፈሩ ሳጣሽ ይባክናል አይኔ ፣
እስኸመቼ ልኖር ናፍቆት ተሸክሜ ፣
ትዝታሽ በረታ ጠናብኝ ህመሜ ፣
..........................እማ
አረ መፈን ሆንሽ ፣
አረ ምን ነካሽ ፣
ነይ እንኳን ሣትይኝ ምነው መሄድሽ ፣
ነይ እንኳን ሣትይኝ ለምን ሄድሽና ፣
ጭር አለብኝ እኮ ከተማው ጎዳና ፣
...........................እማ
ያን ሁሉ ውለታ ጥለሽብኝ ሄድሽ ፣
ከቶ እንዴት አርጌ ልመልስልሽ ፣
እኔ ልቅደምና አንቺ ተመለሽ ፣
.....................እማ
አንቺ ብቻ ጥሪኝ እኔስ እመጣለሁ ፣
ካንቺ ተለይቼ እንዴት እኖራለሁ ፣
እማ አንቺ ነበርሽ እኮ ማድመቂያ ቀለሜ ፣
አሁን ምን ቀርቶኛል አጭር ነው እድሜዬ ፣
እናም ስሚኝ አማ ፣
ጥሪኝ ካለሽበት ከተማ ፣
እመጣልሻለሁ ተጠቅልዬ ሸማ ፣
እማ ባልይዝ እንኳን ሻማ ፣
አንቺ ካለሽልኝ አልፈራም ጨለማ ፣
......................እማ
ብርሀን ባይኖረው መግቢያ ድንበራችን ፣
እኛን አይለየንም አንድ ነው ውላችን ፣
እና እማ ይህ ደብዳቤ ሢደርስ አንቺ ጋራ ፣
ጥሪኝ እንዳትረሽኝ አደራ አደራ ፣
እጠብቅሻለሁ ቆሜ ከተራራ ፣
...........""""""""""""""..........
.........................እማ
በቃ ይበቃኛል ልንጣ ካለሽበት ፣
እኔንም ይውሠደኝ አንቺ ከሄድሽበት ።
ያለ እናት አለም ጨለማ ናት
እናቱን የሚወድ እባክወ ሼር



@Islam_and_Science @Islam_and_Science
ፈራሁ

ለምን ይሆን እማ ልቤ እንዲህ የፈራው
ብዙ እያለምኩኝ ግን ከንቱ የሆነው
እስኪ ለምን ይሆን ለማንስ ልናገር
ፈራ ተባ እያለ ልቤ የሚያንገራግር

ፈተናየ በዝቶ ለማለፍ ስነሳ
ደሞ ትዝ ይለኛል ላለፈው ያለፈው ጠባሳ
እማ ዋናው ህልሜ
ሁሌም የማስበው ደግሜ ደግሜ
ካንች ጎን መኖር ነው ህመምሽን ታምሜ

እቅፍሽ ውስጥ መግባት እንደ ልጅነቴ
ሁሉን እረስቸ ያንን ማንነቴ
ይቅርታ ልበልሽ እማ ውዷ እናቴ
ፍርሀቴም ይወገድ ጭንቀቴም ይፈታ
እማ አይዞሽ በይኝ ልተንፍስ ላንዳፍታ
ሁሌም እወድሻለሁ የኔ ውድ ስጦታ !!!!

ISLAM AND SCIENCE
══ •⊰✿🍃✿⊱• ══

🎖SHARE🎖


@Islam_and_Science @Islam_and_Science
#የረሱል የትዳር ሂወት
👑ክፍል ሶስት~
:
📩ጋብቻ የሰላም የጤና እና የመረጋጋት ምንጭ እንደሆነ ሁሉ በተቃራኒው ትዳር አልባነት ደግሞ ለእብደት ከሚዳርጉ መንስኤወች አንዱ ተደርጎ ይቆጠራል( ኢማሙ አልጁወይኒይ አልሻፊኢ)"
-->ነብዩ ሙሐመድ ሰ ዐ ወ መጀመሪያ ለነብይነት በተመረጡ ሰአት ከጎናቸው የቆመችው ኸድጃ ረ ዐ ነች በገንዘቧ ረድታቸዋለች ..ሰወች ሲያስዋሿቸው ተቀብላቸዋለች .. ሰወች በሸሿቸው ግዜ ከጎናቸው በመሆን እረድታቸዋለች .. ነገር ግን ኸድጃ ስትሞት ረሱል በጣም አዝነው ነበር ከሞተች ሞተች ነው ሴት ቢሄድ ሴት ይተካል አላሉም እንደውም በጣም ከማዘናቸው የተነሳ አመቱ የሀዘን አመት በመባል ይታወቅ ነበር ......
🛍 ኸድጃ ከሞተች በኃላ ሰወች ጋር ሲሆኑ በተደጋጋሚ ያነሷት ነበር ጓደኞቿን ይንከባከቡ ነበር ዓዒሻ እስክትቀና ድረስ ....
=>ወንድሜ ሆይ ልብ በል👓 የነብይህን መንገድ ተከተል እሳቸውን ከተከተልክ ታተርፋለህ እንጅ አትከስርም ረሱል ሚስቶቻቸው በሂወት ሳይኖሩ ምን ያክል ይወዷቸው ጓደኞቻቸው ሳይቀሩ ይንከባከቡ እንደነበር ...
አንተ ግን በሂወት እያለች እንኳ ምን ያክል ለሚስትህ ቦታ ትሰጣታለህ ?
⛔️ወንድሜ ሚስትህ ያገባሀት እንደ እራስህ ልታያት እና ልትከባከባት እንጅ!ይሄን ስላልሰራሽ የተለያየ ምክናየት እየደረደርክ ሌላ ላገባ ነው ልደርብብሽ ነው እያልክ የምታስፈራራት የቤትህ ሰራተኛ አይደለችም❗️..
↪️እወቅ ሁለተኛ ለማግባት እኮ እንደ ማንኛውም ኢባዳ ሸርጥ አለውጂ! ምግብ ጨው ባነሰው እና ምሳ በወቅቱ ባልቀረበ ቁጥር ሌላ ላገባ ነው የሚል ነጠላ ዜማህ አይደለም !;
=> አንችም እህቴ በነጋ በመሸ ቁጥር ከአቅሙ በላይ የሆኑ ነገሮችን እየጠቀሽ መብቴ ነው ካልሆነ እከስሀለሁ እያልሽ እየነዘነዝሽ ሸሪአ ያስቀመጠልሽን ድንበር አትለፊ👀
🔮ነብዩ ሙሐመድ ሰ ዐ ወ ሚስቶቻቸው የተለያየ ህመም ይሁን የተለየ የሀዘን ስሜት ላይ በሚሆኑ ሰአት እጃቸውን ይይዙና በፍቅር ቃላት አይዞሽ ከጎንሽ ነኝ እያሉ ያበረታቷቸውና // ያፅናኗቸው ነበር ...
🎁ባሁን ሰአት ሚስቱ እቤት በምትታመም ሰአት ምንም ትኩረት የማይሰጡ እንዳሉ ብዙወቹ የምናውቀው የምንሰማው ነው እየተደረገም ያለ ነገር ነው ሀቂቃ መሆን ያለበት አንድ ሰው እንኳን በትዳር አብረው እየኖሩ አይደለም እንኳን ኢስላም አዞን እንኳን እረሱል አዘው አይደለም እንደ ሰብአዊነት አንድ ሰው ሲታመም ሌላኛው ለሌላኛው ሊያዝን ይገባል.. ግድ ነው ።
💐ረሱል በምድር ያሉትን ፍጥረታት እዘኑላቸው በሰማይ ያለው ያዝንላችሆል ብለዋል
ከሚስቱ ጋር በኒካህ ተሳስሮ እየኖረ አላህ በቁርአን ላይ እርህራሄና እዝነትን ውዴታን አስቀምጧል
#Part4
ይቀጥላል


🎖SHARE🎖


@Islam_and_Science @Islam_and_Science
Forwarded from ISLAMIC SCHOOL
🎈🎁ውዷ ሙስሊሟ እህቴ ብቻ!!!!!🎁🎈





ረገጥ አድርጊያት 👉Read more..........
//""""" አባ """""//

የአባት ናፍቆት ያለበት ብቻ
በጣም ናፍቀከኛል
ካንተ እርቆ መኖር እጅጉን ከብዶኛል
ያኔ ትዝ ይልሀል አባ !
ስትወጣ ስትገባ ካንተ መራቅ ከብዶኝ
በትንሽ ትልቁ ያኔ ስትሸውደኝ
እደለል ነበረ ብስኩት ከረሜላ


ጣፋጭ ነገር ሳገኝ
.......ምናለ እላለሁኝ ያ ጣፋጭ ልጅነት
ባይሄድ እንደ ድንገት
ዛሬ ላይ ሆኘ ግን መች እሰቃይ ነበር
ባንተ ሀሳብ ናፍቆት
አላህ ሆይ አባቴን አደራ
ሰላም ፍቅር ደስታ ሁሉንም
አብዛለት ከልጆቹ ጋራ
አንዳንዴ ሳስበው በጣም እገረማለሁ
በብዛት የሚፃፍ ስለናት ብቻ ነው
እናት ከሌለች ግን የሷ ምትክ ማነው


እናቴን ነው እንጅ አባቴን አልወድም
የሚል ብዙ ሰው ነው
አባት ካለህ ኩራ አባት ከለህ ዝራ
አይደል የሚባለው
ህይወት ማጣፈጫው መድመቂያ
መክበሪያው አባት ብቻ እኮ ነው

እናም አባይየ በስላም መጥቸ አይንህን እስካየው
እውነቱን ልንገርህ በጣም ጒጉቻለሁ
ሰላምህ ይብዛልኝ በጣም እወድሀለሁ! !!!!!!!!!



@Islam_and_Science @Islam_and_Science
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY
ሰበር ዜና ..ደሴ ከተማ ቁርአን እንዳይቀራ ቁርአን ቤቱ ታሸገ፡፡ አሁንም የመደመር ትርጉም ያልገባቸዉ ደሴን በመበጥበጥ ላይ ናቸዉ ..ከመቅሪብ ሶላት ቡሀላ አረብ ገንዳ ሰዉ ተናዶ ተሰብስቦ ነበር..የሚገርም ነዉ አሁንም ልጆች ቁርአን አይቀሩም እያሉ አህባሾች አስቸግረዋል፡፡ ለመንግስት ደህነነቶች የደሴህዝብ አሳዉቃል
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY
የደሴዉ አረብገንዳ መስጊድ ባለ አምስት ፎቅ መስጊድ ሲሆን ግንባታዉገና ያልተጠናቀቀ ነዉ፡፡ ግን አሁንም አህባሾች ደሴን እንደበፊቱ ለማበጣበጥ ተነስተዋል፡፡ ማንኛዉም የደሴ ሙሰሊም ህዝብ ማክሰኞ ሁለት ሰአት አረብ ገንዳ መስጊድ እንገኛኝ፡፡ ወላሂ ይገርማል ልጅ ቁርአን አይቅራ እየባለ ፡፡ማክሰኞ የደሴ ልጆች እንገናኝ
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY
አሁን ከመቅሪብ ሶላት ቡሀላ ሰዉ ተሰብስቦ ነበር፡፡ ግን መረጋጋቱ ጥሩ ነዉ ስሜታዊ አንሁን በማለት ኮሚቴዉ ለመንግስት አካል አሳዉቀናል፡፡ ሰኞ መፍትሄ አንሰጣለን መንግስት ያለ ሲሆን ማክሰኞ ሙስሊሙ ሁሉም አረብ ገንዳ መስጊድ እንድንገናኝ ብለዋል ኮሚቴዎቹ፡፡ የአላህ አረ ደሴ ይገርማል ልጅ ቁርአን አይቅራ😔😔
#የረሱል #የትዳር #ሂወት🌹
--#ክፍል# አራት4⃣
🔺ረሱል ሰ ዐ ወ በሀያታቸው ከኸድጃ ሌላ ማንንም አላገቡም ነበር ..ኸድጃ በሂወት እስካለች ማለት ነው ..ከሞተች በሆላ ነው ሌላ ያገቡት ከኸድጃ ጋ ማንም ጣውንት ሁኖ የኖረ የለም ነበር
ያ ከመሆኑ ጋር ግን ዓዒሻ ረ ዐ በጣም ትቀና እንደነበር ትናገራለች ለምን ቢባል ሁሌም እረሱል ኸድጃ ይሄን ብላ ነበር ኸድጃ ይሄን አድርጋ ነበር ይሉ ስለነበር ነው ምክናየቱም ሀቢቢ ረሱል ሰ ዐ ወ ውለታን እንድህ በቀላሉ የሚረሱ ባል አይደሉምና እህት አለምዬ አንችም ለባልሽ ተወዳጅ እና የማትረሽ ምርጥ ሚስት እንድትሆኚ ከታች የተዘረዘሩትን ምረጥ ባህሪወች ተላበሺ/ይኑርሽ..።
1~ምንግዜም ውበትሽን በመጠበቅ ለዘላለም ባልሽን አስደስች..
2~ባልሽ አላህን በማያስቆጣ ነገር ታዘዘሽ ቅን ታዛዥ መሆን አለብሽ.።
3~ልጆችሽን በመልካም ስነ ምግባር አሳድጊ..
4~ምንግዜም ባልሽን በፈገግታ እና በመልካም ንግግር ተቀበይው..
5~ለባልሽ ቤተሰቦች ቅን አመለካከት ይኑርሽ ፤ ለቤተሰቦቹ የምትራሪ፤ የምታዝኒ ፤ መሆን አለብሽ..
6~አንደበትሽን የምትጠብቂ ፤ በንግግርሽ እና በተግባርሽ የባልሽን ውስጣዊ ስሜት የማታቆስሊ ሁኚ.
7~ባልሽ ለዋለልሽ ውለታ አመስግኚው..
የረሱል ለኸድጃ ያላቸው ፍቅር ወደር የለውም በችግር ግዜ ተጋብተን በሀብት ስንበሸበሽ ሚስት የምናማርጥ ወንዶች አላህን እንፍራ በአሁኑ ሰአት ባል እና ሚስት በችግር ግዜ ይጋባሉ ሀብት ያገኙ ግዜ ባል ሚስቱን አይንሽን ላፈር ብሎ ምንም ከእሱ ጋ ችግር ፤ መከራ እና ስቃይን እንዳላሳለፈች ይረሳና ወደ ሌላ ሴት ይሄዳል ሀብታም ከሆንክ ሌላ አታግባ እያልኩ አይደለም..
ነገር ግን የችግር ግዜ ሚስትህን ሀብት ስታገኝ አትተዋት ልክ እንደበፊቱ ውደዳት እያልኩህ ነው..
•°•ሁሌም ቢሆን ወደላይ ስንወጣ ወደታች መውረድን መርሳት የለብንም፤ ወደታች ስንወርድ ደግሞ ወደላይ መውጣትን መርሳት የለብንም ......
#Part 5⃣ይቀጥላል


🎖SHARE🎖


@Islam_and_Science @Islam_and_Science
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY
መገን አረብገንዳ
====~~===

ለካስ እናንተዬ…
የነበር ሲያወሩት ይመስላል ያልነበር

በፊት አረብገንዳ መስጊድ እንዴት እንዴት ነበር
አያልቅም ነበረ ኡለማው ተቆጥሮ
አያባራም ነበር ኢልሙ ተዘርዝሮ
የሰጋጁ ብዛት ለጉድ ተትረፍርፎ
ቁሞ ላስተዋለ ኸልቁ ተሸክፎ
ይመስል ነበረ መስጊድ እሱ ብቻ
ይሄው ዘሬ ሊሆን የጃሂል ስልቻ


ከሃጂ አህመድ ኢብራሂም እስከ ሸህ አደም
ምእመኑ ነበረው የበቃ ኢማም
ለዲናቸው ሲሉ እጅጉን የለፉ
ሃቅን የሚያነጥሩ ባጢል የሚያጠፉ
የሸህ ሶሌ አዛን ደርሶ ሲያስተጋባ
የድምፃቸው ለዛ የነበረው ሀይባ
እንኳን በሙስሊሙ በሌላው ህዝብ ዘንድ
ነበረ በክብር በጣም የሚወደድ

ከሚንበሩ አንስቶ እስከ ዋናው በር
በየጥጋጥጉ በምሶሶው ስር
የሚዘራ ሀዲስ የሚወቃ ተፍሲር
እንደዛሬው ሳይሆን አጃኢብ ነበር
ፊቂሁ ሲሞጠል ተውሂዱ ሲቀራ
ነህዉ ሲተነተን ሶርፍ በውቀት ሲብራራ
ቋንቋ(ሉጔ) ስትፈተሽ ሲወሳልን ሲራ
ቁርአን ሲተሀፈዝ ከተጅዊዱ ጋራ


አቤቤቤቤት…
መድረሳም ነበረ እጅግ የዘመነ
በነኡስዐዝ ሱለይማን እውቀት የተካነ
እጅግ ድንቅ ተቋም አዕላፎች ያፈራ
መሰረት የሆነ ለዲን የእውቀት ጮራ

መገን አረብ ገንዳ የኸይራቱ ማሳ
የነበር ኡለማ የነበር ደረሳ
የነበረ አኽለል ኸይር እኮንዴት ይረሳ
የነበረ ጀግና ተተኪ ትውልድ
አኽላቁ ያ‘ማረ ኢስላማዊ ጁንድ
አቤት መናፈቁ የጥንቱ አረብ ገንዳ
ይመጣ ነበረ ለዘያራ እንግዳ

እኩሉ ሊቀራ እኩሉ ሊያቀራ
እኩሌታው ደግሞ ይዞ ሙሀዶራ
ደግሞም ለኢዕቲካፍ ውስጠቱን ሊያጠራ
ዛሬ ግን…
በዚህ የኢልም አምባ ታሪክ ተቀይሮ
ጅህልናና ስልጣን ቦታ ተቆጣጥሮ
መሻኢህ ኡለማን በእብሪት አባሮ

ያቃጥለን ይዟል በትዝታ ፍም
ያረበልአለሚን ያሃዩ ያቀዩም
ያማሊከልሙሉክ ያረህማን ያረሂም
ያመናን ያሰታር ያአሃድ ያሶመድ
ያጀሊል ያከሪም ያወዱድ ያመጂድ
አሏሁ ረበና ሁሉን ለመፈፀም ይቻልሃልና
ያንን መልካም ጊዜ መልስልንና

ጀማ‘ው ተሰብስቦ ናፍቆቱን ይወጣ
በ‘ኛ ወንጀል ብዛት ያረቢ አትቆጣ
ዛሬም ስጠንና የማርታህን እጣ
ደግሞም አዘውትረን ከኸይር እንዳንወጣ

ስለ አረብ ገንዳ መስጊድ ምን ያህል ያቃሉ??
☞አረብ ገንዳ መስጊድ ሁላችንም የምናቀዉ የምንወደዉ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ሸህ አደም ጋር ዲኑን የተማረበት
☞በአረብ እና Nile sat በ ኢቅራዕ ቲቪ በፊት ተቀርፆ አንጋፋዉ መስጊድ በኢትዮጲያ ተብሎ በአለም ታሪኩ የተወራለት
☞በፊት የነበረ የዳኢ እና የተማሪ ብዛት ..ረመዷን ሲደርስ ከተለያዩ ሀገራት መጥተዉ ረመዷንን የሚያሳልፉበት...የደሴ ተወላጆችም ፆመኛን ለማስፈጠር መቅሪብ ሶላት ቡሀላ ከመስጊድም አልፎ ምግብ ቤት እስከሚመስል ሰዉ ለኸይር ስራ የሚሽቀዳደሙበት ነበር
አሁንስ ምን ላይ ነዉ ብትሉ
☞መስጊዱ አሁን አሰራሩ ከኢትዮጲያ አንደኛ ሲሆን ባለ አምስት ፎቅ መስጊድ ነዉ በጣም ሰፊ ነዉ ሽንት ቤቱ ለራሱ በጣም በሚያምር ሁኔታ የተሰራ ነዉ ግን ገና የመስጊዱ ስራዉ የተሰራዉ 60% አካባቢ ነዉ ገና ለመጨረስ ብዙ ነገር ይቀረዋል አላህ እድሜ ሰጥቶን መጨረሻዉን ያሳየን
☞አሁን ላይ አህቦሻች ከመጡ ቡሀላ መስጊዱን በእጃቸዉ ሲያረጉ ያ ሁላ ጀምአ በማስገረፍ በማሳሰር ከመስጊድ እንዲወጣ አረጉት፡፡ ቁርአኑ ኪታቡ ሁሉም መቅራት ቆመ የደሴ ወጣቶች ከዲናቸዉ በዛዉ እራቁ ለምን መስጊድ ከገባህ ከእነሱ ዉጭ ገብቶ የሰገደዉን ያሳቅቁ ይሳደቡ ነበር፡፡
☞ደግሞ አልሀሙዲሊላህ በዶ/ር አብይ ጊዜ አንድ ሁኑ ሲባል የተማረዉ የነቃዉ የደሴ ከተማ ህዝብ እኛ እንደ እናንተ ዉጡ እናስገርፍ አንልም ..ያለፈዉን አዉፍ ብለናል ግን ለወደፊቱ ተቻችለን ተስማምተን እንኑር ሙስሊም አንድ ነን ቢባል,,,.ባለፈዉ እንደ ሰማችሁት ሸዋበር መስጊድ ሰዉን ደበደቡ

,,,,,አሁን ደግሞ አረብ ገንዳ መስጊድ

☞በጣም ሰፊ መስጊድ ተይዞ የሚሰግደዉ ህዝብ ሶስት ሶፍ
☞ዲናችን እንዴት እንደተዳከመ ለማወቅ ..ያ ደሴ የነበረ ወጣት ለዲኑ እንዳልተጋደለ... ከመስጊዱ ዙሪያ እና አለፍ ብሎ ሴቶች እህቶቻችን ገላቸዉን የሚሸጡበት የዚና መስሪያ መገናኛ ቦታ ሁኗል😔😭😭 ስለሆነም የደሴ ማህበረሰብ ይህን ነገር ማስቆም አለብን ዲኑ ከልባችን አይሙት፡፡

☞ደግሞ ትናንት ህገወጡ መጅልስ ባለፈዉ ሸዋበር መስጊድ ህዝቡን ያስደበደቡት ልጆች የሚቀሩበትን ቁርአን ቤት አይቀራም ተብሎ እንዴት በቁልፍ ቆልፈዉ ማሸግ ምን ይባላል????
☞በሌላም መረጃ አሁን ደሴ ላይ ዳዉዶን ፔፕሲ ያለዉን መስጊዶችን አሽገዋል መንግስት የጉዳዩን አንገብጋቢነት አይቶ ዉሳኔ ይስጠን
ማጠቃለያ ህዝቡ ሲያሽጉ የነበሩት ሶስት ሰዎች ሰዉ እነሱን ተዉ ብሎ በሀይልም እርምጃ ቢሆን አላቃተዉም ግን ከአለፈዉ ታሪክ ደሴን ለማበጣበጥ ስለተነሱ ለመንግስት ለደህንነቶች ወጣቱ አሳዉቋል፡፡ ደህነነቶቹም እንዴት ይህን ይሰራሉ በማለት ሰኞ ጠዋት መፍትሄ ይሰጣሉ..ግን ማክሰኞ ጠዋት ሁላችንም አረብ ገንዳ መስጊድ መስጊድ አምስት ፎቅ በዛም ላይ በጣም ሰፊ ስለሆነ የመጣዉን ሰዉ መያዝ ይችላል፡፡

🌙ያአላህ የአንተን የወደድከዉን ሀይማኖት እስልምና አንተዉ ጠብቀዉ


4another channal👇
@Islam_and_Science

JOIN👇👇👇
@IslamisUniverstiy_public_group
@IslamisUniverstiy_public_group
⭐️⭐️ #አንቺ #የአላህ #ባሪያ #ሆይ ! በዚህ ተግባርሽ አላህን ልትፈሪው ይገባል፡

💐ማግባት የባል መብት (ሃቅ) እንጂ የሚስት አይደለም ፡ ባል
☞ሁለተኛም፣
☞ሶስተኛም፣
☞አራተኛም ማግባት ቢፈልግ ሚስት መከልከል አትችልም ፡፡

💐ይሄን የደነገገው ከሰባት ሰማያት በላይ ያለው (አላህ ሱብሃነሁ ወተኣላ)
ነው፡፡ አላህ ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች የሚበጀውን ያውቃል፡፡
ለዚህም ነው አላህ ይሄን የፈቀደው ለብዙ ጥቅሞች ሲል ነው፡ ከፊሎቹ
ጥቅሞች ለራሷ ለሚስት ሲሆኑ ፡ ...... ከዚህ ሁሉ ዋናውና አሳሳቢው
ነገር ግን ባልሽ ሁለተኛ ማግባቱን መጥላትሽ ይህ በአንቺ ላይ በጣም
ከባድ የሆነ አደጋ ነው ፡
💫💫አላህ በቁርአኑ ላይ ካወረደው ህግ ከፊሉን
በመጥላትሽ መልካም ስራወችሽ እንዳይታበሱብሽ የሚያስፈራ ከባድ አደጋ
ነው፡ ምክኒያቱም አላህ ግልፅ በሆነ የቁርአን አንቀፅ እስከ አራት ድረስ
ሚስትን መደጋገም አዟል ፡፡

💐አላህ እንዲህ ይላል፡-
" ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት፣ ሶስት ሶስትም፣
አራት አራትም አግቡ ፡
[ ምዕራፍ፡ ኒሳዕ፣ አንቀፅ 3 ]
አላህ በቁርአን ላይ ያወረደውን ህግ መጥለት መልካም ስራወችን የግድ
ያሳብሳል፡፡

💫አላህ እንዲህ ይላል፡-
" ይህ እነርሱ አላህ ያወረደውን ስለጠሉ ነው ስለዚህ ስራወቻቸውን
አበላሸባቸው "
[ምዕራፍ፡ ሙሃመድ፣ አንቀፅ
ባልሽ ለማግባት ከፈለገ አትከልክይው

እንዳውም አግባ ብለሽ
አበረታችው፡፡

አሁን በዚህ ሳምንት ኬንያ ሀገር ሴቶች ባል አጣን በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ ስለሆነም እንዴት የኬንያ ሴቶች ሰላማዊ ሰልፍ ወጡ የሚለዉን ማሰብ አለብን

ውበት ሲለካ አራት ሚስት ነው ለካ😉

የተስማማ🤙🤙
የማይሰማማ👌👌

@Islam_and_Science @Islam_and_Science
#የረሱል #የትዳር #ሂወት🎓
#ክፍል ~5⃣🌹
አኢሻ ረ ዐ ከነብዩ ሚስቶችቅናት በአንዳቸውም ቀንቸ አላውቅም በኸድጃ ላይ የቀናሁትን ደግሞም በአካል አይቻት አላውቅም ረሱል ሁሌም የሷን ስም ያነሷት ስለነበር እንጅ ከኸድጃ ሞት በሆላ ከ3 አመት በሆላ ነው እኔን ያገቡኝ አላህም አዞታል በጀነት ውስጥ ኸድጃ ቤት እንዳላት አበስራት ብሎ አዟቸዋል ሌላው ረሱል ሰ ዐ ወ ፍየል ያርዱና ስጋውን በደንብ ይመዳድቡታል ከዛም ለኸድጃ አዟቸዋል ያከፋፍላሉ..
ሰው የእናትና አባቱን ሀቅ ከሞቱ በሆላ ለመቀጠል ማድረግ ያለበት ነገር እናትና አባቱ የሚወዷቸውን ጓደኞች ማስደሰት አለበት የሚስቱንም እንደዛው ረሱል ሰ ዐ ወ ይሄን ያደርጉ ነበር ምክናየቱም ውለታን የማይረሱ ስለነበሩ...
አኢሻ ረ ዐ ከእኔ በፊት የሞተች /የጠፋች አሁን በሂወት የሌለች ምንድነው የዚህን ያህል አላህ ከእሷ የበለጠ እንደ እኔ አይነት ወጣት ተክቶሀል ሌሎችም አሉ እለው ነበር ትላለች ረሱልም ኸድጃ እኮ ሰወች ሲከዱኝ ሲያስዋሹኝ ያመነችኝ፤ ሰወች ሲሰድቡኝ ያከበረች ፤ ሲርቁኝ ፣ ሲያንቋሸሹኝ የቀረበችኝ ናት አላህ ውዴታዋን ወፍቆኛል ብለው ይናገራሉ...
ከዚህ ቂሷ የምንረዳው ነብዩ ውለታን የማይረሱ ባል ነበሩ ስለዚህ ወንዶች የሚስቶቻችሁን ውለታ መርሳት የለባችሁም በተለይ በችግር ግዜ ስራ ወይም ገንዘብ ሳይኖርህ ካገባሀት በሆላ አብረሀት ስትኖር ገንዘብ ስታገኝ ወይም ብትሞት ወይም አንተ ራስህ ንቀህ ትተሀት ሌላ ሚስት ብታገባ እና እሶን ብትፈታት ሌላ ሚሰት ስለቀየርክ እሷን መርሳት የለብህም(ኢማም አህመድ ) በዘገቡት ሀዲስ አኢሻ ረ ዐ ምን ትላለች አንድ ቀን በጣም ቀናሁኝና ምንድነው አንተ ሁሌም ኸድጃ ኸድጃ ኸድጃ ማለት የምታበዛው ምንድነውንጯ የቀላች ባልቴት አላህ ከሷ የበለጠ ተክቶህ ስላቸው
ላ ወላሂ አላህማ ከኸድጃ የበለጠ አልተካኝም አሉ በብዙ ነገሯ አብራኝ ከጎኔ ነበረች ወ ዘ ተ ከሌሎቹ ሴቶች /ሚስቶች ልጅ ሲከለክለኝ ከእሷ ግን ሰጥቶኛል አሉ ሚስት መውደድ፤ ሚስት ማክበር ፤ ሚስትን አለመርሳት የክብር እና የጀግኖች ሰወች ባህሪ ነው
#part 6⃣ይቀጥላል



@Islam_and_Science @Islam_and_Science
#ሴት_ልጅ_የህይወትህ_ወሳኝ_መሰረትህ_ናት!!!
ባንድ ወቅት ባልና ሚስት ይጣሉና ሽማግሌ ይሰበሰባል ከዛም ሁለቱም ችግራችሁን ተናገሩ ሲባሉ ...
#ባል 🗣እኔ ደክሞኝ ከስራ ስመለስ ማረፍ እፈልጋለው ነገር ግን ልጅቷን እያንጫጫች አያሳርፉኝም ...
#ሽማግሌዎቹ 🗣እሱን በመታዘብ "ሌላስ ?"ይሉታል
#ባል🗣 እኔ ከስራ ስመለስ ልጅ ያዝ ትለኛና ወጥ ትሰራለች የልጅ ወተት ታፈላለች... ምናለ ስመጣ ጨርሳ ብጠብቀኝ ተቀምጣ እየዋለች ይላል (በንዴት)
👤ከዛ ሚስትም በሰዎቹ ፊት ይቅርታ ትጠይቀውና አይለምደኝም ብላ ሽማግሌዎቹ እንዲሄዱ ይደረጋል...

💫💫በነጋታውም ሚስት ልጇን ይዛ እናቷ ቤት ሄደች ከስራ ሲመጣ ቤቱ ተቆልፏል ልክ ከፍቶ ሲገባ ቤቱ እጅግ ይቀዘግዛል ከሰል ለማቀጣጠል ቢሞክር እምቢ አለው ልብሱን ደራርቦ ሚስት ሰርታ የነበረውን ጠርጎ በላ... ዝምታው ሲጨንቀው TV ከፈተ ግን የለመደው የልጁ ድምፅ ናፈቀው ...ጠዋት ሲነሳ ቁርስና ያ ይሚወዳት ሚስቱ ፈገግታ የለም ...ከፋው ፊቱን ታጥቦ ወደ ስራው ሄደ ቁርሱንም ካፌ በላ ግን አላረካውም... ስልኩን ቢያይም አትደውልለትም ...ውሎ ሲመለስ ራቱን በልቶ ከጓደኞቹ ጋር ቢያመሽም ያባዶ ቤት ግን ጠበቀው....ሀዘን ቤት ይመስል መግባት አስጠላው😔 ነገሩ ዞር ብሎ ሲያስብ
⚠️ለካ ያለ ሚስቱ ጎዶሎ ነው
⚠️ልጁ ለካ አጫዋቹና የመንፈስ እርካታው ነች👶
ይቅር በይኝ ማሪኝ ብሎ በሽማግሌ መለሳት
🔚
💓ደስታ የሚሰጥህን ነገር ከማጣትህ ቀድመህ ለይተህ እወቀው!
#ክብር_ለሚገባው_ክብር_ስጥ!!!
#ሰናይ_ቀን
ሼር ይደረግ

ISLAM AND SCIENCE
══ •⊰✿🍃✿⊱• ══

🎖SHARE🎖


@Islam_and_Science @Islam_and_Science
#ድሃ_ነው_አታግቢው

ምን ያደርግልሻል ባንክ ሂሳብ የለው
መጓዝ ስትፈልጊ መኪና እንኳን የሌለው
ዘና ማለት ሲያምርሽ ቪላ የሌለው
አስቤዛ ማሟያ ቤሳቢስት የሌለው
ዲንኑን ብቻ ብለሽ ምን ልታደርጊው ነው

እነ ገሌትን እይ ኑሯቸው ቅንጦት ነው
ማግባትስ እንደሷ ገንዘብ ያለውን ነው
ዲኒያ ደስታ እንጂ መጨነቅ ምንድነው


እያሉ ሲያምታቷት ያችን ሚስኪን ጀግና
ይቅርብሽ ደሃ ነው እያሉ አታግቢው
አሏህ ፀጋን ለጋሽ መሆኑን ረስተው
ዱኒያ ብልጭ መሆኗን ዘንግተው
ዲኑን ነው የምፈልግ ብላ ስትላቸው
ግራ ሲያጋቧት መረዳት ከብዷቸው
ቀቅለው ሊበሏት አዛኝ መስለው ቀርበው


ሞትን የፈጠረ መግደልን የቻለ
ያጣን መለገስን መች አቃተኝ አለ
ብላ ተወክላ አሏህ ተመክታ
ድሀውን መረጠች መኖር በሰላምታ


ኢማን ተቅዋ ካለ በመካከላችን
ድህነት በስቲግፋር ይጠፋል ደጃችን
አለች ያች ጀግና ኢማን ቀልቧ የገባት
ይቀየራል ማጣት በማግኘት በትእግስት

ሁሉም ከአሏህ ነው
ዲኑን ወይስ ሃብቱን መምረጥ ግን ያንቺ ነው
አኽላቁን ምረጪ እሱ ነው ያንቺባል
ባይወድሽም እንኳን መች ይበድልሻል
አውፍ በይኝ ብሎ በሰላም ይለይሻል


እናማ እህቴ ልንገርሽ እውነቱን
ገንዘብ ባል አይሆንም አትምረጪ ንብረቱን
አህላቁን ምረጪ የዲኑን ብርታቱን
ሰበብ እንዲሆንሽ የጀነት ብርሃኑን
እምነቱን ጠብቂ አታፍርሽ ቃሉን መልካሙ ይምረጥልን ቀጥተኛው መንገድ ይምራን


💐💐ትዳር በነብዬ ሰለላሁ አለህ ወሰለም ሱና አላህ ይወፍቀን %።

ISLAM AND SCIENCE
══ •⊰✿🍃✿⊱• ══

🎖SHARE🎖


@Islam_and_Science @Islam_and_Science
Forwarded from ISLAM IS UNIVERSITY
#የሸህ #ኻሊድ #ረሻድ #የሂወት #ገፅ
#part 7⃣
በIslmic university channal
#እዛች ከተማ ላይ አምስት አመታትን አሳለፍኩ ያቺ አምስት አመታት ሸኽ ኻሊድ አል ራሺድ የሚባል ዳኢ እንዲበቅል አደረገች ይላሉ ።
#በከተማዋ #መስጂዶች አሉ ግን ኢማም የለም እንቅስቃሴ የለም ፣ ዳእዋ የለም…
#ታድያ #ሸኹ አንዳንድ መስጂዶች እየሄድኩ ዳእዋ ማድረግን እሞካክር ነበር … አንድ ቀን ሀሙስ አሱር ሰግጄ ስወጣ የመስጂዱ ኢማም መጥቶ «ነገ አንተ ነህ ኹጥባ ምታደርገው» ሲለኝ #ደነገጥኩ ይላሉ… እረ እኔ አልችልም ፣ እሺ ሳምንት ስጡኝ ፣ ስላቸው ኢማሙ አለኝ «ምንም ማድረግ አልችልም ነገ እኔ አንድ ጉዳይ ገጥሞኝ እዚህ የለውም» አለና የነገውን ሀላፊነት ሸኹ ላይ ጥሎ ሄደ … በቃ ከኢሻ ቡሃላ መስጂዱን እንዳትዘጉት አልኳቸው።
ከለሊቱ ስድሰአት ብቻዬን ሚንበር ላይ ወጥቼ " #ኢነል #ሀምደሊላህ" እያልኩ መለማመዱን ተያያዝኩት …በዛ ሰአት መስጂዱ እና እኔ ብቻ ነን ማንም የለም ።
በነገው ለት የመጀመሪያ ኹጥባዬን አደረኩ በህይወቴ አረሳትም ስለ "ሶላት" ነበረች…
#አንዴ #ከርእሱ እንውጣና
በነገራችን ላይ "ሶላት" የሚለው ኹጥባ እጅግ በጣም የሚጥም የሰላሳ ደቂቃ ኹጥባ ነው ።
#ሸኽ ኻሊድ በዛች ትንሽ የገጠር ከተማ መንገድ ተከፈተልኝ በመስጂዶቿ እየዞርኩ ዳእዋ የማድረግ እንደውም ያንዱ መስጂድ ኢማም ለመሆን በቃው ኪታብ መቅራት እንዲሁም ማስቀራት ውስጥ ገባው ይላሉ።

#ታድያ በአንድ ረመዷን በልዩ ሁኔታ ለሴቶች ብቻ የሚደረግ ዳእዋ ጀመርን በሳምንት አንዴ… #ከዛም ሙሀደራው ይቀዳና ወደ ሌሎች ሴቶች ካሴቱን እናከፋፍላለን ። #ታድያ ያኔ አንድ የካሴት አከፋፋይ መጣና «ይህ የለቀከው "ወደ ተመላሾች ቅፍለት " የሚለው ሙሀደራህ በጣም የሚያስፈልግ ስለሆነ ለምን በትልቅ መድረክ ላይ አትደግመውም? አለኝ… #እኔ #ማነኝ #አልኩት? ማነኝ እና ነው ለትልቅ መድረክ የሚመጥን ዳእዋ የማቀርብ? እምቢ አልኩት አብሽር በአላህ ተማመን አለኝ… እሺ እንደዛ ከሆነ ያለ ማስታወቂያ ያለ ማካበድ አልኩትና በዛ ተስማማን… #ሙሃደራውን ባንድ መስጂድ አደረኩ ድምፁ ተቀረፀ ከዛ ድንገት ሸኽ ኻሊድ ራሱን ካሴት ውስጥ አገኘ ከዛስ… ?
#እንዴት #በመላው ሳውዲ እውቅና አገኘ?
ለምን ታሰረ?
ለታሰረ ቡሃላስ ዳኛው ፊት ሲቀርብ ምን ተናገረ?
ልጆቹ ስለ አባታቸው በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ምን አሉ? በሚቀጥለው ክፍል ኢንሻአላህ

#Part 8⃣
ይ.....
,,,,,,,,,,,ቀ
............ጥ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,ላ
..............,,,,,,,,,,,ል

ISLAM IS UNIVERSITY
🌐══ •⊰✿✿⊱• ══🌐

🎖SHARE🎖

4another channal👇

@Islam_and_Science

JOIN👇👇👇
@IslamisUniverstiy_public_group
@IslamisUniverstiy_public_group
#የረሱል #የትዳር #ሂወት👒
🎓 #ክፍል 6⃣
ባለፈው ሚስትን መውደድ ፤ ሚስትን ማክበር ፥ ሚስትን አለመርሳት ፥ የክብር እና የጀግኖች ሰወች ባህሪ ነው ብለን ነበር ያቆምነው❗️ እስኪ ስለረሱል ጀግንነት እና መልካም ባህሪ በሀድስ የተቀመጡትን እንመልከት እንድሁም ወርቃማ ምክራቸውን ተከተሉኝ^^...
አቡዘር ረ ዐ እንዳወሩት የአላህ መልክተኛ ሰ ዐ ወ እንድህ ብለዋል ፤ ልቦናውን ለኢማን ታማኝ ፣ ቀልቡን ንፁህ ፣ ምላሱን እውነተኛ ፣ ነፍሱን ያረጋጋ እና ሥነ -ምግባሩን ያገራ በእርግጥ ከእሳት ተጠብቆ ጀነትን ተጎናፅፏል ( ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል..
በህብረተሰቡ ውስጥ ጥሩ ስነ ምግባርን ለማስረፅ መርህን መግለፅ ብቻውን በቂ አይደለም ወይም ደግሞ ይሄንን ፈፅሙ ፥ ያንን እንዳትፈፅሙ ማለት መፍትሔ አይሆንም አንድ አስተማሪ ይሄንን ስሩ ወይም አትስሩ ስላለ ብቻ የተባለው ነገር አይተገበርም ወይም አይተውም ነፍስ በዚህ መልኩ አትገራም የሰውን ልጅ ውጤታማ ሥረአት ለማስያዝ ፣ ዘውታሪነት ያለው እንክብካቤ እና ፅናት ያለው ጥረት ይጠይቃል መጥፎ ስነ ምግባር ያለው ሰው በዙሪያው ላሉ ሰወች ጥሩ አራአያ መሆን አይችልም..
ጥሩ አራአያ መሆን የሚችለው የአይንን ትኩረት የሚስብ እና በስብእናው የጎላ እንደሆነ ብቻ ነው ። ይህ ሰው በባህሪው ይገዛል ። ሰወችም ከእሱ ጥሩ ስነ ምግባር ይወስዳሉ ። በመገረም እና በንፁህ ፍቅሩ በመማለል የእርሱን ፋና ይከተላሉ ። ተከታዮቹ አራአያ ከሆናቸው ሰው የሚያገኙት ጥቅም እንዲበዛ ፣ በብዙ ሁኔታወች አራአያ የሚሆነው ሰው ከእነሱ የተሻለ መሆን ይኖርበታል..
በእርግጥ የአላህ መልክተኛ ሰ ዐ ወ በተከታዮቻቸው መካከል በትጋት ለሚጣሩበት ጥሪ ዋና አራአያ ነበሩ ይህንን ስብዕና በሰሀቦቹ(በባልደረቦቻቸው) ላይ የሚተክሉት ንግግርን በማብዛት ሳይሆን በምርጥ ባህሪያቸውና በድንቅ ሂወታቸው ነው..
ዐብደላህ ኢብኑ ኡመር እንድህ ብለዋል የአላህ መልክተኛ ሰ ዐ ወ መጥፎ አልነበሩም ። መጥፎ ነገርን የሚተገብሩ አልነበሩም ። ዘወትር ከእናንተ በላጭ ማለት ጥሩ ባህሪ ያለው ነው ይሉ ነበር (ቡሀሪ ዘግበውታል).
አነስ ረ ዐ እንድህ ብለዋል ፦ በእርግጥ የአላህ መልክተኛን ለአስር አመታት ያክል አገልግያቸዋለሁ በአላህ እምላለሁ !ኡፍ ብለውኝ አያውቁም ለምንም ነገር ይህንን ለምን አልሰራህም ? እንድህ አድርገህ አትሰራም ነበር ? ብለውኝ አያውቁም (ሙስሊም ዘግበውታል..
እኛስ የት ነን ? ባል ከሚስቱ ጋር ፤ ከልጆቻችን ፤ ከቤተሰቦቻችን ፤ ከሰራተኛወቻችን ፤ጋ ያለን ግንኙነት ምን ይመስላል ?ነገ ልጆቻችን ምን አይነት ባህሪ ነው ከእኛ ወርሰው የሚያድጉት ? ሁላችንም እራሳችንን እንፈትሽ !!
=>ስለረሱል መልካም ባህሪ የሚናገሩ ሀድሶች አላለቁም
ክፍል 7⃣

#ይቀጥላል.


@Islam_and_Science @Islam_and_Science
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ነይልኝ
እወድሻለሁ ስል እያነሰኝ ቃላት
አፈቅርሻለሁ ስል እያነሰኝ ቃላት
ስጨነቅ አድራለሁ እያልኩ ምን ልበላት
አንችን ስለማይገልፅ ቃል በቃል ቢተካ
ወር ሞልቶ አገኝቸሽ ሀሳቤ ይሳካ
ባንችኮ ናፍቆት ነው ማሰብ መተከዜ
እዳም በዝቶብኛል ነይልኝ #ደሟዜ ....l
☺️☺️☺️


@Islam_and_Science @Islam_and_Science
አሠላም አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ
#ወይ-ዱንያ-

እጅግ በጣም አስተማሪ ስለሆነ አንብበን ስንጨርስ ለሌሎችም እናካፍል
በዱኑ ውበት ተማርኮ ዛፍ ቅጠሉን እያየ ሳለ ነበር ከኃላው አንዳች የሚንኮሻኮሽ ድምፅ የሰማው...ምንነቱን ለማረጋገጥ ዞረ...ከኃላው የነበረው አንበሳ ነበር አይኑን ማመን አቃተው ደነገጠ እግሬ አውጭኝ ብሎም መሮጥ ጀመረ...አንበሳውም ተከተለው ጥቂት ከሮጠ በኃላ የውሃ ጉድጓድ አየ ሌላ ምንም አማራጭ ስላልነበረው ዘሎ የውሃ ማውጫው ገመድ ላይ ተንጠለጠለ ... #አንበሳውም እያጎራ ይጠብቀው ጀመር...ድንገት ወደ ታች ሲመለከት የውሃ ጉድጓዱ የቆየ ነበርና የእባቦች መጠራቀሚያ ሆንዋል ...የሰውየው የልብ ምት ጨመረ ከላይም ከታችም ሁለት አስፈሪ ነገሮች ተጋርጠውበታል ...የውስጡን ፍረሀት እያስታመመ ወደ ላይ ቀጥ ሲል ሁለት ነጭና ጥቁር አይጦች ገመድ የታሰረበት እንጨት ላይ ሆነው ገመዱን ሲቆረጥውት አስተዋለ "ኦ ጌታየ ዛሬ የመጣብኝ መከራ"ብሎ አይጦቹን ለማባረር ገመዱን በማወዛወዝ ማንቀሳቀስ ጀመረ ...ወደ ቀኝ ወደ ግራ ራሱን ሲያንቀሳቅስ ከአንዱ የጉድጓዱ ጎን የሆነ ወፈር ያለ ፈሳሽ ነገር ነካው በደንብ ቀረብ ብሎ ሲመለከት በጉድጓዱ ግድግዳ ድንጋይ ክፍተት ውሰጥ ንቦች ማር ጥለው ነበር ...ሰውየው የነበረበት መከራ ከላይና ከታች የሚጠብቁትን ነገሮች ረስቶ ማሩን መላስ ተያያዘው ማሩ በጣም ጣፋጭ ነበርና ያለበትን ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ረሳው...ድንገት ከእንቅልፉ ባቶ ነቃ፦ በጣም አስፈሪና የሚረብሽ ህልም ነበር ሲያይ የነበረው።
💫💫 ህልሙን ወደ ሚፈታለት ሰው ለመሄድ ወሰነ ወደ አንድ ህልም ፈች አዋቂ ሰው ሄደና ህልሙን አንድ በአንድ ዘርዝሮ ነገረው ሸህየውም ሳቀና የህልሙ ፍቺ አልገባህም ሲል በመገረም ጠየቀው ሰውየውም መልሱን እንዲህ ብሎ መለሰለት

☞ከኃላህ ሲያባርህ የነበረው "መሊከል ሞት"ነው
☞እባቦች ያሉበት ጉድጓድ ደግሞ ቀብርህ ነው
☞የተንጠለጠልክበት ገመድ ደግሞ እድሜህ ነው
☞ነጭና ጥቁር አይጦች ደግሞ ቀንና ማታ እድሜህን እየበሉብህ ነው ብሎ ሸኹ ነገረው። ያሸኽ ማሩስ ምንድነው ?!ሲል ጠየቀው
☞ሸኺም ማሩማ ዱንያ ነች ጥፍጥናዋ ሞት ሂሳብ እንዳለብህ አስረሳችህ ብለው አሉት። ሱበሃን አላህ
👆ያጀመዓ በደንብ አንብቡት ትልቅ ትምህርት ይሰጣል ሼር በማድረግ ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ይተባበሩ።

ISLAM AND SCIENCE
══ •⊰✿🍃✿⊱• ══

🎖SHARE🎖


@Islam_and_Science @Islam_and_Science
#የረሱል #የትዳር #ሂወት🌹
🎈ክፍል ~7⃣🎓
👓የረሱል ውብ ስነ ምግባር ከክፍል 6 የቀጠለ ..
🏷አነስ ( ረ ዐ ) እንዳሉት^ባለ ጉዳይ ሴት ባሪያ እጃቸውን ይዛ ወደምትፈልገው ቦታ ትሔድ ነበር ከሰው ጋር ሲገናኙ ቀድመው እጃቸውን ይዘረጋሉ እጃቸው የጨበጠውን ሰው እሱ እስኪለቅ እሳቸው አይለቁም እሱ ፊቱን እስኪያዞር ፊታቸውን ከፊቱ አያዞሩም አብሯቸው ለመቀመጥ የመጣን ሰው ቀድመው እኔ እበልጣለሁ በማለት አይቀመጡም ^( ተርሚዚ ዘግበውታል`)
📐አኢሻህ ረ ዐ እንድህ ብለዋል ፦ የአላህ መልክተኛ ሰ ዐ ወ በሁለት ነገሮች መካከል ምርጫ ቀርቦላቸው ወንጀል እስካልሆነ ድረስ ቀናውን ነበር የሚመርጡት ወንጀል ከሆነ ያን ነገር በጣም ይርቃሉ አንድም ቀን ለራሳቸው ብለው ተቆጥተው አያውቁም የአላህ ሀቅ ሲነካ የሚቆጡ ነበሩ በአላህ መንገድ ጅሀድ ካልሆነ በቀር አንድም ቀን በእጃቸው ሴትም ሆነ ሰራተኛን ቀጥተው አያውቁም ( ሙስሊም ዘግበውታል)....
🔶አነስ ረ ዐ እንድህ ብለዋል የአላህ መልክተኛ ወፍራም ጋቢ ለብሰው ወደ መስጂድ ሲገቡ ከሳቸው ጋር አንድ ላይ ነበርኩ አንድ ያልሰለጠነ ባላገር ሰው መጥቶ ጋቢያቸውን ጎተተው የነብዩ አንገት ላይ በመሸምቀቅ ሰምበር ወጣ ሰውየውም ሙሐመድ ሆይ ! አንተ ዘንድ ካለው የአላህ ገንዘብ ስጠኝ አላቸው ነብዩ ወደ ሰውየው በመዞር ሳቅ ብለው የጠየቀው እንድሰጠው አዘዙለት (ቡሃሪ ዘግበውታል)..
አኢሻ ረ ዐ እንዳወሩት የአላህ መልክተኛ ሰ ዐ ወ እንድህ ብለዋል አላህ አዛኝ ነው በቅንነትና በለስላሳነት የሚሆን ነገር ያስደስተዋል በፅንፈኝነት ለሚፈፀም ሽልማት በጭራሽ የለውም ቅንነትና ለስላሳነት የሚያስገኘውን አጅር የሚያክል ደረጃ የለም ( ሙስሊም ዘግበውታል )በሌላ ዘገባ ቅንነትና ለስላሳነት ሁሌም ውጤታማ ያደርጋሉ ቅንነት ሲጓደል ስኬታማነት ይጓደላል..
💧በዚህ ሀዲስ ሴት ባሪያ ማለት ዕድሜዋ ለአቅመ ሔዋን ያልደረሰች ሴት ማለት ነው የአላህ መልክተኛ ሰ ዐ .ወ ከልጅነት እስከ ህልፈት ከጡት እናቶቻቸው በስተቀር ለአቅመ ሂዋን የደረሰችን ሴት ልጅ እጅ ነክተው እንደማያውቁ አኢሻ ረ ዐ አረጋግጠዋል ..
💬አኢሻ ረ ዐ የአላህ መልክተኛ ሰ ዐ ወ እቤት ውስጥ ምን ይሰሩ ነበር ተብለው ሲጠየቁ ሲመልሱም ቤተሰባቸውን በሥራ ያግዙ ነበር ሰላት ሲደርስም ውዱዕ አድርገው ወደ ሰላት ይሄዱ ነበር..
🌸አብደላህ ኢብን ሀሪስ ረ ዐ እንድህ ብለዋል ከአላህ መልክተኛ ሰ ዐ ወ የበለጠ ፈገግተኛ አላየሁም ተርሚዚ ዘግበውታል* .
=>ከነብዩ ሰ ዐ ወ ባህሪያት ውስጥ ፦ ድህነት የማይፈሩ ፤ ቸር፣ በምንም ተአምር ከእውነት የማይነቃነቁ ጀግና ፥ ፍፁም የማይበድሉ ፍትሀዊ ፣ ሂወታቸውን በሙሉ እውነተኛና ታማኝ ነበሩ
"
Part 8⃣*ይቀጥላል.
┏━ 🍃 ━━━━ 🍂 ━┓
🎖ISLAM AND SCIENCE🎖
┗━ 🍂 ━━━━ 🍃 ━┛

🎖SHARE🎖
JOIN👇👇👇

T..➳ telegram.me/Islam_and_Science

T..➳ telegram.me/Islam_and_Science